Monday, February 3, 2020

የሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ማህበር😘 ምዕራፍ 1 ✍️ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ . . . የሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ማህበር እ.ኤ.አ 2004 ዓ.ም ጥር 8 ቀን በኢትዬጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሸራተን አዲስ መኝታ ክፍል በሁለት ግለሰቦች ጠንሳሽነት የተመሰረተ ማህበር ነው፡፡

የሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ማህበር😘

ምዕራፍ 1

✍️ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ
.Image result for areke ethiopian drink"
.
.
የሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ማህበር እ.ኤ.አ 2004 ዓ.ም ጥር 8
ቀን በኢትዬጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሸራተን አዲስ መኝታ
ክፍል በሁለት ግለሰቦች ጠንሳሽነት የተመሰረተ ማህበር ነው፡፡
ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ ያሉትን አባላት ከተላያየ የአለም ጥግ እና
የኢትዬጵያ ክፍል በማሰባሰብ እንዲህ ያለውን ቅርጽ እንዲይዝ
ለማድረግ የሁለት ዓመት ተኩል እልክ አስጨራሽ ትግል እና
ረብጣ የሚባል ዶላር ፈጅቶበታል፡፡
ከዚህ ማህበር ሁለቱ ፈጣሪዎች ውስጥ አንዱ ሻምበል ያሲን
ሁሴን ሲሆን ሌለኛው ግን የማይታወቀው ወይም ስውሩ ሰው
በመባል የሚታወቀው ሰው ነው፡፡ይህን ስውር ሰው ከሻምበሉ
ውጭ ማንም አይቶት ወይም በማንኛውም የመገናኛ ዘዴ አናግሮት
አያውቅም፡፡የዚህ ስውር ሰው እና የሻምበሉ ግንኙነት በኦሪት ጊዜ
የነበረውን የሙሴን እና የእግዚያብሄርን አይነት ግንኙነት ነው፡፡በዛን
ዘመን ህዝበ እስራኤልና ከግብፅ ባርነት ከፈርኦን አገዛዝት
ለማውጣት እና ወደ ተስፋይቱ ምድር ለማድረስ በነበረው ውጣ
ውረድ የሁሉ ነገር ዕቅድ ነዳፊ መንገድ ቀያሽ ስውሩ እግዚያብሄር
ሲሆን ይሄ ስውሩ እግዚያብሄር ግን ለህዝብ ግልፅ ለሆነው ሙሴ
ብቻ በአካል በመታየት ዕቅዱን ያስረዳዋል …ትዕዛዙን ያስተላልፈል
ሙሴ ደግሞ ትዕዛዙን ወደ ህዝቡ በማውረድ ተፈጻሚ ያደርግ
ነበር፡፡እንግዲህ ለዚህ ማህበር ሻምበሉ ልክ እንደ ሙሴ ነው
ልንለው እንችላለን፡፡በስውሩ ሰው ሙሉ ስልጣን የተሰጠው
ፈላጭ ቆራጭ ግለሰብ ነው፡፡አንዳንድ ተጠራጣሪ የሆኑ የማህበሩ
አባለት እንደውም ስውሩ ሰው የሚባል አካል የለም ፤የሁሉ ነገር
መነሻማ መድረሻማ እራሱ ሻምበሉ ነው ይላሉ ፡፡ስውሩ ሰው
የተባለው የፈጠራ ሰው እኛን ለማደናገር የተፈጠረ ነው ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ተሰርቶ ያለቀው
የሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ማህበር ጠቅላላ መዋቅር
እንደሚከተለው ነው፡፡
1የሲኦል ፈጣሪ
ይሄ የስውሩ ሰው ልዩ መጠሪያ ወይም የኮድ ስም ነው፡፡
የማህበሩ ከፍተኛ ስልጣን በእጁ ይገኛል፡፡ከእሱ አንደበት
የመነጨ ማንኛውም ትዕዛዝ በማህበሩ ውስጥ ያለምንም
ማመንታት እንደወረደ ይተገበራል፡፡ስውር ቢሆንም መንፈሱ
በእያንዳንዱ አባላት አዕምሮ ውስጥ ከፈጣሪያችው እኩል
ለአንዳንዱም ከዛ በላይ ሰርጾ ገብቷል፡፡ሁሉም የማህበሩ አባላት
የማህበሩ ዋና አላማ ከግብ ካደረሱ ቡኃላ ካለበት በመውጣት
ለተከታዬቹ ይገለጽ ይሆናል…አብሮን ማዕድ ይቆርስ ይሆናል…
በማለት ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
2ሳጥናኤሉ
ይሄ የማህበሩ ሁለታኛ ሰው ሻምበሉ ነው፡፡በማህበሩ በትክክለኛ
ስሙ በሁሉም የሚታወቅ ብቸኛው ሰው ነው፡፡ይሄ ሳጥናኤል
የማህበሩ ሞተር ነው፡፡ከሲኦል ፈጣሪው የሚደርሰውን ቀጭን
ትዕዛዝ ይሄን አድርግ….ይሄን ገንባ… ይሄን አፍርስ የሚል ጥቅል
ትዕዛዝ ዕቅድ ነድፎ..የአፈጻፀም መመሪያ ቀይሶ ..ለአባላቱ ለእዛ
ሚመጥን ልዩ ስልጠና እንዲያገኙ ሁኔታዎቹን አመቻችቶ ውጤት
ለማግኘት ሙሉ ሀላፊነት ያለመታከት በጫንቃው በመሸከም
ሁሉንም ዕቅድ ተግባራዊ የሚያደርግ በማህበሩ የሚዳሰሰው
አማላክ ነው፡፡ይህ ሻምበል የደርግ ልዩ አየር ወለድ ነበር፡፡በዛኑ
ዘመን ለሶስት አመት ልዩ ወታደራዊ ስልጠና ከራሺያ ወስዶል፡፡
ከአስር አመት በላይ የሻዌ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ የስላጠና
ዘርፍ ኃላፊ በመሆን አገልግሎል፡፡ሻዌ ማሰልጠኛ ጣቢያ በባሌ ዞን
ከደሎ መና ከተማ በሃያ ኪ.ሜ እርቆ ሀረና ጫካ ውስጥ የሚገኝ
በደርግ ጊዜ የሀገሪቱ ወታደራዊ ማሰላጠኛ ጣቢያ የነበር ካምፕ
ነው፡፡ በዚህ ቦታ ከሃያ ዓመት ዘረፋ የተረፍ አንዳንድ ቅሪቶቹ
በቦታው ይገኛሉ ፡፡አሁን ደግሞ የሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ማህበር
ምሽግ ሆኖል ፡፡የዚህ ሳጥናኤል ታሪክ ከደርግ መንኰታኮት ጋር
አብሮ የተንኰታኮተ ቢመስልም በኢትዬ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ
ኢህአዲግ የደርግ ከፍተኛ መኮንኖችን እና የጦር አዛዦችን
ከያሉበት ስርቻ ውዝፍ ደሞዛቸውን እየከፈለ ጦርነቱን በዕውቀት
እንዲያግዙት ከራሱ ጦር ጋር ሲቀላቅላቸው ዳግም የመቀላቀል
ዕድል ገጠመው፡፡ሌላ የህይወት ምዕራፍ ፡፡ከጦርነቱም ቡኃላ
በአገሪቱ የተወካዬች ምክር ቤት በአዋጅ እንዲቋቋም ተደርጎ
በነበረው የአገሪቱ ፈንጅ አምካኝ ቡድን ውስጥ ተሳትፎ
ነበረው..ቡኃላም ብዙ ብዙ ታሪክ አለው…..
አሁን ዕድሜው ስልሳ ሁለት የደፈነ ሲሆን አካላዊ ይዞታው ወደ
አርባ ሁለት አመት ዝቅ ተደርጎ እንዲገመት ያደርገዋል፡፡ግዙፍ
ነው፡፡ዘጠና ሁለት ኪሎ ይመዝናል፡፡እንዲህ ሲባል ታዲያ
የተንዘረጠጠ ተክለቁመና አለው ማለት አይደለም.. በእስፖርት
የዳበረ ፈርጣማ እንጂ፤በዛ ላይ ቁመቱ 2.01ሜትር ነው፡፡
ማንኛውም ሰው ፊት ለፊቱ ሲቆም የማርበድበድ እና የፍራቻ
መንፈስ የመርጨት ልዩ ብቃት አለው፡፡በዛ ላይ ዘወትር ለሳቅ
የማይሸነፍ ኮስታራ ግንባር ነው የተሰጠው፡፡ተስገምጋሚ ጥርት
ያለ ድምጹም ሌላው ስጦታው ነው፡፡ይህ ሰው የአገሪቱ ኢታማዠር
ሹም ጄኔራል ሆኖ ቢሾም አገሪቱ ለጐረቤት የሚያስፈራ ጦር
መመስረት እንደምትችል አያጠራጥርም… ግርማ ሞገሱም
ችሎታውም ስላለው፡፡
ይህ ሳጥናኤል የማህበሩ ጭንቅላት እንደመሆኑ መጠን ስለእሱ
የሚነገሩ ነገሮች ይበዛሉ፡፡የሚቀርቡት ምላጭ ነው ይሉታል፡፡
ምላጭ ለዓይን የማይጥመውን ነገር አስተካክሎ ውበት
ይጨምርበታል …ያሳምራል…የረዘመውን ያሳጥራል…
የተንከረፈፈውን ከርክሞ ያስተካክላል…የረዘመውን ቆርጦ
ይጥላል፡፡በተቃራኒው ደግሞ ምላጭ ይሸረክታል… ጉሮሮ
ይበጥሳል…በእናት እና ልጀ መካከል የነበረውን የአንድነት መንፈስ
እንደቀልድ በጥሶ ይጥላል፡፡
ሳጥናኤል እንዲህ ነው፡፡በጣም ቆራጥ …የሚገርም ነገሮችን
የመፍጠር እና የማደራጀት ልዩ ችሎታ የታደለ ከአምስት በላይ
ቋንቋዎችን አቀላጥፎ መናገር የሚችል(አማርኛ
፤ኦሮሚኛ፤ትግሪኛ፤አረብኛ እና እንግሊዘኛ) ግን ደግሞ
በተቃራኒው፤ጨካኝ ፤ለዓላማው መሳካት የእናቱን ልጅም ቢሆን
ከማረድ የማያመነታ፤በጣም ተጠራጣሪ እና ተነዳፊ
ጀግና፤ሀይማኖቱ በራሱ ስሜት ብቻ ማመን የሆነ ባለ ውስብስብ
ስብዕና ባለቤት ሰው ነው፡፡
3የሳጥናኤል ሴት
ይህቺ ሴት በዋናነት የሳጥናኤሉ የጭን ገረድ ነች ፡፡ዕውቂያቸው
ዘመናት ያስቆጠረ ግን ደግሞ ለዓመታት ተቋርጦ የነበረ ይሄ
ማህበር ሲመሰረት ዳግም የተጀመረ ነው፡፡የሳጥናኤል ሴት ጠይም
መልከ መልካም ግራ ጉንጮ ላይ 8 ሣ.ሜትር ርዝመት በ2 ሚ.ሜ
ስፋት ጠባሳ የተጋደመባት፤ሳቀች ሲሎት ፊቷን የምታጨማድድ …
አጨለመች ሲሏት ውስጥን የሚያረሰርስ ደስታ የሚረጭ ሳቅ
የምትለግስ የማይጨበጥ ባህሪ ያላት የማህበሩ ወሳኝ ሰው
ነች፡፡
በግልፅ ስልጣኖን ለመናገር‹‹የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር
››ማለት ትችላላችሁ፡፡በሲኦል አረቄ ጠማቂዎች ዋና ካምፕ
ውስጥ ያሉ ጠቅላላ የውስጥ እንቅስቃሴዎች በእሷ ነው
የሚመራው፤ይሄም ሳጥናኤሉ አዕምሮው በጥቃቅን የውስጥ
ጉዳዬች እንዳይጨናነቅ እና ዋና ዋና የማህበሩ አላማዎችን ላይ
እንዲያነጣጥር እና የማሰብ ኃይሉም እንዳይበታተንበት የማይናቅ
እገዛ እያደረገችለት ነው፡፡በዛ ላይ ወታደራዊ ዕውቀቱም ልምዱም
አላት፡፡የወያኔ ታጋይ ነበረች፡፡የዛሬን አያድርገውና፡፡
4ሰይጣኖቹ
ሠይጣኖቹ በቁጥር አስር አባላት ያሉት የማህበሩ ዋና አከርካሪ
የኮድ ስም ነው፡፡አስሮቹም ቀድሞም ወታደር ነበሩ ዕድሜያቸው
ከ30-50 ውስጥ ያለ፤በአሁኑ ጊዜ አለ የተባለ ዓለም አቀፍ
ወታደራዊ ስልጠና የሰለጠኑ ለማንኛውም የማህበሩ ግዳጅ
እስከህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በጣም ቁርጠኞች
ከመሆናቸውም በተጨማሪ የማህበሩም ዋና አሴት ተደርገው
ይቆጠራሉ፡፡የአንድ ክፍለ ጦር ወታደር ያ

No comments

Post a Comment

Popular Posts

© የፍቅር ቀጠሮ የፍቅር ታሪክ 2020
Maira Gall