Sunday, January 19, 2020

የፒያሳዋ ወፍ ክፍል ሁለት

የፒያሳዋ ወፍ
ክፍል ሁለትImage result for የፒያሳዋ ወፍ ‹‹ምን አደረግሺው?›› ‹‹ዝርዝሩ ምንም አያደርግልህም ..ግን እድሜ ልኩን እንደተሸማቀቀ እና ምነው ባላደረግኩት ኖሮ እያለ ሲፀፀት እንዲኖር ነው የፈረድኩበት…ቀን ጠብቄ ከሶስት ወር ቡኃላ የዘር ፍሬውን ነው ያፈረጥኩለት ..ዕድሜ ልኩን ሴት ስር እንዳይደርስ….ለእሱ የሴትን ገላ ማቀፍ.. በሴት ፀጋ መደሰት አይገባውም…… ከዚህ በላይ ታሪኳን ለእኔ በመንገር ይበልጥ በውስጥ ሀዘኗ ምርቃዜ እንድትሰቃይ አልፈለኩም ….ከአልጋው ላይ ያለውን አልጋ ልብስ አነሳውና እርቃን ሰውናቷን አለባስኳትና አልጋው ላይ ይዤት ወጣው ..ይዤት ተኛው..በአልጋ ልብሱ አሷንም አራሴንም ጠቅልዬ ..፡፡ ባለፉት ሶስት ቀናቶች ካቀፍኳት በላይ አቅፌያት …አስከዛሬ ካዘንኩላት በላይ አዝኜላት… በእነዚህ ሶስት ቀኖች ከወደድኳት በላይ ወድጄያለት ጭምቅ አድርጌት ውስጤ ሸሽጌት.. ሁሉን ነገር አረስቼ ዓለምን ሁሉ ዘንግቼ ስለእሷብቻ እያሰላሰልኩ በፀጥታ ውስጥ ተዋጥኩ……እሷም በድካምና በእፎይታ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገባች….እኔም….ጩኸቷ ነው ከእንቅልፌ ያባነነኝ…‹‹ተነሳ..ተነሳ›› ወታደር አይደለው… ከመቅፅበት ከእንቅልፌ ተስፈንጥሬ ተነሳውና ወለሉ ላይ ቆምኩ…. ‹‹….ምንድነው.?.ምን ሆነሽ…?››ጩኸቷ እና ድንጋጤዋ የሆነ በቃ መቼስ ይህቺ አመጽ የማያጣት ከተማ ተድበለቅልቃለች ብላ ትንግረኛለች ብዬ እየጠበቅኩ ነው…..በአልጋ ልብሱ ግማሽ እርቃኗን ቅጥ አልባ በሆነ ሁኔታ ለመሸፈን እየሞከረች ሞባይሏ ላይ አፍጥጣ ‹‹‹ቶሎ በል ልብስህን ልበስ…ፍጠን›› ‹‹ምን ተፈጠረ..…?ተረጋጊና ንገሪኝ እንጂ›› ‹‹አስር ሰዓት ሆኗል›› ‹‹እና›› ‹‹አስር ሰዓት ሆኗል እኮ ነው የምልህ…?›› ‹‹እና አስር ሰዓት ምን አለ…?››ምንም ሊገለጽልኝ አልቻለም ‹‹ከአራት ሰዓት በላይ እኮ ነው የተኛነው…ገና አንቦ እኮ ነው ያለኸው›› ‹‹.አረ ተረጋጊ …እኔ ደግሞ ምን ተፈጠረ ብዬ›› ‹‹ይቅርታ ..አጉል አደረግኩህ…በል ተነስ እንውጣ ››ብላ ልብሷን ለመልበስ ስትሞክር ጎተትኳትና ‹‹….ተመልሰሽ ተኚ››አልኳት ‹‹ለምን…?›› ‹‹ዛሬ አልሄድም…ልጄ አያቷ ጋር ነች ..ለአንድ ቀን ምንም አትሆንም…አብረን እናድርና ነገ ጥዋት እንለያያለን..አሁን እኔ ወጣ ብዬ አንድ ቦታ ደረስ እልና እመጣለው ..ሀያ ደቂቃ ቢወስድብኝ ነው… እሰከዛ ተኝተሸ ጠብቂኝ›› ‹‹አረ ተው አንተ ሰወ…አሁን ብትሄድ አትደርስም…?›› ‹‹እርግጥ ይመሻል እንጂ ደርሳለው..ግን መሄድ አልፈልግም…ዛሬ ጥዬሽ አልሄድም›› ‹‹አረ ባክህ… ዛሬ ጥለኸኝ ባትሄድ ነገ መሄድህ የት ይቀራል›› ‹‹ቢሆንም ማምሻም እድሜ ነው ሲባል አልሰማሽም›› እሷ እንደአልኳት ወደ መኝታዋ ተመለሰችና ተኛች ….እኔም ጫማዬን አጠለቅኩና ጉንጯን ስሜ ጥያት ወጣው.. . . . . ከሰላሳ ደቂቃ ቡኃላ ተመለስኩ ‹‹እንዴ !!!አሁንም ተኝተሻል…?›› ‹‹ትዕዛዝ ላክብር ብዬ ነዋ….እኛ ኢትዬጵያውያን የፖሊስ ትዕዛዝ በፍራቻ ነው የምናከብረው ..ይህን መቼስ አንተም ታውቃለህ …?›› ‹‹አረ አለውቅም… ምን ለማለት ፈልገሽ ነው.…?››.አልኳት….አልጋው ጠርዝ ላይ በመቀመጥ… ‹‹ያው ህጻን ሆነን ወላጆቻችን የሆነ ጥፋት እንዳናጠፋ ሲፈልጉ ወይም ስራ አናሰራ ብለን ስንረብሻቸው አደብ እንድንገዛ የሚያስፈራሩን ወይ በጅብ ነው ወይ በፖሊስ ነው›› ‹‹አንቺ ጅብና ፖሊስ አንድ ናቸው እያልሽ ነው….›› ‹አይ አልወጣኝም…እኔ ያልኩት ሁለቱም ማስፈራሪያዎች ናቸው ነው›› ‹‹ሙጢ ነገር ነሽ …ለማንኛውም ተነሺ ልብስ ልበሺና ወጣ እንበል…›› ‹‹እስከነተጠቀለለችበት አልጋ ልብስ አልጋውን ለቃ ወረደችና ልብሷ ወዳተቀመጠበት ወንበር አመራች… በመጀመሪያ ሱሪያዋን አነሳች ..ልትለብስ›› ‹‹አይ እሱን አትልበሺም››አልኳት ‹‹እና ምን ልልበስልህ……?ታጋች እኮ ነኝ ..በለበስኩት ልብስ ብቻ እንደጠለፍከኝ ዘነጋሀው እንዴ…?›› ‹‹አልዘነጋውትም….ግን ይሄንን ልበሺ ››ብዬ ይዤ የመጣውትን አረንጎዴ ፔስታል ከወለሉ ላይ አንስቼ ወረወርኩላት ..በአንድ እጇ ቀለበችውና ወንበሩ ላይ ቁጭ ብላ በመደነቅ ተሞልታ ከፈተችው…..ውስጡ ያለውን ነገር ጠረጵዛ ላይ ዘረገፈችው…በመጀመሪያ ያነሳችው ቀሚሱን ነው….ባለ ሰማያው ቀለም ረጂም የእራት ቀሚስ ….በፍዘት አፎን ከፈታ ምንም ሳትናገር ዝም ብላ ለበሰችው…...ከዛ ከገዛውላት ግማሽ ደርዘን ፓንቶች መካከል አንዱን አነሳችና ፊት ለፊቴ ቆማ አጠለቀች…. በስተመጨረሻ ጫማውን አደረገች…... ተስተካክላ ፊት ለፊቴ ቆመች..
በወንድነት እና በሴትነት መካከል የሚዋልል የነበረው አቋምና ባሀሪዋን ወደሴትነት እንዲህ
በግድም ቢኆን ስትሳብ ውበቷ በእጥፍ ጎላብኝ….
‹‹አረ በስመአብ…ይሄንን ሁሉ ውበት የት ደብቀሽው ነበር………?››
የእኔን ሙገሳ ችላ ብላ‹‹አንድ ሚስጥር ልንገርህ……?››
‹‹ንገሪኝ››
‹‹ማንም ወንድ እንዲህ አይነተ ስጦታ ገዝቶልኝ አያውቅም››
‹‹ይህንን ስለነገርሺኝ ደስ ብሎኛል››
‹‹ሌላም የምነግርህ አለኝ››
‹‹እየሰማው ነው››
‹‹ነፍስ ካወቅኩ ጊዜ አንስቶ ቀሚስ ለብሼ አላውቅም…ምንም ቀሚስ የለኝም….አውነቴን
ነው….አሁን ቀሚሱን ለብሼ ፊትህ ስቆም የተለየ ስሜት ነው የተሰማኝ›››
‹‹የተለየ ስሜት ስትይ..……?የደስታ ››
‹‹አይ እንደዛ ብቻ አይደለም …የሆነ የመረጋጋት…የመቀዝቀዝ….የመሽኮርመም…እኔ እንጃ
መግልፅ አልቻልኩም..ግን በጣም አመሰግናለው፡፡››
‹‹ግድ የለም ምስጋናው ይቆየኝና አሁን ወጣ እንበል….››
‹‹እሺ› አለችና ቀድማኝ ወደ በራፍ እርምጃዋን ቀጠለች…
‹‹እንዴ !!!ወዴት ነው……?››
‹‹እንሂድ አላልከኝም እንዴ..……?››
‹‹አንድ ሴት እኮ እንሂድ ከተባለች ቡኃላ ለመዘጋጀት በጣም ፈጣን ከኆነች አንድ
ሰዓት..ከልሆነም ሁለትን ሶስት ሰዓት ይፈጅባታል..››
‹‹አልገባኝም..ምን ልትሆንበት……?››
‹‹ስትጠጣጠብ..ስትቀባባ..ስትኳኳል ..ልብስ ስትለካ ስታወልቅ….መስታወት ፊት ቆማ
አለባበሷን ስታስተካክል ..››
‹‹ቀልደኛ ነህ…ልኳኳል ብልስ ምኔን እኳኳላለው………?ለዛውስ ያለመደብኝን….ጋሼ ዜና
ምን ይሉኛል መሰለህ ..ሴት ሁኚ…ሁሌ ምክራቸው ሴት ሁኚ ነበር››
‹‹ማናቸው ጋሽ ዜና .. ……?››
ጋሽ ዜና እንደአያቴ የማያቸው ከጎረቤታችን የሚኖሩ ከውልደቴ እስከዛሬ የሚያውቁኝ
እንደአያቴ የማያቸው ሙሁር ግን ደግሞ ደሀ …(ለካ እዚህ አገር ምሁርነት እና ድህነት
አብረው የሚሄዱ ዘማዳሞች ናቸው) አዛውንት ናቸው፡፡››
‹‹እና ሴት ሁኚ ሲሉሽ..አረ ሴት ነኝ ብለሽ ቢያንስ ስንጥቁን በፎቶም ቢሆን አንስተሸ
ማረጋገጫውን አታሳያቸውም››
‹‹እሷቸው እኮ እንደላንጠለጠልኩና ስንጥቅ መሆኔን በደንብ ያውቃሉ..ለማለት የፈለጉት
ሴት ሆነሽ ተፈጥረሻል እና የሴትን ተፈጥሮዊ ባህሪ ተላበሺ ማለታቸው ነው….ሴቶቸ ወበት
አድናቂ ናቸው..ሴቶች ሰላም ወዳዶች ናቸው…ሴቶች የፍቅር ዘማሪዎች ናቸው….ሴቶች
ልስልስ ናቸው..ሴቶች ለተፈጥሮ ቅርብ ናቸው..ሊዩክሌር ቦንብ ለመስራት በላባላቶሪ
ከመዳከር በግቢያቸው ውስጥ ያለ አበባ ውሀ እያጠጡ እና እየኮተኳቱ ማሳደግና በዛ
መደመምን ይመርጣሉ….ሴቶች ቀለል ያለ ያልተወሳሰበ ኑሮን ይመርጣሉ..ሴቶች ስሜተ
ሙሉ ናቸው…ሴቶች እናቶች ናቸው..እናትነት ደግሞ የፍቅር መህደር ማለት ነው….እና ሴት
ሁኚ ሲሉኝ ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ይገባኛል….ድብድብና አንባጎሮውን ቀንሺ ሊሉኝ
ፈልገው ነው….ዘረፋውንና ማጅራት መምታቱን ባንቺ አያምርብሽም ሊሉኝ ነው…››
‹‹ባይገባኝም ገብቶኛል..በይ አሁን እንሂድ..አልኩና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቤርጎውን
ቀለፍንና እጅ ለእጅ ተያዘን ግቢውን ለቀን ወጣን….የሙዚቃ ሁካታ ማያደነቁርበት ቤት
ፈልገን እራታችን ልንበላ
..
..
ሁለት ሰዓት ሲሆን እራታችንን በልተን በማጠናቀቅ ከወደ መጠጡ እየወሳሰድን ጫወታችን
ቀጥለን ነበር..የጫወታው ርዕስ ወደ ሮማን ዞሯል… ወደ አሳዳጊ እናቷ
‹‹ቆይ እናትሽን እሷ እንደገደለቻት በምን አወቅሽ….……?እንደነገርሺኝ በወቅቱ አንቺ ልጅ
ነበርሽ……?››
‹‹አዎ ልጅ ነበርኩ..ያወቅኩት በቅርቡ ነው ..የዛሬ ስምንት ወር አካባቢ››
‹‹እንዴት ልታውቂ ቻልሽ››
‹‹በአጋጣሚ……ምን መሰለህ....እናቴ ስትሞት ለአንድ ሳምንት ታማ ነበር…በዛ
በታመመችበት ሰዓት ከስሯ ኩርምት ብዬ አይን አይኗን ሳይ ነበር የምውለው…እና ትዝ
ይለኛል በመጨረሻዋ ቀን ከመሞቷ ከአንድ ወይም ከሁለት ሰዓት በፊት እሮማን ፍቱን
የባሀል መድሀኒት ነው በሽታሽን ነቅሎ ያወጣልሻል አለቻትና አንድ መድሀኒት በብልቃጥ
አምጥታ አጋተቻት….ብልቃጧ የመድሀኒቱ ቀለም እና ሽታው ምን ጊዜም ከአዕምሮዬ
አይጠፋም…የመድሀኒቱ ቀለም ዝልግልግ አረንጎዴ ሳር መሰል ሲሆን ሽታው ግን እንደዚህ
ነው ብዬ መናገር ማልችለው በህይወቴ ወደ አፍንጫዬ ገባቶ የማያውቅ የተለየ ሽታ
ነው…..እናቴን ግን ሊያድናት አልቻለም..ሁል ጊዜ እናቴ ስትናፍቀኝ ወደ አይምሮዬ
የሚመጣው አልጋ ላይ የተዘረረ የእናቴ በበሽታ የደከመ ሰውነት..አረንጓዴ የተዝለገለገ
ፈሳሽ..ከፈሳሹ የሚበተነው ሽታ..ግርም ነው የሚለኝ..እንዚህ ነገሮችን ለምን ደጋግሜ
እንደማስታውስ ለራሴም ግራ ግብት ይለኝ ነበር…..
‹‹እና ከዛሬ 8 ወር በፊት አንድ ስራ ለመስራት ፈለግኩ››
‹‹ምን አይነት ስራ ?››
‹‹አንድ በጣም የሚያስጠላኝ አራጣ አበዳሪ ሰውዬ ነበር…በህይወቴ ከማውቃቸው ሰዎች
ሁሉ የመጀመሪያው ወንበዴ እና ጨካኝ ሰው ነው….አንድ ቀን ወደ ቤቱ ወሰደኝ..ይገርምሀል
ሚኖርበት ቢላ 13 ክፍሎች ያሉት የተንቆጠቆጠ ነው…፡፡ያን የሚገርም ቤት የገነባው
ጠቅላላ ሀብቱንም ያከማቸው በተዘረፈ ብር ነው..››
‹‹ሚስት የለውም እንዴ ?››
‹‹አለው 32 ዓመት አብራው የኖረች ሚስት አለው…ልብ በሽተኛ ሆና ለህክምና ልጇቾ ወደ
ውጭ ስለወሰዷት ለብቻው ነው የሚኖረው…..የልጅ ልጅ ያየ የስልሳ ወይም የሰባ አመት
ሽማጊሌ እኮ ነው….መጀመሪያ አንድ ሺ ብር ከፈለኝና ይዞኝ ሄደ….መኝታ ቤት ከገባን ቡኃላ
ልክ እንደ ሀያ አመት ጎረምሳ ፊልም ከፈተ..››
‹‹የምን ፊልም… ?››
‹‹የወሲብ ፊልም ነዋ…ፈረንጆች የሚጨመላለቁበትን ፊልም….ልብሱን አወላለቀ እና ያንን
ቀፈታም እንደከበሮ የተነረተ ሆዱኑ አንዘርጥጧ ፊቴ ቆመ..››
‹‹ሰውዬ ተኛ እንጂ››አልኩት
‹‹ተይ እንጂ ቆንጂት ..ምን አስተኛን…እድሜችን ሙሉ ተኝተን ስናረግ ነው የቆየነው…አሁን
በፊልሙ እንደምታያቸው ዘመናዬቹ ነው ማድረግ የምፈልገው…ያኛውማ አይነት ሰልችቶኛል
…ካአሁን ቡኃላ ጸኝጾ ማድድግ ለማለድ ብቻ ና የሚጠቅመው..እኔ ደግሞ አንቺ
እንድታስደስቺኝ እንጂ እንድትወልጂልኝ አልፈልግም››ብሎ ገለፈጠ…በሱ ቤት መቀለድ ነው
‹‹እሱ ይወደድብሀል››አልኩት….
ወደ ኮመዲኖ ሄደና መሳቢያውን ሳበው..ይገርምሀል ኮመዲኖው ሙሉ በገንዘብ የተሞላ
ነው…የተሰረ የታሰረ ብር..አንዱን መዥርጦ አመጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ››
‹‹እንዴት ነው የምትፈልገው ?››
‹‹እንድትጠቢልኝ››
‹‹ምን ? ››
‹‹አዎ እንደዛ ነው የምፈልገው..አየሻቸው አይደል ፊልሙ ላይ ያሉትን ቆነጃጅቶች..እንዴት
እንዴት የሰውዬውን ነፍስያ እንደሚያስደስቱለት››
‹‹ግን እኮ እንትኖት ልፍስፍስ እንዳለ ነው..ካልቆመ እንደዛ ለማድረግ ያስጠላል…››
‹‹አቁሚዋ…. ስራሽ ማቆም አይደል… ?››
‹‹አይደለም ጌታዬ …ስራዬ የቆመውን አባብሎ ማስተኛት ነው ››
‹‹እኔ እኮ አስር እጥፍ የከፈልኩሽ..የተኛውን ቀስቅስሽ በማቆም ..እንዳልሽው ከእንደገና
አባብለሽ እንድታስተኚው ነው…››
‹‹ከዛ እንዴት ሆናችሁ ?››የምታወራለልኝ ወሬ እበሳጨኝም እናደደኝም..በምትለው ሽማግሌ
ልናደድ ወይስ በእሷ በራሷ መለየት አቃተኝ፡ነው ወይስ እየቀናው ነው ?፡፡
‹‹ከዛማ እንዲሁ ሲንበዛበዙብኝ አደሩ…እንትናቸው እንኳን በእኔ ሀይል በቢያግራምም
ሚቆም አይነት አልነበረም ለማንኛውም ነጋና ተለያየን…››
በሳምንቱ ያገናኘኝን ደላላ ላኩት
‹‹ለምን ?››
‹‹ ለመድገም ነዋ..እኔ ደግሞ እንኳን እንደሳቸው አይነት በዝባዛ ሽማግሌ ይቅርና እንደአንተ
አይነት መለሎ ወንድ ቢሆንም መድገም ብሎ ነገር ነው የሚያስጠላኝ…ግን እዛ ኮመዲው
ውስጥ ታጭቆ ያየውት ብር አሻፍዶኝ ስለነበረ..እምቢ ማለት አልቻልኩም…››
‹‹ድጋሚ ልትጠቢ ?››ሳላስብ የጠየቅኩት አስቂኝ ጥያቄ ነው
‹‹አይ እንትናቸውን ሳይሆን ብራቸውን ልጠባ…እና ሮማንን አማከርኳት…..እንዳጋጣሚ
ቤተሰብ ልጠይቅ ብላ ከአዲስ አበባ ውጭ ነበረች..እና በስልክ ነው ያማከርኳት…እና
የሚያደነዝዝ መድሀኒት እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት….ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራ ስሰራ
የምጠቀመውን መድሀኒት የምትሰጠኝ እሷው ስለነበረች…የተለመደ ጥያቄ ነበር የጠየቅኳት
የት እንደሚገኝ በምልክት ነገረቺኝ..ከነተቀመጠበት የእቃ አይነት …ቁልፍን ካለቺኝ ቦታ
አገኘው..መኝታ ቤቷ ጋባው… ቁም ሳጥኗን ከፈትኩ ..በሌላ ቁልፍ ቁም ሳጥኑ ውስጥ
ያለውን አንድ አነስታኛ ሌላ ሳጥን ከፈትኩ..ኣዛ ሳጥን ውስጥም ሌላ የተቆለፈች ሳንቲም
ማጠራቀሚያ የምታህል የብረት ሳጥን አለች …ተቆልፋለች …ቁልፉ የለኝም..ደወልኩላት
‹‹ ሳጥኑን በምን ልክፈታት ?››
‹‹ቁልፍን ይዤ ነው የመጣውት …ገንጥያት..አደራ ቀስ ብለሽ..ውስጥ ያሉት መዳኒቶቹ
በጣም አስፈላጊ ናቸው… እንዳትሰባብሪብኝ እና እንዳይደፈ››
‹‹እሺ ››በማለት ስልኳን ዘጋውና በጥንቃቄ ገነጠልኩት..እንኳን ያቺን የምታክል ሚጢጢዬ
ቁልፍ ይቅርና ሌላውም ቢሆን ቁልፍ መገንጠል የተካንኩበት ሞያዬ ነው፡፡
ስገነጥለው አምስት የሚሆኑ የተለያየ መጠን ያላቸው ብልቃጦች አገኘው…ነጭ ብልቃጥ
ውስጥ ያለው ነው ያለቺኝ..ነጭ ብልቃጥ ደግሞ አንድ ብቻ ነው ..ፈገግ ብዬ አነሳውትና
መልሼ ልከድነው ስል የሆነ ነገር ገፋፋኝና ከጎኑ ያለውን ሌላውን ብልቃጥ አነሳውት..የሆነ
በጣም የማውቀው ብልቃጥ መስሎ ተሰማኝ …በዝግታ ከፈትኩት…አፍንጫዬ በሆነ ሽታ
ተሞላ ….በህይወቴ ይሄንን አይነት ሽታ ለሁለተኛ ጊዜ መማጌ ነው…ወደ መሬት ትንሽ
አፈሰስኩለት ይበልጥ ለማረጋገጥ …የተዝለገለገ አረንጓዴ ፈሳሽ..እናቴን የጋተቻት ላካ
መድሀኒት ሳይሆን ሞት ነበር…እናቴን ለካ በሽታው ሳይሆን በዚያች አረመኔ የተሰጣት መርዙ
ነበር የገደላት….እርግጥ በጣም ጨካኝና አረመኔ እንደሆነች አውቃለው..ዘራፊና ገዳይ
እንደሆነችም የአይን ምስክር ነኝ…..እኔም እራሴ የእሷ ውጤት ነኝ…ግን የገዛ እናቴን
ገድላታለች ብዬ ለደቂቃ እንኳን ተጠራጥሬያት አላውቅም ነበር….እና እንደእብድ
አደረገኝ..ያንን መርዝ በወቅቱ ተግቼ እናቴ የሞተችውን ሞት ለመሞት ተመኘው….ሰውዬውን
ለመዝረፍ የነበረኝን ሀሳብ ተውኩት… ብልቃጡን ኪሴ ከትቼ ጥዬ ወጣው.
.ለካ ያንን ሁሉ ዘመን ስታሾፍብኝ ነበር…ለካ እናቴን ገድላ በእኔ ስትበልፅግ ነበር…..ለካ
ሸርሙጣ ያደረገቺኝ በዕቅድ ነበር..ለካ ስዘርፍ የኖርኩት ለእሷ ነበር…ሁሉ ነገር ግልጽልጽ
አለልኝ..ያንቻው ነው እያለወች በስሞ ስትገዛ ከኖረችው ንብረት አንዲቶንም
እንደማታቀምሰኝ እርግጠኛ ሆንኩ…እግዚያብሄር ባያጋልጣት.. ተጠቅማብኝ ተጠቅማብኝ
የጠገበቺኝ ጊዜ ለዛውም በቅርብ እኔንም በዚያ መርዝ ልታስወግደኝ እንደምትችል እርግጠኛ
ሆንኩ..ከዛን ቀን ጀምሮ እሷንም ሌብነት የሚባለውንም ነገር እርግፍ አድርጌ
ተውኩ…..ሁለቱንም ዞር ብዬ ላላያቸው ለራሴ ማልኩ፡፡
‹‹እሷስ አልፈለገችሽም ?››
እሷማ የነዳጅ ጉድጓድ እንደደረቀበት አረብ ነው ያዘነችው..ከእኔ ለመታረቅ እና ወደ ቤት
እንደምለስ ያላደረግችው ጥረት ያለመነችው ልመና አልነበረም…››
‹‹እና ተስፋ ቆርታ ተወችሽ ?››
‹‹እስከአሁን እንግዲህ እየተጠባበቅን እንኖራለን…እርግጠኛ ነኝ የሆነ ሆነ ቀን እንደማጠቃት
ትጠረጥራለች… ስለዚህ በተጠንቀቅ እና በመበርገግ ነው የምትኖረው..እኔም እንደዛው
ከፍራቻዋ የተነሳ ጥላዋንም የማታምን ሰው ስለሆነች የሆነ ነገረ ልታደርገኝ እንደምትችል
ስለማውቅ እንደሸከከኝ ነው.... የምኖረው ማን እንደሚቀድም እስከአሁን አለየም ››
‹‹በጣም ይገርማል…››
‹‹አዎ ይገርማል››
‹‹ስልኬ ጮኸ››
‹‹ከሻምቡ ነው..የእህቴ ልጅ ነች የደወለችው›
‹‹ሄሎ አጎቴ››
‹‹ሄሎ በሻዱ…ሰላም ነሽ ?››
‹‹ሰላም ነኝ….ነገ ትመጣለህ እንዴ ?››
‹‹አዎ መጣለው ..ምነው ?›
‹‹አይ ምንም አይደል.. ?እንዲሁ ነው የጠየቅኩህ እናንተ ቤት ነኝ››
‹‹መጣሽ እንዴ… ?››.
‹‹አዎ …አኩዬ ስትደውልልን እማዬ ሂጂላቸው አለቺኝ››
‹‹እና ሚጡ አስቸገረቺሽ ?››
‹‹አረ አላስቸገረቺኝም ..አሁን ተኝታለች››
‹‹አይ ጥሩ ነው..እማዬስ ?››
‹‹እሷም ተኝታለች››
‹‹በቃ ነገ አስከ ስድስት ሰዓት እደርሳለው…አሁን አንቺም ተኚ ደህና እደሪ››
‹‹አሺ ደህና እደር አጎቴ››ስልኩን ዘጋው፡፡
‹‹የእህቴ ልጅ እቤት መጥታ ነው..››
‹‹ገባኝ…አሁን ስትሄድ ምንድነው የምታደርገው ?››
‹‹ማለት.. ?›
‹‹ልጅህን ማነው የሚጠብቅልህ ?››
‹‹ሰራተኛ እፈልጋለዋ››
‹‹ታገኛለህ ?››
‹‹የግድ ማግኘት አለብኝ..ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተሯሩጠው ያገኙልኛል ብዬ አስባለው››
‹‹አይ ጥሩ ነው…››
እንግዲያው እኔም ወደ ሸገሬ ገብቼ ሶስት ቀን ሙሉ ወቋረጥኩተ ስራዬ ልመለስ….››
‹‹ስራዬ..የምን ስራ ?››ጥያቄው የእውነቴን ነበር…ስራዋ ምን ነበር…ምን ስትሰራ ነው
የተገናኘነው… ?ከአዕምሮ ተሰርዞል
‹‹የምን ስራ ትላለህ እንዴ.. ?ምን ስሰራ ነው ያገኘኸኝ ….ሽርሙጥና ነዋ››
‹‹ሽርሙጥና››
‹‹አዎ ሽርሙጥና››
‹‹በፍፅም ወደዛ ህይወት አትመለሺም..ሽርሙጥናውንም እንደስርቆቱ እርግፍ አድርገሽ
መተው አለብሽ….››
‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት››
‹‹እየቀለድኩ አይደለም..እኔ በህይወት እያለው አንቺ ዳግመኛ ወደ እዛ ሕይወት
አትመለሺም››
‹‹እና ታዲያ ምን ልሁን ?››
‹‹ምን ሁኚ ልበላት…ሌላ ምን ስሪ ልበላት….ድንግርግሬ ወጣ..በዚህ ጊዜ የእሷ ስልክ
ጠራ..አነሳችው
‹‹ሄሎ እሱባለው››
ማነው እሱ ባለው ? በአዕምሮዬ የመጣብኝ ጥያቄ ነው…‹‹ሄሎ እሱባለው››
‹‹አለሽ እንዴ ጂጂ….?››
‹‹አለውልህ››
‹‹ጥዋት ላገኝሽ ፈልጌ ነበር››
‹‹ትንሽ ራቅ ብያለው…ነገ ከሰዓት እንገናኝ….?››
‹‹ይቻላል››
‹‹ ግን ችግር የለም አይደል….?››
ንግግሯን ሳትጨርስ እና ለጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ ስልኩ ተቋረጠ‹‹…ምን አይነት ቁሺም
ነኝ… ቻርጅ ሳላደርግ ውዬ አሁን ስልኬ ተዘጋብኝ››
‹‹በእኔ ደውይአ››ብዬ አቀበልኳት
‹‹አይ ስልኩን በቃሌ አላቀውም..እንግባና ቻርጅ አድርጌ ደውልለታለው››አለቺኝ ..በውስጤ
ቅሬታ እየተሰማኝ እንዳለችኝ ሂሳብን ከፍዬ አስነሳዋትና አንድን እጄን ትከሻዋ ላይ ሌላውን
ደግሞ በወገቧ ዙሬያ ጠምጥሜ ይዤት ወጣው…
እንደደረስንና ቤርጎቸንን ከፍተን እንደገባን ሁለታችንም ወደ አልጋው ነው የሮጥነው…
አልጋው ላይ ከሰፈርኩ ቡኃላ ልብሴን ማውለቅ ስጀምር..እሷ በተቃራኒው ቀሚሱን
ሳታወልቅ ከውስጥ ጂንስ ሱሪዋን አደረገች
‹‹ሰው ሊተኛ ሲል ልብሱን ያወልቃል አንቺ በተቃራኒው ታደርጊያለሽ..….?››
‹‹መቼም ሁለታችንም አውልቀን አንተኛም››
‹‹ብንተኛ ምን አለበት….?››
‹‹ነገር አለበት››
‹‹የምን ነገር….?
‹‹ትልልቅ ሰዎች ሚያደርጉት ነገር..››
‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም..ልብስሽን አውልቀሽ ብተኚ ደስ ይለኝ ነበር››ቅሬት ባጋተ
የሚርገበገብ ድምጽ
‹‹ምንም አልገባህም እንዴ….?››አለቺኝ ሱሪዋን አጥልቃ ከጨረሰች ቡኃላ ቀሚሷን በአንገቷ
በኩል ሞሽልቃ እያወለቀች
‹‹ምኑ ነው ያልገባኝ….?››
‹‹በጣም እኮ ነው የወደድኩህ..እርግጥ እንዲህ ስል ውስጤን ንዴትና ብስጭት እየወረረኝ
ነው..ቢሆንም ግን ወድጄሀለው…ያ ደግሞ በእኔ ህይወት ትልቅ ነገር ነው ….አዲስ እና
ያልተለመደ ነገር…ስለዚህ ላበላሸው አልፈልግም..እስኪ ጥቂትም ቢሆን ከወንዶችም
መካከል ጥሩዋች አሉ ብዬ እንዳምንና እንዳወራ እርዳኝ››አለቺኝ ከላይ ቲሸርቷን ለብሳ አልጋ
ላይ እየወጣች….እኔም አወላልቄ ጨርሼ በፓንት እና በፓካውት ብቻ ነበርኩና እንደእሷ
አደረግኩ
‹‹አወሳሰብሺብኝ እኮ …. ››
‹‹ባክህ ለራሴም ተወሳስቦብኝ ነው ››
‹‹ቆይ ለአንቺ ወንዶች ሁሉ መጥፎዎች ሆነው ነው የሚታዩሽ….?››
‹‹አይ የሚታዩኝ ሳይሆን በርግጠኝነትም መጥፎዎችና የማረቡ እብሪተኞች ናቸው…እኔ ከጋሽ
ዜና በስተቀር ጥሩ የሚባል ወንድ አላጋጠመኝም..ያው እሷቸውም ምን አልባት አዛውንት
ስለሆኑ ሊሆን ይችላል…በጣም የተማሩ እና አንባቢም ስለሆኑ ሊሆኑ ይችላል …..አዎ
እሳቸው አስተሳሰባቸውም አኗኗራቸውም ሁለ ነገራቸውም ከብዙሀኑ ወንዶች ፍጽም የተለየ
ነው…
‹‹እኔስ…..….?››የምላስ ወለምታ ..አዳልጦኝ የጠየቅኩት ጥያቄ ነው፡፡
‹‹አንተ… እኔ እንጃ …ያንተ ሚዛን የተለየ ነው….ምን አንተ ላይ እንዳየው አላውቅም…….?
ምን አልባት ፍቅር ሲይዝህ በዛ ሰው በጣም ስትሳብና ግን ደግሞ መኑ እንዳማረከገህ
አይገባህም ይሁናል ….? ..ግን ደግሞ አብረኸው መሆን ትራባለህ…. በእቅፉ ውስጥ
መጥፋት ያጓጓሀል….በትንፋሹ መቅለጥ ያምርሀል …ወይም ጭው ያለ በረሀ ውስጥም
ቢሆን ከእሱ ጋር ብቻህን መኖርን ህልምህ ይሆናል….እሱን ስለማጣት ስታስብ ውስጥህ
በሽብር መናጥ ይጀምራል..አዎ ፍቅር የሚሉት የሰው ልጅ ጣጣ እንደዛ አይነቱ ነው
መሰለኝ››
‹‹የሚገርም አገላለጽ ነው….እና አሁን በገለጽሺው መጠን አፍቅረሺኛል ማለት ነው….?››
ደነገጠች‹‹ማ….? እኔ …….?ማንን….?››
‹‹እኔን ነዋ..››ቆፍጠን ብዬ
‹‹እንዴት ሊሆን ይችላል..….?ከተዋወቅን እኮ ገና ሶስተኛ ቀናችን ነው…..በሶስት ቀን
በፍቅር መያዝ አለ እንዴ…….?››
‹‹በፍቅር ለመያዝ ግን ስንት ቀን ያስፈልገል….? ….በሰከንድ ሽራፊም ሊሆን ይችላል እኮ…
እኔ ግን አፍቅሬሻለው…በጣም ነው የወደድኩሽ..ይሄንን ቃል ከሞች ሚስቴ ውጭ ለማንም
ሴት ተጠቅሜው አላውቅም…በጣም ነው ያፈቀርኩሽ…ስላፈቀርኩሽም ደስተኛ ነኝ››ወሬያችን
ሁለታችም ከጭንቅላታችን ቀና በማለት ትራሳችንን በመንተራስ ፊት ለፊት እየተያየን ነው
‹‹አይ እንዳልከው ከሆነ … ፍቅር ሳይሆን መጋኛ ነክቶሀል ..አየህ መጋኝ ድንገት ነው ለሊት
በራፍ ከፍተህ ስትወጣ..ወይንም ተዘግቶ የቆየ ቤት ድንገት ከፍተህ ስትገባ ..አዎ ያዝን
ጊዜ በጋኛ ድንገት አጠናገረው ይባለል…እና ፍቅርም እንደዛ ከሆነ ፍቅር ሳይን እርግማን ነው
በለው….እንዲህ ማረፊያውን እንኳን የማያውቅ….?››
‹‹ምን ማለት ነው..….?››
‹‹እሺ አፈቀርከኝ…ምን ልታደርገኝ ነው..ሰው እንዴት አንድ ሸርሙጣ ያፈቅራል….?››
‹‹እኔ ሸርሙጣ አላፈቀርኩም ..እኔ ያፈቀርኩት አንቺን ነው..አንቺ ደግሞ ሰው
ነሽ….ሰው….እጅጋየው የምትባለዋን ቆንጆ ብሩህ አዕምሮ ያላትን የሚደንቅ የህይወት ታሪክ
ባለቤት የሆነችውን ከአልማዝ የጠነከረች ልጅን እንዳፈቀርኩ ነው የማውቀው..በዛም
በጣም ዕድለኛ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ..››
በጭቃ ተለውሶ አደባባይ ላይ የተጣለን ወርቅ ወርቅነቱን አውቆ በማንሳት ጭቃውን አጽድቶ
ለመጠቀም እድልና ብልሀትን ይጠየቃል፡፡አኔ ብልህ ነኝ ብዬ ባላስብም እድለኛ ግን
እንደሆንኩ እርግጠኛ ነኝ፡፡››
‹‹ጥሩ ነው..ማፍቀር መፍትህ ነው..እኔ ግን ነገ የምለየውን ….መቼም ደግሜ የማላገኘውን
ሰው አፍቅሬዋለው ብዬ መጃጃል አልፈልግም..አዎ አልፈልግም……በፍፅም..አዎ አንተን
ማፍቀርማ የለብኝም››ለእኔ የምታወራ ሳይሆን ከራሷ ውስጠት ጋር ሙግት የገጠመች ነው
የሚመስለው፡፡
‹‹ለምን አንሄድም….?››
‹‹ወደ የት….?››
‹‹ወደ ሻንብ››
‹‹ምን ለማድረግ..….?››..
‹‹በቃ አብረን እንኖራለን..ሻንቡ ታያታለሽ..እርግጥ ካደግሺባት አዲስ አበባ ጋር ስትነጻፀር
ቀበሌ ልትሆንብሽ እና ሊደብርሽ ይችላል … ቢሆንም ልጄን ትተዋወቂያታለሽ..እሷን
በእርግጠኝነት በጣም ነው የምትወጂያት….እናቴም የምትወድሽ ይመስለኛል››
‹‹የእውነትህን ነው….?››
ለእሷ ሳይሆን ለእናንተ እወነቱን ልንገራችሁ የማወራው ነገር ሁሉ የእውነቴን ይሁን ወይስ
የሆነ ቅዣት ውስጥ ሆኜ የምዘባርቀው እርግጠኛ አይደለሁም….ይህቺ ልጅ አዕምሮዬን
እንዲሰለብ እና የማገናዘብ ኃይሌ እንዲሞጠጥ አደረገች እንዴ….?
‹‹እውነቴን ነው..በቃ አብረን እንሂድ ..ታይውና ከደበረሽ ትመለሺያለሽ››
‹‹ካልደበረኝስ…….?ሁሉ ነገር ቢመቸኝስ….….?››
‹‹እሱ አይደል የሚፈለገው..››
‹‹ምንህ አድርገህ ታኖረኛለህ….?››
‹‹ብታገቢኝ ደስ ይለኛል››
‹‹አረ …አንተ ሰው ጤነኛ አትመስለኝም..ነገ የምትፀፀትበትን ነገር ዛሬ አትዘባርቅ..ነው
ወይስ ሰከርክ….?››
‹‹እንዳልሰከርኩ አንቺም ታውቂያለሽ..እሺ ብለሺኝ ካገበሽ በእውነቱ በጣም እድለኛ ሰው
እንደሆንኩነው እራሴን የምቆጥረው…በእወነት አንቺን አጠገቤ እንድትኖሪ የማላደርገው ነገር
የለም..ምን አልባት እቤት መዋል ይደብረኛል የምትይ ከሆነ የሆነ ሱቅ ነገር ከፍትልሻለው…
በቃ ኮስሞቲክ ቤት..ወይንም ቡቲክ…የፈለግሽውን….››
‹‹አላምንህም››አለቺኝ ፍርጥም ብላ..እውነቶን ነው..ለወንዶች መራር ጥላቻና ከልክ ያለፈ
ንቀት ያላት ልጅ እንዲህ መሰሉን የእን ቅዣት እንደውም አመንኩህ ብትል ነበር
የሚገርመው…
‹‹አላምንህም.. ነገውኑ ማለት ጥዋት እዚሁ ደብተሬ ላይ ሀምሳ ሺ ብር አለ… ባንቺ ስም
አዞርልሻለው..አዛ ስንደርስና ስራ...ስትጀምሪ ደግሞ የተወሰነ ተጨማሪ
ጨምርልሻለው..አይዞሽ ልጅ ጠባቂ ያደርገህኛል ብለሽ ሰግተሸ ከሆነ እሷዋን የምትንከባከብ
ልጅ እንደማገኝ ማረጋገጫ ሰጥሻለው..››
‹‹አመረርክ እንዴ ሰውዬ ….?እኔ እንደውም አሁን ካልከኝ ሁሉ ያጓጓኝ ልጅህን መንከባከብ
እና እንደእናቷ ጉያዬ ውስጥ ሸጉጬያት ስታለቅስ ላባብላት እና እሹሩሩ እያልኩ ላስተኛት
ብችል ብዬ ነው…››
‹‹እና አድርጊዋ ..እናቷ ሁኚ…….. ››
‹‹በምንም አይነት መንገድ…….?ላገባህ እንደሆነ አልችልም..››
‹‹እሺ አታግቢኝ …ግን አብረን እንሂድ እና ሌላ ስራ ጀምሪ ….ቢያንስ እንደወንድምሽ
ቁጠሪኝና በቃ ባለውበት አካባቢ ኑሪ …ጥሩ ጓደኛሞች እንሆናለን..በፈጠረሽ ወደ እዛ ከተማ
አትመለሺ….ባይሆን በቅርብ ወደ ነቀምት ቅያሬ ጠይቃለው..ነቀምት ትልቅ ከተማ ስለሆነ
እዛ አይደብርሽም››
‹‹እኔ ሚስትህም እህትህም መሆን አልፈልግም››
‹‹አረ በፈጠረሽ››
‹‹ሰራተኛህ አድርገህ ቅጠረኝ››
‹‹ምን….?››
‹‹አዎ የልጅህ ሞግዚት አድርገህ ቅጠረኝ….ሚስትም መሆን ነጋዴም መሆን አልፈልግም››
‹‹እኔ አንቺን ሰራተኛ አድርጌ.….?.››
‹‹አዎ..ለሄደችው ሰራተኛህ ስንት ነበር የምትከፍላት….?››
‹‹በወር ሁለት መቶ ብር››
‹‹ለእኔ ሶስት መቶ ብር አድርግልኝ…››
‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም….?››አልኮት ሹፈት አዘል በሚመስለው ንግግሯ ተበሳጭቼ…
‹‹እኔም ቀልዴን አይደለም..ነው ወይስ እድሜዬን በሙሉ በሽርሙጥና እና በስርቆት
ስላሳለፍኩ የሞያ ነገር ኔፓ ነች ብለህ አሰብክ….በሞያ አትጠራጠር…አድሜ ለዛች ጭራቅ
ሮማን ተብዬ ….እጄን በማማሲያ እየቀጠቀጠች ነው ሞያ ያስተማረችኝ››
ምመልስላትን አጣውና ዝም አልኩ….በዚህ መካከል እሷ ተነሳችና ተንጠራርታ ስልኳን
ከተሰካበት ነቀለችና ከፈተችው ….ደወለች
‹‹ሄሎ እሱባለው››
ጆሮዬን ቀስሬ ማዳመጥ ጀመርኩ……
‹‹ሄሎ ጂጂ..ስሞክርልሽ እኮ እንቢ አለኝ››
‹‹አዎ ስልኬ ቻርጅ ጨርሶ ነበር…››
‹‹እንደዛ እንደሆነ ገምቼ ነበር..››
‹‹አዎ….ምነው ግን ችግር የለም አይደል….?››
‹‹አረ ፒስ ነው… ዛሬ እሁድ አይደል..የዕቁብ ቀን እኮ ነው››
‹‹እና ጎደለብህ እንዴ….?..››
‹‹አረ አልጎደለብኝም..አስር ሺ ብር ጥዬ እንደውም አንድ ሺ ሶስት መቶ ብር ግልባጭ አለ››
‹‹አይ ጥሩ ነው….ግልባጩ አንተ ጋር ይቆይ..ስፈልገው ደውልልሀለው››
‹‹አይ ለዛ አይደለም የፈለግኩሽ..ዕቁቡ ወጥቶልሻል››
‹‹ወጣ ..››
‹‹አዎ ወጥቶልሻል…ግን አልተቀበልኩትም….አሁን የደውልኩት ጥዋት ተቀብዬ ላቀብልሽ
ወይ ለማለት ነበር…በቃ ከሌለሽ ስትመጪ ይደርሳል ….እንደደረሽ ደውይልኝ››
‹‹አይ አሁን የባንክ ቁጥር ልክልሀለው…. በዛ ታስገባልኛለህ››
‹‹እሺ እንዳልሽ…››
‹‹አሺ ደህና እደር..ደግሞም ግልባጩ የፍንጥር ይሁን››
‹‹አረ ይበዛል››
‹‹አብሽር…..››
‹‹እሺ ይመቺሽ ሲሱ››
ስልኩ ተዘጋ..የእኔ አዕምሮ ግን ክፍትፍት እንዳለ ነው…ወሬቸውን ከመጀመሪያ
እስከመጨረሻው ሰምቼያለው..ግን ግራ ግብትብት እንዲለኝ ነው ያደረጉት..መጀመሪያ እዛ
እራት ላይ እያለን ሲደውልላት..ከወንዶች ጋር የሚያገናኛት ደላላ ነበር የመሰለኝ..አሁን ግን
የሚያወሩት ስለቢዝነስ ነው ..ስለ ዕቁብ ነው››
‹‹የባንክ ቁጥርህን ንገረኝ››ስትለኝ ከሀሳቤ ተነጠልኩ እና ትኩረቴን ወደ እሷ መለስኩ
‹‹የምን የባንክ ቁጥር….?››
‹‹ያንተን ነዋ››
‹‹ምን ሊያደርግልሽ….?››
‹‹አልሰማህም እቁብ ወጣልኝ እኮ….ብሩ አንተጋር እንዲቀመጥልኝ ፈልጌ ነው…50 ሺ ብር
ሰጥተኸኝ የለ..እኔ መቶ ልጨምርበት እና አንድ ላይ 150 ሺ ብር ይሆንልኛል››
‹‹አረ ምን አይነት ናላ አዞሪ ልጅ ነሽ….?››
‹‹እሺ ስጠኝ..እንደውም ተወው ..››አለችና ከመኝታዋ ተነስታ የጃኬቴን ኪስ ጎርጉራ የባንክ
ደብተሩን በማግኘት በስልኳ ቁጥሩን ጻፈችና እንዳለችው ለልጁ ልካለት መሰለኝ ተመልሳ
ወደ መኝታዋ ገባች….አዎ አብራኝ ትሄዳለች ማለት ነው ስል አሰብኩ…ደስስስስ አለኝ
‹‹ለመሆኑ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽው….?››
‹‹እቁብ..››
‹‹እሱንማ አወቅኩ …ግን ምን ሰርተሸ….….?መቶ ሺ ስተይ የሰማው መሰለኝ››
‹‹አዎ ትክክል ነህ..ሚኒባስ አለኝ…ሮማን በተለየዋት በወሩ ወዳ ሳይሆን ፈርታ ትገድለኛለች
ብላ ይመስለኛል የሻከረ ልቤን ምታለሰልስ መስሏት ሚኒባሱን በስሜ አዙራ
መለሳልኛለች››
‹‹ሚኒባስ..እና ስራውን ለምን አልተውሽም…….?››
‹‹እኔ እንጃ …ከሌብነት እና ከሽርሙጥና በስተቀር ሌላ ስራ ያለ ስለማይመስለኝ
ይሆናል….አንድ ለማኝን ከጎዳና ወስደህ በቀን ለምነህ የምታገኘውን ብር በእጥፍ አድርጌ
ሰጥሀለው አንተ ልመናውን ተውና እቤትህ ተቀመጥ ብትለው በአንዴ እርግፍ አድርጎ
የሚተው ይመስልሀል..….?ተደብቋ ወይም ሌላ ሰፈር ቀይሮም ቢሆን ይለምናል..ሌባ
ላመሉ ዳቦ ይልሳል ይባል የለ….
‹‹ደግሞ ስድስት ወር ሆኖኛል በሽርሙጥና የማገኘውን ብር ለገዛ ራሴ መጠቀም ካቆምኩ››
‹‹እና ምን ታደርጊዋለሽ….?››
‹‹…ፒያሳ ውስጥ ከሸሌ ተወልደው ግን እናታቸው የሞቱባቸው በየበረንዳውም በየዘመዱም
ተጠግተው የሚኖሩ ፈላዎች ሞልተዋል…ልክ እንደእኔ አይነት ዕጣ ላይ ህይወት አሸቀንጥራ
የወረወረቻቸው…..እና ከነዚህ መካከል ስምንት ሚሆኑትን ጋሼ ዜና እቤታቸው ያኖሯቸዋል…
ያላቻቸው ቤት ባለአንድ ክፍል ብትሆንም በተደራረበ አልጋ ላይ እዛ ያሳድሮቸዋል…ከዛ በላይ
ሊያደርጉላቸው ግን አቅም የላቸውም እራሳቸውም የሚኖሩት በሽራፊ የጡረታ ብር ነው…እኔ
ደግሞ በቀን አንድ ጊዜ ምሳቸውን እችላቸዋለው..ከዛ የቀረውን እነሱ ተሮሩጠው በመሸቀል
እና እርስ በርስም በመረዳዳት ህይወታቸውን ይገፋሉ… አንድ ደግ የፒያሳ ሀብታም ደግሞ
የትምህርት ቤት ወጪያቸውን ትችላቸዋለች..ሁሉም ይማራሉ …..ከትምህርት ቤት ከቀሩ
ድራሻቸውን ነው የማጠፋቸው…. ጋሼ ዜናም በትምህርት ቀልድ አያውቁም…. ፡፡››
‹‹እኔ አንቺ የምታወሪውን ነገር ሁሉ ለማመን በጣም እየተቸገርኩ ነው..ለመሆኑ በቀን አንድ
ጊዜ እየበሉ እንዴት ነው ትምህርት የሚገባቸው….ለዛውም ህጸናት ሆነው፡፡
‹‹እና በቀን ሁለት እና ሶስቴ ከበሉማ ምኑን ችግረኛ ሆኑ…..ይችሉታል..ላያስችል አይሰጥም
ይባል የለ….ድግሞ ሁሌ በቀን አንዴ ብቻ ነው የሚበሉት ማለት አይደለም…ግን ቢያንስ
ከጠፋ ከጠፋ በቀን አንዴ እስኪጠግቡ ይመገባሉ…››
‹‹እና አሁን ቅር ይላቸዋላ….?፡፡››
‹‹ለምን….?››
‹‹ማለት ሳትነግሪያቸው ስለመጣሽ››
‹‹አይ …የምግቡን ኮንትራት በወር አንዴ ነው ምዘጋላቸው…እንዲሁ ለአይናቸው ሲያጡኝ
ይናፍቁኝ ይሆናል እንጂ ሌላ ችግር የለውም….ደግሞ ነገ ልመለስላቸው አይደል….?››
‹‹በየሰከንዱ ነው እንዴ ሀሳብሽን ምትቀያይሪው..አብረን እንሄዳለን አላልሽም››
‹‹መቼ ነው እንደዛ ያልኩህ….….?ወጣኝ….?››
‹‹ብር ባንተ ደብተር ይግባልኝ እያልሽ አልነበር….?››
‹‹እሱማ ይገባልኛል››
‹‹እና አብረሺኝ ካልመጣሽ ..ብርሽ ምን ያደርግልኛል….?››
‹‹ይቀመጥልኛ››
‹‹በፍፅም …እኔ ባንክ አይደለውም››ኮስተር ብዬ
‹‹እንግዲያው ጥፋቱ ያንተ ነው …ሰራተኛ አድርገህ ቅጠረኝ አልኩህ..እንቢ አልክ››
‹‹አሁንማ ምኑን ቀጠርኩሽ..ይልቅ አንቺው ብትቀጥሪኝ ይሻላል…ለሚኒባስሽ ሹፌር
ስትፈልጊ ንገሪኝ››
‹‹የእወነቴን ነው ቅጠረኝ… ሰራተኛህ ልሁን››
‹‹እሺ››አልኳት ምን አጨቃጨቀኝ ብዬ ….እኔ ራሴ ምን መሆኔ ነው..ከዛ ህይወት ወጥታ
ከእኔ ጋር ለመኖር ትወስናለች ብዬ መጓጓቴ
‹‹ሶስት መቶ ብር ትከፍለኛለህ….?››
‹‹እከፍልሻለው›በወር ሶስት ቀን ትፈቅድልኛለህ….?››
‹‹አረ ለበፊት ለሰራተኛዬ በስድስት ወር አንድ ቀን ብቻ ነው ፍቃድ እሰጣት የነበረው…››
‹‹ስለዚህ አሻሽለው…››
‹‹ለመሆኑ ሶስት ቀን ምን ያደርግልሻል….?››
‹‹አዲስ አበባ እየሄድኩ ልጆቼን የማይበት.. የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማሟላበት››
‹‹እንደዛ ከሆነ ተስማምቼያለው…››
‹‹እሺ ከነገ ጀምሮ የቤትህ ሰራተኛ የልጅህ ሞግዚት ነኝ…አሁን ለመጨረሻ ጊዜ እቀፈኝ››
ለመተኛት ትራሱንት አስተካክላ እየተዳለደለች … እኔ ተመሳሳዩን በማድረግና ለእንቀልፍ
እራሴን እያዘጋጀውና እሷንም እያቀፍኳት››
‹‹ለምንድነው ግን ማቀፌ የመጨረሻ የሚሆነው….?››
‹‹እንዴ የሄደችብህን ሰራተኛህ አቅፋህ ነበር እንዴ ምትተኛው….?››
‹‹በስመአብ ..ምን ለማለት ፈልገሽ ነው….? ››
‹‹ምንም.. ለማለት የፈለግኩት እኔም ከነገ ጀመሮ ሰራተኛህ ስለሆንኩ ላቅፍህም ሆነ
እንደዚህ ልስምህ አልችልም..ጭራሽ አብሬህም መተኛት አልችልም…›› ብላ ጉንጬን
ሳመችኝና.‹‹ደህ አድር›› ብላ አይኗቾን ጨፈነቻቸው..
እኔም ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋውና በስርአቱ አቅፉያት …ፀጉሯን እየዳበስኩ ወደ
እንቅልፍ ሳይሆን ወደ ማሰላሰል ውስጥ ገባው..እውነት ያለችው ነገር ከምሯ ሆኖ አብራኝ
ትሄድ ይሆን ….….?መቼስ ሰራተኛህ እሆናለው የምትለው የአመቱ ታላቁ ቀልድ መሆን
አለበት…ነግቶ የሚፈጠረውን ነገር ለማወቅ ቸኮልኩ..ይዤት ወደ ሀገሬ እበራለው ወይስ
እሷን በሚኒባስ ወደ አዲስ አበባ አሳፍሪያት እኔ በሀዘን እና በትካዜ ወደ ልጄ
እሄዳለው…..እስከዛሬ ለአመታ የኖርኩት ብቸኝነት አሁን አስፈራኝ…እንዴት ነበር ያን ሁሉ
አመት ያለ ፍቅር ያሳለፍኩት…….?ትታኝ ስትሄድ እንዴት ነው የምሆነው…….?አንዴት ነው
ዳግመኛ ማጣትን የምቋቋመው….….?ከእንቅልፌ ስባንን ሰዓቱ ንጊት አካባቢ ሆኖ ነበር…አስራ አንድ ሰዓት ተኩል…ቀስ ብዬ
ተጠንቅቄ መብራቱን አበራውት..ጄጄ ደረቴ ላይ ሽብልል ብላ የሰላም እንቅልፋን
እየለጠጠችው ነው፡፡አትኩሬ በጽሞና አስተዋልኳት…ፊቷ ላይ ፍጽም ሰላም እና መረጋጋት
ነው የሚነበበው…በዛ ሁሉ መከራ በዛ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ያለፈች አትመስልም…በፍፅም …
አረ እንደውም አሁን እንዲህ ሳያት ከቤተሰብ ጉያ ወጥታ የማታውቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤርጎ
ያደረች…ለማጀመሪያ ጊዜ ከእኔ ጋር የተኛች ነው የምትመስለው….
ጉዴ ፈላ… ይህቺን ልጅ በጣም ነው ያፈቀርኳት..አሁን እትኩሬ ሳያት እንኳን እንዴት የልቤ
ምት እንደጨመረ..እንዴት ደሜ በውስጤ ሞቆ መንተክተክ እንደጀመረ እኔ እና እግዜር ብቻ
ነን የምናውቀው…..አዎ ይህቺን ልጅ ከዚህ በላይ ላቅፋት ነው የምፈልገው ….ይቺን ልጅ
ከአዚህ በላይ ነው ልንከባከባት የምፈልገው….ይህቼን ልጅ ከዚህ በላይ ነው ልዋሀዳት
የምፈለገው….ይህቺን ልጅ ለዘላለሙ ነው አብሬያት መኖር የምፈልገው፡፡
ይገርመኛል ስለማንነቷ በአይኔ ያየዋቸው ከእሷም የሰማዋቸው ነገሮች እና በውስጤ ደግሞ
ስለእሷ የማስበው ፍጽም የተለያየ ነው….እንዴት ነወ ሰው በአይኖቹ ያየውን ነገር ላለማመን
የሚችለው…. ዛሬ አንድ አልጋ ላይ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ተቃቅፈን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ
ተጣብቀን ስንተኛ ለሶስትኛ ለሊት ነው…በዚህ ሶስት ቀን ሙሉ ግንኙነታችን በመንፈስ
መቆራኝታችን በብዙ እጥፍ ቢያድግም በአካል ቁርኝት በኩል ግን ከሶስት ቀን በፊት ያለበት
ቦታ ነው ያለው…ያገኘዋትም ቀን እንዲህ እሷ ከእነ ልብሶ እኔ ደግሞ እራቁቴን ተቃቅፈን
ነበር የተኛነው..ዛሬም በሶስተኛው ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ነው ተኝተን የምንገኘው…
…….እና እሷ ስለነገረቺኝ ነገር አይደለም ውስጤ እያሰበ ያለው…. ባሳለፈችው ህይወት
የተነሳ ወንዶች ላይ ባለት ጥላቻ የተነሳ እኔን ላለመጥላት ወደ ወሴባዊ ግንኙነት መግባት
እንዳማትፈልግ የነገረቺኝን አይደለም እያሰብክ ያለውት….ድንግል ሰለሆነች..ከዚህ በፊት
ወንድ ስለማታውቅ ፈርታ ወይም አፍራ እንቢ ያለቺኝ እና በድንብ ስትለምደኝ ሁሉ ነገሯን
ስትደብቅ እና ሳትሰስት ግልጽልፅ አድርጋ እንደምትሰጠኝ ነው የማስበው …፡፡ማልመውም
እንደዛ ነው…እንጂ እሷ ለእኔ አምስት አመት በውሲብ ንግድ ያሳለፈች ….በሺ ወንዶች
ወሲባዊ ላብ የወረዛች…ለሺ ቅንዝራም ወንዶች ጭኖቾን ያስጎበኝች…ከሺ ወንዶች ጋር
ተዳርታ መቶ ሺ ብሮችን የሰበሰበች....ከእድሜዋ እጥፍ የኖረች የችግሮች ማከማቻ..
የመከራ ጎተራ እንደሆነች ባውቅም ያንን እንዴት ማሰብ እችላላው..?በምንስ አቅሜ በዛ
አይነት ምስል እሷን ልሳላት እችላለው..?፡፡አዎ የሰማውትም ያየውትም ይሄንን ነው
..ውስጤ ግን እንዲህ አይደለም የሚያስበው… ልክ እንዷ ልጄን በምወዳት መጠን
ልወዳት..ልክ ልጄን በምጠብቅበት መጠን ልጠብቃት… ልክ የልጁን የነገ ህይወት
ለማሳመር በምጥርበት መጠን ለዚህችም ልለፋላት እፈልጋለው….ረዳት አልባ እና ደካማ …
ማረፊያ ጎጆ የሌላት ወፍ አድርጌ ነው የማስባት….አውቃለው እውነቱ ይሄ አይደለም..
እሷ… ይህቺ ክንዴን ተንተርሳ አንገቴ ውስጥ ተወሽቃ የተኛችው ልጅ ጥንካሬዋ ከአልማዝ
በላይ… በራስ መተማመኗ ከነገስታቶች የበለጠ...መከራ ማይበግራት…ችግር ጠምዝዞ
የማይሰብራት…ለወደደችው ህይወቷን እስከመስጠት የምትሰዋ.. የጠላችውን ህይወቱን
ለመቀማት ድፍረቱና ፅናቱ ያላት…የተራራ ግዝፈት እና ውቅያኖስን የሚያህል ጥልቀት
በሚጢጢ ልቧ ተሸክማ የምትዞር ልዩ ልጅ እንደሆነች አውቃለው….
እውነታው እሷን ለመጠበቅ..እሷን ለመንከባከብ ሳይሆን በእሷ ለመጠበቅ እና በእሷ
የእንክብካቤ ጥላ ውስጥ ለመሸሸግ የፈለኩት እኔ እራሴ ነኝ..በህይወቴ ውስጥ
የተተከለውን ስር የሰደደ ፍርሀት እንድታክምልኝ ነው የፈለኳት..በብቸኝነት እና በፍቅር እጦት
የሚዳክረውን ልፍስፍሱን እኔነቴን እንድትጠግንልኝ እና እንድታበረታልኝ ነው የፈለኳት ..ለገዛ
ሀጃዬ..ለገዛ ደንታዬ..አዎ እወነታው ያ ነው፡፡
1፡20 ላይ ባላችበት እጆቾን ዘረጋግታ ተንጠራራችና ቀስ በቀስ ዓይኖቾን ገለጠቻቸው
‹‹..አዎ ከነቃው ሁለት ሰዓት ሊሆነኝ ነው››
‹‹ሁለት ሰዓት ታዲያ ለምን አልቀሰቀስከኝም…..?ረፍዷል እኮ››
‹‹በተመስጦ እና በፍዘት እያየሁሽ …እንዴት እንደምታምሪ ከጨረቃ ውበት ጋር እንኳን
መዳደር እንደምትቺይ እያሰብኩ… በመደመም ላይ ሰለነበርኩ የሰዓቱ ርዝመት
አልታወቀኝም….››
‹‹ወሬ አለብህ…በል ተነስ››ብላኝ ቀድማኝ ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ገባች፡፡
ተነሳውና ልብሴን መለባበስ ጀመርኩ..እሷም መጣችና ከላይ የለበችውን ቲሸርት
አወለቀች…ያ እንደሰነፍ ገበሬ የእርሻ መሬት በተወለጋገ ጠባሳ እና ሰንበር የተሞላ ግማሽ
ሰውነቷን ዳግመኛ ፊት ለፊት ስትገትር ስቅጥጥ አለኝ….ደግነቱ ቶሎ ብላ ማታ የገዛውላትን
ቀሚስ አነሳችና ለበሰች…ተንፈስ አልኩ..ቀጠለችና ለብሳ ያደረችውን ሱሪ በማውለቅ
ፔስታል ውስጥ ጨመረችው…ሙሉ ዝግጅታችንን ጨርሰን ቤርጎውን አስረክበን ለመውጣት
15 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀብን፡፡
ወደ ሚኪናችን እያመራን ነው..የልቤን ምት አትጠይቁኝ.. ተፈጥርቃ በአፌ ልትወጣ
እየተንፈራገጠች ነው…የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ወደ መሰቀያው ወይም ወደ መቀያው
በፖሊስ ታጅቦ የሚሄድ ፍርደኛ በመጨረሻው ደቂቃ የሚሰማው አይነት ስሜት ነው
እየተሰማኝ ያለው…የእውነት አሁን አብራኝ ትሄዳለች…የእወነት ዛሬ ይህቺ ልጅ የእኔ ልትሆን
ነው….የእውነት ቀዝቃዛ አንሶላ ለብሼ በድን ትራስ ታቅፌ የምተኛበት ያለፈ የብቸኝነት
ህይወቴ መቋጫ ሊያገኝ ነው…
ገቢናውን ተንደርድሬ ከፈትኩላት..በዝምታ ገባችና ቁጭ አለች..ተመስገን ነው…ይህ
መልካምና የብሩህ ዕድል ብርሀናማ ምልክት ነው..አብራኝ ባትሄድ ኖሮ መኪናው ውስጥ
አትገባም ነበር፡፡ግን ለምንድነው የጨገጋት .. ..?ግን ለምንድነው ፊቷ ኮሶ እንደጠጣ ሰው
እንዲህ በጥዋቱ የተኮሰታተረው…....?ምን አይነት የሰነፍ ጥያቄ ነው እራሴን እየጠየቅኩ
ያለውት…...?ወደ ማታውቀው ሀገር እኳ ነው የምትሄደው… ተወልዳ ያደገችበት 19 አመት
የኖረችበትን ፒያሳን የመሰለች ያራዶች መንደር እኮ ነው ጥላ ልትሄድ የወሰነችው….
ብዙ ጓደኞቾን እና ብዙ ትዝታዎቾን እኮ ነው ለእኔ ስትል በመታው ወደ ማታውቀው ሀገር
ከማታውቃቸው ሰዎች ጋር ለመኖር የምትሄደው..እንደውም እሷ ስለሆነች እንጂ ሌላ
ልፍስፍስ እና ስሜተ ድፍርስ ሴት ብትሆን ኖሮ ይሄኔ ከመኮሳተር እና በዝምታ ከመሸበብም
አልፋ በእንባ ትታጠብ ነበር…በሽራፊ ሰኮንዶች ውስጥ ነው ይሄንን ሁሉ ያሰብኩት… ገቢና
ገብቼ የሹፌሩን ቦታ በመያዝ መኪናውን በማስነሳት ሞተሩ እስኪሞቅ እየጠበቅኩ
ባለውበት ሽራፊ ሰዓት…..
መኪናዋን አንቀሳቀስኩና ወደ በሩ እንቅስቃሴ ጀመርኩ.‹‹እርቦኛል›› አለቺኝ…ከሩቅ የተለቀቀ
በሚመስል የደከመና እና የተጎተተ ድምጽ
‹‹ምን ችግር አለው....?ቁርሳችንን በልተን ጉዞችንን መቀጠል እንችላለን››አልኳት ከግቢው
እየወጣን
‹‹ወደእዚህ ይሻለናል ወይስ ወደእዚህ....?››ደህና ቁርስ የምናገኘው በየትኛው አቅጣጫ
ብንሄድ እንደሆነ ከእሷ ምክር እየጠየቅኩ ነው…ምክንያታዊ ሳይሆን ግምታዊ ምክር
እንድትሰጠኝ…የነቀምትና አቅጣጫ ተወችና ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ በእጆ ምልክት
ሰጠቺኝ…የመኪናዋን አቅጣጫ ወደ እዛ አዞርኩት…የተከፈተ ቁርስ ቤት ከአስፓልቱ ግራና
ቀኝ እያየንበዝግታ እነዳው ጀመር..ግን ስራ የጀመረ ወይም የተከፈተ ቤት ለማግኘት
መነኸሪያው ድርስ መጓዝ ነበረብን…ከመነኸሪያው በተቃራኒ መንገዱን ተሸግሮ ካለ ህንጻ
ምድር ቤት ያለ ካፌ ተከፍቷል፡፡አንድ አምስት የሚሆኑ ደንበኛች በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው
ቁርስ ሲበሉ እና ትኩስ ነገር ሲጠቀሙ ይታያሉ… ወደ እዛው ነዳውና መሪዬን ጠምዝዤ
የመኪናዋን አፍንጫ ወደመሄጃችን ወደ ጉደር አቅጣጫ አዙሬ አቆምኩና
‹‹..በይ እዚህ እንብላና መንገዳችንን እንቆስቁስ››አልኳት
‹‹እሺ›› አለችና ፔስታሏን ይዛ ልትወርድ ተዘጋጀች….. ግራ ገባኝ ..በጣም
ደነገጥኩ..የድንጋጤ ግራ መጋባት፡፡
‹‹ምን ያደርግልሻል….....?ፔስታሉ ይቀመጥ እንጂ››
ትቃወመኛለች ብዬ ስጠብቅ…‹‹እሺ›› አለችና ፔስታሉን ከፍታ ጅንስ ሱሪያዋን አወጣችና
ከኪስ ውስጥ አነስተኛ የኪስ ቦርሳዋን በማውጣት ሱሪውን ወደ ፔስታሉ መልሳ ከታ
ወደነበረበት በመመለስ በአንድ እጇ የኪስ ቦርሳዋን በሌላ እጇ ሞባይሏን በመያዝ.‹‹.ቁርስ
ገባዦ እኔ ስለሆንኩ ገንዘብ ልያዝ ብዬ ነው››ብላኝ መኪናውን ለቃ ወረደች፡፡
የእፎይታ ትንፋሽ ተንፍሼ እኔም ከመኪናው ወረድኩና ቆልፌ ተከተልኳት
‹‹አንድ እንቁላል በስጋ እና አንድ ዱለት››አዘዝኩ
‹‹ አንድ ምግብ ይበቃ ነበር››
‹‹ምነው ከፋይ አንቺ ስለሆንሽ ቆጨሽ እንዴ..?››
‹‹አይደለም ..ጥዋት ስለሆነ አፒታይቱን ከየት እናመጣዋለን ብዬ ነው››አለቺኝ
‹‹ግድ የለሽም የቻልነውን ያህል እንሞክራለን..››አልኳት…..ወዲያው ሳናስበው ወደ
ዝምታችን ተመለስን…ሁለታችንም አንድ የፈራነው ነገር እንዳለ ያስታውቅብናል…ይህቺን
ከተማ መልቀቅ…ወደ ሻንቡ መብረር…ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገር…..
አንድ ልጅ እግር ሴት አንድ አመት የሚሆነው ሕጻን ልጅ የታቀፈች ከጎናችን
ተቀምጣለች….ልጇ በጣም እየረበሻት ነው…..በሀይለኛው ያለቅሳል..ዝም እንዲልላት
ልታባብለው እየሞከረች ነው…..ግን በዋዛ ሚደለል ልጅ አልነበረም….እፍ ውስጥ ጡጦ
ለማስገባት ትሞክራለች… ተንፈራግጦ ከአፉ ውስጥ በምሬት ያወጣል..
‹‹ምን ሆኖ ነው..?››አለቻት …እንደእኔ በልጁ ሁኔታ ቀልቧ የተሰረቀባት የእኔዋ ጂጂ
‹‹ጡት ስጪኝ እያለ ነው መከራዬን የሚያሳየኝ››
‹‹ጡት…!!!!››ግራ ገባኝ..አይኖቼን ወደ ደረቷ ላኳቸው… ዱባ ሚያካክሉ ግዙፍ ጡቶች
በደረቷ ግራና ቀኝ ይታዩኛል
.‹‹እና ለምን አታጠቢውም....?እናቱ አይደለሽም እንዴ....?ጡትሽ እንዳይወድቅ ፈራተሽ
እንዳይሆን....መቼስ ዘመኝኛ ሴቶች እራስ ወዳድነታችው ቅጥ እያጣ ነው››አልኳት
‹‹የልጅቷ ፊት በአንዴ ቅይርይር አለ…አይኖቾ በእንባ ተሞሉ..አረ ለቀቀችው….ልክ እንደነሀሴ
ጅረት መስመር እየሰራ በጉንጮቾ ላይ እየተንኳለለ..መርገፍ ጀመረ….ደነገጥኩ..በጣም
ደነገጥኩ
‹‹ምን አይነት ቀሺም ነህ....?የት ታውቃታለህ እንዲህ ምትዘባርቀው…..?››ጂጂ በእኔ ላይ
አውሬ ሆነችብኝ፡፡ደነገጥኩ፡፡
‹‹እኔ እኮ ስቀልድ ነው..እህቴ ይቅርታ… ማይኆን ነገር ዘባረቅኩ እንዴ..?››
‹‹ልጇን ማጥባት የማትፈልግ እናት እንዳለች እኔ አላውቅም..ለሌቱን ሙሉ እንቅልፋ በአይኔ
ሳይዞር ነው የደርኩት..እንዲመገብልኝ ያልሞከርኩት የህጻናት ምግብ አልነበረም …
ከማልቀስ በስተቀር አንድንም አልቀመሰልኝም..እና ይሄን ያህል በልጄ ምጨክን
ይመስልሀል..?፡፡››እየተነሰቀሰቀች በምሬት ተናገረች፡፡
‹‹አይዞሽ ተረጋጊ…ምን ሆነሽ ነው..?፡፡››ጅጅ ነች ልታረጋጋት እየሞከረች በሀዘኔታ
የጠየቀቻት
አሞኝ ከዋዩ ከተማ ነው ለህክምና የመጣውት …የጡነቀርሳ እንዳለብኝ ከሶስት ቅን በፊት
ነው የተነገረኝ…ለልጄ ጡት ማጥባቱት እንዳቆም አጥብቀው ነግረውኛል…እሺ ምን
ላድርግ….አሁን እዚህ የተቀመጥኩት ወድጄ መሰለህ..ጨንቆኝና የማደርገው ጠፍቶኝ
ነው..ዝም ቢልልኝ ብዬ ለመሞከር ነው….ልጇን አቀፈች… እቃዋን ሰበሰበችና መቀመጫዋን
ለቃ ወደ ታች መንገዷን ቀጠለች..ከአይኔ እስክትጠፋ በዓይኖቼ ሸኘዋት
…ምንም ልል አልቻልኩም..በጣም ነው በራሴ ያፈርኩት…እውነትም ጂጂ እንዳለችው ምን
አይነት ቀሺም ነኝ፡፡
‹‹በጣም አዝናለው..ልጅ ግን ወተት መጥባት ማለት ጡጦውን ለምንድነው እንዲህ
አልጠባም ብሎ ሚያሰቃያት፡፡
‹‹ወላጅ አይደለህ እንዴ ..?ስለእናት ጡት እና ስለ ላም ወተት ልዩነት አታውቅም....?የእናት
ጡት በሜኔራልና መአድን የበለፀገ እረሀብ ማስታገሻ ምግብ ብቻ አይደለም……የእናት ጡት
ከወተትነቱ ባሸገር ከእናቲቱ ልብ ከመነጨ ፍቅር ጋር የተቀየጠ የመንፈስ ምግብም ጭምር
ነው…ለዛ ነው የእናት ጡት ለህጻኑ ሙሉ ጤንነት የሚያጎናፃፈው …ለዛ ነው የእናቱን ጡት
በበቂ መጠን የጠባ ልጅ ዕድሜውን በሙሉ በአካልም በመንፈስም ፅኑና ጠንካራ
የሚሆነው..
አንድ ህጻን ልጅ የእናቱን ጡት ከላም ወተት ብዙ እጥፍ እስበልጧ የሚወደውና
የሚፈልገው የእናት ጡት የበለጠ ጣፋጭ ስለሆነ ይመስልሀል..አይደለም የእናት ፍቅርም
አብሮት እየተቀየጠ ስለሚፈስለት ነው….አንድን ህጻን በደህንት ከኖረበት የእናቱ መህጽን
ወጥቶ ከእናቱ የሚያገናኛው እትብቱም ሲበጠስበት በደመነፍስም ቢሆን ያዝናል
ያለቅሳል..ግን ያንን የሚያካክስለት ጡት ነው… ቀጥታ የእናቱን ጡት አፍ ውስጥ ሲገባ
በእትብቱ ምትክ ከእናቱ ሚገናኝበት የፍቅር ድልድይ ይሆንለታል…
‹‹ገባኝ..››አልኩ ከመግባትም በላይ ገለጻዋ እየገረመኝ..ቁርሱ ቀረበ… በቅጡ ግን
አልበላነውም …ሁለታችንም የምግብ ፍላጎታችን ቁልፍልፍ ብሎ ነበር..እንደነገሩ ቀማምሰን
ከጨረስን ቡኃላ ሂሳብ ከፈለች..ከዛ ድንገት..ፈጠን ብላ ቀድማኝ ተነሳች ወደ… እኔ
ቀረበች… ጉንጬን ጠበቅ አድርጋ ሳመችኝና ..ምንም ሳትናገር..ፊቷን አዙራ መንገዷን
ቀጠለች….አፌን ደም ደም አለኝ…..ምን እያደረገች ምን እየሆነች እንደሆነ መገመትም
እልቻልኩም….ከመቀመጫዬም አልተነሳውም..በተቀመጥኩበት ደንዝዤ በአይኔ ብቻ
እየተከተልኳት ነው..ዞር ብላም አላየችኝ..እንዳቀረቀረች በተጓተተ እርምጃ ቀጥታ እስፓልቱን
ተሸገረች… ሄደች …. ተጠመዘዘች..መነኸሪያ ጊቢ ውስጥ ገብታ ከእይታዬ ተሰወረች፡፡
እውነትም ይህቺ ወፍ ነች…የፒያሳ ሚስጥራዊ ወፍ……ምን ያህል ጊዜ እዛው ትታኝ የሄደቺኝ ቦታ ከነ ድንዛዜዬ እንደቆየው አላውቅም....ምን ሰዓት
ላይ መቀመጫዬን ለቅቄ መኪናዬ ውስጥ እንደገባውም ትዝ አይለኝም…ጉደርን አልፌ
ተራራማ እና ጠመዝማዛውን መንገድ ተያይዤው ጌዶ ከተማ ልገባ ሀያ ኪሎ ሜትር አካባቢ
ሲቀረኝ ነው በመጠኑ ወደ ቀልቤ የተመለስኩት..
ቆይ ግን ሳላውቅ ያስቀየምኳት ነገር ይኖር ይሆን እንዴ…..?ሁሉ ነገር በሳለም እየተጓዘ
አልነበረ እንዴ…..?ለሊት በእንቅልፍ ልቤ በማይሆን መልኩ የማይሆን ቦታ ነካክቼያት
ስሜቷን እስቆጣዋት ይሆን እንዴ..?ምንም ትዝ ሚለኝ ነገር የለም፡፡ነው ወይስ ያቺኝ እናት
ለቀልድ ብዬ የተናገርኩት ነገር ለእኔ ያላትን አመለካከት እንድትቀይር አድርጓት
ይሆን..?..አይ እንደዛማ አይሆንም…ለቀልድ ብዬ ባዳለጠኝ የምላስ ወለምታ ያን ሁሉ ፍቅር
..ያን ሁሉ ተስፋ እንዲህ በአንዴ ገደል አትከተውም..አዎ በፊቱንም ውሳኔዋ ወደ ፒያሳዋ
መመለስ ይሆናል
…አዎ እንደዛ ነው..እንደዛ መሆኑ ደግሞ ያንገበግባል…….አካባቢዬን ቃኘው …የት
እንደደረስኩ ሳውቅ ግርም አለኝ…እንዴት እንዴት ነው የነዳውት....?እንዴትስ ከሌላ መኪና
ጋር ሳልጋጭ....?ያስ ባይሆን እንዴት መንገድ ስቼ ወደ አንዱ ገደል ያልተሸቀነጠርኩ…...?ዝ
ግንን አለኝና አማተብኩ..አማትቤ ዞር ስል ከጎኔ ያለው መቀመጫ ስር ፔስታል አየው …
መኪናውን መንዳቴን ሳላቋርጥ ተንጠራራውና አነሳውት … አዎ የእሷ ቲሸርት እና ጄንስ ሱሪ
ነው…በመስኮቴ አሻግሬ ወደ ቁልቁለቱ ጫካ ውስጥ አርቄ ወረወርኩት….
እንኳን ቡትቶዋን ምኗንም አልፈልግም….አትረባም…እንዴት እንደዚህ ታደርገኛለች…..?
እንዴት እንደዚህ እንደህጻን ልጅ ታታልለኛለች…..?በእሷ ቤት እኔ የገጠር ልጅ ፋራ እሷ
የፒያሳ ልጅ አራዳ መሆኖ ነው….፡፡እሰከአሁን ለሶስት ቀን ስትደበርብኝ ነበር ማለት ነው…..?
ስለእሷ ማሰብ አልፈልግም፡፡›..ፎከርኩ …ግን ውስጤ አሁንም እየተቃጠለ ነው…የሆነ ሹል
ጦር መሳይ ነገር ልቤን እየሰቀሰቀኝ ነው…እና ደግሞ ድክምና ስልምልም እያደረገኝ ነው
…..እናንት በአንዴ መኖር እንዲህ ያስጠላል እንዴ…..? ግን ከዚህች ልጅ ጋር ያሳለፍኩት
ሶስት አመት ነው ወይስ ሶስት ቀን…....?ግራ ግብት አለኝ ፡፡ የእውነቴን እኮ ነው..በሶስት
ቀን ትውውቅማ እንደዚህ ብትንትኔ አይወጣም..እንደዚህ ፍርክስክስ አልልም….፡፡
ልጄ በጣም ናፈቀቺኝ ..መኪናዋ እንደፕሌን ክንፍ ኖሯት በአየር ላይ ብትበርልኝ እና ፈጥኜ
ሾንቡ ብደርስ ደስ ይለኝ ነበር..አሁን የሚያጽናናኝ የልጄ ፈገግታ ብቻ ነው..አሁን ሊያረጋጋኝ
የሚችለው የልጄ ትንፋሽ ብቻ ነው…ውስጥ እግሬን ሁሉ እያቃጠለኝ ነው…፡፡
….ጌዶ ደረስኩ… ዝምብዬ ከተማውን ሰንጥቄው ላልፍ አልኩና ቢያንስ እያቅለሸለሸኝ
ያለውን ነገር ያስታግስልኝ እንደሆን ጥቁር ቡና ልጠጣበት ፈለኩ… መኪናዬን አንድ የጀበና
ብና የሚሸጥበት ቤት አጠገብ አቆምኩና ወርጄ ብና አዘዝኩ…እየጠጣው እያለው ሞባይሌ
ድምጽ አሰማች… ተደውሎልኝ አይደለም…የመልዕክ መጥቶልሀል አብሳሪ ድምጽ
ነው..በግዴለሽነት ከፈትኩት…አፌውስጥ የነበረው ብና ወደ ስርኔ ሾለከ… ትን አለኝ
..እየጠጣው ያለውትን ሲኒ በድንጋጤ ለቀቅኩት …አካባቢው ያሉት ሰዎች ሁሉ
በረገጉ‹‹..አይዞህ…እኔን…ውሃ ጠጣበት››ሁሉም ሊያጽናኑኝ ሞከሩ …ማንንም አልሰማው…
ከኪሴ 5 ብር አወጣውና ጠረጵዛ ላይ አስቀመጬ ቦታውን ለቅቄ ሄድኩ …መኪናዬ ውስጥ
ገባው……
ሞተሩን አስነሳውና የመኪናዬን መሪ ጠምዝዤ አዞርኩ..ወደ መጣውበት ተመልሼ መንዳት
ጀመርኩ..በቃ ላብድ ነው….በትክክል እያበድኩ ነው……ይህቺ ልጅ እያሳበደቺኝ ነው….ሀያ
ኪሎ ሜትር ያህል ነዳው አቆምኩ…እና መንገዱን ተሸገርኩ…ከመኪናዬ ወረድኩና ቀስ ብዬ
በጥንቃቄ ገደሉን ወደ ታች እየተንሸራተትኩ ወረድኩ….ጫካ ውስጥ ገባው … እሾክ
ይወጋኛል አውሬ ያገኘኛል ብዬ ሳልጨነቅ ማሰስ ጀመርኩ… አዎ አገኘውት ..፡፡ተበታትኗል …
ጂንስ ሱሪው ለብቻው የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ተንጠልጥሏል… ቲሸርቱ ደግሞ ለብቻው መሬት
ላይ ተነጥፎ አገኘውት… በፈገግታ ሁለቱንም ከያሉበት አንስቼ ያዝኩ… ፔስታሉን ለማግኘት
ግን አልተሳካልኝም..ምን አልባት ንፋስ ወስዶት ይሆናል…አላስጨነቀኝም ..፡፡በዳዴ የመሄድ
ያህል እየቧጠጥኩ አቀበቱን ወጣው..ለካ መውጣት የመውረድን ያህል አይቀልም
…..ከወጡ መውረድ የሚከብደው ለካ ተመልሶ መውጣት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ
ከልምድ ስለሚታወቅ ነው፡፡
….እያለከለኩ ወደ መኪናዬ ሄድኩና ገቢና ገባው…ሱሪውን በስነስርአትና በጥንቃቄ
አጣጠፍኩ… ቲሸርቱንም በተመሳሳይ አጣጣፍኩት ..በፍቅር ወደ አፍንጫዬ አስጠግቼ ወደ
ውስጤ ማግኩት..በጣም በጥልቀት ሳብኩት..ጠረኗን ለማግኘት..አዎ ጠረኗ ወደውስጥ
ከማግኩት አየር ጋር ተቀላቅከሎ ወደ ውስጤ ገብቶ በሰውነቴ ውስጥ በመበተኑ እያንዳንዱ
የሰውነቴ ሴል ሲነቃቃ እና ሲፍታታ ታወቀኝ…ልብሱን ቦርሳዬ ውስጥ ከእኔ ልበሶች ጋር አንድ
ላይ አስቀመጥኩት… መኪናውን አንቀሳቀስኩ ቦታው ለማዞር ስለማይመች ሰፋ ያለ ቦታ
ለማግኘት የተወሰነ መንገድ ወደ ፊት መንዳት ነበረብኝ… ብዙ ተቸግሬ ነው ያዞርኩት….አሁን
ጭልም ባለ ሳይሆን በጭላንጭል ቢሆን አጨንቁሮ በሚታይ ተስፋ በመረጋጋት እየነዳው
ነው ..ተመልሼ ጌዶ ደርሼያለው….ዋናውን የአስፓልት መንገድን ለቅቄ ወደ ቀኝ ታጥፌ
የሻንቡን መንገድ ይዤያለው…አሁን እንደቅድሙ ቡና አላማረኝም ከተማዋን ሰንጥቄ
አለፍኩ….
ወይኔ የእኔ ነገር እንዲህ ያደረገኝ ምን እንደሆነ ሳልነግራችሁ… ..ማለት የጽሁፍ መልዕክት
ከባንክ ቤት ነው የተላከልኝ … የባንክ ደብተሬ ውስጥ 100 ሺብር እንደገባልኝ ሊነግሩኝ
ነው…ብሩ ወደ እኔ መላኩ አንድ ጭልም ያለ ተስፋዬን በመጠኑ አለምልሞልኛል..መቼም
ልታገኘኝ ባትፈልግ ኖሮ ብሩን አትልክም ነበር…የሚል ሀሳብ በውስጡ እንዲጸነስ ምክንያት
ሆኗል… ለዛ ነው ወደኃላ የተመለስኩት..አንድ ቀን ማለቴ በቅርብ..ነገ ወይም ተነገ ወዲያ
መጥታ ሱሪዬስ ስለትለኝ ጥዬዋለው ልላት ድፍረቱን ከየት አገኛለው… ለዛ ነው የጣልኩትን
ልብሷን ፍለጋ ወደ ኃላዬ ያን ሁሉ መንገድ የተጓዝኩት…..…
ግን ይህቺን ልጅ እኮ ላምናት አልችልም …..ብሩን ወደ እኔ ደብተር ማስገባት ያሰበችው
ቁጥሩንም ለልጁ የላከችለት ትናንት ማታ ነበር..ማታ ደግሞ ለእኔም ብዙ ነገር ብላኝ ነበር…
አብራኝ እንደምትመጣ…ለልጄ እናት መሆን እንደምትፈልግ ቃል ገብታልኝ ነበረ… ግን
አላደረገችውም..የማታ ንግግሯን ሙሉ በሙሉ ሰርዛዋለች..ታዲያ ይሄንንስ ለልጁ ማታ
የነገረችውን ነገር እንዳያደርገው መንገሩን ዘንግታው ቢሆንስ …..?ይሄንን ሳስብ ከእንደገና
በሰውነቴን ጥልቅ ድረስ ቅዝቃዜ ተሰራጨብኝ..ትንፋሼን ወደ ውስጥ መሳብ
አቃተኝ…..ወይኔ ሰውዬው … !!!!መኪናዋ ወዲህና ወዲያ ጆካ ማምታት ጀመረች…
እንደምንም በደመነፍስ ፍሬን ይዤ አቀዘቀዝኩና አቆምኩ…..መሪው ላይ ተደፍቼ ለመረጋጋት
መክርኩ…አስር የሚሆኑ ደቂቃዎችን በደነዘዘ ስሜት ካሳለፍኩ ቡኃላ ስልኬን አነሳው…
ደወልኩላት..በአራተኛው ጥሪ ተነሳ….
‹‹ሄሎ..››
ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ገባው‹‹ ልጁ ብሩን ተሳስቶ አስገብቶታል››
‹‹የቱን ብር..?››የደነገጠ እና የሚርገበገብ ድምጽ ተሰማኝ..ከሰማውት ድምጽ በእጥፍ
የእኔም...ድንጋጤ ጨመረ…
‹‹አይዞሽ…የባንክ ቁጥርሽን ላኪልኝና አሁን ዋዩ ወይም ፊንጫአ ስደርስ መልሼ
ልክልሻለው››
‹‹ምኑን ነው ምትልክልኝ..?››
‹‹መቶ ሺ ብሩን ነዋ…ደብተሬ ውስጥ እንደገባ አሁን በሚሴጅ አሳውቀውኛል››
‹‹…እ እሱን ነው እንዴ....?››ብላ ሌላ ቅዝቅዝ ያለ ስሜት ውስጥ ከተተቺኝ
‹‹አዎ..በሚሴጅ የባንክ ቁጥርሽን ላኪልኝ››
‹‹የባንክ ደብተር የለኝም…አንተ ጋር እንዲቀመጥልኝ ነው ያስላኩት››
‹‹ለምን..?››
‹‹እንዴት ለምን .. ..?ይቀመጥልኛ፡፡››
‹‹ይቀመጥልኝ ማለት .. ..?ትመጪያለሽ …..?ማለት ብርሽን ልትወስጂ››
‹‹በህይወቴ ወሳኝ የሆነ አንድ መፈጸም ያለብኝ የረጅም ጊዜ ዕቅድ አለኝ….ያንን ጉዳይ
በዕቅዴ መሰረት ለመፈፀም ከአስር እስከ ሀያ ቀን ይፈጅብኛል..ከተሳካልኝ ወዲያው
እመጣለው…ማለቴ ብሩ ጋር ሳይሆን አንተ ጋር..ይቅርታ አንተ ጋር ሳይሆን ልጅህ ጋር…
ልጅህን ልጄ ላደርጋት…..››
‹‹እቅድሽ እንዳሰብሽው ካልተሳካልሽስ..?››
‹‹ካልተሳካልኝማ አልተሰሳካልኝም ማለት ነው..ከዛ ቡኃላ እኔም የለውም ማለት ነው››
‹‹አልገባኝም..?››
‹‹በቃ.ጂጂ የምትባል ልጅ የለችም ማለት ነው..እስከ ዛሬ ወር ድረስ ያለህበት ድረስ
ካልመጣው የለውም ማለት ነው..መቼም አልመጣም መቼም አታገኘኝም ማለት ነው…››
‹‹የማትረቢ ነሽ …..የሰው ስሜት መሰባበር የሚያስደስትሽ መጥፎ ሰው ነሽ….በይ አሁን
ስለሌላው ነገር መቀባጠርሽን አቁሚና የባንክ ቁጥርሽን ላኪልኝ..አንቺን ነው እንጂ ብርሽን
አልፈልግም….››ብስጭትጭት ..ንጭንጭ..እልኩባት
‹‹እንግዲያው የባንክ ደብተር የለኝም አልኩህ እኮ››
‹‹የሌላ ሰው ቢሆንም ላኪልኛ …ትቀልጂ.. ››
‹‹ካንተ በላይ የማምነው ሌላ ሰው የለኝም››
‹‹አትቀልጂ.. እኔ መጫወቻ አሻንጉሊትሽ አይደለውም….››
‹‹አውቃለው አይደለህም ..አንተ እስከዛሬ ካወቅኮቸውና ከቀረብኮቸው ሰዎች መካከል
በጣም የተለየህ ተወዳጅ ሰው ነህ….አንተ የህልሜ ወንድ ነህ…በህይወት ካለው ካንተ ርቄ
መኖር አልፈልግም….ሆዴ አንድ ወር ጠብቀኝ ..አንድ ወር ብቻ…..እስከዛ ካልመጣውልህ
ተስፋ ትቆርጥብኛለህ..እስከዛ ካልመጣውልህ ትረግመኛለህ..እስከዛ ካልመጣውልህ
ትጠላኛለህ…እስከዛ ካልመጣውልህ ትረሳኛለህ…››
‹‹…ሄሎ አንቺ ምን እያልሽ ነው....?ሄሎ ..ሄሎ እኮ ነው የምለው..?››ስልኩ
ተዘግቷል..መልሼ ደወልኩ ጥሪ አይቀበልም ይላል….
ምን እያለች ነው....?ምንስ እያደረገች ነው....?ከእኔ እና እሷ ግንኙነት የሚበልጥ ምን
አይነት የህይወት አላማ ቢኖራት ነው…..?ከሞት ወዲህ ማዶ እና ከሞት ወዲያ ማዶ
መሸጋገሪያ ድልድይ ላይ የሚያቆም ጉዳይ ምን አይነት ጉዳይ ቢሆን ነው....?ከመስመሩ
በቀኝ በኩል ከወደቅኩ በህይወት ስለምኖር ወደ አንተ እመጣለው..ከመስመሩ ወደግራ
ከወደቅኩ ደግሞ ወደ ሞት አለም የሚያደርስ ገደል ውስጥ ስለምሰምጥ መምጣት
አልችልም እለቺኝ እኮ ..አዎ ቀጥታ እንደዛ ነው ያለቺኝ..…ልክ በእሳት ተንቀልቅሎ
እንደሚንበለበል የመስቀል ደማራ ወደ ምዕራብ ወደቀ ወደ ምስራቅ እያልን አወዳደቁን
በማየት ትርጉሙን ለመተንበይ እንደምንጨነቅ ….ህልውናን ለእድል አደራ መስጠት…
አንደምንም መኪናዬን አስነሳውና ጉዞዬን ቀጠልኩ… ዋዩን አለፍኩ…ገበቴን በድን ሆኜ
ሰነጠኳት… ፊንጫአ ደረስኩ ..የፊንጫአ ከተማ እንኳን ደህና በጣችሁ ብላ እንግዶቾን
የምትቀበለው በአስፓልቷ ነው… ከጌዶ የጀመረው ኮረኮንች መንገድ ልክ ከተማዋ መግቢያ
ጋር ያበቃና አስፓልቱ ይጀምራል ከተማዋ ስታልቅ አስፓልቱም አብሮ ያልቃል..›
እኔ ግን እስፓልቱ ከማለቁ በፊት መኪናዬን አቆምኩና የባንክ ደብተሬን ይዤ መንገዱን
ተሸገሬ ወደ ንግድ ባንክ ገባው….አዎ ገንዘብ ማውጫ ፎርም ላይ 100 ሺ ብር ጻፍኩና
ፈርማዬን በጥንቃቄ ፈርሜ አዘጋጀው…ሌላ ገንዘብ መላኪያ ፎርም አወጣው…የባንክ ደብተር
ቁጥር ባትልክልኝም በስሟ መላክ እችላለው….የሷን ብራም ፍቅሯንም እኔ ጋር አኑሬ
በስቃይ ማቃተት አልፈልግም …. ቢያንስ ብሯን ትውስድልኝ…ስለዚህ በስሟ
እልክላታለው…፡፡
ቀን ጻፍኩ..የላኪ ስም በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ሙሉ ስሜን ሞላው…የተቀባይ
ስም..ጂጂ..ተሳሳትኩ..ለካ እጅጋየው ነች….ግን እጅጋየው ማ…...?አላውቅም…የአባቷን
ስም አላውቅም..ምን አይነት ቀሺም ነኝ..ግን ይሄማ ቅሽምና አይደለም…ምን ጊዜ ኖሮኝ ገና
እሷን እንኳን በደንብ አውቄ መች ጨረስኩ …..?ለማንኛውም ስልኬን አወጣውና
ደወልኩላት..አሁንም ስልኳ ጥሪ አይቀበልም..ደገምኩት ተመሳሳይ ነው…የሞላውትን
ሁለቱንም ፎርም ጭምድድ አድርጌ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ወረወርኩና
ደብተሬን መልሼ ኪሴ ውስጥ በመክተት የባንክ ቤትቱ ግቢ ጥዬ ወጣው …ወደ መኪናዬ
ገባወና ነዳውት ….አሁን በቃኝ….. እንኳን ከእናንተ ጋር ከእራሴ ጋርም የማውራት አቅሙም
ሞራሉም የለኝም …
ይህቼ ልጅ መልሳ ወደ ህይወቴ ካልመጣች በስተቀር ከእናንተ ጋር መገናኘት
አልፈልግም…..ላወራችሁ ፍላጎቱም አቅሙም የለኝም..በቃኝ…ዝም ማለት ነው
የምፈልገው..ማሰብ ደክሞኛል..ማውራትም ደክሞኛል…
.
.
.
.
እንግዲህ ዋቅቶላ ጂጂ ዳግመኛ ወደ ህይወቴ እስካልተመለሰች ድረስ ምንም
አላወራችሁም ካለ ልናስገድደው አንችልም…ህገ መንግስቱም አይፈቅድልንም…ግን አንድ
ነገር አስቤያለው..ለምን ጂጂን እንከተላትም..እዛ አንቦ መነኸሪያ ጥለናት አይደል እሱን
ተከትለኝ ፊንጫአ ድረስ የመጣነው..እስኪ ደግሞ ወደ እሷ እንመለስና ታወራን እንደሆነ
እንሞክር….ከመቀመጫ ስነሳ.. ወደእሱ በፍጥነት ስራመድ… ጎንበስ ብዬ ጉንጩን ስስመው… ፊቴን
አዙሬ እና አንገቴን ደፍቼ ወደፊቴ ስርመድ..አስፓልቱን ተሸግሬ መነኸሪያ ግቢውስጥ
ስገባ..ይህን ሁሉ በብዥታ እና በደመነፍስ ነበር የከወንኩት….እዛ መቀመጫ ላይ ጥዬው
የመጣውት ሌላ ሰውን ሳይሆን የገዛ ግማሽ አካሌን እንደሆነ ነው የተሰማኝ..ነፍሴም
ስጋዬም ተገምሶ የቀረ…
ቋንቋ ድርጊትን በአግባቡ መግለፅ እና ማስረዳት ይችላል….ስሜትን ለመግለፅ ግን አቅም
ያንሰዋል…..፡፡ በፍፅም በቂ የሆነ አቅም አይኖረውም…በተለይ አንዳንድ ስሜቶችን ዛሬ እኔ
እንደተሰማኝ አይነት ስሜቶችን በትክክል አፍታቶና በታትኖ ለለማስረዳት ቃላቶች
ተሰባጥረው እና ተቀናብረው የሚፈጥሩት ዓረፍተ ነገር በቂ ሊሆን አይችልም….ዝም ብሎ
ሙከራ ነው..ላይ ላይን መዳከር…
...ወይኔ ጉዴ አንባዬ በጉንጬ ተንኳሎ እየወረደ ነው..ይሄ በጣም የሚገርም ነገር
ነው..ደግሞ የተለየ ለቅሶ ነው እያለቀስኩ ያለውት.. በአንድ አይኔ ብቻ ነው እንባዬ
የሚፈሰው…የአንድ አይኔ ምንጭ አሁንም እንደደረቀ ነው…..ቢሆንም ግን በአንድ አይኔም
ቢሆን እያለቀስኩ ነው…መነኸሪያ ውስጥ ገብቼ አጥር ጥግ ይዤ ድንጋይ ላይ ቁጭ
ብያለው….እንደዚህ ያደረግኩት አስቤበት አይደለም…ወደ አዲስአባ የሚሄደው ሚኒባስ
የትኛው እንደሆነ..? የት ጋር እንደምሳፈር…ወያላዎች ሲጣሩ ሰምቼም ሆነ ካፔላ አንብቤ
ወይንም ሌላ ሰው ጠይቄ ልሳፈር የምችልበት ሁኔታ ላይ አይደለውም…..ጆሮዎቼም
ተደፍነዋል አይኖቼም ታውረዋል….
እርግጥ ማታ የዘበራረቅኩት ነገር ትክክል እንዳልነበረ እየተሰማኝ ነው..አዎ
አጎጉቼዋለው…‹‹አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል›› ይባል የለ..በእንደእኔ አይነቱ ላይ
የተተረተ ነው…. እርግጥ በወቅቱ እኔም ተወዛግቤ ነበር…አንድ ልቤ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን
ተከትለሺው ሂጂ ሲለኝ… ሌላው ልቤ ደግሞ ወደ ፒያሳ ሲጎትተኝ ነበር፡፡
ይሄን ሰው በጣም ተሸንፌለተለው..ተሸንፌለታለው ስል አፍቅሬዋለው ለማለት አይደለም…
እርግጥ ለእሱ ለራሱ እንዳፈቀርኩት ነግሬዋለው…ልዋሸው ፈልጌ አይደለም..ግን ከፍቅር
የሚበልጥ ስሜት ነው ለእሱ እየተሰማኝ ያለው…ምን ማለቴ ነው…...? ከፍቅር የሚበልጥ
ስሜት ማለት ምን ማለት ነው…...?ምን አልባት ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር…...?አንድ ሰውን
ማፍቀር ማለት ለዛ ሰው የሚሰማን በጣም የተጋነነ እና ጫፍ ድረስ የተለጠጠ መውደድ
ማለት ነው…..አዎ ያንን አውቃለው..እኔ ግን ለዚህ አይነት ስሜት የታደልኩ ሰው
አይደለውም…ይሄንን ስሜቴን ሮማን ድሮ.. ገና ድሮ ከማንነቴ ውስጥ ሰርዛዋለች….የቀረውን
እንጥፍጣፊ ስሜት ደግሞ ግብዝ እና ትምክህተኛ ወንዷችን ቀን በቀን ተፈራርቀው
አንጠፍጥፈው ደምስሰውታል፡፡
ዋቆቶላን ሳገኘው…ከእሱ ጋር ያሳለፍኳቸው ቀናት …በቃ ሰው እንደሆንኩ እንዳስብ ነው
ያደረገኝ….አባቴ ይመስለኛል..ታላቅ ወንድሜ ይመስለኛል..አጎቴም ይመስለኛል….ከእሱ ጋር
ስሆን በብዙ የስጋ ዘመዶቼ ተከብቤ ምፈነድቅ ይመስለኛል…ይሄን ደግሞ ለዘመናት ከፍቅር
በላይ ስራበው የኖርኩት ስሜት ነው….ለአንድ ሰው ምንም አይነት ዘመድ ኖሮት ካለማወቅ
በላይ ስቃይ የሚሆንበት ነገር የለም….እና ዋቅቶላን ሶስት ቀን ሙሉ ስከተለው የዋልኩት
የማንነቴ ክፋይ ነው ብዬ አስቤ ነው…ይሄንን ክፍተት የደፈነልኝ ስለመሰለኝ ነው…የሆነ
ለዘመናት ጠፍቶ በተአምር ያገኘውት ዘመዴ.. የቅርብ ስጋዬ ..ታላቅ ወንድሜ መስሎኝ
ነው…፡፡
ተከትዬው ላለመሄድ የወሰንኩት አሁን ቁጭ ብለን ቁርስ እየበላን ሳለ ሳይሆን ለሊቱን
ነው…ለሊት እሱ ደረት ላይ ተለጥፌ በእቅፉ ውስጥ ሆኜ አይኖቼን ጨለማው ላይ አፍጥጬ
ለሳዕታት ሳስብ ነበር…..የእሱ አቅፍ ማለት ለእኔ የእናት ማህፀን ማለት ነው….ሲያቅፈኝ
ፍጽም ደህንነት ፍጽም ሰላም ነው የሚሰማኝ…እናቴን ካጣው ቡኃላ ፍጽም ተሰምቶኝ
የማላውቀው አይነት ሰላም…አዎ ሁሉ ነገር እንዳዛ እንዳቀፍኩት ለዘላለም ቢቀጥል ምኜቴ
ነው.. ይሄንን በእሱ እቅፍ ውስጥ የማገኘውን ደስታ ላለማጣት ስል ገነት እንኳን የእኔ
ብትሆን መተው እችላለው…አዎ ምንም ሳላቅማማ እተዋታለው…፡፡ግን በቀሌን ልተው
አልችልም..ፈጽሞ ሮማንን ለማጥፋት ለወራት የነደፍኩትን እቅድ መሰረዝ አልችልም….ለዛ
ነው ጥዬው ለመመለስ የወሰንኩት..አትፍረዱብኝ ፡፡ ይሄ በቀል ለእኔ ከገዛ ህይወቴ በላይ
ዋጋ አለው….፡፡ይሄንን ደግሞ ለእሱ ላስረዳው አልችልም..እንዴት አድርጌ..?፡፡ ስለዚህ
ዝም ብዬው መሄድ ነበር ያለብኝ ….ያደረግኩትም እንደዛው ነው….፡፡
ከአንድ ሰዓት ቡኃላ ይመስለኛል…አዲስአባ አዲስአባ የሚል የጥሪ ድምጽ በጆሮዬ ገባ…
የድንጋይ መቀመጫውን ትቼ ተነሳው..መንቀሳቀስ ግን አልቻልኩም..እግሬ አብጦ ዝሆኔ
የነፋፋው ይመስል ያበጠ መሰለኝ..ከእግሬም አልፎ ጭንቅላቴ ድረስ ነው ብዥ ያለብኝ….
ከድንዛዜዬ ለማገገም 5 የሚሆኑ ደቂቆችን ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ ማበከን የግድ ብሎኝ
ነበር..ከዛ ቀስ በቀስ እያለማመድኩ ወደ ሚኒባሱ ተራመድኩና ተሳፈርኩ…..ሚኒባሱ
እስኪሞላ ሃያ ደቂቃ ቆየን…
ይሄኔ ሄዶ ይሆን .. ..?ምን ተሰማቶት ይሆን…..?ልደውልለት ይሆን…..?ከአምስት ጊዜ
በላይ ስልኬን ለመደወል አመቻችቼ ነበር.. ላደርገው ግን አቅም አልነበረኝም…፡፡
አንቦን ለቀን ወጣን ቡራዩ ልደርስ 25 ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረኝ ነበር ስልኬ የጠራው…
….እሱ ነው የደወለው ..አዎ እሱ ነው ..ምን ማድረግ አለብኝ....?ዝም ልበለው....?
ላንሳው...?.ነፍስና ስጋዬ ነው የተላቀቀው…..ግን አነሳውት….
…..እሱባለው የእቁብን መቶ ሺ ብር በእሱ ደብተር እንዳስገባ ሊነግረኝ ነው
የደወለልኝ…..እና ያ በመሆኑ ደግሞ ከገመትኩትም በላይ አበሳጭቶታል…..የላኩለትን ብር
መልሼ እንድወስድለት ፈልጎል….መጨረሻ በስድብና በእርግማን ሲያንቧርቅብኝ
ድንጋጤውን መቋቋም አልቻልኩም… ጠረቀምኩት…. በፍጥነት መለሶ ሳይደውልልኝ በፊት
ሙሉ በሙሉ ስዊች ኦፍ አደረግኩት..
ምንድነው የሰራውት…...?ወራጅ ሁሉ ማለት አምሮኝ ነበር..እርግጠኛ ነኝ እራሴ የምነዳው
የግል መኪናዬ ቢሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት ምንም ሳላቅማማ ወደ ኃላ ተመልሼ ወደ እሱ እበር
ነበር …አዎ በርሬ እሄድና ጉያው ውስጥ ሽጉጥ ብዬ ለሳዕታት ፀጥ ብዬ የሰላም እንቀልፍ
እተኛ ነበር…ግን አሁን ምንም ማድረግ አልችልም… ወራጅ ብዬ ብወርድ ወደኃላም ሆነ ወደ
ፊት መጓዝ አልችልም..ወደ ሁለቱም አቅጣጫ ትራንስፖርት ማግኘት አልችልም…አውላላ
ሜዳ ነው….በእግርም የማይሞከር ነው..ስለዚህ ያለኝ አንድ ምርጫ ስሜቴን ዋጥ ማድረግ
ነው…ማፈን..፡፡የታፈነ ነገር ደግሞ ይቆያል እንጂ መፈንዳቱ አይቀር …እና
እንዳልፈነዳላችሁ፡፡
የተሳፈርኩበት ሚኒባስ አስኮ መነኸሪያ ወስዶ ጣለኝ …..ቀጥታ ወደ ፍል ውሀ ነው
የሄድኩት… ሰውነቴ ሲጠራ እና ሲነቃቃ ውስጤም ይፍታታልኛል ብዬ በማሰብ…አስከ12
ሰዓት እዛው ቆየው…አዎ ያሰብኩትን ያህል ባይሆንም በተወሰነ መልኩ ተረጋግቼያለው..
ግን ፈልውሀን ለቅቄ ወደፒያሳ መንገዴን ስቀጥል.. በሩቅ ያየውት ሰው ሁሉ ዋቅቶላን
እየመሰለኝ ጠርቼ ላስቆመው ሮጬ ልይዘው እፈልጋለው…እንዴት አንድ ሰው ሌላ ሰውን
እንደዚህ ይርባል…..?በፊት ‹
ሰው ራበኝ› ሲሉ ስሰማ ማጋነን ይመስለኝ ነበር…ለካ ሰውን
መራብ ከምግብ በላይ ነው ስጋንም መንፈስንም የሚያደክመው…ወደ ቤቴ አይደለም
የሄድኩት…
አሁን ጋሼን ማግኘት አለብኝ ..ከዚህ ቁዘማ ውስጥ ሊያወጣኝ የሚችለው የጋሼ ምክር ብቻ
ነው፡፡
ደረስኩና ገርበብ ያለደረስኩና ገርበብ ያለውን የቤቱን በራፍ ገፋ አደረግኩት… ሲጢጢ አለና ተከፈተልኝ..ሹልክ
ብዬ ገባው…ጋሼ አልጋው ላይ ጋደም ብለው መፃሀፍ ቅዱስ ያነባል…አይኛቸውን ወደ በራፍ
ሲመልሱ ተመለከቱኝ…ያ የተሸበበ ጨምዳዳ የሽማጊሌ ፊታቸው እየተላቀቀ… እየፈገገ
ሲደምቅ ታየኝ… ሲያነቡ የነበረውን መፃፋ አጥፎ ከመኝታቸው ቀና ብለው ተነሱ….››
‹‹አንቺ ወፍ የት አባሽ ጠፍተሸ ነበር...?ደግሞ አለባበስሽ ..ፐ..ፐ..ፐ እንዴት አባቱ ነው
ሚያምርብሽ…..?››
ምንም አልመለስኩለትም..አካባቢዬ ያገኘውትን ኩርሲ ያዝኩና ወደ እሳቸው ተራመድኩ…
ውሪዎቹ እቤት ባለመኖራቸው በጣም ነው ደስ ያለኝ….ኩርሲውን ወደ ራስጌው አስጠግቼ
አስቀመጥኩትና ተቀመጥኩበት ..አንገቴን አቀርቅሬ ዝም አልኩ….
‹‹ማን አባቱ ነው ..የእኔን ወፍ እንዲህ ያስከፋት..?››ጎተቱኝና ታፋቸው ላይ አስተኙኝ…
በእድሜ የጠነከረ ቆርፋዳ እጃቸውን ጭንቅላቴ ላይ አሳርፈው በፊቱም ተተረማምሶ
የነበረው ፀጉሬን ይበልጥ ያተረማምሱት ጀመር..እንዲህ ሲያደርጉ ደስ ይለኛል…በቃ ሁሌ
ሲከፋኝ ወደ እሳቸው የምሮጠው እንዲመክሩኝ ወይም እንዲያፅናኑኝ ብቻ አይደለም…
እንደውም ከዛ በላይ እንዲህ እንዲዳብሱኝ ነው የምፈልገው..ይሄ እናቴን ያስታውሰኛል…
በህይወት ሳለች እናቴ ከምታደርጋቸው ነገሮች መካከል ዋናው ይሄ ነው… ሲከፋኝ ወይም
ሲያመኝ ጭንቅላቴን በመዳበስ ማረጋጋት..ማባበል…ማስተኛት..
‹‹የእኔ ወፍ እንዲህ አምሮብሽ… እንዲህ ሴት መስለሽ ልትስቂና ልትደሰቺ ሲገባሽ
ምንድነው ሚያስከፋሽ…..?የእኔ ጀግና አንቺ እንዲህ ስትሸበሪ ማየት ጭራሽ ያስረጀኛል
ታውቂያለሽ አይደል…..?እኔ እንደውም ይሄን ሶስት ቀን ከአይኔ ስትጠፊብኝ ሰግቼ እኮ
ቢቸግረኝ ልጆቹን ተበትነው እንዲፈልጉሽ አዝዤቸው ነው …አንቺ እኮ ለእኔ ፒያሳዬ
ነሽ..ፒያሳን የሚያደምቅልኝ የሰው ትርምስ ወይም የሙዚቃው ጩኸት አይደለም…ያነቺ
በውስጦ መኖር ነው፡፡
እጆቻቸው በፀጉሬ ውስጥ እየተርመሰመሰ ጭንቅላቴን እየደባበሱ ያወራሉ..ሲያወሩኝ ዝም
ብለው ነው…መልስ እንድሰጣቸው ሳይሆን ዝም ብዬ እንዳዳምጣቸው ነው…
‹‹…..ልጄ ያቺ ከይሲ ተተናኮለቺሽ እንዴ…...?እንዴ አንቺ..!!!››ደንግጠው ቀና
አደረጉኝ….አትኩረው አዩኝ..ልክ እንደጥዋቱ አሁንም እንባዬ በአንድ ጉንጬ
ይፈሳል..ጎትተው አስነሱኝና አልጋቸው ላይ ከጎናቸው አስቀመጡኝ…አቅፈው ጉያቸው ውስጥ
ከተቱኝ…
ልጄ በራስሽ አትጨክኚበት…ግድ የለም እስቲ ለስሜትሽ ተሸነፊ….በእኛ ማህበረሰብ
ውስጥ ለስሜት መሸነፍ ደካማ ነት ነው…ለስሜት ስትሸነፊ ለሀጥያት እንደተሸነፍሽ ነው
የሚቆጠረው..ግን ግዴለሽም በእኔ ይሁንብሽ ለስሜት መሸነፍ ሰዋዊነት ነው….እንባሽን
አትገድቢው…ድምጽ አውጥተሸ አልቅሺ …ተንሰቅስቀሽ አልቅሺ..በአንድ አይንሽ ሳይሆን
በሁለቱም አይኖችሽ እንባሽ ይፍሰስ…ለዚህ እንዲረዳሽ ያበሳጨሽን ሰው ያደረገሽን ነገር
አስቢ..ያጣሻትን እናትሽንም አስቢ …ያም ካልበቃሽ ያቺን መሰሪ በህይወትሽን እንዴት
ስትጫወትብሽ እንደኖረች አስቢ…….››ጋሼ መሰሪ ብለው ሚጠሩት ሮማንን ነው..ከበፊትም
ጀመረው ስሟን መጥራት ይቀፋቸዋል..
የማላውቀው ኃይል ከልቤ ተቦጭቆ ተነሳ …ልቆጣጠረው የማልችለው እሳተ ጎመራ
ከውስጤ ፈነዳ… ድምጽ ከጉሮሮዬ እየተምዘገዘገ መውጣት ጀመረ…. እንባዬ በሁለቱም
አይኖቼ በሁለቱም ጉንጮቼ ይወርድ ጀመር..አዎ ያጋተው የስሜቴ ደመና ከውስጥ በፈነዳው
ኃይል ተበታተነ..የራሴን ድምጽ የራሴን መንሰቅሰቅ እራሴው አዳምጠው ጀመር …
ህእ..ህእ..ህእ……ህእ….
ጋሼ ዜና እያባበሉኝ አይደለም…እያወሩልኝም አይደለም..ብቻ እንዳቀፍኝ ነው…ብቻ
ጭንቅላቴን እየደበሱኝ ነው….
በተተረማመሰ ሁኔታ በራፉ ተከፈተ…
‹‹ጋሼ የለችም..››
‹‹ጋሼ አጣናት…››
‹‹እኔም አላገኘዋትም…››
ሁሉም በተሰማሩበት ተልዕኮ እንዳልተሳካላቸው እየተናገሩ ጋሼ ፊት ሲቆሙ …እኔን ጋሼ
ጉያ ውስጥ ኩርምት ብዬ ሌላ ሰው መስዬ(ቀሚስ ለብሼ አይተውኝ
ስለማያውቁ)ሲመለከቱኝ …በደስታ ተውጠው….
‹‹መጥታለች..››
‹‹እቺውና….››
ተራ በተራ እየትንደረደሩ እላዬ ላይ ተንጠለጠሉብኝ
‹‹..ቀስ ቀስ..አረ ገደላችዋት››ጋሼ ናቸው እየተከላከሉልኝ ያሉት..እኔም እንባዬን እንዳያዩ
በዘዴ እየጣራረግኩ ሁሉንም በየተራ ሳምኳቸው….
‹‹የት ጠፍተሸ ነው..?››
‹‹ፖሊስ ጣቢያ ሁሉ ጠየቅን እኮ››
‹‹እያለቀስን ነበር እኮ››
‹‹የት ተደብቀሽ ነው..?››
‹‹ለምን ቀሚስ አደረግሽ..?››
ሁሉም ያለመጣባበቅ እና ያለመደማመጥ የተሰማውን ያወራታል….፡፡አለው….ይሄው
መጣው አይደል…
‹‹ሁለተኛ ሳትነግሪን እንዳትጠፊ..››
‹‹አሺ አላደርገውም…አሁን እራት በላታችሆል....?››አልኳቸው… ከጭቅጭቃቸው
ለመገላገል
‹‹አይ አንቺን ስንፈልግ ነበር ..››
‹‹ስለዚህ እራት አምጡና አብረን እንባላ… ››በማለት ቦርሳዬን አወጣውና ሁለት መቶ ብር
አውጥቼ ሰጣዋቸው‹‹..ደስ ያላችሁን ምግብ ገዝታችሁ ኑ››
የሰጠዋቸውን ብር ተቀብለው ግር ብለው እንደገቡ ግር ብለው በደስታ እየተንጫጩ ወጡ…
‹‹ልጄ አየሽ አይደል እንዴት እንደሚወዱሽ…...?እራት በላችሁ ወይ ብለሽ ጠየቅሻቸው
አይደል…..?እራት ሳይሆን ምሳቸውን አልበሉም..ቀኑን ሙሉ አንቺን በመፈለግ ሲንከራተቱ
ነው የዋሉት…ሁላችንም በጣም ነው የምንወድሽ….አንቺም ትወጂናለሽ አውቃለው..፡፡ግን
እኛን ብቻ ሳይሆን ሌላ ሰውም ለመውደድ ሞክሪ…ቅድም እንደነገርኩሽ ለስሜትሽ መሸነፍን
ተማሪ….ስሜትሽ ውደጂ ካለሽ ውደጂ…..››
ደነገጥኩ… ጋሼ ምንድነው የሚያወሩት....?የምን መውደድ ነው....?ስለዋቅቶላ
ነግሬቸዋለው እንዴ....?ከእቅፉቸው ወጣውና አትኩሬ አየዋቸው… ጥያቄያዊ አስተያየት….
‹‹አዎ ገብቶኛል….እኔ እናትሽ እቅፍ ሆነሽ ጡት ከምትጠቢበት ጊዜ ጀምሮ
አውቅሻለው..አንቺ ማለት ለእኔ ልጄ ነሽ…. አባት ደግሞ የልጁን እያንዳንዱን የስሜት
ለውጥ ያስተውላል..ዛሬ ደሰ ብሎኛል… በአንቺ ላይ ባየውት የስሜት ለውጥ ደስተኛ ነኝ…››
‹‹እንዴ ጋሼ ስለከፋኝ ነው ደስ ያሚሎት....?ስላለቀስኩ ነው የተደሰቱት..?››
‹‹አዎ …በተለይ ስላለቀሽ ደስ ብሎኛል..ይሄ በአንቺ ህይወት አዲስ ባህሪ ነው …አዲስ
ባህሪ ደግሞ ሚወለደው በህይወት ውስጥ አዲስ ነገር ሲከሰት ነው..እርግጠኛ ነኝ አንድ
ሸጋ የልብሽ ደጃፍ ላይ ቆሞ እያንኳኳ ነው… አንቺ ደግሞ ያን በር መክፈት መሸነፍ አድርገሽ
ስለወሰድሽው እየገፋሽው ነው…ልብሽና አዕምሮሽ ጦርነት ገጥመዋል…..››
‹‹አረ ጋሼ እንደዛ አይደለም..››
‹‹ታዲያ እንዴት ነው..?››ሽማጊሌው በአባታዊ ትዝብት ጠየቁኝ
‹እርግጥ በጣም ጥሩ ሰው ነው…ግን በቃ ወንድሜ እንዲሆን ነው የምፈልገው… ታላቅ
ወንድሜ…ከእሱ ጋር መኖር ከእሱ ጋር ማደር እፈልጋለው..ግን እህቱ ሆኜ ….እንደዛ ነው
የምፈልገው..ያንን ማድረግ ስላልቻልኩ ነው የከፋኝ››
‹‹ፈገግ አሉ ጋሼ.. ይህቺን አይነት የጋሼን ፈገግታን አቃታለው…የነገር ፈገግታ ነች…
የምታወሪውን ነገር አላመንኩሽም የሚል መልዕክት አላት…የምታወሪውን ወንድ ከመውደድ
በላይ አፍቅረሽዋል እያለኝ ነው..ይሄንን ከሳቃቸው ተረድቼያለው››
‹‹ጋሼ እርሶ ደግሞ የውስጤን ከእኔ በላይ ያውቃሉ እንዴ…...?ጋሼ እኔ ልሙት እወነቴን ነው
አላፈቀርኩትም..ስታስበው እኔ...፡

በማግስቱ በጥዋት ነው ከጋሼ የተለየውት … ቀጥታ ወደ ስራዬ ነው የገባውት…ምንም
የሚባክን ጊዜ የለኝም…አዎ ጊዜ የለኝም…ቁርጤን ማወቅ አለብኝ፡፡አላማዬን ለማሳካት
ሶስት ሰዎችን መርጬያለው… ሶስት የልብ ጓደኛቼን ..በጣም የማምናቸውን እና
ህይወታቸውን ጭምር ብጠይቃቸው እንደማይከለክሉኝ የማምንባቸውን፡፡ይህንን ስል መቼስ
አይገባችሁም …የአንቺ ጓደኞች ማን የሚሏቸው ክርስቶስ ናቸው ለሰው ሲሉ ህይወታቸውን
የሚሰጡት…? ትሉኝ ይሆናል..፡፡ተሳስተሸል..ወይም ጓደኞችሽን በተመለከተ ያለሽ ግንዛቤ
የተጋነነ ነው ብላችሁም ምክር ልትለግሱኝ ትቃጡ ይሆናል፡፡ይሄንን ለእናንተ በማስረዳት
ላሳምናችሁ አልችልም…ማሳመንም አይጠቀበቅብኝም..እኔ ግን እንደዛ ነው የሚሰማኝ…ያ
ደግሞ በቂ ነው፡፡
..ለማኛውም እነዚህን ጓደኞቼን በመጠኑ ላስተዋውቃችሁ… ሶስቱም ሌቦች ናቸው፡፡
ስራቸውን ልብነት ነው ልላችሁ ፈልጌ ነው..ያው መተዳደሪያ ከሆነ መኪና ማጠብም ኪስ
ማጠብም ስራ ነው..ዋናው ገንዘብ ማስገኘቱ አይደል…ምነው ተሳሳትኩ እንዴ…? ሶስቱ
ሌቦች ሁለት ወንዶችና አንዷ ሴት ነች…እነዚህ ሶስት ሌቦች ዕድሜያቸው ያው ከ19-23
ይሆናል… ግምት ነው…፡፡ትውውቃቸውም ያው ከዕድሜያቸው ጋር ተቀራራቢ ነው…፡፡ይሄንን
ስላችሁ አንድ ቤት ነው እንዴ ያደጉት…? ወይም የአንድ ሰው ልጆች ይሆኑ እንዴ…?
ብላችሁ በውስጣችሁ ጥያቄ ማንሳታችሁ አይቀርም … ብዙም አልተሳሳታችሁም…አንድ
ቤት ባይሆንም አንድ በረንዳ ላይ አንድ ጆንያ እየተናጠቁ በመልብስ..አንድ ቂጣ ለሶስት
በጣጥቀው በመቃመስ …አጫሽ የጣለውን አንድ የሲጋራ ቁሩ ተቀባብለው በማጬስ…
ከጫት ቤት የተሰበሰበ ገራባ አንድ ላይ ተከፋሎ በመቃምና በመመርቀን…ከአንድ መኪና
በአንድ ትንፋሽ ቤንዚል በመሳብ ክፉውንም ደጉንም አብረው ያሳለፉ በአንድ ቤት ሳይሆን
በአንድ ልብ የሚኖሩ ልጆች በሏቸው..እርግጥ ሶስቱም በተለያዩ እናቶች ተፀንሰው
በተቀራራቢ ጊዜ ተቀራራቢ ቦታ ተወልደው በተለያየ ምክንያት እናቶቻውን ያጡ ፒያሳዊያን
ናቸው…..
….ሁለቱ ወንዶች አቃሟቸው ፍፅም ተቀራኒ ነው፡፡አንዱን ስንዝሮ እንለዋለን….ብጭጭ ያለ
ቀይ..አጭር…ቀጭን..ተንኮለኛ እና ለፍላፊ ነው፡፡ሌላኛው ዋርካ ብለን ነው የምንጠራው ...
ግዙፍ ነው..ረጂም ጥቁር…ዝግ ..ቢኮረኩሩትም የማይስቅ… የአፉ ስፋት ስንዝሮን
ጠቅልለው ቢያጎርሱት ሳያላምጥ ዋጥ ማድረግ የሚችል አይነት ተፈጥሮ ያለው ነው…
ትግስተኛና እርግታ የተላበሰ ነው..ግን የትግስቱ ጫፍ ላይ ከደረሰ በቃ አስር ሰው
አይመልሰውም….የቆሰለ ጎሽ በሉት….ፊት ለፊት ያገኘውን ሁሉ በመደረማመስ ከገደል
ሚደበላልቅ…
እንዲህ ተቃራኒ ባህሪ ያላቸው ሁለቱ ጓደኛሞች ግን የእወነት መንትያ ነው የሚመስሉት
..አንዱ ሳይናገር ሌላው ምን እንዳሰበ በቀላሉ ያውቃል…አንዱ ካንዱ ውጭ መኖር ፈጽሞ
አያስብም …እድሜ ልካቸውን የግል የሚባል ነገር የላቸወም..ህፃን ሆነው ውሻ ሲያሳድጉ
ራሱ ውሻው የጋራቸው ነበር….ፀባቸው የጋራ ነው ፍቅራቸውም የጋራ ነው፡፡በአንዱ
ሚወደደድ ሰው በሌላውም በተመሳሳይ መጠን ይወደዳል…በአንደኛው ቂም የተያዘበት
ሌለኛው ነው የሚበቀለው….ሌላው ይቅር ህመማቸው እንኳን የጋራ ነው…ልክ ከአንድ
እንቁላል ተከፍሎ እንደተሰራ እና ከአንድ ማህፀን በአንደ ጊዜ እንደወጣ የእውነት
ተፈጥሮአዊ መንታ አንዱ ከታመመ ከሳዕታት ቡኃላ ሌላውም ያታመማል….
ይሄ ሁሉ ስለእነሱ በቅርብ በሚያውቁ ሰዎች በገረሜታና በአድናቆት ሚያወሩላቸው
ታሪካቸው ነው…ግን ከዛም ከፍ ያለ ታሪክ አላቸው …ከኩኩሻ ጋር የሚያያዝ ታሪክ…ኩኩሻ
ሶስተኛዋ መንትያ ወይም ሴቷ ነች ..ሶስተኛዋ ተጣማሪያቸው ..ውሪ ህጻን ሳሉ ማንም
እንዳይተናኮላት ከህብረታቸው ቀላቀሏት..አብራቸው መኖር አብራቸው መተኛት
ጀመረች..ሰው እንዳይተናኮላት ወይም እንዳትፈራባቸው መሀከላቸው ነበር
የሚያስተኞት….እዛ ጎዳና ላይ ከኩታራነት እድሜያቸው ጀምሮ መሀከል አድርገዋት ግራና
ቀኞ ሲተኙ ከጥቃትም ከብርድም ነበር የሚከላከሉላት…እኩል እያጎረሷት እኩል እየጠበቋት
..እኩል እየተንከባከቧት አብራቸው አደገች…እኩል አደጉ..ለአቅመ መዳራትም እኩል
ደረሱ….የትኛው አጋጣሚ እና በምን ሁኔታ እንደሆነ አላውቅም ሁለቱም በእኩል ጊዜ
ከኩኩሻ ፍቅር ያዛቸው..…እኩል ጠየቋት..እሷም እኩል ተቀበለቻቸው..፡፡
ይለይልን ብለው አልተደባደቡም…የግሌ ነች ብለው አልተፈነካከቱም…ከሁለታችን አንዳችንን
ምረጪ ብለው ፈተና ውስጥ አላስገቧትም…በደስታ ፍቅራቸውን ቀጠሉ…
ይሄው አምስት አመት አስቆጥሯል ኩክሻ የስንዝሮ እና የዋርካው ሚስት
ከሆነች….የአንደኛው ደረት ላይ ተለጥፋ የአንደኛውን ከንፈር ስትስም ለሚመለከት ሰው
ፊልም እየሰሩ እንጂ የእውነት ህይወት አይመስልም…
የሚገርመው ኩክሻ እንደስንዝሮም ያላጠረች እንደዋርካውም ያረዘመች መሀከለኛ ቁመት
ያላት የጠይም ቆንጆ ሴት ነች… እና ሶስቱ አብረው ሲሄዱ ያስቃሉ..ብዙ ጊዜ እሷን
መሀከላቸው አድርገዋት ነው የሚሄዱት ልክ እንደልጅነታቸው እና ስታወራቸው ስንዝሮ
ወደላይ አንጋጦ ሲያዳምጣት ዋርካው ደግሞ ወደታች አዘግዝቆ ይሰማታል…ይሄም
ለተመልካች ፈገግ ያሰኛል፡፡
በነገራችን ላይ አሁን በረንዳ አይደለም የሚኖሩት ከበረንዳ ህይወት ከተላቀቁ ቢያንስ 7
አመት ይሆናቸዋል…አዋሬ አካባቢ ሁለት ክፍል ቤት ተከራይተው ይኖራሉ…ሁለት ክፍል ቤት
ስላችሁ መቼስ በአዕምሮችሁ ሁለቱም ክፍል ላይ አንድ አንድ አልጋ ተዘርግቶ አንዱ
የአንደኛው ሌላው ክፍል የሌላው ….፡፡እንደዛማ አይደረግም…አንደኛው መኝታ ቤት አንደኛው
ሳሎን ነው..አልጋቸው አንድ ብቻ ሆኖ ባለሜትር ከሰማንያ ሲሆን ሶስቱም የሚተኙት አንድ
አልጋ ላይ ነው…እስር ቤት ገብተው በመንግስት ቁጥጥር ስር የመሆን አጋጣሚ ካልተፈጠረ
በስተቀር አንደኛው ከአንደኛው ተለይቶ መተኛት የማይታሰብ ነው…ሲተኙ እሷን መሀል
አድርገው ነው….
በነገራችን ላይ ከሁለት አመት በፊት ወልዳላቸው ነበር…ምታምር እራሷን የምትመስል ሴት
ልጅ …አቤት እንዴት ይወዷት እንደነበር…አንዱ ሰውነቷን ሲያጥባት አንዱ ዳይፐር
ይቀይርላት ነበር..አንዱ ሲመግባት አንዱ ያጫውታታል….ክፋቱ ከስድስት ወር በላይ በምድር
እንድትቆይ አልተፈቀደላትም ነበር ..ድንገት ተቀጨችባቸው..ከእናትዬው በላይ ያዘኑት ሁለቱ
አባቶች ናቸው….አንድ የጋራ ልጃቸውን ነበር ያጡት…ከዛ ቡኃላ ግን እንዴት ደግማ
እንዳላረገዘችላቸው አላውቅም…እኔም ሀዘናቸውን መቀስቀስ ይሆናል ብዬ ስለሰብኩ
ጠይቄያቸው አላውቅም…ለማንኛውም የእኔ ጓደኞች እንዲህ አይነት ናቸው….ብዙ ብዙ ታሪክ
አብረን አሳልፈናል..ክፍውንም ደጉንም…ሌባ በነበርኩበት ጊዜም አብዛኛውን ስራዬን
ከእነሱጋር በቅንጅት ነበር የምሰራው…እወዳቸዋለው ይወዱኛል….
ዛሬ ለከባድ ተልዕኮ ጠረቼያቸዋለው..ለምን እንደፈልግኮቸው ስነግራቸው ያለምንም
ማንገራገር ሶስቱም በአንድ ድምጽ ተስማምተው ነው የመጡት….እነዚህ ጓደኞቼ ያው ጨዋ
ከሚባለው ማህበረስብ ሚለዩበት ነገር አላቸው….አሪፍ ፕሮፌሽናል ሌባን አምነህ አንድ
ሻንጣ ብር ብትሰጠው አትጠራጠር አድርስ ያልከው ቦታ አንድ ነጠላ ብር እንኳን ከላዩ ላይ ሳይቆነጥር ያደርሰልሀል…ህይወትህንም አደራ ከሰጠሀው ህይወቱን ሰጥቶ ይጠብቅልሀል…
ለዛ ነው እንዲህ በእነሱ ላይ የተማመንኩት….
አራት በአራት በሆነችው በእኔ ክፍል ውስጥ ነው ያለነው…እያንዳንዳችን አንድ አንድ ዙርባ
በለጬ ይዘናል….ከእኔ በስተቀር ሁሉም ኒያላቸውን እያቦነኑት ነው…እቤቷ ታፍናለች…እኔ
እራሴ ምርቅን ቅን ብያለው…ጫት ስቅም ከአምስት ቀን ቡኃላ ነው …ዕድሜ ለዛ ዋቅቶላ
ለተባለው ሰው… ከእሱ ጋር በሆንኩበት ጊዜ እኮ ሁሉን ነገር ትቼውና እረስቼው ነበር…
አይደለም ለመቃም ጫት ሚባል ነገር እንኳን መኖሩን ትዝ ብሎኝ አያውቅም ነበር…አይ የኔ
ነገር..ሰበብ ፈልጌ አስታወስኩት አይደል…?ምን ላድረግ ወድጄም አይደለ…በነገራችን ላይ
አሁን ጓደኞቼ ከመምጣታቸው ከአንድ ሰዓት በፊት ደውዬለት ነበር..እንዲህ ነበር የስልክ
ልውውጡ
‹‹ሄሎ ዋቅቶላ››
‹‹ሄሎ ..ደህና ነሽ…ላክሺልኝ››አለኝ ….ከዚህ ጥያቄ ይልቅ ሞቅ ያለ ሰላምታ ነበር
የጠበቅኩት…
‹‹ምኑን…?››
‹‹የባንክ ቁጥሩን..››
‹‹አንተ መቶ ሺብር ብርቅህ እው እንዴ .. …?እኔ እኮ ሰላም ልልህ ነው
የደወልኩት››ተንዘረዘርኩበት
‹‹ያንቺ ሰላምታ ከራስ ምታቴ ይፈውሰኛል……?ሰላምታሽ ናፍቆቴን ያስታግስልኛል….…?
ሰላምታ..ሰላምታ ››
‹‹አረ አረጋጋው››
‹‹አልረጋጋም ..ምንም ልረጋጋ አልችልም››
‹‹እና ምን ይሁን…?››ተበሳጨው..በጣም አበሳጨኝ
‹‹ምን ይሁን .. …?ነያ..መጣለው ብለሽ አልነበር …?ነይ..አብሬህ እኖራለው ብለሺኝ
አልነበር ነይና አብረን እንኑር››
‹‹አንድ ወር ጠብቀኝ ብዬአለው እኮ….…?››
‹‹አንድ ወር ማለት እኮ …. ቆይ ከተለየውሽ ስንት ቀን ሆነው…?.››
.‹‹አንድ ቀን››
‹‹እና ይሄ አንድ ቀን ምን ያህል ረጂምምምምምምመም እንደሆነ ታውቂያለሽ……?
አታውቂም….30 ቀን ማለት ደግሞ እስካአሁን ያሳለፍኩትን ጣር እና መከራ 30 ጊዜ እጥፍ
ማለት ነው…፡፡ታዲያ አስበሽዋል..…?ይሄንንማ አልችልም..ልጠብቅሽ አልችልም…፡፡ዛሬውኑ
ወይም ነገ ማትመጪ ከሆነ ልጠብቅሽ አልችልም..ካልሆነ አንቺን ከመጠበቅ መርሳት
መሞከሩ ይሻለኛል…››
‹‹ልመጣማ አልችልም..ጉዳዬን ሳልጨርስ ልመጣ አልችልም››
‹‹እሺ አንቺ ካልቻልስ እኔ ልምጣ…?››አለኝ በተሰባበረ እና በተቆራረጠ ድምጽ
‹‹ወደ የት…?››ሌላ ድንጋጤ
‹‹አንቺ ጋር ነዋ››
‹‹ልጅህስ…?››
x

ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየዋት ሁሉ ፍዝዝዝ ነው ያልኩት…..በጣም ነው የምታምረው…

No comments

Post a Comment

Popular Posts

© የፍቅር ቀጠሮ የፍቅር ታሪክ 2020
Maira Gall