Sunday, January 19, 2020

የፒያሳዋ ወፍ ሙሉ ክፍል

😘የፒያሳዋ ወፍ💞

❣️ምእራፍ ➀
✍️ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ


Image result for የፒያሳዋ ወፍ

ዋቅቶላ እባላለው፡፡ከክልል ለስራ ነው የመጣውት ፡፡እርግጥ አዲስ አበባ ስመጣየመጀመሪያ ቀኔ አይደለም፡፡በተለያ አጋጣሚዎች በአመት አንዴም ሁለቴም ለቀናቶች ቆይታእመጣለው፡፡አዲስ አበባ ለስራ ስመጣ ደስተኛ ሆኜ አይደለም የምመጣው፡፡አብዛኞቹነገሮቾ አይመቹኝም፡፡ልክ ከሆነ ሰርጐ ገብ ጠላት ጋር ለመፋለም ወደ በረሀ የተላኩ አይነትስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡ወደ ጦርነት እንደምሄድ አይነት፡፡


ሁለ ነገሯ የተጨናነቀ ነው፡፡ወከባ እና ኳኳታ የሚመረትባት የትርምስ ፋብሪካትመስለኛለች፡፡የሰው ልጅ ከሰባአዊነት ዝቅ ብሎ በየጥጋ ጥጉ የተወሻሸቀባት ..እናትልጆቾን ለመለመኛነት የምትገለገልበት….ጎልማሳው ለማኝ የሰውን ልብ ለማራራት ሰውነቱንየሚያቆሳስልባትና የሚቆራርጥባት መኖር የየእለት ፈተና የሆነባት….ሰው ለሆዱ ብቻሲባትት የሚውልባት …ለአብዛኛው የወር የቤት ኪራዩን ከወር ደሞዙ እኩል የሆነባት….የብዙ ምንድባኖች ማጠራቀሚያ መጋዘን ትመስለኛለች፡፡


ይሄን ስል በተቃራኒው በድሎት የሚቃትቱ ቱጃሮችን በውስጧ ሳላይ ቀርቼ አይደለም፡፡በከተማዋ ዳርቻዎች እየታነፁት ህንፃዎች ከተማዋን የሲወዘርላድን ከተማ ነች እንዴ …?ብለን እንድንገረም የሚያደርጉትን አፍን የሚያሲዙ ድንቅ መንደሮችም ታዝቤያለው.. ግንፖሊስ ስለሆንኩ መሰለኝ ዓይኖቼ ወደ ተገፉት ያደላሉ…ትኩረቴ ጓስቆሎች መንደር መክርምይወዳል፡፡ላዳር የመረጥኩት ፒያሳን ነው፡፡ለምን ብትሉኝ ምክንያጽ የለኝም፡፡ግን አላውቅምጨለምለም ሲል እግሬ ወደእዛ መራኝ ፡፡የለበስኩት የሲብል ልብስ ነው፡፡በእጄም ምንምአይነት ሻንጣ ወይም ሌላ ዕቃ አልያዝኩም፡፡ምክንያቱም ዕቃዎቼ ጠቅላላ ይዘናት የመጣነውመኪና ውስጥ ነው ያስቀመጥኩት፡፡


ትንሽ ዞር ዞር ካልኩ ቡኃላ ከጣይቱ ሆቴል ቀጥለው ካሉ ሆቴሎች መካከል ወደ አንድ ጐራብዬ ማደሪያዬን 150 ብር ተከራየው፡፡ቤርጐዋ መፈናፈኛ የሌላት በጣም ጠባብ ብትሆንምብዙም ግድ አልሰጠኝም፡፡‹‹ደግሞ ለአንድ ቀን…›› አዳር ብዬ እራሴን አጽናንቼዋለው፡፡ቤርጐ ከያዝኩበት ክፍል ወጣውና በእግሮቼ መንቀሳቀስ ቀጠልኩ፡፡እራቴን እንዳልበላውያወቅኩት በመንገዴ ላይ የይሆሚያ ክትፎ ቤትን ሳይ ነው፡፡አንጀቴ በምግብ አምሮትግልብጥብጥ ስላለብኝ አላወላወልም ገባው፡፡


በጥንድም በብድንም የሆኑ ተመጋቢዎች በብዛት ይታያሉ …እኔም እጄን ታጥቤ መቀመጫያዝኩ፡፡የቤቱ አብዛኛውን ነገሮች ባህላዊ እንዲመስሉ ለማድረግ ተሞክሮል …ያዘዝኩትምክትፎ ሲቀርብልኝ የበላውት በጣም ጣፍጦኝ ነው፡፡ቢሉ እጄ ላይ ሲደርስ ግን በተቃራኒውእንዴት እንደጐመዘዘኝ አትጠይቁኝ፡፡አይ አዲስ አበባ …አንድም ለዚህ ነው የምታስጠለኝ..፡፡እንድከፍል የተጠየኩት ብር እኮ በሀገሬ አንድ ደህና ጠቦት ይገዛል፡፡


ለማንኛውም ከፈልኩና ስወጣ ሰዓቱም ገፋ ብሎ ነበር ፡፡ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ›…በዚህሳዓት ወደ መኝታዬ መመለስ አልፈለግም..በዚህ ሰዓት ገብቼ ልተኛም ብል እንቅልፍ እሺአይለኝም.. ..የአስፓልቱን ጥግ ይዤ በቀጥታ መንገዴን ቀጠልኩ…ግራና ቀኝ ያሉ አጥሮችሁሉ በቆነጃጅት ተሞልተዋል….በ14 ዓመት እና በ40 ዓመት መካከል ያሉ ሴቶችእራሳቸውን ለገበያ አቅርበዋል፡፡ብቲክስ ውስጥ ለሽያጭ እንደተሰቀሉ የልብስ ሞዴሎችይመስላሉ ፡፡ልክ ሸማቹ መጥቶ በዓይኖቹ መርምሮ በእጆቹ ደባብሶ ይሆነኛል አይሆነኝምብሎ አመዛዝኖ ሂሳብ ተደራድሮ ቀንሱ አልቀንስም ተባብሎ ቀልቡ ከወደደለት ከፍሎአስጠቅልሎ ይዞቸው እንደሚሄድ ከልሆነው ደግሞ እዛው እነበሩበት ማንጠልጠያ ላይሰትሮቸው ጉዞውን እንደሚቀጥል አይነት ነው፡፡


እኔም ልክ እንደሸማች እያንዳንዷን በአይኔ እየመረመርኩ፤ እየተደነቅኩ እና እየተገረምኩጉዞዬን ቀጠልኩ …ያ ብቻ አይደልም የሚያስደንቀው እነዛው ቆነጃጅት የቆሙበት አጥርወይንም ግንብ ወይንም ቤት ግድግዳ ስር ማዳበሪያ ውስጥ ገብተው የተኙ፡በላስቲክተጠቅልለው የተጋደሙ ፤በለበሱት ልብስ ተኮራምተው በተቀመጡበት ድፍት ያሉ የጓዳናልጆች ይታያሉ…የሚበላ ዕንቁላል ቅቅል የሚያዞሩ ጨቅላ ወጣቶች..ጥግ ይዘው ሲጋራናመስቲካ የሚቸረችሩ..ኮንደምና ብሱክት በካርቶን ዳርድረው ሚሸጡ… ብዙ ብዙ ትዕይንትይታያል፡፡ነፍሱ አንድ ብር ስጠኝ…ቆንጆ አትለፈኝ…..ልጅ አዝለው በስራቸው ወደላይ እናወደታች ሚመላለሰውን ሰው የሚማፀኑ…….ወታደሮችም መሳሪያቸውን ደቅነው በቡድን አምስትና ስድስት በመሆን በየሁለት መቶ ሜትርርቀት ልዩነት ይንጎራደዳሉ…አንዳንዴም መንገዱ ላይ የተኮለኮሉትን የምሽት ንግስቶችንከአንዱ የመንገዱ ጠርዝ ወደ ሌላው ያባርራሉ….ይመቶቸዋል መሰለኝ ሲመጡባቸው ግርብለው ይሸሾቸዋል፡፡ብቻ ለእኔ ለገጠሬው ከማሰብ አቅሜ በላይ የሆኑ ብዙ የሚገርሙና ናላ የሚያዞሩትዕይንቶችን ፒያሳን በመሽለኩለክ ስታዘብ ከቆየው ቡኃላ ደከመኝና ወደ አንዱ ሆቴል ጎራብዬ ..አንድ ሁለት ማለት ጀመርኩ…ሆቴል ውስጥም ከጠጪዎች ቁጥር በላይ ቁጥርያላቸው ሴቶች ይርመሰመሳሉ‹‹አሁን እኚ ሁሉ እናትና አባት አላቸው አይደል…?እሺ እናትአባት አይኑራቸው ወንድም እና እህት ያጣሉ..?እሺ እሱስ ይቅር አጎትና አክስት…?እኔ እንጃእኔ የገባኝ ብዙ ቤተሰቦች እዚህም እዛም እየፈረሱ እንደሆነ ነው…ምክንቱም እነዚህ ከፈረሰቤተሰብ …ባይፈርስ እንኳን ተሸንቁሮ ማፍሰስ ከጀመረ ቤተሰብ ሾልከውና ተመዘው የመጡብኩኖች ናቸው…ብዙ ቤተሰብ እዚህም እዛም መፍረስ ሲጀምር ደግሞ አገርም እየተናደችመሆኑ ማሳያ ነው…እንደዛ ነው የተሰማኝ..፡፡ይንን እያሰላሰልኩ መጠጤን ከቢራ ወደ አልኮልአዘዋውሬ ስጋት ..እናም ደግሞ በተከፈተው ሙዚቃ ስደንስ ..ከማላቃቸው መስል ጠቺዎችእየተጋፋውን እየተሻሸው ሀገርኛውንም ፈረንጅኛውንም ሳስነካው ቆየውና ሺደክመኝናሽከሬም ጠንከር እያለ ሲመጣ …ምነካህ ዋቅቶላ ?አዲስ አበባ እኮ ነው ያለሀውይበቃሀል››አልኩና እራሴን በመምከር ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሂሳቤን ከፍዬ እራሴንላለመንገዳገድ እየጠራኩ የነበርኩበትን ሆቴል ለቅቄ ልወጣ ስል አብሬያቸው ስደንስከቆየዋቸው የስካር ጎደኛቼ አንድ ጎትቶ ወደ ኃላ መለሰኝና አንድ ሙሉ ቢራ በእጄእያስጨበጠኝ ‹‹ነፍሱ በጣም ተመችታሀኛል..በዚህች መዚቃ የመጨረሻ ፈታ እንበል እናትሄጃለሽ›› አለኝተወዳጅ መሆንን የሚጠላ የለምና ተወዳጅና ተመራጭ በመሆኔ ኩራት በውስጤ እየተሰማኝየተጋበዝኩትን ቢራ እየተጎነጨው በተከፈተው ሙዙቃ እስኪያልበኝ መወራጨት ጀመርኩአራት ሆነን ሆቴሉን መሀከል ክብ ሰርተን ቀወጥነው..ሙዚቃው እንዳለቀ አመስግኜቸውሹልክ ብዬ .ወደ ቤርጎዬ መንገድ ጀመርኩ…. እንሰደተቃረብኩ አንደ ልጅ እግር በብዥታውስጥ ቢሆንም ደማቅ ቀይ መሆኖ የሚያስታውቅ እንስት ሳለስበው እየተጋላመጥኩሳስተውላት ‹‹ሀይ ቆንጆ›› አለችኝ…ውስጤ ያለው የሴት ፍቅር ይሁን የጠጣውት መጠጥፊቴን አዞርኩና ወደእሷ ቀረብኩ ተጠጋዋት..ጮርቃ ወጣት ብትሆንም ታምራለች…ግንሁለመናዋ የተንቀዠቀዠ ነው..አይኖቾ ራሳቸው ከወዲህ ወዲያ ይሽከረከራሉ..እጆቾም ከቀኝወደ ግራ ይወናጨፋሉ..ምርቅን ቅን ብላለች መሰልኝ ከንፈሯንም እያኘከች ነው‹‹እሺ ሰላም ነሽ?››ብዬ እጄን ዘረጋውላት..እንደመጨበጥ በመዳፎ ነካ አድርጋ መልሳግንባሯን በማቀርቀር ፀጉሯን መጠቅለል ጀመረች‹‹..ቆንጆ ነሽ››አልኳት ሌላ ምላት ጠፍቶኝ‹‹ሾርት ነው አዳር››አለችኝ እኔ ያልኳትን እንዳልሰማ ሆናየምለው ግራ ገባኝ…የመዳራት ዕቅድ ፈፅሞ በዕቅዴ አልነበረም..ግን ካልነበረ ድምጻን

..........ሰምቼ ለምን ወደ እሷ ተጠጋው? ለምን ዝም ብያት አልሄድኩም..?ምን አይነት እንከፍ ነኝ…

አሁንም መሄድ አለብኝ…››እግሬን ግን ማንሳት አልቻልኩም

‹‹ሰማሀኝ ነፍሱ..?››

‹‹አዎ ሰምቼሻለው..አዳር ነው አዳር››ወይኔ ተበላው ምን ማለቴ ነው፡፡

‹‹አምስት መቶ ብር››

‹‹አምስት መቶ››ደንግጬ

‹‹አሺ አራት ይሁን…እንዲሁ ሳይህ ስለተመቸኸኝ ነው እሺ…ፀዳ ያልክ ነህ..እንጂ በአራ እሺ

አልልም ነበር››አለችኝ

እኔን ፀዳ ያድርገኝ…ሙገሳዋ ግን በውስጤ የሆነ ሙቀት እረጭቶብኛል….‹‹እሺ

እንሂድ››አልኳት… በህይወቴ እንደዛሬ አእምሮዬ እና አንደበቴ መግባባት አቅቶቸው አይቼ

አላውቅም፡፡

ይዤት ገባው…አልጋው ጠርዝ ላይ ግራ በመጋባት ተቀመጥኩ…. እሷ ደግሞ አለፈቺኝና

በክፍሉ ያለች አንድ ብቸኛ ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጠች …በቆሪጥ ደግሜ አየዋት…ቅድም

በከፊል በከፊል ጭለማ እና በከፊል ብርሀን ካየዋት በላይ ቆንጅዬ ነች..የሆነች የዱርዬ

ቆንጆ…..ግን የዱርዬ ቆንጆ ስል ምን ማለቴ ነው…?ድርዬ ማለት ምን ማለት ነው…?ድርዬስ

ምን ይመስላል….?

‹‹ተጫወቺ››

እስታይል››አለችኝ እንዳቀረቀረች…

‹‹መተኛት እንችላለን››

‹‹መጀመሪያ ውረዳ››

‹‹ወዴት ልውረድ..››

ሰቋን ለቀቀችው..ሳቋ ከመልኳ በላይ ገዳይ ነው..ደግሞ የጥርሶቾ ንጣት ….

ምን ለማለት እንደፈለገች ቆይቶ ገባኝ…‹‹ኦኬ ሂሳብሽን ነው..አልኩና እጄን ወደኪሴ ላኩ

ባዶ ነው …ሌለኛው ኪሴ ውስጥ ፈለግኩ.. የለም …፡፡ጃኬት ኪሴ ውስጥ ስገባ ዝርዝር

አስር አስር ብሮች አገኘው..አልጋ ላይ ወረወርኩትና ቆሜ ዘቅዝቄ መበርበር ጀመርኩ

..፣፣ሞባይሌ ብቻ ከአንደኛው ኪሴ ተንከባሎ ወለሉላ ወደቀ..ሌላ ምንም የለም‹‹…እንዴ

ተበላው…አሁን እኳ ነው ሄሳብ ከፍዬ መልሼ የከተትኩት››

‹‹ተረጋና ፈልገው››

ለሁለተኛ ዙር መበርበር ጀመርኩ‹‹የለም ከነቦርሳዬ ነው የጣልኩት››

ከተቀመጠችበት ተነሳችና ጃኬቴን ተቀብላ በረበረች..ቁርጥራጭ ወረቀቶችና ቁልፎች ብቻ

ነው ማግኘት የቻለችው..

‹‹ምን አይነት ቀሺም ነኝ…››

‹‹አይዞህ ያጋጥማል››አለችኝ

‹‹ይቅርታ እዚህ ድረስ ስላለፋውሽ…በቃ ልሸኝሽ››

‹‹አንተስ እንዴት ትሆናለህ››

‹‹እኔማ ችግር የለውም …ደግነቱ እንኳንም ሞባይሌ አልጠፋ …ጥዋት

አስተካክለዋለው..አሁን ከመተኛት ውጭ አማራጭ የለኝም››

‹‹በጣም አዝናለው..መጥፎ አጋጣሚ ነው››አለችኝ ግንባሯን ግራና ቀኝ እያወዛወዘች

‹‹ምን ታደርጊዋለሽ..ልሸኚሽ ››አልኩና ጃኬቴን ለብሼ ተነሳው

‹‹በፍጽም አትሸኘኝም..እኔ እኮ መወጫ መግቢያውን እያንዳንዷን ጉድጓድ አውቃለው…››.

ብላ ለመውጣት ወደበሩ ተጠግታ መክፈት ስትጀምር የሆነ የመከፋት መንፈስ በውስጤ

ተሰራጨ..እንደበደልኮት ተሰማኝ.. ይሄኔ እዛው ብትሆን ገበያ ቀንቶት ነበር…‹‹ቆይ አንዴ..››

አልኩና..ከኪሴ ውስጥ ከተገኘው ብር አስር ብር መዝዤ አስቀረውና በግምት ስልሳ ወይም

ሰባ ብር የሚሆን ይመስለኛል..‹‹ይቺን ያዢያት››በማለት ወደእሷ በመጠጋት አስጨበጥኮት

‹‹ግራ መጋባቷን ከሁኔታዋ ያስታውቃል

‹‹እንዴ ምንም የለህም እኮ››

‹‹ግድ የለም ለጥዋት ታክሲ 10 ብሩ ይበቃኛል..ከዛ ጓደኛቼ ስላሉ ከእነሱ እበደራለው››

‹‹የት ነበር ግን ስጠጣ የቆየሀው››ብላ ስናወራ ከነበረው ጋር የማይገኛኝ ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡

የቆየውበትን ሆቴል ነገርኮት..የከፈተችውን በራፍ በአንድ እጇ እንደያዘች ወደ እኔ ራመድ

አለችና ተንጠራርታ ጉንጬን በስሱ ስማኝ ‹‹ደህና እደር ››በማለት ወጥታ ሄደች....

እኔም በራፌን ቀረቀርኩና አልጋው ላይ በመዘረር መብራቱን አጥፍቼ መብሰልሰልጀመርኩ….ከሁለት ሺ ብር በላይ ነበር ቦርሳዬ ውስጥ..እንዴት ሊሆን ቻለ…?ለሰው እንኳንለማውራት ያሳፍረኛል..ስንትና ስንት አመት ዘራፊና ሌባ ሳሳድድ እና ስይዝ…ለተዘረፉትንብረታቸውን ሳስመልስ የኖርኩ ሰው ዛሬ እንዲህ በቀላሉ..፡፡ስጨፍር ይሆናል የጣልኩት….?አዎ መቼስ ኪሴ ሰው ገብቶ ሊወስድብኝ አይችልም..ካልሆነም ቦርሳው ከኪሴ ተንሸራቶወድቆብኝ ሊሆን ይችላል …አዎ እንደዛ መሆን አለበት..፡፡..ወይኔ ተበልቼያለው ሂሳብ ከፍዬ ልወጣ ካልኩ ብኃላ የመለሰኝ ልጅና ጓደኛው…ተስፈንጥሬከአልጋዬ ላይ ተነሳው…ጫማዬን አጠለቅኩ…ግን መልሼ አወለቅኩና በተስፋ መቁረጥ ወደአልጋዬ ተመለስኩ..ምክንያቱም ጅሎች አይደሉም እስከአሁን እዛው ቁጭ ብለውሚጠብቁኝ…፡፡የንዴቴ መጠን ከልክ ያለፈ ስለነበር ውስጤ መንደድ ጀመረ…አሁን ለሰውስ ምን ብዬአወራለው...?በፍፅም… ለአንድ የሰለጠነ እና ልምድ ላለው ፓሊስ በእንዲህ አይነት ሁኔታመዘረፍ ውርደት ነው..አዎ የራሱን ኪስ መጠበቅ የማይችል እንዝላልና ከርፋፋ እንዴትየህብረተሰብን ንብረት ከዘረፋ ሊጠብቅ ይቻለዋል….?በራሴ አፈርኩ…ለምን ያህል ጊዜ ስብሰለሰል እንደቆየው ባላውቅም የሰማውት ድምጽ ነበር ከሀሳቤያናጠበኝ… በራፌ እየተንኳኳ ነው፣አልጋ ክፍሏ ሳትሆን አትቀርምቀ‹‹ምንድነው ….?መታወቂያዬን ከሆነ ጥዋት ትመልሺልኛለሽ››አሁን ትዝ አለኝ …ቅድም አልጋውን ስከራይ መታወቂያ መልሺልኝ ብዬት ብዙ ተጨቃጭቀንነበር…..የዛን ጊዜ ያልኳትን ሰምታ መልሳልኝ ቢሆን ኖሮ እሱም ጠፍቶ ነበር….እንኳንምአበሳጨችኝና ጥዬ ወጣው‹‹ክፈት እኔ ነኝ››‹‹አንቺ ማ?››‹‹ጂጂ››‹‹ይቅርታ ጂጂ ..ምን ፈልገሽ ነው .. .?ተኝቼያለው››‹‹ክፈተልኝ አልኩህ እኮ …አሁን ከአንተ ጋር የወጣውት ልጅ ነኝ…ብር የሰጠኸኝ››ተስፈንጥሬ ከመኝታዬ ተነሳውና መብራቱን በማብረታ በራፍን በረገድኩት..ምንእንዳስገበገበኝ አላውቅም…አዎ እውነትም አራሷ ነች..ግቢ ሳልላት ገፍትራኝ ወደ ውስጥገባች…እኔም ገባውና በራፉን እንደበለቀጥኩ ግራ በመጋባት ወደእሷ ዞሬ አፈጠጥኩባት‹‹ዝጋው እንጂ››ቀጭን ትዕዛዝለቃሏ ታዛዥ ሆኜ ዘጋውትና ‹‹ምነው .. .?እንዴት ተመለሽ.?››ጠየቅኳትከለበሰችው ጅንስ ሱሪ የኃላ ኪስ እጇን ሰደደሰችና ቦርሳዬን ..የራሴን ቦርሳ.. የገዛቦርሳዬን… የጠፋብኝን ቦርሳ እጄ ላይ አስቀመጠችው…ባለማመን አንዴ ቦርሳውን አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅ ስመለከት ከቆየው ቡኃላ‹‹እንዴትአገኘሽው.?››‹‹የነደፉህ ልጆች ጀለሶቼ ነበሩ…››‹‹እና ታዲያ…››‹‹ባሉካዬ ነው ብዬ ለምንኳቸዋ››‹‹ባሉካዬ…እና መለሱልሽ››‹‹አዎ ጀለሶቼ ናቸው አልኩህ እኮ!!!››‹‹ቦርሳውን እንደያዝኩ አልጋው ላይ ዝርፍጥ ብዬ ተቀመጥኩ‹‹ከየት ነው የወሰዱብኝ››‹‹ሆቴል ስትጨፍር …እያጫፈሩ የነበሩ ሁለት ልጆች …››‹‹አዎ ገምቼ ነበር…ይገርማል ..አንቺ ግን ይሄ ሁሉ..ብሩን ከቦርሳው ወስጥ አውጥቼብዛቱን እያሳየዋት……እንዴት ልታስመልሺልኝ ቻለሽ..?ለምንስ ያን ማድረግ ፈለግሽ.?››‹‹አንጀቴን በላኸዋ..››‹‹አንዴት ነው አንጀትሽን የበላውት››‹‹አንደኛ..ሌላው እንዳንተ ቢዘረፍ አካኪ ዘራፍ ብሎ አገር ይያዝልኝ ይል ነበር…እኔንምዘረፍሺኝ..ወይም አዘረፍሺኝ ሊልና ሊመታኝ ይጋበዝ ነበር….አንተ ግን በክብር እና በቁጭትነው የሸኘኸኝ…፡፡ከዛም በላይ ከተረፈችህ ብር አስር ብር ብቻ ነው አስቀርተህ የሰጠኸኝ…እናበጣም ነው ውስጤን የከየፍከው…ቦርሳህን ባላገኝ እንኳን እቤት ሄጄ ብር ይዤልህ ልመጣነበር እቅዴ..በል አሁን ደህና እደር..በነገራችን ላይ ሁለት መቶ ብር ከላዩ ላይ አንስቼሰጥቼቸዋለው..››‹‹ኸረ ችግር የለም እንኳን ሰጠሻቸው..ግን አንቺ ወዴት ነው የምትሄጂው…››‹‹ወደ ቦታዬ ነዋ …ቅድም እኮ ሸኝተኸኝ ነበር››አለች እንደ መፍገግ ብላ‹‹በዚህ ሰዓትማ ወዴትም አትሄጂም ..ቅድም እኮ ሂጂ ያልኩሽ የምከፍልሽ ስለሌለኝ ነው››‹‹አሁንስ ?››‹‹አሁንማ ይሄው አመጣሺልኝ››እንደማቅማማት አለችና…‹‹ግን ክፍያ አልፈልግም..ማለት ዝም ብዬ ነው ምተኛው..››‹‹እሱማ አይሆንም››‹‹እንግዲያው ልሂድ›› ብላ በሩን ለመክፈት አምርራ ስትሳብ‹‹እሺ እንዳልሽ››ብዬ እንዳትበርብኝ የፈራው ይመስል እጇን አፈፍ አደረግኩት…‹‹ከተስማማን እሺ ››ብላ ተመለሰችና ከላይ የለበሰችውን ፓካውት ነገር በማውለቅ ወንበሩላይ ጣል በመድረግ ከነሱሬዋ ብርድልብሱን እና አንሶላውን ገልጣ ከውስጥ ገባች… እኔምከላይ በቦዲ ከስር በፓንት ሆኜ ተከትዬት አልጋ ውስጥ ገባው‹‹የዚህ አገር ሰው አይደለህም አይደል?››ስትለኝ እፍረት ተሰማኝ‹‹አዎ አይደለውም … ከክፍለሀገር ለስራ መጥቼ ነው..የዚህ አገር ልጅ ብሆንማ መችእንደዚ በቀላሉ እዘረፍ ነበር?››አልኳት‹‹በቀላሉ አልክ..በጣም እሳት የላሱ ሌቦች እኮ ናቸው ያጋጠሙህ… የቦሌ ልጅም ሆንክየባሌ ልጅ አይምሩህም….ለእነሱ ከሰው ኪስ ገንዘብ መዞ ማውጣት አየር ወደውስጥየመሳብ ያህል ቀላል ነው.››ብላ አፅናናችኝ‹‹በጣም ነው ያፈርኩት››‹‹መዘረፍ ደግሞ ያበሳጫል እንጂ እንዴት ነው ሚያሳፍረው?››አለችኝ ፊቷን ወደ እኔ አዙራእነዛ እረፍት የሌላቸውን አይኖቾን እያቁለጨለጨች‹‹አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ..››‹‹ምንድነው…?››‹‹ፖሊስ ነኝ…በፖሊስ ደግሞ መዘረፍ አያምርበትም››‹‹እና መዝረፍ ነው ሚያምረበት››ብላ የቅድሙን አይነት ጣፋጭ ሳቋን ለቀቀችው፡፡‹‹አይ ማለቴ..››‹‹ገብቶኛል..መበለጥህ ነው አይደል እንዲህ ያንገበገበህ…?አይዞህ ቻለው ..አንዳንዴያጋጥማል፡፡››ፊቷን ወደ እኔ ዞራ እኔም ወደ እሷ ዞሬ ፊት ለፊት በቀጥታ እየታያየን በመሀከላችን የግማሽሜትር ያህል ክፍት ቦታ ትተን ነው የምናወራው…ደግሞ እንዲህ ተጋድማ ሲያዩት እንዴትአባቶ ታጓጓለች፡፡‹‹…ግን ጓደኞቼ ናቸው ነው ያልሺኝ?፡፡››‹‹ከጓደኞኛም በላይ ናቸው..››‹‹አልገባኝም››‹‹ከጓደኛ በላይ ምንድነው…?››‹‹ባሎችሽ..ወንድሞችሽ..ሌላም ሌላም ሊሆን ይችላሉ፡፡››‹‹ባሎችሽ አልክ ..ባሎቼ እንኳን አይደሉም..ወንድሞቼ ብትላቸው ይቀላል፡፡‹‹አይ ጥሩ ነው››አልኳት በለሰለሰ ድምጽት፡፡‹‹ምነው ሌቦችን ከወንድሞቼ በላይ ናቸው ስላልኩ ቅር የተሰኘህ ትመስላለህ…እኔምሸርሙጣ መሆኔን አትሰርሳ››‹‹ሁኚያ ..ሌባና ሸርሙጣን ምን አገናኘው?››ይገናኛል..እርግጥ ሸርሙጣ ሁሉ ወዳ አትሸረሙጥም…ሌቦች ሁሉም ወደው አይሰርቁም…ግን ቢሆንም ይመሳሰላሉ…..ሽርሙጥና በራሱ ሌብነት ሚሆንበት ጊዜ አለ…ሚስት ያለውወንድ ሲመጣና አብሮኝ ሲያድር ከሚስቱ ሰርቄው ነው…በፍቃደኝነት ቢሰረቅልኝም ያውነው..ከእሱ የምቀበለውም ገንዘብ የሚስቱም ጭምር ነው…ስለዚህ የተሰረቀ ወይምእንደተጭበረበረ ብር ተቀበልኩ ማለት ነው…፡፡ከፍቅረኛው ሸውዶም የሚመጣውምእንደዛው ማለት ነው..ብቻ ያው ነው….በዛ ላይ እኔ በቅርብ ተውኩ እንጂ አብሬያቸው እሰራነበር..››በድንጋጤ ከተኛውበት ቀና አልኩና አፈጠጥኩባት‹‹እሰራ ነበር ስትይ?››‹‹ተረጋጋ..እሰርቅ ነበር…አብረን ነበር ወደስራ ምንሰማራው››‹‹አንቺም እንደነሱ ኪስ አውላቂ ነበርሽ?››‹‹እንደነሱ ብቻ ሳልሆን ከእነሱም የተሸልኩ..እንደውም አንደኛውን ያሰለጠንኩት እኔነኝ…

ለዛም ነው ብዙ ታሪክ አብረን ስላሳለፍን እና ስለሚያከብሩኝ ሳያንገራግሩና ሳይቆጫቸው

ብርህን የመለሱልኝ››

‹‹ይገርማል…ወይ ያንቺን ብር ሳልሰጥሽ ብዬ ከተኛውበት ተነሳውና ፖርሳዬን

ወዳስቀመጥኩበት ወንበር ተንጠራርቼ እጄን ስዘረጋ

‹‹የምን ብር ተስማምተን መሰለኝ የተኛውት..››

‹‹ቢሆንም ..ስራ ስራ ነው››

‹‹አርፈህ ተኛ ትቼዋለው ብዬሀለው ትቼዋለው››አለቺኝ ወደ ቦታዬ እንድመለስ እየገፈተረቺኝ

‹‹ምኑ ነው የተውሺው..››

‹‹ዝም ብዬ መተኛት ስለፈለግኩ ነው ..ምንም ማድረግ አልፈልግም››

‹‹ችግር የለውም እንደፈለግሽ.. ብሩን ግን ልስጥሽ››

‹‹አይ ብሩንም ብድንም አልፈልግም…ባይሆን ጥዋት ቁርስ ትጋብዘኛለህ››አለቺኝ ምርጫ

ስለሌለኝ ተስማማው…ግን የሆነ ቅሬታ ከውስጤ ሲመነጭ ታወቀኝ

‹‹..ለምንድ ነው ከእኔ ጋ ምንም ላለማድረግ የወሰነችው…?ምኔ ደበራት ይሆን?››

በአዕምሮዬን ማገላብጠውን አሳብ ያነበበች ይመስል‹‹ስለወደድኩህ ነው ምንም ማድረግ

ያልፈለኩት?››አለቺኝ

‹‹አልገባኝም…ማለቴ እንደውም ከወደድሺኝ በተቃራኒው ነበር የምትፈልጊው››

‹‹አየህ እኔ ወሲብን በጣም ነው የምጠላው ….የምጠላውን ወሲብ የምፈጽመው ደግሞ

ምንም ከማይመስለኝ ወይንም ከምጠየፈው ወንድ ጋር ነው፡፡አንዴ አብሬ የተኛውትን ሰው

መቼም መልሼ ላገኘው አልፈልግም..ማግኘት ተወው በአእምዬ እንኳን መልኩ ከመጣብኝና

ካስታወስኩት ቀኑን ሙሉ እረሴን ስረግም ነው የምውለው…ምን መሰለህ ወሲብ ለእኔ

ገንዘብ ማመርትበት ማሽኔ ብቻ ሳይሆን ወንዶችን የምበቀበልበት የጦር መሳሪያዬ

ነው..ለከፈለኝ ወንድ ስሜቴን ከርችሜበት ጭኔን ግን በርግጄለት እላዬ ላይ ሲንደፋደፍ እና

ስሜቴን ቀስቅሶ ብልቴን ለማርጠብ አሳሩን ሲያይ..ምንም ማድረግ አቅቶት በማለክለክ

ሲቃትት እየታዘብኩ ዘና ማለት እንዴት መሰለህ የሚያስደስተኝ…››

‹‹እንዴ ስሜትሽን ሚቀሰቅስ ወንድ አጋጥሞሽ አያውቅም ማለት ነው?››

‹‹እሱማ በዓመት አንድ ቀንስ ቢሆን ማጋጠሙ የት ይቀራል?››

‹‹እና የዛን ጊዜ ትበሳጫለሽ ወይስ ትደሰቻለሽ..?››

‹‹ወይ መደሰት…ልክ ስሜቴ መነቃቃት መጀመሩን ከታዛብኩ ወዲያው ተስፈንጥሪ

ከሰውዬው ጉያ ወጣና ብሩን ወርውሬለት ወደ ቤቴ ….››

‹‹ወደ በቴ…!!!ስሜቱን ስታሸማቅቂው ዝም ብሎ ይልክሻል..?››

‹‹እና ምን ያደርገኛል?››

‹‹ሊመታሽ ይችላል…አስገድዶ…››

‹‹ሊሞክር ይችላል…በእኔ ላይ ግን እስከአሁን ያንን ማድረግ የተሳካለት ወንድ የለም››

‹‹ማለት?››

‹‹በቃ የለም..ዝርዝር ኪስ ይቀዳል ሲባል አልሰማህም››

‹‹ወይ የዛሬው ቀን ደግሞ ምኑን ነው የሚያሰማኝ .. ?ምኑን ነው የሚያስመለክተኝ….?አንዳ

ንዴ አንድ አመት ሙሉ ምንም አዲስ ነገር ሳንሰራበት..የተለየ ነገር

ሳንመለከትበት..ሚያስደምም ነገር ሳንሰማበት እንደቀልድ ተንዘላዝሎ ያልቃል..በተቃራኒው

ደግሞ በአንድ ሰዓት ውስጥ አንድ መጻፍ ሙሉ የሚወጣው በድርጊት የተሞላ በመደመም

አፍን የሚያስከፍት ታሪክ ይሰራል…..ወሲብን በመንገሽገሽ የምትጠላ የ19 ዓመት ውብና

አማላይ ወጣት…..

‹‹ያልሺው ነገር ግልጽ ባይሆንልኝም ፍላጎትሽን ግን አከብራለው››

‹‹አመሰግናለው..ብላ ወደእኔ በመሳብ ከንፈሬን የመዳበስ ያህል ሳመቺኝና በፍጥነት

ወደነበረችበት ተመለሰች እና‹‹በድንጋጤ ስካሩ ጥሎህ ጠፋ አይደል››ብላ ጠየቀችኝ

እውነትም የጠጣው መሆኑን እንኳን እስከመዘንጋት ደርሼያለው

‹‹ቅድም ሰክሬ ነበር እንዴ?››

‹‹ሰክሬ..?እየተወለጋገድክ አይደል ይዘኸኝ የመጣኸው..››ብዙ ብዙ ነገር ከወራን ቡኃላ

ሲደክመን እሷ እንዳለችውና እንደፍላጎቷ ተቃቅፈን ተኛን..በገባውላት ቃል መሰረት ጥዋት

ቆንጆ ቁርስ ጋበዝኳትና ስልክ ቁጥሯን ተቀብዬ ቅር እያለኝ ተለየዋት..

ቀኑን ሙሉ የተሳተፍኩትን ስብሰባ በግማሽ ልብ ነበር ስከታተል የነበረው..ግማሽ ቀልቤ እሷ

ጋ ነበር..ስብሰባው ተጠናቆ ወጥቼ እስክደውልላት..ደውዬም ድምጻን እክሰማ..እናም

ደግሞ እስካገኛትና እነዛን ተቁለጭላጭ አይኖቾን ዳግም እስካያቸው ቸኩያለው…ወይኔ

ጀግናው ምን ነካኝ?››.....ስብሰባውን አጠቃልዬ የውሎ አበሌን ተቀብዬ ከግቢው ሳልወጣ ነው የደወልኩላት…ስልኳ

ጥሪ አይቀበልም ይላል….አቤት አደነጋገጤ.. ምንድነው እንደዚህ ፍርስርሴ ያወጣው…?ነው

አቅፌት ስጎመዣት ስላደሩኩና እንዳልዋሀደት ስለተከለከልኩ ይሆን …?መከልከሌ

የፈጠረብኝ ወሲብ ረሀብ ይሆናል..መልሼ ሞከርኩ…አሁንም ደገምኩ…ይጠብቀኝ የነበረው

ሹፌሬ ጋር ሄድኩና ገቢናውን ከፍቼ ገባው

‹‹ወዴት ላድርስህ ሀለቃ…?››

‹‹አይ አንተን ላድርስህና መኪናዋን ፈልጋለው..አንድ ቦታ ምደርስበት ጉዳይ አለኝ…››

‹‹እንደዛ ከሆነማ እኔ እዚሁ ልወረድና በተክሲ ልሂድ… እዚሁ ቅርብ ሳሪስ ነው

የማድረው››አለኝ… በወቅቱ ያለነው ላንቻ አካባቢ የሚገኘው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጽ/

ቤት ውስጥ ነበር…

ይሉኝታም አላገደኝ‹‹እንደዛ ከሆነ ደስ ይለኛል››አልኩት

እሺ ብሎ ቁልፉን እዛው እተንጠለጠለበት ትቶት ገቢናውን ለቆ በመውረድ‹‹..ነገ እንሄዳለን

ወይስ እንውላለን››

‹‹ነገ ቅዳሜ አይደለ .. …?ካልቸኮልክ ብንውል ደስ ይለኛል››

‹‹አረ እኔም ደስ ይለኛል››

‹‹በል እሺ እንደዋወል››አልኩትና ወደ ሹፌር መቀመጫ ቦታዬን ቀይሬ ቁልፉን አሽከርክሬ

ሞተሩን አስነሳውና ግቢውን ለቅቄ በእስቴዲዬም አቅጣጫ ተፈተለኩ..የምሄደው ወደ ፒያሳ

ነው..ሰዓቴን ተመለከትኩት 11፤15 ይላል በዚህ ሰዓት ፒያሳ ሄጄ ምን እንደማገኝ ለራሴም

አልገባኝም…የቤቷን አድራሻ አላውቅ…እሷ በዚህ ሰዓት ለስራ አትወጣ..እና ፒያሳ ደርሼ ምን

ላደርግ ነው..ቸርቸር አካባቢ እንደደረስኩ ስልኬ ጮኸ..በቆሪጥ አየውት..አዎ እራሷ ነች እሷ

ነች…በፍጥነት መኪናዬን የአስፓልቱን ጥግ ይዤ አቆምኩና አነሳውት

‹‹ሄሎ ሄሎ ..ሰላም ነሽ..…?እንዴት ነሽ.…?አለሽ…?›› ተንሰፈሰፍኩ

‹‹አለው…ደህና ነህ..ሞክረህልኝ ነበር..…?ሰልኬ እኮ ቻርጅ ጨርሶ ነው››

‹‹አይ ብዙም አልሞከርኩልሽም …አንድ 20 ጊዜ ብቻ ነው…?››

ሳቋን ለቀቀችው….ከወደ ገነት የተላከ መንፈስ አረጋጊ ጥኡመ ዜም መሰለኝ…

‹‹ትገርማለህ..እና የት ነህ…?››

‹‹ወደ ፒያሳ እየመጣው ነው››

‹‹ምን ልትሰራ…?››

‹‹እንዴት… .…?ምን ልትሰሰራ ትያለሽ እንዴ…? ስልክሽ አልሰራ ሲለኝ ግራ ገብቶኝ ነዋ››

‹‹እና ደረስክ አሁን››

‹‹ቸርቸር አካባቢ ነኝ››

‹‹እኔ እኮ ፒያሳ አይደለውም …ሳር ቤት አካባቢ ነኝ››

‹‹እና ልምጣና ልውሰድሻ››

‹‹ታውቀዋለህ››

‹‹አዎ ..››

‹‹እሺ ከእስቴዲዬም ታክሲ ያዝና…››ማብራራቷን ቀጠለች

‹‹መኪና ይዤለው››አቋረጥኳት

‹‹መኪና አሪፍ ነዋ…ብስራተ ገብርኤል በቤተክርስቲያን አካባቢ ስትደርስ ደውልልኝ››

‹‹ስልኬን ዘጋውና በእፎይታ እና በደስታ መኪናዬን አዙሬ በብሄራዊ አድርጌ በዋቤ ሸበሌ

ፊት ለፊት ወደ ሳር ቤት ነካውት

ያለችኝ ቦታ ደርሼ መኪናን ጥግ አስይዤ ካቆምኩ ብኃላ …ደወልኩላት፡፡…ከአስር ደቂቃ

በላይ አላስቆየችኝም…

ጉልበቷ አካባቢ የሚቀር ሮዝ አይነት ልዩ አይነት ቀሚስ ለብሳ… አንገቷ ላይ ሻርፕ ጣል

አድርጋ …ባለረጅም ተረከዝ ጫማ ሰክታ..ከንፈሯን ሊፒስቲክ፤ አይኖቾን ኩል ተኩላ… ፀጉሯን

ግማሽ ተፈጥሮ ግማሽ ዊግ ደባልቃበትና ተሰርታው ጀርባዋ ላይ ዘፍ እንዲል አድርጋ ቀጭ

ቋ እያለች ወደአለውበት መጣች..አረ ይሄ ምኞቴ ነው..እሷን እየጠበቅኩ ባለውበት ቅፅበት

ያለምኩት…እንጂ እሷማ መች ስራ አጣችና…፡፡

ነጭ እስኒከር ጫማ..ጉልበቱ የተባተራረፈ(ፍሽን መሆኑ መሰለኝ) ጅንስ ሱሪ…ጥቁር ሌዘር

ጅኬት እስከአንገቷ ቆልፋ ለብሳ እጆቾን ኪሷ ውስጥ ከታ እየነጠረች ፊቴ ገጭ ነው

ያለችው..ሊፒስቲክ የለ ቻፒስቲክ..ያ የተጠቀለለ ፀጉሯ እንኳን ወግ አልያዘም..ግን

እንዲያም ሆኖ የሆነ ልብን ቀጥ የሚያደርግ ውበት አላት..ማንም ሌላ ሴት ላይ አይቼው

የማላውቀው ውበት..››ጉንጭ ለጉንጭ ከተሳሳምን ብኃላ በከፈትኩላት ገቢና ገባችና ከጎኔ

ተቀመጠች..

‹‹እሺ ወደ የት እንሂድ…?››ጠየቅኳት

‹‹ወደፈለከው››

‹‹ወደ ፈለከው ስትይ..ወደሀገሬም ቢሆን››

‹‹ምንችግር አለው …ያንተ ሀገር እኮ የእኔም ሀገር ነው..ሱዳን ወይ ኬኒያ ይዘኸኝ አትሄድ››

‹‹የእወነት ግን ለምን ከከተማ አንወጣም››

‹‹የት…››

‹‹ደብረዘይት ወይም ናዝሬት…ጥዋት መልስሻለው››

‹‹ንዳው››ያልጠበቅኩትን ፈጣን ፍቃድ ነው ያገኘውት

‹‹ወዴት ልንዳው…?››

‹‹ወደ አዳማ››

‹‹ይመችሽ አልኩና በለቡ በኩል አድርጌ በአዲሱ መንገድ መኪናዬን ልክ እንደልቤ ሁሉ

በአይር ላይ እያንሰፈፍኩ ወደ አዳማ

‹‹መኪና ይዤለው ስትለኝ እኮ የራስህ መኪና መስሎኝ ገርሞኝ ነበር…››

‹‹እንዴ !!!ለምን ይገርምሻል……?

‹‹እኔ እንጃ እንዲሁ››አለች እየተቅለሰለሰች..ምን ለማለት እንደፈለገች እንዲሁ

ተረድቼታለው

‹‹ያው የመንግስት ቢሆንም ቦታው ላይ እስካለው ድረስ የራሴው በየው››

‹‹አይ እንዳዛ እኮ አይደለም ቦታው ላይ እስካለህ ድረስ ሳይሆን ..ያለህበት ቦታ የሚያዘውን

ስራ በምትሰራበት ጊዜ ብቻ ነበር ያንተ መሆን ያለበት..››

‹‹አልገባኝም››

‹‹እንዴት አይገባህም..አሁን እኮ አንድ ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላትን ሴት

ጭነህበት ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት ወደሌለው ቦታ እየሄድክ ነው…መንግስት ህዝብን

እንድታገለግልበት የሰጠህን መኪና ለግልህ ደስታ እየተጠቀምክበት ነው…እርግጠኛ ነኝ

ከዚህ አዳማ የምንሄድበትን ነዳጅ ከኪስህ ነው የሞላሀው››

‹‹ትቀልጂያለሽ…ለመኪናው መንግሰት የሚመድብለት የራሱ ባጀት አለው እኮ..ለምንድነው

ከኪሰ የምቀዳው..የታዳሉት ሁለት ሶስት መኪኖችን በዚህም በዛያም ብለው የራሳቸው

ያደርጋሉ….አንቺ ወቅቶላ ከአዲስአባ አዳማ ለሚሄድበት ነዳጅ ቁምነገር ሆኖ እንዲሞላ

ትጠብቂያለሽ››

‹‹አይ የታደሉት አልክ..እዚህ አገር ዘራፊ የበዛው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ መዝረፍ

እንደእድል..እንደችሎታና ክብር ስለሚታይ ነው…እከሌ በሙስና እኮ ነው የተታሰረው ሲባል

ሰዉ አዕምሮ ውስጥ ሚፈጠረው ምስል…አንድ ሀብታም የተድቦለቦለ ፊት እና ያበጠ

ሰውነት ያለው…ብልጥ እና አምላክ የመረቀው…ብዙ የሚፈሩት እና ሚከያከብሩት ሰዎች

ያሉት..የታደለ ሰው አድርገን ነው…እንደእሱ ከመዋረድ አድነን ሳይሆን የእሱን እድል ለእኛም

አመቻችልን የዕድሜ ልክ መኖሪያችንን ቦጨቅ ቦጨቅ እናድርግና ብንታሰርም ሶስት አራት

አመት ነው…ለዛውም በድሎትና በምቾት.. ብለን ነው የምንጸልየው ››

‹‹አንቺ ፀረሙስና ውስጥ ነው እንዴ የምትሰሪው…?››

‹‹አይ አንተ.. ፀረ ሙስና እራሱ ሌላ ፀረ ሙስና ያስፈልገዋል››

‹‹ስንት አመቴ ነበር ያልሺኝ…?››

‹‹ቁጥሩን ከሆነ የፈለክ 19 ነኝ››

‹‹አይ ንግግርሽን ሳዳምጥ የ29 መሰልሺኝ

‹‹ቀለድክ ማለት ነው..…?››

‹‹አልቀለድኩም …ግን ጫወታ እንቀይርና በጣም ናፍቀሺን ነበር››

‹‹እንዲ በቃለሉ…ናፍቆት ማለት ትርጉሙ ጠፍቶሀል ማለት ነው..ዳሩ የዘመኑ ወንድ ልቡና

አንደበቱ አይተዋወቁም››

‹‹ማለት...…?››

ልባችሁ አስቦ እንኳን የማያወቀውን አንደበታችሁ ያንበለብለዋል.. አፈቀርኩሽ..ተከሰከስኩል

ሽ…ተፈጠፈጥኩልሽ በቃ ስትቀባጥሩ ትንሽ እንኳን አያደናቅፋችሁም››

‹‹አረ ተይ ጨፈጨፍሽን..ደግሞ ልባችሁ አስቦ ስትይ የሚታሰበው በልብ ነው እንዴ……?››

‹‹እኔ እንጃ ..ፍቅር ግን በጭንቅላት የሚታሰብ አይመስለኝም..ስሜት ነክ የሆኑ ነገሮች

በልብ የሚቀመሩ ይመስለኛል..የሆነ ሰው ስታፈቅር ወዲያው ልብህ ምቱ ጨምሮ ድው

ድው ሲል ታዳምጠዋለህ …ጥሎህም ሲሄድ ህመሙ ቀድሞ ሚሰማህ ልብህ ላይ

ነው..ልብህ ቀድማ ትደክማለች››

‹‹በፍቅር እና ጥላቻ ጥሩ ልምድ ያለሽ ይመስለኛል››

‹‹አይ በፍቅር ያለኝ ልምድ በጣም ኢምንት ነው..በጥላቻ ግን ዳቢሎስ እንኳን ሚበልጠኝ

አይመስለኝም…››

‹‹መቼስ ካንጀትሽ አይደለም ..አንቺን የመሰለች የዋህ የፒሳ ወፍ..ከዳቢሎስ ጋር እንዴት

እራሷን ታነጻፅራለች…?››

‹‹እወነቴን ነው..እግረ መንገዴንም እያስጠነቀቅኩህ ነው…ማለቴ እንዳትመሰጥብኝና አጉል

እንዳትሆን ..››

‹‹ይህቺ ወደ ውስጥሽ እንዳልገባ በዙሪያሽ የገነባሻት አጥር መሆኗ ነው..…?ለማንኛውም

ፖሊስ ነኝ..ፖሊስ በመሆኔ ደግሞ ፈተና ወዳለው…ታግዬ ማሸነፍ ተፋልሜ መርታት በቃ

የሚመስጠኝ ተግባር ነው….››

‹‹እንግዲያው በህይወትህ የመጀመሪያው ወደሆነው ወደአስደናቂው እና አስቸጋሪ የፈተና

ሜዳ እንኳን በሰላም ገባህ››

ፈገግ አልኩ..ምክንያቱም በዚህ ጮርቃ ዕድሜዋ በሴተኛ አዳሪነቷ እና ነበርኩ ባለችው

የሌብነት ህይወት ውስጥ ያጋጠሞትን ጥቃቅን የህይወት ውጣ ውረዶች ባልበሰለው

አዕምሮዋ አግዝፋና የአለምን ትልቁን ፈተናና መከራ ያሳለፈች አድርጋ አስባለች…አይ መከራ

እቴ!! ከስንትና ስንት ወንጀለኟች ጋር ስባረር እና ስፋለም..ስንት ሙሰኞችን በተቀነባበረ እና

በተወሳሰበ የምርመራ እና የክትትል ዘዴዬ ስጥል ያን ሁሉ ታሪኬን ብተሰማ እንዲህ

እንደማንም የፒሳ አውደልዳይ ወጣት ቆጥራኝ አትንቀኝም ነበር››ስል አሰብኩ

መኪናዋን እያከነፍኩት ነው አዳማ እየተቃረብን ነው..ከክፍያው ጣቢያ አልፈን የከተማዋን

ድንበር ተጠግተናል..የአባ ገዳ አካባቢ አልፈን ጥቂት ወደ ከተማዋ እንደገባን ድንገት

‹‹አቁም አቁም አለችኝ….››

ደንግጬ ፍሬኔን ሲጢጢጥ አድርጌ አቆምኩ‹‹ምነው ምን ሆንሽ.…?››

አታያቸውም እነዛን ኮርመዎች..በቆምንበት የመንገድ ጠርዝ ወደውስጥ በሚያስገባ መንገድ

ቅያስ ሁለት በሀያዎቹ ዕድሜ መጀመሪያ የሚገኙ ወጣት ወንዶች አንድ ታዳጊ ልጃገረድ

በመሀከላቸው አድርጋው ከወዲህ ወዲያ ያንገላቷታል

‹‹መጣው ብላ ገቢናውን ከፍታ መውረድ ጀመረች››

‹‹አረ እኔ እሻላለው ..አንቺንም ይተናኮሉሻል››አልኮት ሽጉጤን ካስቀመጥኩበት አውጠቼ

በጀርባዬ እየሻጥኩ….እኔ ከመውረዴ በፊት እሷ ስራቸው ደርሳ ነበር..አንደኛው ባለ በሌለ

ኃይሏ ልጅቷ ላይ ጥፊ ሲሰነዝር የልጅቷ ፊት ላይ ከማረፉ በፊት ተምዘግዝጋ እጁን በአየር

ላይ ቀለበችው..ፈጠን ብዬ ተጠጋዋቸው አንድ ሶስት ሜትር ሲቀረኝ ቆሜ መታዘብ ጀመርኩ

ሆለ ደጀን መሆኔ ነው…

‹‹አንቺ ደግሞ ምን ሚሉሽ ነሽ.…?››

አሁን ሳትወረዱ በሰለም ልጅቷት ትታችሁ ጥፉ‹‹መሀል ያለችው ታጋች ልጅ በፍራቻና

በድንጋጤ እየተንዘፈዘፈች እንባዋን ታነባለች››

እጄን ወደ ወገቤ ልኬ ሽጉጡን ላውጣ እና ላስፈራራቸው ወይስ ትንሽ ልታገስ እያልኩ ነው

‹‹ነፍሱ ሰውዬሽን ተማምነሽ ከሆነ ይቅርሽ ..በማያገባሽ ጥልቅ እትበይ አላት›› ሌላው

አይ ለእንደእናንተ አይነት ያልተቆነጠጡ ህጻናትማ እኔው በቃለው››

ምን አንቺ ለእኛ..ደፋር ነሽ››በድፍረቷ ተንከተከቱ..እውነቱን ለመናገር እኔም በንግግሯ

ተገርሜያለው..ያው እነሱ እንዳሉተ በእኔው ተማምና ነው ስል ገመትኩና እራሴን ማዘጋጀት

ጀመርኩ…

ግን ወዲያው የሚስፈነጠር… የሚወናጨፍ ..የሚንሳፈፈ አካል ታየኝ..በሰከነዶች ሽርፍራፊ

ሁለቱም ጓረምሶች መሬት ተዘርረዋል..የእኔዋ ጂጄ እንደብሩስሊ እየተወነች ነው…ታጋቾ

ልጅቷ የበለጠ ደንግጣ መርበትበቷን ቀጥላበታለች..እኔም ከእሷ በላይ ደንግጫለው…

እንዴት እንዴት እርጋ ነው የዘረረቻቸው.…?

ይህቺ ልጅ ወሬ ብቻ ሳተሆን እውነትም እንዳለችው መፈራት ያለባት አደገኛ ወፍ ሳትሆን

አትቀርም…ልቤ ፈራ

በአካባቢ ራቅ ራቅ ብለው ትዕይንቱን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች በአድናቆት ያጨበጭቡላት

ጀመር ..ወዲያው ሁለት የአካባቢው ፖሊሶች ከየት መጡ ሳይባል ፊት ለፊቷ ገጭ አሉ

..እኔም ተንደርድሬ እናሱ ፊት ገጭ….እዳ ከሜዳ ይሏችሆል እንዲህ ነው…ከዛ ግርግር መሀል እንዴት እንደወጣን ዝርዝሩን አልነግራችሁም… ግን ደግሞ እንደምንም

ወጣን..ወደመሀል ከተማ ደርሰን ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል ጎራ በማለት አልጋ ለመያዝ ሪሴብሺኗ

ፊት ለፊት ስንቆም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡

‹‹እህት አልጋ ይኖራል…?››

‹‹አዎ አለ ››

‹‹ባለ አራት እና ባለ ሰድስት መቶ ብር አለ …የትኛው ይሁንላችሁ…?››

‹‹ደብል ቤድ ሩም የላችሁም…?››ጠየቀች

‹‹አለ… ሰባት መቶ ብር ነው እንጂ››

‹‹ይሁን እሱን አድርጊልን ››አለችና እኔ ገና ነገሩን አስልቼ..ባለሁለት አልጋ ለምን ፈለገች…?

ቢያንስ ተቃቅፈን እንኳን የመተኛት እድል አይኖረንም ማለት ነው…?ብዬ አስቤ ሳልጨርስ

ከጅንስ ሱሪ ኪስ ውስጥ ብሯን ላጥ አድርጋ አወጣችና ቆጠር ቆጠር አድርጋ ሰጠቸት

‹‹መታወቂያ››

‹‹ነፍሱ መታወቂያ አንኳን ያንተ ቢሆን ይሻላል››

‹‹እ ምን አልሺኝ…?››ግራ ገብቶኝ

‹‹መታወቂያ እያለች ነው››

‹‹እ..› አልኩና ወደኪሴ ገብቼ ዋሌቴን አወጣውና ብሩንም መታወቂያውንም አቀበልኳት

‹‹ሁለት ነው እንዴ የምትፈልጉት…?››

‹‹አይ የእሷን ብር መልሲላት››

‹‹እ.አንደዛ ነው…?›› አለችና ብሩን ነጥላ ተረጵዛው ላይ በማድረግ መታወቂያውን ወሰደችና

መዝገብ ላይ የሚጻፈውን ከጻፈች ብሃላ እንድፈርምላት አስጠጋችልኝ…ፈረምኩና

መለስኩላት…

ቁልፉን እየሰጠቺኝ…‹‹24 ቁጥር ነው..በዚህ ሂዱና በዚህ ታጠፉና ብላ ጠቆመችን

‹‹ብሩን አንሺውና እንሂዳ››

‹‹እሺ ካልክ …በማለት ብዙም ሳትግደረደር ብሩን ከጠረጵዛው ላይ አንስታ መልሳ ኪሷ

ውስጥ በመክተት ተያይዘን ሄድን…. ወደ ቤርጎ….

ቤርጎው ጠባብም ሰፊም የማይባል ልከኛ መጠን ያለው ነው …ሁለቱ አልጋዎች በትይዩ

ወዲህ ማዶ እና ወዲያ ማዶ በተቃራኒ ግድግዳ ተጠግተው ተዘርግተዋል..ሁለቱም

ተመሳሳይ ነጭ እና ጽዱ የአልጋ ልብስ ተነጥፎባቸው ይታያሉ …በመሀከል አልጋዎችን

ተጠግተው አንድ አንድ ደረቅ ወንበር ይታያል ….መሀከል ላይ አንድ መለስተኛ ጠረጳዛ

አለ……………..

አንድ አንድ አልጋ ሳንነጋገር ተከፋፍልና በተመሳሳይ ጊዜ ዘፍ ብለን ተቀመጥን … እሷ

ጫማዋንም ሳታወልቅ እግሮቾን በአየር ላይ አንጠልጥላ ግን ዳግሞ ሌላውን መላ ሰውነቷን

ነበር ዘረጋግታ የተኛችው

‹‹አንድ አ10 ደቂቃ አረፍ እንበል››አለችኝ

እኔም መረጋጋት ስለፈለግኩ አልተቃወምኳትም‹‹ይቸላል›› አልኳትና እኔም እንደእሷ እልጋው

ላይ ወገቤን አሳራፍኩ…ይገርማል ጭልጥ ያለ እንቅልፍ መቼ እንደወሰደኝ አለውቅም//

‹‹ጋሽ ፖሊሱ..ጋሽ ፖሊሱ›› እያለች በተደጋጋሚ ጥሪ ስትቀሰቅሰኝ ነው ደንግጬ ተስፈንጥሬ

የተነሳውት

‹‹አረ ተረጋጋ ሀገር ሰላም ነው››

‹‹አንቺ… ምን አይነት እንቅልፍ ነው የወሰደኝ..…?ስንት ሰዓት ሆነ…?‹ሞባይን ከፍቼ ሰአቴን

ስመለከት 3 ሰዓት ሊሆን ደቂቃዎች ነው የቀሩት፡፡

‹‹አረ ተነሽ እራት ፍለጋ እንውጣ›› አልኳትና ተያዘን ወጣን..ብዙም ሳንርቅ ከአስፓልቱ ጠርዝ

ከሚገኝ አንድ ሆቴል ገባንና ሁለተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ሆነን ቁልቁል አስፓልቱን

እያተመለከትን እራታችንን በጥሩ ሁኔታ እየተጎራረስን ከበላን ቡኃላ ወይናችንን አዘን በወሬ

እያዋዛን ዘና ማለታችንን ቀጠልን …

… ከተማዋ በማታ ምን ትመስላለች…?ብዬ ስቃኛት …እንደ ፒሳውን አይነት አይሁን እንጂ

ወዲህ ማዶ እና ወዲያ ማዶ ሆነው መብራት ፖል ተደግፈው ደንበኛ የሚጠብቁ እንስቶች

ይታዩኛል.. ወደየሆቴሉ የሚገቡትንና ከየሆቴሎቹ ወጥተው ባጃጅ ኮንትርታ በመያዝ

ወደየቤታቸው የሚሄዱ እዚህም እዛም ይታያሉ..ለሌላ ተግባር ወዲህ ወዲያ ውር ውር

የሚሉ ኑዎሪዎችም አይብዙ አሉ…እና ከተማዋ በማታም ቅውጥ አትበል እንጂ ድምቅ ያለች

ነች…ወሬያችንን እየጠረቅን..መጠጣችንን እየጨለጥን…ብዙ ብዙ ትዕይንት እየታዘብን ሳለ

ሁለት መንታ የሚመስሉ ዕድሜያቸው 15 ወይም 16 ማያልፋቸው እኛ ካለንበት አስባልት

ትይዩ ወዲያኛው ማዶ ዳር ቆመው ተመለከትን….

ሳለስበው ቀልቤንም እይታዬንም ተቆጣጠሩት ..አጅሪት ስትከታተለኝ ነበር መሰለኝ

‹‹ነፍሱ ምነው መሰጡሽ እንዴ?››

‹‹ምኖቹ…?››

‹‹ምኖቹ ትላለህ እንዴ?ሴቶቹ ናቸው ..ማዶ ፖሉን የተደገፉት .. አይንህ እኮ እንደተሰካባቸው

ቀረ››

‹‹ማዶ ስንት የሚታይ ነገር አለ ..ህንጻው አለ….በረንዳውን ሞልተው የተኙት ጎዳና

ተዳዳሪዎች አሉ…..እዛጋ ደግሞ ተቃቅፈው በዝግታ ወክ እያደረጉ ዘና የሚሉ ፍቀረኛሞች

አሉ….ታዲያ ለይተሸ እነሱን እንዳየው በምን እርግጠኛ ልትሆኚ ቻልሽ..?ደግሞ ካንቺ ጋር

እያለው እንዴት ነው በእነሱ የምመሰጠው?››

እነሱን እያየህ እንደነበር መቶ ፐርሰንት እርግተኛ ነኝ…ደግሞ ምን ችግር አለው እኔ እኮ በቃ

ጓደኛህ ነኝ…››

‹‹ባክሽ ወሬ አታብዤ››

‹‹አይ ወሬ ማብዛት አይደለም ..ሄጄ ወርጄ ይዤቸው ልምጣ እንዴ ?››

‹‹እየቀለድሽ መሆን አለበት?››

‹‹እቀለድኩ አይደለም….ከፈለክ ሁለቱንም ይዤልህ መምጣት እችላለው››

‹‹ደግሞ ሁለቱ ምን ይሰሩልኛል…?

‹‹ምን አልባት የግሩፕ ይመችህ እንደሆን ብዬ ነዋ.…?.››

‹‹የግሩፕ ስትይ…? ››

‹‹በቃ ሁለቱንም ይዘህ ማደር ማለቴ ነዋ ..ግሩፕ አንድ ወንድ ከሁለት በላይ ሴቶችን

ለብቻው ሲያስተናግድ ወይም አንድ ሴት ከሁለት በላይ ወንዶችን ስታስተናግድ ማለት

ነው››

‹‹ይሄ በፊልም ላይ እንደምናየው ማለትሽ ነው..…?ፊልሙ ሁሉ እውነት ይመስልሻል

አይደል..ያ እኮ የፈረንጆቹ የሀጥያታቸው ፅንፋ ማሳያ ነው… ፡፡››

ፈገግ አለችና‹‹..ገና ነሽ ማለት ነው››አለቺኝ

‹‹ገና ነህ ስትይ…?››

የወይኗን ብርጭቆ አንስታ ካንደቀደቀችው ቡኃላ ባጎደለችው ምትክ ከጠርሙስ መልሳ

ቀድታ አስቀመጠችና ንግግሯን ቀጠለች…ሰዓቱ ወደአምስት እየተጠጋ ሲሆን ወይኑን

ሁለተኛ ጠርሙሳችንን በማገባደድ ወደ ሶስተኛው ለመሸጋገር እየተንደረደርን ነው፡፡

‹‹እንዲህ አይነት ነገር አታርፍም ማለት ነው..ያልኩህ ነገር በፈረንጅ ፊልም ያለ የሩቅ ሀገር

ተአምር ብቻ አይደለም…እኔ አብጠርጥሬ በማውቀው በእኛ ከተማ በፒያሳ የተለመደ እና

የእኛም ሰራ አንድ ክፍል ነው፡፡አዎ ይገርምሀል ይሄንን ድርጊት የእኔ ቢጤ ሸሌዎች ደህና

ገንዘብ የሚከፍላቸው ሲያገኙ ያለማንገራገር ያደርጉታል…ማለቴ ሁሉም ባልልህም አብዛኞቹ

ያደርጉታል ››

‹‹እንደዚህ ሚያደርግ ያበሻ ወንድ አለ?››

‹‹አዎ አለ ብቻ ሳይሆን አሉ..በደንብ አድርገው አሉ..ብዙ የናጠጡ የሚባሉ ሀብታሞችና

ልጆቻቸው፣በተለይ ወጭ ሀገር ደረስ ብለው ለረፍትም ሆነ አንደኛቸውን የተመለሱ

ዲያስፖራዎች ከዛ ቀስመው ከሚመጡት ለሀገር ግንባታ የሚበጅ አዲስ ቴክኖሎጂ እውቀት

ብቻ አይደለም እንዲህም አይነት የሲክሶሎጅ እውቀትም በማምጣት በፍጥነት

ያሰራጩታል››

‹‹ይገርማል››

‹‹አረ አይግረምህ…አሁን ከነገርኩህ ውጭም የዬኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመጠጥ ናውዘውና

በሀሽሽ ነፍዘው ደርዘን ሙሉ ወንድ እና ደርዘን ሙሉ ሴት አንድ ቤት በመታጎር በወሲብ እርስ

በርስ እየተቀያየሩ ሲጨመላለቁ ለማየት ያን ያህል ብዙ ምርምር እነ ክትትል ማድረግ

አይጠበቅብህም…ቦታውን ብቻ ለይተህ ማወቅና በትክክለኛው ቀንና ሰዓት መገኘት ነው፡፡

ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ..ክሬዚ ደይ…ቨላንታይን ደይ…ከለር ደይ..በሚባሉት ፈረንጂኛ

በአሎች ቀን ጎራ ብለህ ብትከታተል ያስደምሙሀል፡፡

‹‹ምትይውን ለማመን ይከብደኛል››

‹‹ሳያዩ የሚያምኑ ብፅአን ናቸው ይባላል..ብታምን ይሻልሀል፡፡ግን እንደ ቶማስ ካላየው

አላምንምካልክ…›› አለችና ሞባይሏን አውጥታ በማብራት ፎልደሮችን ከፈት ከፈት

አደረገችና አንድ ቪዲዬ በመምረጥ ከፈታ ሰጠቺኝ …እንዳይ ..፡፡‹‹ይሄ እኔ በአጋጣሚ

የተካፈልኩበት የተማሪዎች ፓርቲ ላይ የተቀረጸ ነው…በጣም መስጦኝ ስለነበረ ሳይሾፉኝ

ቀረጻኮቸው››

….. አየውት… አስር ደቂቃ የሚፈጅ ቪዲዬ ነው..የማየው ነገር ካወራችውም በላይ ነው…

እዚህም ደርሰናል እንዴ……?ላካ ዝም ብለን ነው በየአደባባዩ እና በየሚዲያው ባህላችን

ሀይማኖታችን እያልን በባዶ ምንደሰኩረው..…?ከስር ተቦርቡረን አልቀን የለ እንዴ……?እኚ

አፍላ ወጣቶች ማለት እኚ የኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማለት እኮ የዚህች ሀገር የነገ..አረ ምን

የነገ የዛሬ መሰረቶች ናቸው፡፡መሰረቱ የተቦረቦረ ግንባታ ደግሞ ቀኑን ጠብቆ መደርመሱ

አይቀርም.. ለዛውም በቀላሉ..

‹‹ይህቺ ሀገር በሞራልም በምግባርም እየጠፋች ነው እኮ..በቃ ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ

እየሆነ ነው››ነበር ያልኳት ፊልሙን አይቼ ከጨረስኩ ቡኃላ ሞባይሏን እየመለስኩላት

‹‹እንደዘማ አትደምድም..እነዚህ እኮ ከጠቅላላው አንድ ወይም ሁለት ፐርሰንት ቢሆን

ነው..ሌላው ወጣት ግን …..››

‹‹አንድ ፐርሰንትም ቢሆን አሳሳቢ ነው…አየሽ አንድ ባልዲ ውሃ ላይ አንድ ብልቃጥ ቀለም

ብትጨምሪበት የውሀውን ጣዕምም ሆነ ቀለም ሙሉ በሙሉ ነው ሚቀይረው…..አንድ

ቅንጣት ቫይረስ እንደቀልድ ሰውነት ውስጥ ከገባች ቡኃላ ነው ቀስ በቀስ ተራብታና ተዛምታ

አስር ሺ እና መቶ ሺ በመሆን መላ ሰውነትን በመቆጣጠር ለአልጋ ከዛም አልፎ ለሞት

የምትዳረገው…››

‹‹ይሄ አሁን አንድ ወይም ሁለት ፐርሰንት ቢሆኑ ነው ያልሺኝ ነገ በዝተውና ተስፋፍተው አርባ

እና ሃምሳ ፐርሰንት አለመሆናቸውን ምንም ማረጋገጫ የለንም…››

‹‹ምንም ማድረግ አይቻልም …››

‹‹እንደዛም ምንም ማድረግ አይቻልም ብለን እጅና እግራችንን አጣጥፈን ቁጭ ማለት

የለብንም ..መንግስትም ሆነ ህዝቡ የሆነ ነገር ማድረግ አለበት..ወላጆች ልጆቻቸው የት

እነደሚውሉ…? ምን እንደሚያደርጉ …?መከታተል አለባቸው…እንዲህ በየጎዳናው

የተዛመተውን የወሲብ ንግድም ሀይ መባል አለበት››

ከት ብላ ሳቀችብኝ

‹‹ምን ያስቅሻል…?››

‹‹አይ ይህቺ ሀገር ብዙ መካሪዎችና ፎካሪዎች አሎት እና እሱ ትዝ በሎኝ ነው››

‹‹አልገባኝም…››

‹‹ማለቴ ሁላችንም የሆነ ችግር እዚህም እዛም እንዳለ እናውቃለን..ግን ያን ችግር

ለመፍታት የሆነ ሰው ከሆነ ቦታ የሆነ አካል ከሆነ ጥግ እንዲመጣ እና መፍትሄውን

እንዲያበጅ ነው የምንጠብቀው..ቢያንስ በራሳችን የሆነ ነገር ለማድረግ አንሞክርም››

‹‹አይ የልጅ ነገር..እንዲህ አይነት ስር የሰደደ ችግር እኮ በግለሰብ ደረጅ የሚሞከር

አይደለም..እስኪ አሁን እኔ እስከአሁን ባወራነው ነገር ላይ ምን ማድረግ እችላለው…?››

‹‹ትችላለህ…?››

‹‹እኮ ምን…?››

‹‹ሚስት አለህ..ማለቴ አግብተሀል…?››ከምናወራው ጋር የማይገኛኝ ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡

‹‹አላገባውም››

‹‹እስቲ ከእነዛ ብርድ ከሚመታቸው ልጆች መካከል አንዷን ምረጥና አግባት…እና ከዛሬ

ጀምሮ ሴት ለመግዛት ወደ ቡና ቤት ጎራ ማለቱንም አቁም.››

‹‹ምን ማለትሽ ነው..ይ ምን ሊፈይድ……?ደግሞ ጋብቻ ዝም ብሎ ከመንገደኛ ጋር

የሚመሰረት ነው እንዴ…?››

‹‹… መንገደኛ ያልከው ..ከማንም ሸርሙጣ ጋር ለማለት ፈልገህ ነው…፡፡አየህ አንዴ እዚህ

ህይወት ውስጥ የገባች ሴት በስራው ወይም በሌላ አጋጣሚ ገንዘብ አግኝታ ኑሮዋን

ለማሰተካከል ብትሞክር እራሱ ፈታናዋ ቀላል አይደለም….ህብረተሰብ ለዘላለሙ ሸርሙጣ

እንደሆነች ነው የሚያስበው..አንድ ወንድ ቢያፈቅራት እንኳን ሊያገባት ድፍረት አይኖረውም

…ምክንቱም ቤተሰቦቹም ሆኑ ዘመዶቹ ሸርሙጣ አገባህ እያሉ ህይወቴን ይበጠብጡኛል

ብሎ ይፈራል..ወደፊት ምወልዳቸው ልጆችስ እናታቸው ሸርሙጣ እንደነበረች ሲሰሙ ምን

ይሰማቸዋል ብሎ ይሰጋል…ደግሞም ቢሰጋም እወነት አለው….ላግባት ብሎ ቢወስን

ከፈራቸው ነገሮች አንዱ ወይም ሁለቱ መከሰታቸው አይቀርም…አዎ ሁሉም ነገር ቀላል

አይሆንለትም….፡፡

‹‹አዎ እሱ እንኳን እወነትሽን ነው …›››

‹‹ግን እንዲሁ ያሳዝኑኛል..እያቸው እስቲ እነዚህን ሲቶች.. በጣም ልጆች እኮ ናቸው››ከታች

ወደሚታዩን መንታ መሰል ልጆች እየጠቀምኩ..

‹‹ወይ አንደኛዋ ቀናት መሰለኝ አንዶ ብቻ ነች ያለችው››

‹‹አዎ በወሬ ተመስጠህ አላየህም እንጂ ከአስር ደቂቃ በፊት ነው አንዱ በቤት መኪና

ጨልፎት የተፈተለከው››

‹‹ይህቺም ባገኘች›› አልኩ

‹‹አሳዘነችህ››

‹‹አዎ ..››

‹‹ለምን ይዘናት አንገባም?››

‹‹ወዴት?››

‹‹ከእኛ ጋር ትደር …እንክፈላት››

‹‹አልገባኝም››

‹‹በቃ ለየት ያለ ነገር ደስ አይልህም…?እንክፈላት እና ይዘናት እንግባ.. ሁለት አልጋ አይደል

ያለው አንዱ ላይ ዘና ብላ ትተኛ››

‹‹እወነትሽን ከሆነ ደስ ይለኛል››አልኩ..ግን እወነት ደስ እያለኝ አልነበረም ..ግራ እየተጋባው

እንጂ ..ሌላ ሰው እኛ ክፍል ውስጥ አብሮን ማደሩ ነፃነታችንን ይሻማብናል ብዬ

አስቤያለው..ግን ደግሞ የተለያየ አልጋ ላይ ለየብቻ ከመተኛት አንዱን አልጋ ለቆ አንድ ላይ

ቢያንስ ተቃቅፎ የመተኛት እድልን ያመቻችልናል፡፡

‹‹እ ምን ወሰንክ?››

‹‹እንደተመቸሽ..ግን አንቺ ነሽ ምታነጋግሪያት››

‹‹አንተስ ?››

‹‹አረ እኔ ሰቶችን ማነጋገር እኮ አይሆንልኝም››

ሰቆን አስነካችው‹‹ትናንትና ታዲያ እኔን ማነው ያነጋገረልህ?››

‹‹እሱን ለእኔም ግራ ገብቶኛል፡››

በቃ መጣው ..ይዤት ልምጣ ..አይዞህ ለሊት ካሰኘህ እየተጋላበጥክ ስትሰቃይ ከምታድር

መጠባበቂያ መያዙ አይከፋም››ብላ መቀመጫዋን ለቃ በፎቁ ደረጃ ቁልቁል ወደ ታች

መውረድ ጀመረች.....፡

በአስር ደቂቃ ልዩነት ልጅቷን ይዛ መጥታ ከጎኔ አስቀመጠቻት

‹‹ወንድሜ ነው ተዋወቂው››

ልጅቷም በሚርገበገቡ አይኖቾ እየገመገመችኝ እጀቾን ዘረጋችልኝ..እኔም በተመሳሳይ እጄን

ዘርግቼ የተዘረጋ እጆን እየጨበጥኩ ‹‹ዋቅቶላ እባላለው››አልኳት

‹‹ቲቲ››አለችኝ..ቲቲ በአመርኛ ሲተረጎም ምን ማለት አንደሆነ በቀላሉ ሊገለጽልኝ

አልቻለም..ደግሞስ ለምንድነው ስማቸው ቲቲ..ጂጂ…ፊፊ…የሚሆነው…?በውስጤ

የተፈጠረ ሌላ ጥያቄ ነበር…

‹‹ምን ትጠጪያለሽ..…?ወይን ከተመቸሽ ብርጭቆ ይምጣ…?››አልኳት

‹‹አይ ወይን ላይ እስከዚህም ነኝ..››

‹‹የፈለግሺውን እዘዢ›› አለቻትና አስተናጋጇን ጠራችላት..

‹‹ተኪላ›› ስትል አዘዘች..እንዲህ የሚባል መጠጥ አለ እንዴ..…?በውስጤ እራሴን ነው

የጠየቅኩት..እኔ ተኪላ ሳይሆን ካቲካላ የሚባል መጠጥ ነው በደንብ ማውቀው…

ድምጽ አውጥቼ በመጠየቅ መፎገር አልፈለኩም ስለዚህ ዝም አልኩ…

ብዙም ሳንቆይ የልጅቷ ስልክ እረፍት አልባ በሆነ ሁኔታ ይደውልላት ጀመረ…በማንሳት እና

ባለማንሳት መካከል ስትዋልል ታዘብኩና‹‹..አንስተሸ አናግሪ አንጂ›› አልኳት

ፈገግ እንደማለት አለቺልኝና አነሳችው

‹‹ሄሎ…››

‹‹አትምጣ… አግኝቼያለው››

‹‹አይ. መኖሪያ ቤት አይደለም የምሄደው.. ሆቴል ነው ››እሷ የምታወራውን ብቻ ነው

የሚሰማኝ..ቀጥላለች፡፡

‹‹በቃ ደህና እደር..ደግሞ እራት ሳትበላ እንዳትተኛ››

‹‹አሺ ቸው..ጥዋት እመጣለው››

‹‹እኔም እወድለው››ተዘጋ

‹‹ወንድምሽ ነው…?›››ተቅለብልቤ የጠየቅኳት እኔው ነኝ..እስኪ ወንድሞ ቢሆን አባቷ ምን

ይፈይድልኛል

‹‹አይ አይደለም››ተሸኮረመመች

‹‹ባልሽ ነው ማለት ነው…? ››አለቻት ጂጂ

‹‹እንዴት ባሏ ሊሆን ይችላል……?››

‹‹ለምን አይችልም……?››ተፋጠጥን

‹‹እኔ እንጃ በዚህ ሰዓት ደውሎ ..ገባሽ ወይስ ታድሪያለሽ…? የሚል ባል ይኖራል

እንዴ…?››ቀዝቀዝ ባለ ድምጽ ሀሳቤን ሰነዘርኩ

‹‹አይ ወንድሜ …አታርፍም ማለት ነው፡፡ ባሏ ማለት እኮ ያው ፎንቃ ያሲያዛት እና በነፃ

የሚጠልዛት ወንድ ማለት ነው..አይደል እናት…?››

ልጅቷ በጥርጣሬ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…?የሚል በሚመስል አስተያየት እያየቻት‹‹አዎ

ትክክል ነሽ››አለቻት

‹‹እና ባልሽ ነው ››ጠየቅኩ የሰማውትን ካለማመን በመነጨ ገረሜታ

‹‹አዎ ባሌ ነው..ስራ ካልቀናኝ መጥቶ የሚወስደኝ እሱ ነው…››

‹‹ወስዶሽስ…?››

‹‹እንዴ ወስዶኝ ያው ቤታችን አብረን እንተኛለና››ምንአይነት የጅል ጥያቄ ነው

‹‹ምንድነው ሚሰራው…?››

‹‹ተማሪ ነው …አዳማ ዩኒቨርሲቲ በማታው ክፍለጊዜ ይማራል…እኔ ነኝ ከፍዬ

የማስተምረው››

‹‹የማስተምረው..እንደዚህ እየሰራሽ ነው የምታስተምሪው››

‹‹አዎ …ምን አለበት…?››

‹‹እሱማ ምንም የለበት …ዋናው በፎንቃው መጠለፍሽ ነው…››አለቻት ጂጂ

‹‹አይ ፎንቃ ስለጠለፈኝ ብቻ ሳይሆን ስለሚያሳዝነኝ ነው..ሚስኪን ልጅ ነው ..ምንም

ቤተሰብ የለውም ..ደግሞ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው..በሚቀጥለው አመት ይመረቃል..››

‹‹እና ሲመረቅ እንዴት ነው የምትሆኑት…?››መጠየቅ የፈለግኩት እንደዛ አልነበረም

..ትምርቱን ጨርሶ ስራ ካገኘ ቡኃላ ቢተውሽስ…? ብዬ ነበር መጠየቅ የፈለግኩት..ግን

በምን አይነት ድፍረት እንደዛ ጠይቃታለው…?

‹‹እንዴት እንሆናለን .. …?››መልሳ ጥቄውን ለእኔው ደገመችው

‹‹ያው ተመርቆ ስራ ከያዘ ቡኃላ ስራሽን ታቆሚያለሽ ለማለት ፈልጌ ነው…?››

‹‹እሱ ሚስጥር ነው››

‹‹በፈጠረሽ ንገሪኝ››ተስገበገብኩባት..እስኪ ለወሬ በእናትሽ ..በፈጣሪ ብዬ መለመን ከእኔ

ሚጠበቅ ነው…?

‹‹ጠፋበታለው…ትምህርቱን ጨረሶ ስራ ከያዘ ቡኃላ ወዲያው ጠፋበታለው››

‹‹ጠፋበታለው ስተይ..…?ለምንድነው የምትጠፊበት…?››

‹‹እያፈቀርኩት እንድኖር..እነዚህ በፍቅር ያሳለፍናቸው የእውነት የሆኑ ጊዜያቶች መቼም

ከታሪኬ ውስጥ ከሽፈው ሲበኑ ማየት ስለማልፈልግ ….በኑሮ መቀየር ምክንያት ትቶኝ

ወይም ችላ ብሎኝ በእሱ እንዳዝንበት ስለማልፈልግ››

‹‹ታዲያ ትተሸው እንደምትሄጂ እያወቅሽ ለምንድነው የምትለፊው…?››ጥያቄዬ ከውስጤ

ሊያልቅልኝ አልቻለም..ለጂጂ እንኳን እድል ልሰጠት ስላልቻልኩ በፅሞና የተሞላች

አድማጭ ብቻ ሆናለችት …

‹‹የምን መልፋት…?››

‹‹እንዲህ ብርድ እየጠበሰሽ ከማታውቂያቸው ሰዎች ጋር አንሶላ እየተጋፈፍሽ እሱን

የምታስተምሪው ነዋ..››

‹‹ይሄን በማድረጌ ነው ለህይወቴ አንድ ትርጉም ያገኘው..ጠቃሚ ሰው እንደሆንኩ ማሰብና

ማመን የጀመርኩት ከእሱ ጋር ከተገናኘውና እሱን ማስተማር ከጀመርኩ ቡኃላ ነው…ከዛ

በፊት ባገኘውት ብር ፋሽን ልብስ መግዛት፤ መቃምና ማጬስ ብቻ ነበር…የዛን ጊዜም

የባንክ ደብተር አልነበረኝም አሁንም እሱን ሳስተምር የለኝም…ግን ለህይወት ያለኝ

አመለካከት ቀይሮታል…ወደእዚህች ምድር የመጣውት ትርጉም ያለው ጠቃሚ ተግባር

ለመከወን ነው ብዬ እንዳምን አድርጎኛል››

‹‹ይገርማል….እሱስ ምን ያስባል..…?ምንድነው የወደፊት ዕቅዱ…?››

‹‹ያው እሱማ ..ትምህርቱን እንደጨረሰና ስራ እንደያዘ ስራዬን እንደማቆም በስርአት

ተጋብተን የተረጋጋ በፍቅር የተሸመነ የጋብቻ ህይወት እንደሚኖረን ነው ..እኔም ትምህርቴን

እንደምቀጥል እና ቀስ በቀስ ኑሮችንን እንደምናሻሽል በየቀኑ ይነግረኛል..ልጆች

እንደምንወልድ ያልማል..አዎ እንደዛ ነው የሚያስበው..እኔም እንዲረበሽብኝ ስለማልፈልግ

እንዳልክ ነው የሚሆነው እለዋለው…ግን የማደርገው እንደነገርኮችሁ ነው..ከእሱ ጋር ወደ

ጋብቻ ህይወት ገብቼ ቢቀየርብኝስ..…?››አንድ ቀን ሸርሙጣ ብሎ ቢሰድበኝስ……?››በላዬ

ላይ ጨዋ የተባለች ሴት ቢወሽምና ጀርባውን ቢሰጠኝስ……?›› እኚንና የመሳሰሉትን አሳቃቂ

የመከዳት ስጋቶችን በማብሰልሰል ህይወቴን በጣር መግፈት አልፈልግም..እነዚህን ነገሮች

ምን አልባት እሱ ባያደርጋቸውና አሁን ቃል እንደገባልኝ ለማድረግ ቢጥር እንኳን እኔ በገዛ

ሀሳቤ እየቀረጽኩና እየፈጠርኩ እሱንም ሰላም መንሳቴና በገዛ ስጋቴ ና ቅናቴ እሱን

በመገፋፋት ያላሰበው ነገር ውስጥ መክተቴ አይቀርም…እና ለእኔም ለእሱም ስል እንደልኩ

ነው የማደርገው..››ለማንኛውም ሽንት ቤት ደርሼ መጣው ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ

ውስጥ ገባች

‹‹ምትገርም ልጅ ነች..ባንቺ ተገርሜ ሳልጨርስ ሌላ የምትገርም ሴት አጋጠመችኝ..በጣም

ታሳዝናለች››

‹‹አንድ ሳምንት ከእኔ ጋር ፒያሳ ውስጥ ብትኖር ከዚህ የበለጡ የሚገራርሙ ትንግርት

መሳይ ታሪኮችን አስኮመኩምህ ነበር››

‹‹አረ ይቅርብኝ..ከዚህ በላይማ እራሴን ሀዘን ውስጥ መክተት አልፍልግም… ይታይሽ በዚህ

ሰዓት ፍቅረኛዋ የእውነት የሚወዳት ከሆነ ምን እንደሚሰማው..?የእሱ የሆነች ሴት የእሱ

የወደፊት ህይወት ለመቀየር ስትል ከሌላ ሰው ጋር ስታድር ….አረ ለማሰብ እንኳን

ይከብዳል..እኛ ያፈቀርናትን ሴት መንገድ እንኳን ሲለክፋት ድንገት ካየን እንዴት ነው ቡራ

ከረዩ ስንል የምንውለው..አረ በጣም ይከብዳል..››ተንገሸገሽኩ፡፡

‹‹እና አታወጣትተም ማለት ነው?››

‹‹አረ ምን ነካሽ..እንኳን ይሄንን ታሪክ ሰምቼ ድሮውም ሀሳቡ አልነበረኝም…››

‹‹እንግዲያው ወደ ፍቅረኛዋ ትሂዳ››

‹‹እወነትሽን ነው››

‹‹እወነቴን ነው ..ብሩን እንስጣትና መጥቶ ይውሰዳት..››

‹‹ደስ ይለኛል..›ተስማማን

ልጅቷ መጥታ ለፍቅራኛዋ ደውላ ጠርታው..እኛም ገንዘብን

ሰጥተናት ተደስታና ተገርማ ..ነገ ከዋልን እንድንገናኝ ቁጥሯን ሰጥታን....ስትለየን ከለሊቱ

ስድስት ሰዓት ከሀያ ሆኖ ነበር..

እኛም ከዛ በላይ የምንቆይበት ምክንያት ስላልነበረ ሂሳባችንን ዘግተን ወደ ቀጠታ መኝታችን

ነበር ያመራነው…ሁለታችንም ጋል ያለ መንገዳገድና መኮላተፍም ያስከተለ ስካር ሰክረናል፡፡

እንደገባን እሷ ሮጣ ቀን ተኝታበት የነበረው አልጋ ላይ ተዘረረች..እኔ ፊኛዬ በሽንት ተሞልቶ

ስለነበረ ወደ ሽንት ቤት ገባውን ተንፍሼ ስመለስ ከላይ ተኝታ የነበረችው ልጅ ከውስጥ

ገብታ በብርድልብሱ ተጠቅልላ ተኝታለች..ፊት ለፊት ያለው ጠረጵዛ ላይ ልብሶቾ

ተቆልለዋል…በደንብ አየዋቸው፡፡ሱሪዋ ፤ቲሸርቶ ..ጃኬቷ ..እያልኩ በየተራ ተመለከትኩ…

ልብሶን አወላልቃ ባንቶ ብቻ ነው ጠረጵው ላይ የማይታየው..ስለዚህ ሰውነቷ ላይ የቀረው

ልብስ እሱ ብቻ መሆኑን ተረዳውና ሳለስበው ፈገግ ብዬ እኔም በተመሳሳይ አወለቅኩ

..በይ ጠጋ ብይ ብዬ ከጎ ከጎኖ ተዘረርኩ››

‹‹እንዴ ሰውዬ አልጋህ ላይ ተኛ እንጂ…ሁለት አልጋ ያለው ክፍል የተከራየነው እኮ ለዚህ

ነው››

‹‹ባክሽ እኔ ብቻዬን አልተኛም››

‹‹ተኛለው ብለህ እኮ ነው ያመቻቸውልህን ልጅ የሸኘሀት››

‹‹እንደዛ ማለቴ አይደለም…ማለቴ እንትን ማድረግ ፈልጌ ሳይሆን እንዲሁ አብረን እንድንተኛ

ስለፈለኩ ነው..ልክ እንደትናንቱ››

‹‹አይ አንተ ሰው….በቃ ሲነግሩህ አትሰማም አይደል..በል እሺ ከውስጥ ግባ..ተጣድፌ እና

ተስገብግቤ ገባው…በዛው ቅጽበት ግን እሷ ወጣች››ግራ ገባኝ…

‹‹አንዴ ምነው..ወዴት ነው?››

‹‹ልብሴን ልልበስ››

‹‹ለምን?››

‹‹አብሬህ ለመተኛት ነዋ››

‹‹አብረሺን ለመተኛተ ልብስ ማውለቅ እንጂ ልብስ ማድረግ ነው እንዴ ?››

‹‹እንግዲህ ምርጫው ያንተ ነው››

‹‹እሺ እንዳልሽ››

ያወለቀችውን ጅንስ ሱሪያዋና ቲሸርቷን መልሳ በመልበስ መጣችና አርቃን እቅፌ ውስጥ

ገባች..ወይ ጉዴ

ሀሳቤ ሁሉ ብትንትን አለብኝ እራሴን ለመቆጣጠር ዝም ብዬ ማውራት ፈለግኩ…ግን ልጅቷ

በዚህ እድሜዋ እንዲህ ማሰቦ አይገርምሽም ልጅ እኮ ነች››አልኳት

‹‹ያን ያህል እንኳን ልጅ የምትባል አይደለችም …

‹‹እንዴ አረ ልጅ ነች?››

‹‹አዎ ልጅ ነች ግን ያን ያህል የሚጋነን ልጅነት አይደለም.. እኔ በእሷ ዕድሜ ስደርስ ቢያንስ

ሀያ ድንግልና ሸጪያለው››

‹‹ድንግልና ሸጬያለው..ምን አይነት ድንግልና››

‹‹ድንግልና ነዋ..ድንግልና አታውቅም››

‹‹አውቃለው..ግን ሀያ ድንግልና እኮ ነው ያልሽው››

‹‹አዎ ሀያ ድንግልና››

‹‹እንግዲያው አላውቅም.. እኔ የማውቅም ድሮ ድሮ ሴቶች ከአንድ አንድ ድንግልና ጋር

እንደሚወለዱነው..››

‹‹አሁንስ››

‹‹አሁንማ ከእነጭራሹም የለም ይባላል››

‹‹እንግዲያው እኔ በ15 ዓመቴ ላይ ጀምሬ ለሁለት አመት ያህል ስራዬ ድንግልና መሸጥ

ነበር… ቢያንስ ከ30 ጊዜ በላይ ሸጬያለው››

‹‹እኮ እንዴት አድርገሽ..››

‹‹ታሪኩ ረጅም ነው…››

‹‹አጠር አድርገሽ ንገሪኛ››

እኔ እዚህም እዛም እንደምታያቸው ሴተኛ አዳሪዎች እንደልመስልህ …ለስራው ፕሮፌሽናል

ባለሞያ ነኝ…ከ10 ዓመቴ ጀምሮ ከፍተኛ ስልጠና ወስጄበት ነው ከ15 ዓመቴ ላይ

ወደስራው የተሰማራውት…

‹‹ሰልጠና..ጭራሽ ስልጠና.. እየቀለድሽ ነው፡፡››

አይ እወነቴን ነው…እናቴ አራዳ አካባቢ አንድ የቀበሌ ቤት ወስጥ ይሄንኑ ስራ እየሰራች ነው

የወለደችኝ…እና ያኑም እየሰራች ነው ስታሳድገኝ የነበረው…ቤቷ አንድ ክፍል እና አራት

በአምስት ስፋት ያላት ብትሆንም እሷኑ ለአንድ አልጋ ማዘርጊያ የምትሆን ከፍላ ሌላ ሴት

በማስገባት የእኩል ታሰራ ነበር››

‹‹የእኩል ስትይ››

ሴትዬዋ በሰዛች ቤት ወስጥ ከወንድ ጋር አድራ ወይም አጭርም ቢሆን ሰርታ አስር ብር

ብትሰራ አምስቱን ለእናቴ ትሰጣትና እምስቱን ለራሷ ትወስዳከለች ማለት ነው…እንግዲህ

እናቴ የቤቱ እመቤት መሆኗ ነው…በተቀረችው ክፍል ደግሞ እራሷ ትሰራበት ነበር…››

‹‹ይቅርታ አድርጊልኝና እናትሽ ግን የሚከብድ ነገር ነው ይሰሩ የነበሩት..ማለቴ የእኩል

ያልሽው… አረ ይከብዳል››ተሸማቀቅኩ

‹‹ያ የእናቴ የግሏ ህግ አይደለም …አዛ አካባቢ ሁሉም በዚህ ስራ ላይ የሚተዳደሩ እና

እቤት ያለቸው ተመሳሳዩን ነው ሚያደርጉት….ግን ሴትዬዋ ቀላል አልነበረችው..ሁሉን ነገር

ካጠናች እና ሰፈሩን በጣም ከተለማመደች ቡኃላ እናቴን አስወገደቻት..

‹‹አስወገደቻት ስትይ..››

‹‹በመርዝ ገደለቻት››

‹‹እና ታሰረች››

አረ ምን በወጣት…በመርዝ ገደለቻት ስልህ እኮ በግልጽ አይደለም ያደረገችው በከፍተኛ

ጥንቃቄ እና ሚስጥር ነው..እኔ እንኳን እሱን ለማወቅ አምስት አመት

ፈጅቶብኛል….መንግስትማ እሷም ምስኪን ናት ብሎ ማለቴ ቀበሌው ቤቱን በስሞ

አዘዋወረላት እና …እኔንም መረቁላት››

‹‹አዎ ..አሳድጋታለው ብላ ወሰደችኝ..ደግነቱ አላሳድገታም ብትል እንኳን ጎዳና ከመውጣት

ውጭ ሌላ ምርጫ አልነበረኝም…››

‹‹አይ ምንም እንኳን እናትሽን መግደሏ ጭካኔ ቢሆንም አንቺንም ጎዳና አለመጣሏ

ያስመሰግናታል፡፡››

‹‹አይ እንደዛማ አይደለም… እንደውም የእሷ ጭካኔ እናቴን ለመግደል ከመወሰኖ በላይ እኔን

ላሰሳድግ ብላ በመውሰዶ ነውየሚገለፀው፡፡

‹‹እንዴት››

‹‹እናቴን ለመግደል መወሰኖ እቤቱ አጎጉቷት ሁሌ ገላዋን በመሸጥ ለሌላ ሰው ግብር

መክፈል አንግሽግሾት ነው ብለህ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ምክንያነት አለው ልትል

ትችላለህ…. እኔን ለማሳደግ የወሰነችው ግን ለአራት አመት እናት ስትቀበላጥ የነበረውን

በወር እኔ እንድመልስላት አስብና ወስና ነበር…..እና አንድ ሺ እጥፍ አድርጋ ተቀብላኛለች…

በእኔ ባለ ቤት በእኔ ባለ መኪና ሀናበታለች…እርግጥ እኔ ብቻ እልነበርኩም ሌሎች አራት

አምስት እኔን መሰለሎች ነበሩ ግን ጅማሬዋ እኔ ነኝ..መነሻዋ እኔነኝ፡፡

‹‹አወሳሰብሽብኝ እኮ..እንዴት አድርጋ ነው ያስከፈለችሽ››

‹‹ሌላውን ተወው ድንግልና ብቻ 30 ጊዜ ሸጬላታለው….በአንዱ ድንግልና ከሁለት ሺ እስከ

አስር ሺ ትቀበልበታለች…››

‹‹እንዴት አድርጋ?››

ይሄንን የሚሰሩላት ደላሎች አሏት…እሷ እድሜዋን በዚህ ስራ ላይ ስላሳለፈች የማታውቀው

ነገር የለም..ድንግል ነች ትልና ለሶስት ቀን በሆነ ጭስ በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ራቁታችንን

በቁርበት አፍና ታጥነናለች..የምታጥነን እግራችንን ወዲህና ወዲያ በለቃቅጣ ጭሹ በደንብ

ወደ ማህጻነችን እንዲገባ አድርጋ ነው..በሶስተኛ ቀን ማለቴ ሰውዬው ጋር ያለውን ነገር

ደላላው ይጨርሳል ብሩን ይቀበላል እኛን ወስዶ ያስረክበናል..ከመሄዳችን በፊትም በደንብ

አድርጋ እራሷ እኛን ስለማታምነኝ ኮካ እና የሆነ ምንነቱን የማላውቀውን ዝልግልግ ቅባት

ነገር በመቀላቀል በደንብ አድርጋ ብልታችንን ታጥበናልች..እንዲህ በቀላሉ አይምስለህ

እጣቶን ውስጣችን እየሰነቀረች በደንብ ታጥበናለች…….ውስጡንም ውጭንም….

ከዛ የየትኛው ወንድ ብልት ነው ያንን ሰንጥቆ መግባት የሚችል…?››ሰውዬው ድንግል

አገኘው ብሎ መፋተግ እኛ ድግሞ በጣርና በስቃይ መቃተት ነው…ከዛ እንዴት የበረታው

በስንት መላላጥ እና መፋተግ ወደውስጥ መግባት ይችላል…እና ደም በደም ሆኖ….

እሱ መሸወዱን ሳያውቅ በእርካታና በደስታ ሲጨፍር ..እኔ በህመምና በስቃይ ሳለቅስ

ለሊቱ ይነጋል…ከዛ አስራ አምስት ሀያ ቀን አገግምና ደግሞ ሌላ ድንግልና ግዤ ተገኘ

ሲባል..ሌላ ዝግጅት፡፡

ይሄንን መቼሽ በእውነት አለም ለዛውም በዚህች በእውነት ኢትዬጵያ ውስጥ የተደረገ ታሪክ

ነው ብዬ ለማመን በጣም ይከብደኛል፡፡››

‹‹እንግዲህ አመንክም አላመንክም እውነት ነው…ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም ማስረጃ

ፈልጋለው ካልክ ደግሞ ጥዋት አስታውሰኝ . አሁን ግን እቀፈኝና እንተኛ …እንቅልፍ

እያንገላጀ..ጀኝ ነው››አለቺኝ

አረ እሺ ብዬ ጭምቅ አድርጌ አቀፍከዋትና ፀጥ አልኩ….ወደ እንቅልፍ አለም የሚያደርስ

በፍትወት አምሮት ኡኡታ የታጀበ......ምን አይነት በቅዠት እና በሙቀት የተሞላ በተቆራረጠ እንቅልፍ የታጀበ ለሊት እንዳሳለፍኩ

አትጠይቁኝ…

አጅሪት ግን !!! እሷማ ምን አለባት..ልክ እናቷ እቅፍ ውስጥ እንዳለች ጨቅላ ህጻን ሀሳበን

ጥላ ሰውነቷን ደረቴ ላይ ዘረጋግታ የደሀ እንቅልፍ ተኝታ አደረች..የደሀ እንቅልፍ ግን ምን

አይነት ነው….?

ይህን ለማወቅ አንድ ምሽት ላይ የአዲስ አበባን ጎዳናዎች ዞር ዞር ብሎ መቃኘት በቂ

ግንዝቤ ለማግኘት ይረዳል ብዬ አስባለው….የደሀ እንቅልፍ እስፕሪንግ ፍራሽ እና ኮምፎርት

ብርድልብስ አይጤይቅም…የደሀ እንቅልፍ በሀሳብና በስጋት አይቆራረጥም…የደሀ እንቅልፍ

ከቅዠት ይልቅ በንጹህ ህልም የተሞላ ነው…የደሀ እንቅልፍ ከፍርሀት ይልቅ በእፎይታ

የተከበበ ነው…

ደሀና ህልም ይወደዳሉ…ህልም የድብቁ ምኞታችን ምንዛሬ ነው… ቅዠት ደግሞ የፍርሀታችን

ነጻብራቅ ነው፡፡ደሀ ምኞቱን በሰላማዊ እንቅልፍ ውስጥ ያልማል…ሀብታሙ፤ሙሰኛው ወይም

ወንጀለኛው የፍርሀቱን ነጸብራቅ በሆነ ቅዠት ሲቃትት ያድራል፡፡

አንዳንዴ ህልማዊው አለም ከእወነቱ አለም በተሸለ ፍትሀዊ እና ምክንያታዊ ድርጊቶች

የሚከወኑበት …የተሻለ ደስታ የምናገኝበት… ምኞታችንን ምንኖርበት አለም ነው..

በዛም ምክንያት በህልማችን እንደውስጣችን ምኞት የምንኖርበት እና ጣፋጭ ደስታም

ምናገኝበት ዓለም ነው፡፡ስለዚህ ህልም ለደሀው ፤ለጭቁኑ እና ለተገፋው እንደማካካሻ

ተፈጥሮ የሰጠችው ፀጋ ይመስለኛል…ለዚህም ነው ከረጅም ተከታታይ ህልም ጋር ረጅም

እንቅልፍ የተደለው..ተረቱስ ደሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ንቃቃት ይገለው ነበር አይደል

የሚባለው…..አንድ ደሀ በአይን ፍቅር የተነደፈላትን አማላይ ከላይኛው ማህበረሰብ ወይም

ከዝናው ጣሪ ላይ የለችን ሴት አግኝቶ አናግሮ አሳምኖ ወደ ማረፊያ ክፍል ይዞት ገብቶ..

ልብሱን አውልቆ እና አስወልቆ ስሞና ተስሞ ..ያሻውን ሚያደርገው በህልሙ ነው..በጣፋጭ

ህልሙ…የሙሉ ደስታው ማህተም የሆነውን የዘር ፍሬውን እስከመርጨት ያደረሰውን ሀሴት

የሚያጎናፀፈው ህልም ነው፡፡እና ደሀ እንቅልፍና ህልም እንዲህ ይመስሰላሉ…

ያ ማለት ግን ሀብታም ሁሉ እንቅልፋ አልባ እና ህልሙ የማያምርለት ነው ማለት

አይደለም..ረጅም ያልተቆራረጠ እንቅልፍ ከጣፋጭ ህልም ጋር በህይወቱ የታደለ ሀብታም

ካለ በምድር እያለ እንደፀደቀ ቁጠሩት…እርገጠኛ ሆኜ መናገር እችላለው እንደዛ አይነቱ

ሀብታም ሀብቱ ውስጥ ምንም አሻጥር፣፣ምንም ዘረፋ.፤ምንም ያልተከፈለ የሰው ላብ

የለበትም፡፡ለዛ ነው በሀብቱ ላይ የደሀ እንቅልፍ የታደለው፡፡

ለማንኛውም ወደ ዋናው ቁም ነገር ልመለስ እና እሷ ማለቴ የእኔዋ ጂጂ…የእኔዋ ጂጂ

አልኩ እንዴ …….?ለሁለት ቀን ሳይሆን ለሁለት አመት አብሬያ እንደኖርኩ ነው እየተሰማኝ

ያለው….ለዛ ነው መቀባጠሬ…ወይ ዘንድሮ መጨረሻዬ ለማየት ነው የጓጓውት…

..ሁለት ሰዓት ላይ ስልክ ተደወለልኝ..ስልኩ ከቤት ነው የተደወለልኝ..ከሻንቡ አነሳውት

‹‹ሄሎ እማዬ››

‹‹ሰላም ነህ ልጄ….?››የእናቴ የደከመ እና ተቆራረጠ ድምጽ

‹‹አዎ ሰላም ነኝ…ምነው በጥዋት ….?ሰላም ነው አይደል….?››

‹‹አረ ሰላም ነው..መቼ ነው የምትመጣው….?እሱን ልጠይቅህ ነው….?››

‹‹ነገ እመጣለው…ምነው ምትፈልጊው ነገር አለ..ምን ይዤልሽ ልምጣ….?››

‹‹አይ ምንም አልፈልግም..ቶሎ መምጣት አለመምጣትህን ብቻ ለማወቅ ስለፈለግኩ

ነው….?››

‹‹እማዬ ምንድነው የተፈጠረው …ድምጽሽ ትክክል አይመስለኝም››ያው እናቴ አይደለች

ያለችበትን ሁኔታ በድምጾ ቃና አውቃለው…

‹‹አረ ሰላም ነው..ብቻ ….››

‹‹ብቻ ምን….?››ልቤ ተሰቀለች

‹‹ልጅቷ ሄዳለች››

‹‹የቷ ልጅ….? ››ግራ አገባችኝ‹..የቷ ልጅ ነች የሄደችው…….?ወዴት ነው የሄደችው..….?

ለምንድነው የሄደችው….?›ምንም ሊገለጽልኝ አልቻለም፡፡

‹‹ፋጤ ነቻ..ሰራተኛዋ››

‹‹እንዴ!!! ለምን .. ….?ምን ሆና…….?.ልጄንስ የት አድርጋ…….?እራሴን መቆጣጠር

አቃተኝ..ደረቴ ላይ ተኝታ የነበረችውንና ከእንቅልፍ ተፅዕኖ ሳትወጣ በከፊል ንቃት

እያዳመጠችኝ የነበረችውን ጂጂን አስፈንጥሬ ከላዬ ላይ ከወረወርኳት ቡኃላ አልጋውን

በመልቀቅ እርቃኔን ቤት ወስጥ ወዲህ አወዲያ እየተሯሯጥኩና እየተወራጨው ማውራቴን

ቀጠልኩ››

‹‹ልጅቷንማ ለእኔ ትታልኝ ነዋ››

‹‹እማ ልጄ ሰላም ነች ግን ….?››

‹‹አረ ሰላም ነች…››

‹‹ለመሆኑ ምን ሆንኩ አለችሽ..….?እስክመጣ ድረስ መጠበቅስ ያቃታት ምን አይነት የነፍስ

ጉዳይ ቢያጋጥማት ነው….?››

‹‹አላውቅም ልጄ ..ልትነግረኝ አልፈለገችም..››

‹‹እሺ እማ እስክመጣ አደራ.›››

‹‹እንዴ ምን አደራ ያስፈልገዋል ..ለእኔም እኮ ልጄ ነች….?ስለገዛ ልጄ እኮ ነው

የምናወራው››እናቴ የተለመደ ቅሬታዋን ማሰማት ጀመረች…ሁል ጊዜ እንዲህ አይነት ጥያቄ

ሳቀርብላት ቅር ትሰኛለች..ለልጅ ልጇ ያላትን ፍቅር ጥያቄ ውስጥ ያስገባውባት

ይመስላታል፡፡

‹‹እሺ እማ… ከቻልኩ ዛሬውኑ ለመምጣት እሞክራለው››

‹‹አረ ተረጋጋና እንደእቅድህ ነገ ና..››

‹‹እሺ እማ ቸው››

‹‹ቸው ልጄ ››ስልኩን ዘጋውና.ቀጥታ ልብሴን መልበስ ጀመርኩ…

‹‹ሰላም ነው አለችኝ….?››ግራ በመጋባት አስተያየት

‹‹ምን ….?ሰላም ነው..….?ዛሬ መሄድ አለብኝ …ተነሽ ቁርስ እንብላና እንሂድ››

‹‹ልጄን ጥላ ስትል የሰማው መሰለኝ..ሚስትህ ጥላህ ጠፍታ ነው..….?ግን ሚስት የለኝም

ብለሀኝ ነበር እኮ››ለምን ዋሸኸኝ በሚል ጥያቄ የታጀበ ትዝብታዊ አስተያየት እያየችኝ

‹‹ባክሽ ሚስቴ አይደለችም… ልጄን የምታሳድግልኝ ሰራተኛዬ ነች ››

‹‹ሰራተኛዬ..ሰራተኛህ ብቻ….?››

‹‹አዎ ሰራተኛዬ ብቻ ..ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ግን….?››

‹‹አይ አደነጋገጥህ ሲታይ ሰራተኛህ ብቻ የሄደችብህ አይመስልም››

‹‹ያልተነካ ግልግል ያውቃል የሚባለው እኮ ለዚህ ነው.. አንቺ ምን አለብሽ..ለእኔ ሰራተኛ

ትሁን እንጂ ለልጄ እኮ እናት በያት…ከአንድ ወሯ ጀምሮ ይሄው ሶስት አመት ሙሉ እሷ ነች

ያሳደገቻው..ልጄ እንደ እናቷ ነው የምትወዳት….››ለብሼ ጨርሼለው …እሷም አልጋውን ለቃ

መቀመጫው ላይ ቁጭ በማት ለብሳ ያደረችውንና እላዬ ላይ የተሸበሸበ ልብሶን

እያስተካከለች ነው እያወራቺኝ ያለችው..፡፡

‹‹ቢሆንም ለመፍረድ ቸኮልሽ አትበለኝ እንጂ እንኳን ሰራተኛህ ይቅርና ዋናዋ ሚስትህ

ማለት የልጅህ እናትም አንተንም ልጇንም ትታችሁ ሄዳ የለ…..….?››

ፊቴ ሁሉ ልውጥውጥ ሲል ለእኔው ለራሴ እየታወቀኝ ነው.ሰወነቴ ሁሉ መንቀጥቀጥ

ጀመሯል..

‹‹አረ አረጋጋው..ዝም ብዬ አስተያየት ልስጥህ ብዬ እንጂ የሚመለከተኝ ጉዳይ ሆኖ

አይደለም››

‹‹አይ እወነትሽን ነው..እናቷም ጨክና ጥላኝ ሄዳለች..አዎ በእኔ ጨክና..አዎ በልጇ

ጨክና…››

ጃኬቴን ከተቀመጥኩበት አንስቼ አንጠለጠልኩና ክፍሉን ለቀቅቄ ወጣው..

‹‹አረ ጠብቀኝ..ፊቴን እንኳን ሳልታጠብ ››እያለች ከኃላዬ ተከተለቺኝ

እንደምንም እራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ቁርስ ወደምንበላበት ቤት ይዤት

ገባው..አዘዝንና ፊት ለፊት ተፋጠን ቁጭ አልን…..ምግቡ መጣ..ኩርፊያ በተቀላቀለበት

ፀጥታ የቀረበውን ቁርስ በልተን ወደመኪናችን ገባንና …ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ….፡፡በፍጥነት

መንገድ ገብተን መሀል ከደረስን ቡኃላ

‹‹በቃ አሁን ቀጥታ ወደ ሀገርህ ልትሄድ ነው ….?››

‹‹ምን ምርጫ አለኝ… ልጄ እኮ ነች….?››

‹‹አይ እናትህ ጋር አይደል እንዴ ያለችው››

‹‹እናቴ አቅመ ደካማ ነች…ጎንበስ ቀና ብላ እሷን መንከባከብ በጣም ነው

የሚከብዳት..እሷም እራሷ በሌላ ሰው እንክብካቤ የምትኖር ነች››

‹‹አይዞህ..የህፃኗ እናት እዛ አካባቢ አይደለም እንዴ የምትኖረው….?ማለቴ ለጊዜውም

ቢሆን ..››

ለማለት የፈለገችው ስለገባኝ አላስጨርኳትም…‹‹አይደለችም…እሷ አንደኛዋን ነው ጥላን

የኮበለለችው››

‹‹አንደኛዋን ስትል….?››

‹‹ልጄ በተወለደችበት ቅጽበት ነው የፍቅሬ እስትንፋስ የተቆረጠው›› ድክም ባለድምጽ

መለስኩላት…ዛሬ ደግሞ ምን አይነት ቀን ነው…….?ይሄንን ህመሜን..ይሄንን ቁስሌን

እንዳስታወስ ..አስታውሼም እንዳወራ የተገደድኩበት..ፍጽም በሆነ በደስታ እና በጉጉት

የተሞላ ሁለት ቀን ካሳለፍኩ ቡኃላ ደስታዬን አጣጥሜ ሳልጨርስ እንዲህ ደስታዬን

የሚያደፈርስ ቀጥታ ከህመሜ ጋር የሚቆራኝ ዜና የሰማውት…የልጄ እናት …የውስጥ

ህመሜ ..ፍቅሬ ..ተዳሬን ካጣው ሶስት አመት ሆነኝ..፡፡አዎ ልጅ እንድትወልድልኝ ሆስፒታል

አስገባዋት…ህይወት ያላት ልጅ ሰጥታኝ የራሷን ህይወት ግን ተነጠቀች…፡፡በአንድ ቀን

በአንድ ቀንም አይደለም በሰከንድ ሽርፍራፊ ሰከንድ ለህይወቴ በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር

ማጣትና በዛው በተመሳሳይ የጊዜ ሽራፊ በህይወቴ ወሳኝ የሆነ ነገር ማግኘት…ስሜቱ

ሲኦልና ገነት ለመለያ የተገነባ በግማሽ እሳት እና በግማሽ ውሀ በተሰራ አጥር ላይ

እንደመቀመጥ ነው… የሚያቃጥል የሀዘን እሳት እና የሚያቀዘቀቅዝ የደስታ ወሀ……

‹‹በጣም አዛናለው..እወነቴን ነው…እኔ እንደዛ አልገመትኩም.. ይቅርታ የማይሆን ነገር

ስለተናገርኩ..እኔ ለሞት ደንታ የለኝም ..ሰው ሞተ ሲባልም አንጄቴ እንዲህ በቃላሉ

አይንቦጫቦጭም..አንድ እናት የሆነች ሴት ስትሞት ግን በጣም ነው ውስጤ በሀዘን

የሚላወሰው…በተለይ ህጻን ልጅ ጥላ ምትሞት እናት…፡፡

‹‹‹እንግዲህ ምን ታደርጊዋለሽ..››

‹‹አይዞኝ..ሰራተኛዋ ምን አልባት የሆነ ጊዜያዊ ችግር አጋጥሞት ይሆናል..ትመለሳለች››

‹‹አይመስለኝም››

‹‹አይመስለኝም ስትል….?››

‹‹አንድ ዙሪያዋን እየተሸከረከረ ሲያባብላት የነበረ ጎረምሳ ነበር..እሱ ነው ያስኮበለለብኝ….››

‹‹አይዞህ..እንደዛም ከሆነ ሌላ ሰራተኛ ትፈልጋለህ››

‹‹አዎ እፈልጋለው …….ግን ከልጄ ጋር ተላምዳ እንደእናት ልትንከባከባት የምትችል ሴት

አለች አወይ ነው.? ጥያቄው..ልጄ ማለት ለእኔ ልጄ ብቻ አይደለችም…ሚስቴም ጭምር

ነች…ልጄን ሳቅፍ ሚስቴ ከሰማይ ሆና ፈገግ ስትል አያታለው…ልጄን ስትስቅ እሷም ከሰማይ

የምሰጋና ዝማሬ ስትዘምርልኝ ይሰማኛል…ከልጄ ጋር የማሳልፋቸውን ጊዜያቶች ሁሉ

ከሚስቴ ጋር እንደማሳልፋቸው የፍቅር ጊዜ ነው የሚሰማኝ…..እና በተቃራኒውም ልጄ

ስታለቅስ…የእናትዬው እንባ ከሰማይ ተነስቷ ሰውነቴ ላይ ሲንጠባጠብ ይሰማኛል..

‹‹በጣም ነበር የምታፈቅራት.?››

‹‹ፍቅር አይገልፀውም.. አንድ ሚስጥር ልንገርሽ..እሷን ካጣዋት ቡኃላ ከሌላ ሴት ጋር

አንሶላ የመጋፈፍ አምሮት እና ፍላጎት የተሰማኝም የሞከርኩትም ካንቺ ጋር ነው ከናቺ ጋር

ብቻ..››

ይሄንን ስትሰማ የተደሰተች እንዳይመስላችሁ..ፊቷ የፈገገ እንዳይመስላችሁ… አመዷ ብን

ነው ያለው…አይኖቾ ፈጠጡ

‹‹እወነትህን እንዳይሆን.?››

‹‹ከልጄ ይነጥለኝ እወነቴን ነው››

‹‹በጣም አዝናለው፣የእወነት በጣም ነው የማዝነው››ብላ አንገቷን በሀዘን ደፋች

‹‹ለምኑ …አንቺ ምን አደረግሽ››

‹‹ምንም ባላደርግም በአጋጣሚው አዝናለው…ከእኔ ጋር መገጣጠምህ ትክክል

አልነበረም..ላንተ የሚያስፈልግህ ትክክለኛ ስሜትህን የምታክምልህ እንጂ ..ከአንተ የባሰ

የተዘበራረቀ ስነልቦና ላይ ያለች ሴት አልነበረም…...››

‹‹ያ ያንቺ ሀሳብ ነው..እኔ ግን ባሳለፍነው ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ…ቢያንስ ለአመታት

ተዳፍኖ የኖረውን ስሜቴ መነቃቃት ችሏል..ሲለምኑኝ እና ሲፈታተኑኝ የምበረግግ ሰውዬ

አሁን እኔ እራሴ ሰጪኝ ብዬ መለመን መጀመሬ እራሱ በራሱ ትልቅ የለውጥ ተስፋ ነው

‹‹እንዳልክ ..አንተ ሳናውቀው እኮ አዲስአበባ ገባን….››

‹‹ይገርማል..ሹፌሬ ሳሪስ አካባቢ እየጠበቀኝ ስለሆነ በዛ ነው የምንሄደው..ከዛ የፈለግሽው

ባታ እናደርስሻለን››

‹‹የምትፈልጊው ቦታ..አይ ስቴዲዬም ከጣልከኝ ይበቃኛል››

‹‹አረ ችግር የለውም..ደግሞ ሁኔታዎችን አስተካክዬ በቅርብ እመጣለው››

‹‹በቅርብ ሌላ ስብሰባ አለህ ማለት ነው.?››

‹‹አይ የለኝም..አንቺ ጋር እመጣለው..እስከዛውም በየቀኑ እደውልልሻለው››

‹‹የእውነትህን ነው.?››ባለማመን ጠየቀቺኝ

‹‹አዎ እወነቴን ነው..ቢያንስ ከአስራአምሰት ቀን ቡኃላ መጥቼ አይሻለው››

‹‹ደስ አሰኘሀኝ…ማለቴ የሆነ ማላውቀው አይነት ስሜት እንዲሰማኝ አደረግከኝ››

‹‹ማለት..ምን አይነት ስሜት››

‹‹እኔ እንጃ ..ልትለየኝ ስትል መፍራት..ብቻ አላውቅም…››አይኖቾ እንባ አቀረሩ

‹‹እኔም እንዲህ ባለ ሁኔታ ባንለያይ ደስ ይለኝ ነበር…..››

‹‹ብሸኝህ ቅር ይልሀል.?››አለቺኝ

ግራ ገባኝ‹‹ብሸኝህ ስትይኝ.?››

‹‹እስከ አንቦ አብሬህ ብሄድና እዛ ድረስ ብሸኝህ››

‹‹እወነትሽን ነው.?››ከመደንገጤ ብዛት ሳለስበው ተሳስቼ ፍሬን ያዝኩና መኪናዋን አቆምኩት

ከሆላ ከሚከተለኝ መኪና ጋር ተጋጭቼ ነበር ..ለጥቂት ነው የተረፍኩት

‹‹አዎ…በትራንስፖርት እመለሳለው…ሹፌርህ ግን ..ማለቴ ወሬ ምናምን ሚደብርህ ከሆነ

ጣጣ የለውም…››

‹‹አረ ችግር የለውም ..እንደውም ቆይ..አልኩና መኪናዬን ዳር አዝይዤ አቁሜ ስልክ

አውጣና ደወልኩ ሹፌሬ ጋር…እኔን ፍቃድ መጠየቅ ፈርቶ እንጂ አንድ ሁለት ቀን አዲስአባ

መቆየት እንደሚፈልግ አውቃለው…እና ፈቀድኩለት… በደስታና በምስጋና ተቀበለኝ..የጋራ

ጥቅም ማለት ይሄ አይደል…እሱም ጉዳዩን ይፈጽማል እኔም ነጻነቴን አገኛለው፡፡

‹‹በይ ልነዳው ነው…››

‹‹ወዴየት.?››

‹‹ወዴት ትያለሽ እንዴ . .?.ልሸኝህ አላልሺም ..ወደ አንቦ ነዋ..››

‹‹እንግዲያው ንዳው አለቺኝ›› በደስታ

ከመጨፍገግ በወጣ ስሜት እንዳለቺኝ ነዳውት…፡

መብራት ከሌለ ቻርጅ የለኝም...ካልቸረጅኩ ደሞ ኦን የለሁም ማለት ነው...በሠአቱ ካላቀረብኩ በዚህ ውሠዱት!!

.

ከዚህች ወፍ ጋራ ወደ አንቦ በመጓዝ ላይ እንዳለው ማመን ነው ያቃተኝ…ደግሞ ሰራተኛዬ

ልጄን ጥላ መሄዷን ዜና በመስማቴ የተነሳ ድፍርስርስ ያለው ስሜቴ አሁን ፈካ ብሏል…

ፈካም ብቻ ሳይሆን ዘናም ብያለው….፡፡የባጥ የቆጡን እየቀባጠርን ጊንጪ ደርሰናል፡፡ጂጂ

ማለቂያ የሌላቸውን ከሆረር ፊልም የተቀዱ የሚመስሉ የግል ታሪኮቾን በጣፋጭ አንደበቷ

እያወራችኝ ነው..እኔም መኪናዬን በደመነፍስ እያሽከረከርኩ በተመስጦ እያዳመጥኳት ነወ፡፡

‹‹…አሳዳጊዬ ማለት የእናቴ ገዳይ እና የቤታችን ወራሽ ሮማን ትባላለች..ስሞ ያምራል

አይደል..?ለነገሩ ስሞ ብቻ አይደለም መልኳም ያምራል…ዘንካታ የቤት እመቤት ነው

የምትመሰለው…ረጋ ያለ ያነጋገር ለዛ ያላት ከፊቷ ፈገግታ የማይለይ…ንጻህ የህፃን ፊት

ባለቤት የሆነች ሴት ነች…..የእግዜያብሄር ስራ ግን አንዳንዴ በጣም ያስገርመኛል፡፡››

‹‹እንዴት..?››ንግግሯ ስላልገባኝ ጠየቅኮት…..

‹‹ያን የመሰለ ማራኪና አሳዛኝ ገላ ውስጥ እንደዛ ያለች ከሲኦላዊ ጭለማ የተቀመመ

የክፋት ማምረቻ መጋዘን የሆነ ነፋሰ ማስቀመጡ…..››

‹‹እሱ ነው ብለሽነው እንዳዛ ያደርገው..?›

‹‹አይ እሱማ ላይሆንም ይችላል …መቼስ የፈጠረን እግዜር የሚባል አካል ያለ ከሆነ ብዬ

ነው…››

‹‹እሱማ አለ..የፈጠረን ፈጣሪ አለ..ግን ክፋትን በገዛ ፍቃዳችን ወይም ሃብትን ለማጋባስ …

ወይንም ስልጣንን ለማግኘት ካለን የተጋነነ ፍላጎት አንፀር በውስጣችን ዘርተን

የምናሳድገው ክፈትና አሻጥር ከገዛ ራሳችን የሚፈበረክ የራሳችን ድክመት ውጤት

ነው..ማለት ሴጣንም ቢያግዘን ማለቴ ነው››

‹‹ይሁንልህ… እኔ የሰው ልጆች የራሳቸውን ክፋትና ሀጥያትን ኃላፊነት ላለመቀበል ሲሉ

በሰይጣን የሚያሳብቧት ነገር ስለማትመቸኝ ነው፡፡››

‹‹እሺ ይሁን ከክርክሩ ወደ ታሪኩ ተመለሺልኝ››

‹‹…ታሪኩማ ይህቺ ሮማን ያልኩህ አሳዳጊዬ ማንም ሰው አይቷት በቀላሉ የሚወዳት ሰው

ነች…ምንም ነገር ብትነግርህ ታምናታለህ..አንደበቷ ቁጥብና በጣም ልስልስ ነው…ትንኝ

ለመግደል ስትንቀጠቀጥ እንድተመለከት ታደርግሀለች…በጨለማ ግን የህፃን ልጅ አንገት

ጠምዝዞ ለመቀንጠስ ለሰከንድ አታመነታም…….፡፡

….ተመልካች ባለበት ልትጎርስ ያለችውን ጉርሻ ከአፎ ዳር በመመለስ ምንተማሪያም ብሎ

ደጇ ለመጣ ለማኝ ስታጎርስ ለተመልካች በማሳየት ማስደመም የተከነችበት ነው…..በስውር

እና በጨለማ ግን ስትዘርፍህና ባዶ ስታስቀርህ የውስጥ ፓንትህን እንኳን

አትተውልህም…..እጣትህ ላይ ያለውን ሶስት ግራም ቀለበት አልወልቅ ካላት ጣትህን

ቆርጣ ለመውሰድ አታመነታም…

‹‹አረ የሲሲል ማፍያ አደረግሻት እኮ…!!!››

‹‹የሲሲል ትላለህ..ከእነሱ ባትብስ አይደል…››

‹‹እና እናቴ ስትሞት እኔ የዘጠኝ አመት ልጅ ነበርኩ ብዬሀለው አይደል…ከሶስት ወር ብኃላ

ነበር ሌብነት ያሰተማራችኝ…››

‹‹ሌብንት ስትይ..?››

‹‹….ሌብነት ነዋ..እሷ መጀመሪያውኑ እኔን ላሳድግ ብላ ስትረከበኝ ያው እንዳነገርኩህ

በየዋህና አሳሳች ፊቷ እንባዋን እያረገፈች ጉያዋ ውስጥ ወሽቃኝ … ፀጉሬን

እያሻሸች‹‹የእናትዬዋ አደራ አለብኝ…..ባልወልዳትም ለእኔም ልጄ ነች…..ከአሁን ወዲያ

የምኖረው ለእሷ ነው….እናትዬዋ እህቴ ነበረች…ስትሞት አዳራ በምድር የሰጠውሽን

በሰማይ እቀበልሻለው ብላኛለች…ለሙት እህቴ የገባውትን ቃል አላጥፍም…ይሄንን በመሰሉ

የማንንም ልብ በቀላሉ የሚያባቡ ቃላትን በመጠቀም ብዙ ብዙ ነገር ቀባጥራ ነው

የተረከበቺኝ…..እሷ ግን እኔ ላይ ታላቅ እቅድ ነበራት….እኔን ለማሳደግ ስትረከብ አንድ

ለመተዳደሪያው ታክሲ እንደገዛ ሰው ነበር የተፍነከነከችው….››

‹‹….እና ሌባ አደረገችኝ ነው ምትይው....?››በገረሜታ እና ባለማመን ጠየቅኳት፡፡

‹‹ለዛውም ተራ ሌባ እንዳይመስልህ….እንዳልኩህ እናቴ ከሞተች ከሶስት ወር ቡኃላ ምን

እንዳረገች ታውቃለህ… ቴኮንዶ ት/ቤት አስገባችኝ..››

‹‹ቴኮንዶ ት/ ቤት..ለምን ..?››

‹‹..ተረጋጋ ልነግርህ አይደል…በየወሩ በደስታ ብር እየከፈለች …እያሞጋገሰች…..የእኔ ልጅ

እኮ የሴት ጀግና ነች..ወደፊት እንደ ነኪታ ጀግና አክተር ነው የምትሆነው…..(የዛን ሰሞን

ነኪታ የሚል ርዕስ ያለው ተከታታይ ፊልም እየተካራየች በየቀኑ ታሳየኝ ነበር)..ብቻ ለስድስት

ወር አስተማረችኝ..እኔም የልጅነትም ጉጉት አለመብሰልም ታክሎበት ከልቤ እሷ

ከምትፈልገው በላይ ውጤታማ ስልጠና ወስጄ አጠናቀቅኩ…

‹‹እሺ ከዛስ..?››

‹‹ከዛማ አንድ ደምበኛዋ የሆነ .. ኮማንዶ ሆኖ ለአመታት በውትድርና ካገለገለበት

በስነምግባር ተባሮ ማጅራት በመምታት እና በመዝረፍ ለሚተዳደር ሰው ሰጠቺኝ….››

‹‹ለምን…. ..?ሰጠቺኝ ስትይ እንዴት…..?››

‹‹…ለሌላ ስልጠና ..… አየህ ቴኮንዶ ቤት የተማርኩት ሰውነቴን እንደፈለኩ ማዘዝ ለካራቴ

እግሮቼን ማወናጨፍ..እራሴን ከጥቃት መከላከል አስፈላጊም ሲሆን መልሶ ማጥቃትን

የመሳሰሉትን ስፖርታዊ የሆኑ ተራ ስልጠናዎችን ነው..እሱ ጋር ግን

‹‹…እሱ ጋር ምን..?››.እስክትነግርኝ መታገስ አልቻልኩም ….ይሄን ታሪክም መኪና እየነዱ

አልነበረም ማዳመጥ…..ብቻ እንዳልላተምና ታሪኩም ሳያልቅ የእኔው ታሪክ እንዳያልቅ…

‹‹እሱም ተግባራዊ የሆኑ ወታደራዊ ስልጠናዎች…ካዛም አልፎ ሌባዊ ስልጠናዎች››

‹‹እስቲ አብራሪልኝ…..?››በአስራ ምናምን የፖሊስነት ህይወቴ ያላገጠሙኝንና ምን አልባት

በውጭ በፊልም ብቻ አይቻቸው ማውቃቸውን ታሪኮች ነው እያሰማቺኝ ያለችው..፡፡.

‹‹..ሳንጃ አጠቃቀም… አጥር መዝለል…በጭለማ ማጥቃት…..ማንኛውንም ቁልፍ

መክፈት……..ይሄንን እንዲያስተምረኝ ብዙ ገንዘብ ከፍላዋለች…ከዛም አልፎ አብራው ሁሉ

እስከመተኛት ደርሳለች…››

‹‹ከዛስ....?››

‹‹ከዛም ከእሱ ጋር ለሶስት ወር ያህል ከሰለጠንኩ ቡኃላ ለሌላ ሞጭላፋ ሰጠችኝ..››

‹‹ለሌላ ሞጭላፊ ስትይ..?››

‹‹ለኪስ አውላቂ … እሱ ደግሞ እንዴት ከሰው ኪስ በቅልጥፍና ቦርሳና የመሳሰሉትን ጠቃሚ

ዕቃዎች ማውጣት እንደምችል….ሞባይል እንዴት መመንተፈ እንደሚቻል ..ሀብል እና

ጌጣጌጥ እንዴት መንጭቆ ማምለጥ እንደሚቻል አስተማረኝ…….››

‹‹እሺ ከዛስ ..?››

‹‹ከዛማ እልል ያልኩ ሌባ ሆንኩአ..በአስር አመቴ ሞጭላፊ ሌባ ሆንኩ…ያው ሽርሙጣ

ከመሆኔ በፊት ሌባ ነበርኩ ያልኩህ ለዚህ ነው..

‹‹አረ በፈጠሪ…እናትሽን መግደሏ ሳያንሳት…አንቺ ላይ እንዲህ ታደርጋለች…..?ምን አይነት

ጭካኔ ነው…....?››

‹‹አይ እናቴን የመግደሏን ምክንያት እረዳታለው…የሚያም ቢሆንም ይቅር እላታለው…..በእኔ

ላይ ስላደረገችው ነገር ግን ፈጽሞ ፈፅሞ ይቅር ልላት አልችልም..››

‹‹አው …እንደዚህ አይነት በደልን ይቅር ለማለት የክርስቶስን አይነት ልብ

ያስፈልጋል..››አልኩ እኔም በሀሳቧ ተስማምቼ

‹‹አዎ እውነትህን ነው..እኔ ደግሞ ጂጂ እንጂ ኢየሱስ አይደለውም…ስለዚህ ከእኔ ይቅርታ

አታገኝም…፡፡ይገርምሀል መጀመሪያ ሌብነት ስታስለምደኝ ምን እንዳደረገች ታውቃለህ…

የባንክ ደብተር በስሞ አወጣችና…ደሀ ሆነሽ ልክ እንደእናትሽ የድህነት ኑሮ መኖር

የለብሽም…ለማንም ሰው ማዘን፤ ለማንም ሰው መራራት የለብሽም…በዚህ አለም ላይ

ከገንዘብ ውጭ ምንም ጠቃሚ ነገር የለም…ገንዘብ ሲኖርሽ ማንም ሰው ይወድሻል …ማንም

ሰው ያከብርሻል…..የተናገርሽው ...ቀልድ እርባን ሌለው ቢሆንም የከበቡሽ ሁሉ

ይገለፍጡልሻል….ትዕዛዝሽ ህገወጥ እና አደጋ ውስጥ የሚያስገባ ቢሆንም ማንም ለምን

ብሎ ሳይጠይቅ ይተገበራዋል…..ስለዚህ ለገንዘብ ምንም አይነት መስዋዕትነት ቢከፈልለት

ተገቢ ነው…ለአንድ ቦርሳ ብር አንድ አዳራሽ ሰው መጨረስ ካለብሽ እንዳታቅማሚ….ሰው

አንቺ ገደልሽውም አልገደልሺውም አንድ ቀን መሞቱ አይቀርም …………..የዚህ አገር ህዝብ

አንቺ ዘረፍሺውም አልዘረፍሺውም ከችግር እና ከችጋር አይላቀቅም..ስለዚህ ለማንም

ለምንም አትዘኚ…የዚህችን ከተማ ኑዋሪዎችን ልክ እንደሰፈር ተልከስካሽ ውሻ ቁጠሪያቸው

………..ነዝናዞች እና ተናካሾች ናቸው....ስለዚህ በመርዝ ብትጨርሺያቸው….በሳንጃ

ብትዘነጥያቸው…. በሽጉጥ ግንባራቸውን ብትነድያቸው ምንም እንዳይፀፅትሽ…ምንም ፡፡ ልክ

መዘጋጃ ከተማዋን ለማጽዳት ሲፈልግ በመርዝ አንደሚያስወግዳቸው ባለቤት አልባ ውሾች

አንቺም እንደዛ እያደረግሽ እንደሆነ አስቢው…ከተማዋን እያፀዳሻት እንደሆነ….፡፡

እኚህና የመሳሰሉትን ስብከቶች በየቀኑ ነው የሚትሰብከኝ..በህጻንነት አዕምሮዬ ሰማዋት

..አመንኳት፤ ተቀበልኳት እንዳለችኝ መሆን ጀመርኩ..፡፡የባንክ ደብተር ከፈትኩልሽ አለችና

የኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ደብተር አሳየቺኝ….18 ዓመት ሲሞላሽ በስምሽ ቀይርልሻለው…..

አሁን ግን ስለማይቻል በእኔ ስም ይሁንልሽ አለቺኝ….አመንኮት…፡፡በዛ ትህትና በዛ እንባ

በታጀበ ምክር እየነገረቺኝ ባላምናት ነበር የሚገርመው….

እና እየዘረፍኩ እያመጣው ስሰጣት እንዳለችው ባንክ ደብተር ውስጥ ስትከትልኝ..አንድ ሺ

ሆነልኝ ስል….አስር ሺ ደረሰልኝ ስል…መቶ ሺ ሆነልኝ ስል አምስት መቶ ሲሆንልኝ…..በቃ

እንዳለችው ሀብታም የሆንኩ መሰለኝ……..አለምን ሁሉ በቁጥጥሬ ስራ ያስገባው

መሰለኝ..ድህነትን እየተበቀልኩ እንዳለው ተሰማኝ…..ምን እንደምገዛ ምን እንደማደርግበት

ማለም ጀመርኩ እሷ ግን ይህቺማ ምን አላት..ሀብታም ከሆንሽ በጣም ሀብታም መሆን ነው

ያለብሽ ትለኝ ነበር…….ሽርሙጥናውንም አስጀመረቺኝ…በቅንጅት፡፡…ሽርሙጥናና

ሌብነት…..ከሁለት አመት በፊት ብሩ በጣም ሲጠራቀም እቤት እንግዛ አለቺኝ ..ምንም

ሳላቅማማ እሺ አልኳት…ሲ ኤም ሲ አካባቢ በ5 ሚሊዬን ብር ገዛች……አከራየችው….የወ

ደፊት ቤትሽ ነው አለቺኝ….፡፡የዛሬ አመት በአንድ ሚሊዬን ብር ሚኒባስ እንግዛ

አለቺኝ..ገዛን…..››

‹‹ቆይ በማን ስም ነው ሚገዛው...?››

‹‹በራሷ ነዋ..እኔማ 18 ዓመት መች ሞላኝ…በእሷ ስም ሊሆንና 18 ዓመት ሲሞላኝ

እንደምታዘዋውርልኝ ነግራኝ በራሷ ስም ነው የገዛችው… ግን ይገርምሀል በተለይ ሚኒባሱ

ሲገዛ አስራ ስምንት አመት ሞልቶኝ ነበር..እሷ ግን ወራቶች ይቀሩሻል አለቺኝ››

‹‹ቆይ ግን አንድ ያልገባኝ ነገር …ይሄን …ይ ሁሉን ነገር ስትዘርፊና ስትሰርቂ ተይዘሽ

አታውቂም.....?››

‹‹እሱማ የት ይቀራል…. አልፎ አልፎ ቢሆንም ያጋጥማል…ግን የዋዛ አትምሰልህ …ከሁለት

ቀን በላይ እስር ቤት እንዳሳልፍ አድርጋ አታውቅም….በፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ወሳኝ ወሳኝ

ሰዎች አሏት…በዛ ላይ እንዲዚያ አይነት ክፍ ቀን ሲመጣ ከተጠራቀመው ብር መዥረጥ

አድርጋ በማውጣት ለማከፋፈል አትሰንፍም…ወዲህ ወዲያ ብላ ወዲያው ነጻ ታደርገኛለች››

‹‹በእወነት ለማመን ነው የሚያስቸግረው…›››አልኩ …ለማመን የሚያስቸግረው የሰማውን

ታሪክ ብቻ አይደለም….አንቦ መድረሻችንም ጭምር እንጂ….

‹‹አንቦ ይህቺ ነች…....?››ብላ ጠየቀችኝ ድንገት ከታሪኩ ወጥታ

‹‹አዎ ..አንቦ..የደም ገንቦ የተባለቺው ይህቺ ነች››

‹‹ይገርማል…አልጠበቅኩም››

‹‹ትልቅ ሆነችብሽ አይደል…...?አሪፍ ከተማ ነች››

‹‹አይ ትልቅ ሆናብኝ አይደለም ….እንደውም በተቃራኒው ነው የተሰማኝ..፡፡እንዲያ የስሞ

ገናናነት እና የግርማ ሞገሷ አስፈሪነት አሁን ከማየው ጋር …አረ አይመጣጠንም፡፡››

መቼስ ይመለከተኛል ብዬ ማብራራቱን ቀጠልኩ‹‹አየሽ አንቦ የዕድሜዋን ያህል አላዳገችም

ይሆናል…እንደሚገባት በመሰረተልማት አለማችም ይሆናል፣ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችና አጓጊ

ሞሎች አልተገነቡባትም ይኆናል..ግን ጥሩው ነገር ሰው አላት….አንቦ ትላልቅ ልብ ያላቸው

ኑዋሪዎች አሏት…ለነጻነት መዘመር የማይደክማቸው..ለፍትህ መታገል የማይሰለቻቸው

ኑዋሪች ባለቤት ነች….፡፡.ልባቸው ያልደከመ ወኔያቸው ያልተሰለበባቸው ኑዋሪዎች

መኖሪያ..ይሄ ነው ትልቅ ያደረጋት..ይሄ ነው ግርማ ሞገሶ አስፈሪ ስሞ በአፍ የሚሞላ

የሆነችው……፡፡የአንድን ሀገር ትልቅነት መጠን መለኪያ የድንጋይ ድርድር እና የመስታወት

ቁልል አይደለም…የአንድ ሀገር ወይም ከተማ ትልቅነት የሚመነጨው ከኑዋሪዎቾ የአንድነት

ጥምረት፤መንፈሳዊ እሴት፤ ቁሳዊና ባህላዊ ሀብት ነው ፡፡ዋናው ሰው ነው….ሌላው ነገር

ለሰው ምቾት… ለሰው መጠቀሚያ የተፈጠረ ወይም የተሰራ ነገር ነው….ስለዚህ ትልቅ

ሀገር ማለት ትልልቅ ልብ ያላቸው ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ማለት ነው እንጂ ትልልቅ ህንፃ

ያላበት ,ማለት አይደለም፡፡

‹‹እሺ ገብቶኛል››

‹‹እወነቴን እኮ ነው››

‹‹እኮ ምን አልኩ… ማብራሪያህን ተቀብያለው››አለች እየፈገገች

‹‹ጥሩ አልኩና››የ መኪናዬን አፍንጫ ወደ ደራራ ሆቴል አዙሬ ወደ ግቢው ስት አስገባውና

አቆምኩ…..

‹‹ፈጥነን ደረስን ..››

‹‹አዎ ፈጥነናል….አሁን ምሳ እንብላ››

‹‹እንዳልክ እንብላና የማይቀረውን መለያየት እንለያይ ››አለችኝ ቅሬታ ባዘለ ድምጽ….

ከመኪናው ወርደን ወደ ምግብ አዳራሹ አመራን

አይ ነገሮችን እንደዚህ በእንጥልጥል ትተሽማ መለያየት የለም ምሳ እንብላና ቢያንስ አንድ

ሰዐት ሆነ ቦታ ተቀምጠን የጀመርሽውን ታክ ትጨርሺልኛለስ››

‹‹አንድ ሰዓት….››

ይመሽብሀል ያለቺኝ መስሎኝ‹‹አዎ አንድ ሰዓት ..ግዴለሽም እደርሳለው›››አልኳት

‹‹መድረሱ አይደለም ..የጀመርኩልህን ታሪክ ለመጨረስ ቢያንስ አንድ አመት አብሬህ መኖር

አለብኝ››

‹‹እና አብረሺኝም ልትኖሪ አሰብሽ እንዴ.....? ››…ተሳሳቅን.......ምሳችንን በልተን እስክንጨርስ ያወራናቸ ወሬዎች ቁም ነገር የሌላቸውና ቀልዳ ቀልዶች

ስለሆኑ ዘልዬቸዋው…ምግብን አጠናቀን ሂሳብ ከፍለን የምግብ አዳራሹን በመልቀቅ

እየወጣን እያለ አንድ ሀሳብ በአዕመሮዬ መጣልኝ..ወደ መኪናችን መሄድ ሲገባን ወደ ሌላ

አቅጣጫ ይዤት ሄድኩ

‹‹እንዴ!!! ወዴየት ነው?››አለችኝ ግራ በመጋት

‹‹ዝም ብለሽ ተከተይኝ›››.

‹‹እሱማ ምን አንዳስነካሀኝ ባለውቅም ይሄው ስንት ቀን ሙሉ ዝም ብዬ እየተከተልኩህ

ነው››አለቺኝ…ምን እንደነካኝ ነው የለችው..?እንደውም በተቃራኒው እኔንስ ምን ብታስነካኝ

ነው? እንዲህ ሙጫ የሆንኩባት በማለት እራሴን በጣም እየታዘብኩት ነው፡፡

ቀጥታ ይዤት የሄድኩት ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ነው››‹‹አልጋ አለ? ››እንግዳ ተቀባዬን

ጠየቅኳት

‹‹አለ››መለሰቺልኝ

‹‹አንድ ንጽህ አልጋ ስጪን‹››ጂጂ በፍዘት አፍጥጠ እያየችኝ ነው…የተጠየቅኩትን ብር ከፍዬ

ቁልፍ ተቀብዬ ወደ ተባለው መኝታ ክፍል ይዤት መንገዴን ቀጠልኩ……

‹‹ምን እያደረግክ እንደሆነ ግልጽ አልሆነልኝም?››

‹‹ለአንድ ሰዕት ያህል አብረን እንቆያለን ብዬሽ አልነበር… የጀመርሺልኝን ታሪክ ነግረሺኝ

ቢያንስ የተወሰነ መቆጫ ማበጀት አለብሽ…ሰስፔንስ እንደሆንኩ ልለይሽ አልችልም››

‹‹ታዲዬ ለአንድ ሰዓት ነው ቤርጎ የምትይዘው..?የሆነ ካፌ እኮ ቁጭ ብለን ማውራት

እንችላለን››

‹‹አረ የምን ካፌ..ምን አንከራተተን..ቤርጎችን አረፍ ብለን ምንም አይነት እይታም ሆነ ምንም

አይነት ድምጽ ሳይረብሸን እንድታወሪኝ ነው የምፈልገው…እኔም ባልተናጠበ ተመስጦ

ላዳምጥሽ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንዳልክ..ግን የምነግርህ ከእኔ የባስክ እብድ እንደሆንክ ነው ››አለቺኝ

…..ደርሰን ከፍተን ገባንና ከውስጥ ቆለፍነው፡፡ከላይ ለብሼ የነበረውን ጃኬት አወለቅኩና

ጠረጵዛ ላይ አስቀመጥኩት.. ጫማዬን አወለቅኩ..ከዛ አልጋው ላይ ወጥቼ ተዘረርኩ….እሷ

ግን አሁንም ግራ በተጋባ ሁኔታ የክፍሉ መሀል እምብር አካባቢ ተገትራ ቁልቁል እያየቺኝ

ነው

‹‹ምነው ፈራሺኝ እንዴ..?ትናንትና አብረሺኝ ያደርሽው ልጅ ነኝ እሺ›› አልኳት

‹‹…ጉረኛ ..ፈርዶባችሁ ወንዶች ስትባሉ የተቀመማችሁበት አፈር መሰለኝ ጉረኞች ናችሁ…

እራሳችሁን አንበሳ አድርጋችሁ መሳል ትወዳላችሁ..እናንተ ብቻ ምትፈሩ..እናንተ ብቻ

ምታርበደብዱ…አሁን አንተን ምንህን እፈራለው…..ካንተ ይልቅ መንግስት ያስታጠቀህ

ሽጉጥህ ያስፈራል››

‹‹ታዲያ ካልፈራሺም ምን ይገትርሻል….ነይና ጋደም በያ…. ነው ወይስ አልደከመሽም?››

‹‹ደክሞኛል.. ግን ከዛም በላይ ሞቆኛል.. ገላዬን ልለቃለቅ ወይስ ይቅርብኝ? ብዬ

በማሰላሰል ላይ ነበርኩ››

‹‹እንደዛ ከሆነማ ብትታጠቢ ነው ሚሻልሽ..››

‹‹አዎ እወነትህን ነው እንደዛ ይሻለኛል..››አለችና ወንበር ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን ፎጣ

አንስታ ወደ ሻወር ቤት ገባች….

እኔም ስለ እሷ እያሰብኩ….ስለ እራሴም እያሰብኩ…እንዴት እንደተገናኘን እያሰላሰልኩ…

እስከአሁን የነገረቺኝን ተአምራዊ ታሪክ እያሰብኩ..አሁን ሻወር ወስዳ ስትመጣ ምን

ልትነግረኝ እንደምትችል እየገመትኩ…የእኔን እና የእሷን መድረሻ ወይም መለያያ የት ጋር

እንደሆነ በፍራቻም በጉጉትም እየገመትኩ …ሿ..…ሿ……ሿ. የሚለውን ከሻወሩ

እየተስፈነጠረ የሚንዠቀዠቀውን የውሀ መውረድ ድምጻ እየሰማው ጠበቅኳት

….. ረዥም ለሚመስሉ ግን ጥቂት ለሆኑ ደቂቆች የሻወሩን በራፍ ላይ አይኖቼን ተክዬ

ጠበቅኳት…. ለብሳ የገባችውን ልብስ አወላለቀ በእጆቾ እንዳንጠለጠለች ግማሽ

ገላዋን..ከወገቧ በታች በፎጣው በማገልደም… ..የተቀረውን ግምሽ ገላ ማለት ከወገቧ

በላይ የሆነ አካሏን እርቃን ጥላ መጣች…

..በተኛውበት አፌን ከፈትኩ….ይሄንን ገላ ማታም አይቼዋለው…ግን ስካርና ድካም ላይ

ስለነበርኩ…ደግሞም በደብዛዛ ብርሀን ስለነበር እንዲህ አላተኮርኩበትም ነበር

….ባተኩርበትም እንደዚህ አልታየኝም ነበር….በተኛውበት ብቻ ፈዝዤ እና አፌን ከፍቼ

አልተውኩም…. ቀስ ብዬ ተነሳውና ቁጭ አልኩ..ወደ እኔ እስክትመጣ አልጠበቅኳትም….

አልጋውን ለቅቄ ተነሳውና ወለሉ ላይ ቆምኩ… ወደ እሷ መራመድ ጀመርኩ…. ወደ አልጋው

ልትመጣ መንገድ የጀመረችው ልጅ በእኔ እንቅስቃሴ እና ሁኔታ ግራ በመጋባት እርምጃዋን

ገታ ባለችበት ተገተረች…..ተጠጋዋት…በጣም ተጠጋዋት …. ከሰውነቷ ለመጣበቅ ወይም

ለመላተም ምን አልባት አስር ወይም አምስት ሳ.ሜ ክፍተት ብቻ ሲቀረኝ ቆምኩ…አይኖቼ

የተጋለጠውን የሰውነቷን ክፍል እንደኤክስ ሬይ ሰርስሬ እያተመለከትኳት ነው..ድንዝዝ

ብያለው..ማደርገውንም ማስበውንም አላውቅም….

ቀኝ እጄን አነሳውና ትከሻዋ ላይ አሳራፍኩ …. ቀስ ብዬ ዳሰስኳት…ከዛ አነሳውና በእንብርቷ

እነ በጡቷ መካከል ያለው አካሏ አካባቢ ጣቶቼን አማላለስኳቸው…በድን ሆና በፍዘት

የማደርገውን እየተመለከተች ነው..ያለምን ተቃውሞ ያለምንም ትብብር…. ልክ ሰዓሊ ቀርፆ

ለኤግዚብሽን እይታ ያቀረበው በድን ሀውልት መስላ…ከዛ እግሮቼን አንቃሳቀስኩና ወደ ኃላዋ

ዞርኩ..ጀርባዋን ከመሀከል ጀምሬ እስከ ቂጧ ስንጥቅ ድረስ ዳሰስኳት…..

‹‹በተሰቀለው ….!!!ምን አይነት ጉድ ነው?››በጣም በደከመ እና በሀዘን ስብርብር ባለ

ድምጽ ጠየቅኳት

‹‹አይ …ቀላል እኮ ነው››

‹‹አይደለም እኔ ቆንጆ …ብዙ ቶርቸር የሆኑ ሽብረተኛች…ብዙ ሰውነታቸው የተተለተለ

ፖለቲከኛች…ብዙ ጠባሳና ቁስለት የደረሰባቸው ወንጀለኞች አይቼ አውቃለው..ግን አንድ

ሴት ለዛውም የአስራ ዘጠኝ አመት ልጅ እንደዚህ ሰውነቷ ተተልትሎ..እንደዚህ ጠባሳ

በጠባሳ… እንደዚህ ስፌት በስፌት ሆኖ አይቼ አላውቅም…››የምሬን ነው አንዲት ሴት

በምንም አይነት ስቃይ በምን አይነት መከራ ውስጥ ብታልፍ ነው ይሄን ሁሉ የስቃ

ማስታወሻ የሆኑ ጠባሳዎችን በአካሏ ላይ ሊኖር የሚቻለው….

‹‹ምን ታደርገዋለህ.. ግን ይገርምሀል…አሁን በአይንህ ከምታየው ጠባሳ በብዙ እጥፍ

የሚልቅ ህመም ያለው ጠባሳ በውስጤ ነው ያለው..እነዚህ የምታያቸው እነዚህ

የምትዳስሳቸው ምልክታቸውን ብቻ ነው .. ህመም የላቸውም..ድነውልኛል…የማይታየው

ስውሩ የውስጤ ጠባሳ ግን ትኩስ ቁስል ነው….በየቀኑ ይቆጠቁጠኛል….በየጊዜው

እያመረቀዘ ሰው መሆኔን እንድጠየፍ ያደረገኛል….አዝኜ እንዳላለቅስ እና ተደስቼ እንዳልስቅ

ሆኜያለው››

‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው የእኔ ቆንጆ …አልገባኝም…?››

‹‹አንድ በእኔ እድሜ ያለች ሴት ስትከፋ በቀላሉ ስቅስቅ ብላ ማልቀስና ..ስትደሰት ደግሞ

በቀላሉ ክትክት ብላ መሳቅ ትችላለች…ይህ ደግሞ የሰው ልጀ ተፈጥሮአዊ ባህሪ

ነው…...የአንድ ሰው በቀላሉ ማልቀስ እና በቀላሉ መሳቅ አለመቻሉ እንደብስለት እና

ጥንካሬ ይታሰባል…ግን የሰውዬው ስነልቦናው እየቆሰለ እና አየተመመ የመሄዱ ምልክት

ነው…የመደንዘዝ እና በህይወት ጣዕም ከማጣት መንሴው የተወለደ በሽታ ነው…የስሜት

መድረቅ እና የደስታ መንጠፍ ምልክት ነው፡፡

ስለዚህ የሰው ልጅ እንደእኔ ማልቀስ ካቃተው እና መሳቅም ከቸገረው በቃ በጣም ታሞል

ማለት ነው ……ህይወትን የሚያጣጥምበት የስሜት ምላሱ ደንዝዞል ማለት ነው….ኩላሊቱ

ፌል እንዳደረገ ሰው..ወይም ወይም ጉበቱ እንደተበላሸበት ሰው…ከፍተኛ ህክምና

ያስፈልገዋል…፡፡በጣም ሊታዘንለት እና እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል…እኔ እንደዛ ነው

ሆንኩት…. የውስጤ ጠባሳና ቁስለት ከመብዛቱ የተነሳ ሳቄ አርቴፊሻል ለቅሶዬ የማስመሰል

ከኆነ አመታቶች ነጉደዋል…..በነገሮች የመደሰት ስሜቴን በቻ ሳይሆን በነገሮች የማዘን

ሰዋዊ ባህሪዬንም ነው የተሰለብኩት…››

‹‹ለመሆኑ ይሄን ሁሉ እንዴት ቻልሽው..እንዴትስ በህይወት ተረፍሽ?››

…አገልድማ የነበረችውን ፎጣ ፈታችና ወደ ታች ለቀቀችውና ሙሉ እርቃኗን ፊት ለፊቴ

ቆመች‹‹..ማየትህ ካልቀረ በደንብ እይ ..አየህ ባቴ ላይ ያለውን ጠባሳ ..ሽጉጥ ነው..ሁለት

ጥይቶች ናቸው በዚህ ተለቀውብኝ… በዚህ ጋር በህክምና እርዳታ ተቀዶ የወጣልኝ…እዚህስ

ይታይሀል በጡቴ እና በእንብርቴ መካከል ያለው የጩቤ ቅድ …..የዚህን ታሪክ ልንገርህ

መሰለኝ

….የዛሬ ሁለት አመት ነው..በወቅቱ አደገኛ ሌባም ሸርሙጣም በነበርኩበት ጊዜ …አንዱ

የፔያሳ አራዳና ጉልቤ ነኝ በሚል እራሱን አንደጋንግስተር የሚቆጥር ወጠምሻ ያስቸግረኝ

ጀመር ..ከሚስቶቼ አንዷ ካልሆንሽ አለኝ…እኔ ደግሞ እንደዛ አይነት ሙድ አይመቸኝም

….በዛ ላይ ልጁ እንዲሁ ጉራውም መልኩም ያስጠላኝ ነበር…አንድ ቀን ታዲያ በአጃቢዎቹ

ተከቦ ወደአለውበት መጣና …ተለፋደደብኝ..ተወኝ አልኩት ..ሊያስፈራራኝ ሞከረ …

ያንቋሽሸኝም ጀመር

‹‹በጣም አስጠሊታ ሸርሙጣ የሸርሙጣ ልጅ እኮ ነሽ…የማላቅሽ መሰለሽ እንዴ?››አለኝ

‹‹ታዲያ ሸርሙጣ ..ለዛውም የሻርሙጣ ልጅ ምን ያደርግልሀል?›› አልኩት በትዕግስት

‹‹ያው ልተባበርሽ ብዬ ነው..በዛ ላይ ከእኔ ጋር መሆን ላንቺም ክብር ነው..እንደሌሎቹ

ሚስቶቼ አንቺም የተፈራሽና የተከበርሽ ትሆኚያለሽ››አለኝ በመንጠባረር

ከዛ እኔም ደሜ ፈላና ልክ ልኩን እነግረው ጀመር…‹‹ለራስህ ክብር ሳይኖርህ ለሌላ

ከየትአባትህ አምጥተህ ነው ክብር የምትሰጠው?›› አልኩት..

‹‹እንደውም ትቼዋለው እራስሽ አውጣኝ ብልሽ ለልመና ስሬ እንድትንበረከኪ ነው

የማደርግሽ››አለኝ

‹‹አኔ ደግሞ ለአንተ ከምሰጥ ..ለዚህ ውሻህ ብሰጥ ይሻለኛል›› አልኩት ስሩ ጭራውን

የሚቆላውን የገዛ ውሻውን እየጠቆምኩ

‹‹እንዴት?›› አለኝ

‹‹ካንተ ውሻህ ያምራል..ካንተ ውሻህ ያስባል..ካንተ ውሻህ ተወዳጅ ነው››አልኩት… በጣም

አበሳጭቶኝና ቁም ስቅሌን አሳይቶኝ ስለነበረ ላሸማቅቀው እና ላዋርደው ስለፈለግኩ ነበር

እንደዛ የተናገርኩት..እንዲተወኝ አጠገቤ እንዳይደርስ ስለፈለኩ … ተስፋ ላስቆርጠው፡፡

እሱ ግን በተቃራኒው እልክ ያዘው..እንዴት በሴት እሰደባለው…?እንዴት በሴት እንዲህ

እጠቃለው? አለ…

‹‹በሶስት ቀን ውስጥ አንቺን አወጣሻለው››ብሎ በጓደኞቹ ፊት ፎከረ

እኔም ‹‹አንተ ችለህ በግድም ሆነ በውድ እኔን ካወጣሀኝ ..በፍቃደኝነት ለውሻህም

እሰጠዋለው..ከዛም ጀግና ወንድ መሆንህን እየዞርኩ ለድፍን ፒያሳ

እመሰክርልሀለው››አልኩት

‹‹እኔ ደግሞ ያን ማድረግ ካቃተኝ ..ቀሚስ ለብሼ በዚህ ግዛቴ በሆነው ፒያሳ ውስጥ በቀን

እዞራለው›› አለ…ልክ እንደሰሜን ኮሪያ እና እንደአሜሪካ በምስክሮች ፊት ተዛዝተን

ተለያየን… ያዳመጡት ሁሉ ለእኔ ሰግተውና አዝነውልኝ..በድፍረቴ እና በንግግሬ ጤንነቴን

ተጠራጥረው ተበተኑ…

እስከአሁን እያወራቺኝ ያለችው እርቃኗን ፊት ለፊቴ እንደቆመች ነው….ግን ለውጥ የለውም

..እኔ አሁን ልቤ ያለው ሴትነቷ ላይ አይደለም…መላ ቀልቤ ያለው ጣባሳዋ ላይ ነው… ያለፈ

የመከራ የህይወት አሻሯዋ ላይ ነው…ሌላ ሴት ብትሆን እንዲህ አይነት ታሪኳን አይደለም

ተራ የመከዳት የፍቅር ህይወቷን ስታወራ እንኳን እየተንሰቀሰቀች ነው..ይህቺ ግን ሌላ

የማታውቀው ሰው ታሪክ ወይንም ከመጻሀፍ ያነበበችውን የፈጠራ ልብ ወለድ የምትተርክ

ነው የምትመስለው..እወነትም እሷ እራሷ እንዳለችው የመሳቅም ሆነ የማልቀስ ስሜቷን

ተቀምታለች…

ያለ ስሜት መደበላለቅ ታሪኳን ቀጥላለች

… እንደዛ ከተዛዛትን ከሁለት ቀን ቡኃላ ስራ ወጥቼ ነበር ..ማለት አንድ ሰው አሪፍ ጨላ

ያጨቀ ሰካራም ልሰራው እየተከታተልኩት… እየተከታተልኩት…ጨለማ አካባቢ ገባብኝ…ሁሌ

የማደርገው ሰለሆነ ተከትዬው ገባው…፡፡ለካ ተሸውጄ ነበር..የምበላበት ሳይሆን የምበላበት

ቀን ነበር..ያ ሰውዬ ብር እያሳኝ የሰከረ መስሎ ወደ ወጥመድ ነበር ይዞኝ የገባው…››

‹‹የምን ወጥመድ .. ?››

‹‹ጨለማ ውስጥ ..ያ ጀግና ነኝ ባይ አንድ የአስራ ሰባት አመት ሴት ለማጥቃት..ሶስት ቦዲ

ጋርዶችን ይዞ እየጠበቀኝ ነበር..ሰውዬው ተሰራቂ መስሎ ወስዶ ለእነሱ እዲያስረክበኝ

በእነሱ ተቀጥሮ እራቅ ካለ ሰፈር የመጣ ወመኔ ነበር››

‹‹እሺ ከዛስ..?››ትንፋሼ እንዳትቆረጠጥ ፈራው

ከዛማ ሶስቱም አሽከሮቹ ከበቡኝ …እሱ ከፊት ለፊቴ ገጭ አለ

‹‹እሺ ትቢተኛዋ..አሁንስ በፍቃደኝነት ትሰጪኝለሽ ወይንስ በግድ እናድርገው….? ››

‹‹የእውነት አደረግከው እንዴ….እኔ እኮ ስቀልድ ነበር››አልኩት ….ምን አልባት መሸወድ

ብችል ወይም የሆነ ተአምር እስኪፈጠር ትንፋሽ መግዣም ወይም ምን ማድረግ እንዳለብኝ

ማሰቢያ ደቂቆች ባገኝ እንኳን ብዬ

‹‹አረ ባክሽ!!! እዛ ሁሉ የሚያከብሩኝና ሚንቀጠቀጡልኝ ሰዎች መካከል የሞለጭሺኝ

ስትቀልጂ ነበር..በይ አሁን በግድ አናርገው ወይስ ..››

‹‹አረ አያስፈልገም..ተስማምቼያለው ..እንሂድ››አልኩት

‹‹ወዴት ነው የምትሄዱት?››ደንግጬ ጠየቅኳት

እሱም እንዳንተው ነበር የጠየቀኝ‹‹..ወዴት?›› ነበር ያለኝ

‹‹ወደ ቤትህ ወይም ወደ ቤርጎ ነዋ››ብዬ መለስኩለት…እንደዛ ካደረገ እና ሰው ወዳለበት

ቦታ ከደረስኩ አንድ ዘዴ ፈጥሬ ማምለጥ አያቅተኝም ብዬ በማስላት

እሱ ግን ተዘጋጅቶበት እና አስቦበት ስለመጣ አልተበገረልኝም‹‹አረ ባክሽ!!! ላንቺማ እንደዛ

አይነት ክብር አይገባሽም…እንደዛ አይነት ክብር ምትፈልጊ ቢሆን ያኔ መጀመሪያ ስጠይቅሽ

መስማማት ነበረብሽ…ይህቺን መንገድ ከእኔ በላይ አንቺ በደንብ ታውቂያታለሽ ..በዚህ ሰአት

ማንም መንገደኛ ወደእዚህ ደፍሮ ዝር አይልም…ስለዚህ እዚሁ ነው የማወጣሽ..እዚሁ

ይሄንን አጥር አስደግፌ..ከዛ ይታይሻል አይደል ውሻዬም አለ….የምትወጂውና

እንደምትሰጪው ቃል የገባሽለት ውሻዬ…ከውሻዬ በፊት ግን እነዚህም ጓደኞቼ

እንዲቀምሱሽ ፈቅድላቸዋለው…….ደግሞ ይሄንን ሀሉ ትእይንት በጨለማ መቅረፅ የሚችል

አሪፍ ካሜራ አዘጋጅተናል..ከዛ በኢንተርኔት እለቅልሽና ኢትዬጵያቷ ድንቅ የወሲብ ተዋናይ

ተብለሽ ትሸለሚያለሽ…››

‹‹ከዛስ እንዴት ሆነ››እኔው ነኝ በጉጉት ጣር ታፍኜ ምጠይቃት

‹‹ከዛማ ተግባር ለመሸጋገር ተጠጋኝና የለበስኩትን ቲሸርት በሁለት እጆቹ ይዞ ባለ በሌለ

ጉልበቱ ወደ ታች ሸረከትው…ለሁለት ተከፈለ…የተጋለጡትን ጡቶቼን አስፈሪ ቅዝቃዜ

ሲገርፋቸው ተሰማኝ…. በቃ ወሰንኩ …ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ እጅ ሰጥቶ ከመኖር ተስፋ

እያደረጉ ሲፋለሙ መሞት ይሻላል ብዬ ወሰንኩ… በውጊያ ሜዳ ላይ ንጉሱ ከወደቀ ሰራዊቱ

እንደሚበታተን ስለገባኝ ሳየስበው ዋናውን ጠላቴን ተስፈነጠርኩና በእግሮቹ መካከል

እግሮቼን ልኬ የተገተረ ብልቱን በጠነከረ እርግጫ እናጋውለት.አጓርቶ ከቆመበት ሽብርክ

ብሎ ቁጭ አለ…ወደ ሌላኛው ተስፈነጠርኩና አንገቱን ቆለፍኩት ..ሁለት ጣልኩ ማለት

ነው..ሶስተኛው ግን አገኘኝ …በቦክስ ናላዬን አፈረሰው…እኔም ስሰነዝር ብዙም በማይጎዳ

መልኩ አገኘውት ..ለሁለት አጣደፍኝ..አስከፍቼ መሮጥ እንዳለብኝ ወሰንኩ …ያሰብኩትን

ከማድረጌ በፊት አንደኛው አብረቅራቂ ገሀነማዊ ሳንጃ አንጀቴ ላይ ሲሳካ ነው ያየውት …

እዚህ ጋር ነው የሰካብኝ…በጣም በፍጥነት እና በየት በኩል መሮጥ እንዳለብኝ በማሰላሰል

የተዛናጋውበትን ሰከንድ ስለተጠቀመባት መከላከል እንኳን አልቻልኩም….የሚገርመው

ወግቶ ብቻ አልተወኝም የፋሲካ በግ ቆዳ እንደሚገፍ በግ አራጅ ወደ ታች ተረተረኝ…

ሽብርክ ብዬተዘረርኩኝ … ከዛ ዝልፍልፍ ብዬ ተኛው….እያየው አንጀቴ ተጎልጉሎ ተዘረገፈ …

‹‹ገደልካት ገደልካት..››ሲባባሉ ይሰማኛል..ከዛ ተደጋግፈውና ..የወደቁትን ጓደኞቻቸውንም

አዛዝለው እኔን እዛው ጭለማ ውስጥ ጥለውኝ ሔዱ

‹‹ጂጂሻ በዚህ ውሻ እጅማ መሞት አይመጥንሽ ..›› ስል ራሴን አበረታው…እራሴን

ላለመሳት መጣር ጀመርኩ …ደሜ ቱቦው እንደተሰበረ የውሀ መስመር

ይንፎለላል..እንደምንም ከጭለማው ወደ ብርሀኑ መውጣት አለብኝ..ወደ ዋናው

መንገድ..ለሁለት ተከፍሎ የተቀደደውን ቲሸርቴን እንደምንም አወለኩና የሞት ሞቴን በወገቤ

አዙሬ የተዘረገፈውን አንጀቴን አንድ ላይ ሰብሰብ አድርጎ እዲይዝልኝ በታቻለኝ ኃይል

አጥብቄ አሰርኩትና መሳብ ጀመርኩ …አንዴ በአንብርክክ አንዴ በእንፉቅቅ…ዘላለማዊ

በሚመስል አታካችና በስቃይ የተሞላ የእንፉቅቅ ጉዞ ብቻ የመንገዱ ጠርዝ ጋር መድረሴን

እና የመንገድ ብርሀን እንዳረፈብኝ ሳውቅ… ዣው አለብኝና በጨለማ ተዋጥኩ……እራሴን

ሳትኩ

በሶስተኛ ቀን ነው አፍንጫዬና አፌ ቱቦ ተሰንቅሮ.. እጄ ላይ ጉሉኮስ ተሰክቶ ሆስፒታል ክፍል

ውስጥ እራሴን ያገኘውት …መትረፌን አላመንኩም….ፖሊሶች እዛው ሆስፒታል መጥተው

ነበር ስለ አደጋው የማስታውሰውን የጠየቁኝ..ማንነታቸውን ነገርኮቸው..ሶስቱም ተለቅመው

ታሰሩ››

‹‹ሶስቱም ስትይ… አራት መስለውኝ ?››

‹‹ዋናውን ውሻማ አላሳሰርኩትም..እሱ በቦታው አልነበረም…እነሱ ናቸው የወጉኝ››አልኩና

እሱ እንዳይታሰር አደረግኩ

‹‹ምን አይነት ልጅ ነሽ…ዋናው እኮ እሱ ነው ..ወንጀለኛው እሱ ነው …..››አሁን ወደኃላ

ተመልሳ ታሪኩን የማስተካከል ስልጣን እዳላት ነገር ግራና ቀኝ ትከሻዋን ይዤ ፊት ለፊቴ

የተገተረው እርቃን ገላዋን በንዴት እና በቁጭት ናጥኩት

‹‹አዎ አውቃለው… ዋናው ወንጀለኛ እሱ መሆኑንና በዋናነትም መቀጣትም ያለበት እሱ

እንደሆነ አውቃለው…እንደዛም ስለሆነ ነው እንዲታሰር ያልፈለግኩት››

‹‹አልገባኝም…?››

‹‹አየህ ሶስቱ የእሱ ተላላኪዎችና ልክ እንደውሻው አድርጉ ያላቻውን በማድረግ እሱ

የሚሰጣቸውን ፍርፋሪ እየለቃቀሙ የሚኖሩ ናቸው.. ስለዚህ እኔ ከእነሱ ጉዳይ የለኘም..ለዛ

ነው ለህግ አሳልፌ የሰጠዋቸው…የእኔና እና የእሱ ጉዳይ ግን በህግ የሚፈታ አልነበረም…

እሱን በራሴ ፍርድ ቤት እራሴ ዳኛ ሆኜ በራሴ ህግ ነው ልቀጣው የፈለግኩት እናም እንደዛ

ነው ያደረግኩት..››

‹‹ምን አደረግሺው?››

‹‹ዝርዝሩ ምንም አያደርግልህም ..ግን እድሜ ልኩን እንደተሸማቀቀ እና ምነው ባላደረግኩት

ኖሮ እያለ ሲፀፀት እንዲኖር ነው የፈረድኩበት…ቀን ጠብቄ ከሶስት ወር ቡኃላ የዘር ፍሬውን

ነው ያፈረጥኩለት ..ዕድሜ ልኩን ሴት ስር እንዳይደርስ….ለእሱ የሴትን ገላ ማቀፍ.. በሴት

ፀጋ መደሰት አይገባውም……

ከዚህ በላይ ታሪኳን ለእኔ በመንገር ይበልጥ በውስጥ ሀዘኗ ምርቃዜ እንድትሰቃይ

አልፈለኩም ….ከአልጋው ላይ ያለውን አልጋ ልብስ አነሳውና እርቃን ሰውናቷን አለባስኳትና

አልጋው ላይ ይዤት ወጣው ..ይዤት ተኛው..በአልጋ ልብሱ አሷንም አራሴንም ጠቅልዬ ..፡፡

ባለፉት ሶስት ቀናቶች ካቀፍኳት በላይ አቅፌያት …አስከዛሬ ካዘንኩላት በላይ አዝኜላት…

በእነዚህ ሶስት ቀኖች ከወደድኳት በላይ ወድጄያለት ጭምቅ አድርጌት ውስጤ ሸሽጌት..

ሁሉን ነገር አረስቼ ዓለምን ሁሉ ዘንግቼ ስለእሷብቻ እያሰላሰልኩ በፀጥታ ውስጥ

ተዋጥኩ……እሷም በድካምና በእፎይታ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገባች….እኔም….ጩኸቷ ነው ከእንቅልፌ ያባነነኝ…‹‹ተነሳ..ተነሳ››

ወታደር አይደለው… ከመቅፅበት ከእንቅልፌ ተስፈንጥሬ ተነሳውና ወለሉ ላይ ቆምኩ….

‹‹….ምንድነው.?.ምን ሆነሽ…?››ጩኸቷ እና ድንጋጤዋ የሆነ በቃ መቼስ ይህቺ አመጽ

የማያጣት ከተማ ተድበለቅልቃለች ብላ ትንግረኛለች ብዬ እየጠበቅኩ ነው…..በአልጋ

ልብሱ ግማሽ እርቃኗን ቅጥ አልባ በሆነ ሁኔታ ለመሸፈን እየሞከረች ሞባይሏ ላይ አፍጥጣ

‹‹‹ቶሎ በል ልብስህን ልበስ…ፍጠን››

‹‹ምን ተፈጠረ..…?ተረጋጊና ንገሪኝ እንጂ››

‹‹አስር ሰዓት ሆኗል››

‹‹እና››

‹‹አስር ሰዓት ሆኗል እኮ ነው የምልህ…?››

‹‹እና አስር ሰዓት ምን አለ…?››ምንም ሊገለጽልኝ አልቻለም

‹‹ከአራት ሰዓት በላይ እኮ ነው የተኛነው…ገና አንቦ እኮ ነው ያለኸው››

‹‹.አረ ተረጋጊ …እኔ ደግሞ ምን ተፈጠረ ብዬ››

‹‹ይቅርታ ..አጉል አደረግኩህ…በል ተነስ እንውጣ ››ብላ ልብሷን ለመልበስ ስትሞክር

ጎተትኳትና

‹‹….ተመልሰሽ ተኚ››አልኳት

‹‹ለምን…?››

‹‹ዛሬ አልሄድም…ልጄ አያቷ ጋር ነች ..ለአንድ ቀን ምንም አትሆንም…አብረን እናድርና ነገ

ጥዋት እንለያያለን..አሁን እኔ ወጣ ብዬ አንድ ቦታ ደረስ እልና እመጣለው ..ሀያ ደቂቃ

ቢወስድብኝ ነው… እሰከዛ ተኝተሸ ጠብቂኝ››

‹‹አረ ተው አንተ ሰወ…አሁን ብትሄድ አትደርስም…?››

‹‹እርግጥ ይመሻል እንጂ ደርሳለው..ግን መሄድ አልፈልግም…ዛሬ ጥዬሽ አልሄድም››

‹‹አረ ባክህ… ዛሬ ጥለኸኝ ባትሄድ ነገ መሄድህ የት ይቀራል››

‹‹ቢሆንም ማምሻም እድሜ ነው ሲባል አልሰማሽም››

እሷ እንደአልኳት ወደ መኝታዋ ተመለሰችና ተኛች ….እኔም ጫማዬን አጠለቅኩና ጉንጯን

ስሜ ጥያት ወጣው..

.

.

.

.

ከሰላሳ ደቂቃ ቡኃላ ተመለስኩ

‹‹እንዴ !!!አሁንም ተኝተሻል…?››

‹‹ትዕዛዝ ላክብር ብዬ ነዋ….እኛ ኢትዬጵያውያን የፖሊስ ትዕዛዝ በፍራቻ ነው የምናከብረው

..ይህን መቼስ አንተም ታውቃለህ …?››

‹‹አረ አለውቅም… ምን ለማለት ፈልገሽ ነው.…?››.አልኳት….አልጋው ጠርዝ ላይ

በመቀመጥ…

‹‹ያው ህጻን ሆነን ወላጆቻችን የሆነ ጥፋት እንዳናጠፋ ሲፈልጉ ወይም ስራ አናሰራ ብለን

ስንረብሻቸው አደብ እንድንገዛ የሚያስፈራሩን ወይ በጅብ ነው ወይ በፖሊስ ነው››

‹‹አንቺ ጅብና ፖሊስ አንድ ናቸው እያልሽ ነው….››

‹አይ አልወጣኝም…እኔ ያልኩት ሁለቱም ማስፈራሪያዎች ናቸው ነው››

‹‹ሙጢ ነገር ነሽ …ለማንኛውም ተነሺ ልብስ ልበሺና ወጣ እንበል…››

‹‹እስከነተጠቀለለችበት አልጋ ልብስ አልጋውን ለቃ ወረደችና ልብሷ ወዳተቀመጠበት

ወንበር አመራች… በመጀመሪያ ሱሪያዋን አነሳች ..ልትለብስ››

‹‹አይ እሱን አትልበሺም››አልኳት

‹‹እና ምን ልልበስልህ……?ታጋች እኮ ነኝ ..በለበስኩት ልብስ ብቻ እንደጠለፍከኝ ዘነጋሀው

እንዴ…?››

‹‹አልዘነጋውትም….ግን ይሄንን ልበሺ ››ብዬ ይዤ የመጣውትን አረንጎዴ ፔስታል ከወለሉ

ላይ አንስቼ ወረወርኩላት ..በአንድ እጇ ቀለበችውና ወንበሩ ላይ ቁጭ ብላ በመደነቅ

ተሞልታ ከፈተችው…..ውስጡ ያለውን ነገር ጠረጵዛ ላይ ዘረገፈችው…በመጀመሪያ ያነሳችው

ቀሚሱን ነው….ባለ ሰማያው ቀለም ረጂም የእራት ቀሚስ ….በፍዘት አፎን ከፈታ ምንም

ሳትናገር ዝም ብላ ለበሰችው…...ከዛ ከገዛውላት ግማሽ ደርዘን ፓንቶች መካከል አንዱን

አነሳችና ፊት ለፊቴ ቆማ አጠለቀች…. በስተመጨረሻ ጫማውን አደረገች…... ተስተካክላ

ፊት ለፊቴ ቆመች..

ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየዋት ሁሉ ፍዝዝዝ ነው ያልኩት…..በጣም ነው የምታምረው…

በወንድነት እና በሴትነት መካከል የሚዋልል የነበረው አቋምና ባሀሪዋን ወደሴትነት እንዲህ

በግድም ቢኆን ስትሳብ ውበቷ በእጥፍ ጎላብኝ….

‹‹አረ በስመአብ…ይሄንን ሁሉ ውበት የት ደብቀሽው ነበር………?››

የእኔን ሙገሳ ችላ ብላ‹‹አንድ ሚስጥር ልንገርህ……?››

‹‹ንገሪኝ››

‹‹ማንም ወንድ እንዲህ አይነተ ስጦታ ገዝቶልኝ አያውቅም››

‹‹ይህንን ስለነገርሺኝ ደስ ብሎኛል››

‹‹ሌላም የምነግርህ አለኝ››

‹‹እየሰማው ነው››

‹‹ነፍስ ካወቅኩ ጊዜ አንስቶ ቀሚስ ለብሼ አላውቅም…ምንም ቀሚስ የለኝም….አውነቴን

ነው….አሁን ቀሚሱን ለብሼ ፊትህ ስቆም የተለየ ስሜት ነው የተሰማኝ›››

‹‹የተለየ ስሜት ስትይ..……?የደስታ ››

‹‹አይ እንደዛ ብቻ አይደለም …የሆነ የመረጋጋት…የመቀዝቀዝ….የመሽኮርመም…እኔ እንጃ

መግልፅ አልቻልኩም..ግን በጣም አመሰግናለው፡፡››

‹‹ግድ የለም ምስጋናው ይቆየኝና አሁን ወጣ እንበል….››

‹‹እሺ› አለችና ቀድማኝ ወደ በራፍ እርምጃዋን ቀጠለች…

‹‹እንዴ !!!ወዴት ነው……?››

‹‹እንሂድ አላልከኝም እንዴ..……?››

‹‹አንድ ሴት እኮ እንሂድ ከተባለች ቡኃላ ለመዘጋጀት በጣም ፈጣን ከኆነች አንድ

ሰዓት..ከልሆነም ሁለትን ሶስት ሰዓት ይፈጅባታል..››

‹‹አልገባኝም..ምን ልትሆንበት……?››

‹‹ስትጠጣጠብ..ስትቀባባ..ስትኳኳል ..ልብስ ስትለካ ስታወልቅ….መስታወት ፊት ቆማ

አለባበሷን ስታስተካክል ..››

‹‹ቀልደኛ ነህ…ልኳኳል ብልስ ምኔን እኳኳላለው………?ለዛውስ ያለመደብኝን….ጋሼ ዜና

ምን ይሉኛል መሰለህ ..ሴት ሁኚ…ሁሌ ምክራቸው ሴት ሁኚ ነበር››

‹‹ማናቸው ጋሽ ዜና .. ……?››

ጋሽ ዜና እንደአያቴ የማያቸው ከጎረቤታችን የሚኖሩ ከውልደቴ እስከዛሬ የሚያውቁኝ

እንደአያቴ የማያቸው ሙሁር ግን ደግሞ ደሀ …(ለካ እዚህ አገር ምሁርነት እና ድህነት

አብረው የሚሄዱ ዘማዳሞች ናቸው) አዛውንት ናቸው፡፡››

‹‹እና ሴት ሁኚ ሲሉሽ..አረ ሴት ነኝ ብለሽ ቢያንስ ስንጥቁን በፎቶም ቢሆን አንስተሸ

ማረጋገጫውን አታሳያቸውም››

‹‹እሷቸው እኮ እንደላንጠለጠልኩና ስንጥቅ መሆኔን በደንብ ያውቃሉ..ለማለት የፈለጉት

ሴት ሆነሽ ተፈጥረሻል እና የሴትን ተፈጥሮዊ ባህሪ ተላበሺ ማለታቸው ነው….ሴቶቸ ወበት

አድናቂ ናቸው..ሴቶች ሰላም ወዳዶች ናቸው…ሴቶች የፍቅር ዘማሪዎች ናቸው….ሴቶች

ልስልስ ናቸው..ሴቶች ለተፈጥሮ ቅርብ ናቸው..ሊዩክሌር ቦንብ ለመስራት በላባላቶሪ

ከመዳከር በግቢያቸው ውስጥ ያለ አበባ ውሀ እያጠጡ እና እየኮተኳቱ ማሳደግና በዛ

መደመምን ይመርጣሉ….ሴቶች ቀለል ያለ ያልተወሳሰበ ኑሮን ይመርጣሉ..ሴቶች ስሜተ

ሙሉ ናቸው…ሴቶች እናቶች ናቸው..እናትነት ደግሞ የፍቅር መህደር ማለት ነው….እና ሴት

ሁኚ ሲሉኝ ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ይገባኛል….ድብድብና አንባጎሮውን ቀንሺ ሊሉኝ

ፈልገው ነው….ዘረፋውንና ማጅራት መምታቱን ባንቺ አያምርብሽም ሊሉኝ ነው…››

‹‹ባይገባኝም ገብቶኛል..በይ አሁን እንሂድ..አልኩና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቤርጎውን

ቀለፍንና እጅ ለእጅ ተያዘን ግቢውን ለቀን ወጣን….የሙዚቃ ሁካታ ማያደነቁርበት ቤት

ፈልገን እራታችን ልንበላ

..

..

ሁለት ሰዓት ሲሆን እራታችንን በልተን በማጠናቀቅ ከወደ መጠጡ እየወሳሰድን ጫወታችን

ቀጥለን ነበር..የጫወታው ርዕስ ወደ ሮማን ዞሯል… ወደ አሳዳጊ እናቷ

‹‹ቆይ እናትሽን እሷ እንደገደለቻት በምን አወቅሽ….……?እንደነገርሺኝ በወቅቱ አንቺ ልጅ

ነበርሽ……?››

‹‹አዎ ልጅ ነበርኩ..ያወቅኩት በቅርቡ ነው ..የዛሬ ስምንት ወር አካባቢ››

‹‹እንዴት ልታውቂ ቻልሽ››

‹‹በአጋጣሚ……ምን መሰለህ....እናቴ ስትሞት ለአንድ ሳምንት ታማ ነበር…በዛ

በታመመችበት ሰዓት ከስሯ ኩርምት ብዬ አይን አይኗን ሳይ ነበር የምውለው…እና ትዝ

ይለኛል በመጨረሻዋ ቀን ከመሞቷ ከአንድ ወይም ከሁለት ሰዓት በፊት እሮማን ፍቱን

የባሀል መድሀኒት ነው በሽታሽን ነቅሎ ያወጣልሻል አለቻትና አንድ መድሀኒት በብልቃጥ

አምጥታ አጋተቻት….ብልቃጧ የመድሀኒቱ ቀለም እና ሽታው ምን ጊዜም ከአዕምሮዬ

አይጠፋም…የመድሀኒቱ ቀለም ዝልግልግ አረንጎዴ ሳር መሰል ሲሆን ሽታው ግን እንደዚህ

ነው ብዬ መናገር ማልችለው በህይወቴ ወደ አፍንጫዬ ገባቶ የማያውቅ የተለየ ሽታ

ነው…..እናቴን ግን ሊያድናት አልቻለም..ሁል ጊዜ እናቴ ስትናፍቀኝ ወደ አይምሮዬ

የሚመጣው አልጋ ላይ የተዘረረ የእናቴ በበሽታ የደከመ ሰውነት..አረንጓዴ የተዝለገለገ

ፈሳሽ..ከፈሳሹ የሚበተነው ሽታ..ግርም ነው የሚለኝ..እንዚህ ነገሮችን ለምን ደጋግሜ

እንደማስታውስ ለራሴም ግራ ግብት ይለኝ ነበር…..

‹‹እና ከዛሬ 8 ወር በፊት አንድ ስራ ለመስራት ፈለግኩ››

‹‹ምን አይነት ስራ ?››

‹‹አንድ በጣም የሚያስጠላኝ አራጣ አበዳሪ ሰውዬ ነበር…በህይወቴ ከማውቃቸው ሰዎች

ሁሉ የመጀመሪያው ወንበዴ እና ጨካኝ ሰው ነው….አንድ ቀን ወደ ቤቱ ወሰደኝ..ይገርምሀል

ሚኖርበት ቢላ 13 ክፍሎች ያሉት የተንቆጠቆጠ ነው…፡፡ያን የሚገርም ቤት የገነባው

ጠቅላላ ሀብቱንም ያከማቸው በተዘረፈ ብር ነው..››

‹‹ሚስት የለውም እንዴ ?››

‹‹አለው 32 ዓመት አብራው የኖረች ሚስት አለው…ልብ በሽተኛ ሆና ለህክምና ልጇቾ ወደ

ውጭ ስለወሰዷት ለብቻው ነው የሚኖረው…..የልጅ ልጅ ያየ የስልሳ ወይም የሰባ አመት

ሽማጊሌ እኮ ነው….መጀመሪያ አንድ ሺ ብር ከፈለኝና ይዞኝ ሄደ….መኝታ ቤት ከገባን ቡኃላ

ልክ እንደ ሀያ አመት ጎረምሳ ፊልም ከፈተ..››

‹‹የምን ፊልም… ?››

‹‹የወሲብ ፊልም ነዋ…ፈረንጆች የሚጨመላለቁበትን ፊልም….ልብሱን አወላለቀ እና ያንን

ቀፈታም እንደከበሮ የተነረተ ሆዱኑ አንዘርጥጧ ፊቴ ቆመ..››

‹‹ሰውዬ ተኛ እንጂ››አልኩት

‹‹ተይ እንጂ ቆንጂት ..ምን አስተኛን…እድሜችን ሙሉ ተኝተን ስናረግ ነው የቆየነው…አሁን

በፊልሙ እንደምታያቸው ዘመናዬቹ ነው ማድረግ የምፈልገው…ያኛውማ አይነት ሰልችቶኛል

…ካአሁን ቡኃላ ጸኝጾ ማድድግ ለማለድ ብቻ ና የሚጠቅመው..እኔ ደግሞ አንቺ

እንድታስደስቺኝ እንጂ እንድትወልጂልኝ አልፈልግም››ብሎ ገለፈጠ…በሱ ቤት መቀለድ ነው

‹‹እሱ ይወደድብሀል››አልኩት….

ወደ ኮመዲኖ ሄደና መሳቢያውን ሳበው..ይገርምሀል ኮመዲኖው ሙሉ በገንዘብ የተሞላ

ነው…የተሰረ የታሰረ ብር..አንዱን መዥርጦ አመጣና እጄ ላይ አስቀመጠልኝ››

‹‹እንዴት ነው የምትፈልገው ?››

‹‹እንድትጠቢልኝ››

‹‹ምን ? ››

‹‹አዎ እንደዛ ነው የምፈልገው..አየሻቸው አይደል ፊልሙ ላይ ያሉትን ቆነጃጅቶች..እንዴት

እንዴት የሰውዬውን ነፍስያ እንደሚያስደስቱለት››

‹‹ግን እኮ እንትኖት ልፍስፍስ እንዳለ ነው..ካልቆመ እንደዛ ለማድረግ ያስጠላል…››

‹‹አቁሚዋ…. ስራሽ ማቆም አይደል… ?››

‹‹አይደለም ጌታዬ …ስራዬ የቆመውን አባብሎ ማስተኛት ነው ››

‹‹እኔ እኮ አስር እጥፍ የከፈልኩሽ..የተኛውን ቀስቅስሽ በማቆም ..እንዳልሽው ከእንደገና

አባብለሽ እንድታስተኚው ነው…››

‹‹ከዛ እንዴት ሆናችሁ ?››የምታወራለልኝ ወሬ እበሳጨኝም እናደደኝም..በምትለው ሽማግሌ

ልናደድ ወይስ በእሷ በራሷ መለየት አቃተኝ፡ነው ወይስ እየቀናው ነው ?፡፡

‹‹ከዛማ እንዲሁ ሲንበዛበዙብኝ አደሩ…እንትናቸው እንኳን በእኔ ሀይል በቢያግራምም

ሚቆም አይነት አልነበረም ለማንኛውም ነጋና ተለያየን…››

በሳምንቱ ያገናኘኝን ደላላ ላኩት

‹‹ለምን ?››

‹‹ ለመድገም ነዋ..እኔ ደግሞ እንኳን እንደሳቸው አይነት በዝባዛ ሽማግሌ ይቅርና እንደአንተ

አይነት መለሎ ወንድ ቢሆንም መድገም ብሎ ነገር ነው የሚያስጠላኝ…ግን እዛ ኮመዲው

ውስጥ ታጭቆ ያየውት ብር አሻፍዶኝ ስለነበረ..እምቢ ማለት አልቻልኩም…››

‹‹ድጋሚ ልትጠቢ ?››ሳላስብ የጠየቅኩት አስቂኝ ጥያቄ ነው

‹‹አይ እንትናቸውን ሳይሆን ብራቸውን ልጠባ…እና ሮማንን አማከርኳት…..እንዳጋጣሚ

ቤተሰብ ልጠይቅ ብላ ከአዲስ አበባ ውጭ ነበረች..እና በስልክ ነው ያማከርኳት…እና

የሚያደነዝዝ መድሀኒት እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት….ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራ ስሰራ

የምጠቀመውን መድሀኒት የምትሰጠኝ እሷው ስለነበረች…የተለመደ ጥያቄ ነበር የጠየቅኳት

የት እንደሚገኝ በምልክት ነገረቺኝ..ከነተቀመጠበት የእቃ አይነት …ቁልፍን ካለቺኝ ቦታ

አገኘው..መኝታ ቤቷ ጋባው… ቁም ሳጥኗን ከፈትኩ ..በሌላ ቁልፍ ቁም ሳጥኑ ውስጥ

ያለውን አንድ አነስታኛ ሌላ ሳጥን ከፈትኩ..ኣዛ ሳጥን ውስጥም ሌላ የተቆለፈች ሳንቲም

ማጠራቀሚያ የምታህል የብረት ሳጥን አለች …ተቆልፋለች …ቁልፉ የለኝም..ደወልኩላት

‹‹ ሳጥኑን በምን ልክፈታት ?››

‹‹ቁልፍን ይዤ ነው የመጣውት …ገንጥያት..አደራ ቀስ ብለሽ..ውስጥ ያሉት መዳኒቶቹ

በጣም አስፈላጊ ናቸው… እንዳትሰባብሪብኝ እና እንዳይደፈ››

‹‹እሺ ››በማለት ስልኳን ዘጋውና በጥንቃቄ ገነጠልኩት..እንኳን ያቺን የምታክል ሚጢጢዬ

ቁልፍ ይቅርና ሌላውም ቢሆን ቁልፍ መገንጠል የተካንኩበት ሞያዬ ነው፡፡

ስገነጥለው አምስት የሚሆኑ የተለያየ መጠን ያላቸው ብልቃጦች አገኘው…ነጭ ብልቃጥ

ውስጥ ያለው ነው ያለቺኝ..ነጭ ብልቃጥ ደግሞ አንድ ብቻ ነው ..ፈገግ ብዬ አነሳውትና

መልሼ ልከድነው ስል የሆነ ነገር ገፋፋኝና ከጎኑ ያለውን ሌላውን ብልቃጥ አነሳውት..የሆነ

በጣም የማውቀው ብልቃጥ መስሎ ተሰማኝ …በዝግታ ከፈትኩት…አፍንጫዬ በሆነ ሽታ

ተሞላ ….በህይወቴ ይሄንን አይነት ሽታ ለሁለተኛ ጊዜ መማጌ ነው…ወደ መሬት ትንሽ

አፈሰስኩለት ይበልጥ ለማረጋገጥ …የተዝለገለገ አረንጓዴ ፈሳሽ..እናቴን የጋተቻት ላካ

መድሀኒት ሳይሆን ሞት ነበር…እናቴን ለካ በሽታው ሳይሆን በዚያች አረመኔ የተሰጣት መርዙ

ነበር የገደላት….እርግጥ በጣም ጨካኝና አረመኔ እንደሆነች አውቃለው..ዘራፊና ገዳይ

እንደሆነችም የአይን ምስክር ነኝ…..እኔም እራሴ የእሷ ውጤት ነኝ…ግን የገዛ እናቴን

ገድላታለች ብዬ ለደቂቃ እንኳን ተጠራጥሬያት አላውቅም ነበር….እና እንደእብድ

አደረገኝ..ያንን መርዝ በወቅቱ ተግቼ እናቴ የሞተችውን ሞት ለመሞት ተመኘው….ሰውዬውን

ለመዝረፍ የነበረኝን ሀሳብ ተውኩት… ብልቃጡን ኪሴ ከትቼ ጥዬ ወጣው.

.ለካ ያንን ሁሉ ዘመን ስታሾፍብኝ ነበር…ለካ እናቴን ገድላ በእኔ ስትበልፅግ ነበር…..ለካ

ሸርሙጣ ያደረገቺኝ በዕቅድ ነበር..ለካ ስዘርፍ የኖርኩት ለእሷ ነበር…ሁሉ ነገር ግልጽልጽ

አለልኝ..ያንቻው ነው እያለወች በስሞ ስትገዛ ከኖረችው ንብረት አንዲቶንም

እንደማታቀምሰኝ እርግጠኛ ሆንኩ…እግዚያብሄር ባያጋልጣት.. ተጠቅማብኝ ተጠቅማብኝ

የጠገበቺኝ ጊዜ ለዛውም በቅርብ እኔንም በዚያ መርዝ ልታስወግደኝ እንደምትችል እርግጠኛ

ሆንኩ..ከዛን ቀን ጀምሮ እሷንም ሌብነት የሚባለውንም ነገር እርግፍ አድርጌ

ተውኩ…..ሁለቱንም ዞር ብዬ ላላያቸው ለራሴ ማልኩ፡፡

‹‹እሷስ አልፈለገችሽም ?››

እሷማ የነዳጅ ጉድጓድ እንደደረቀበት አረብ ነው ያዘነችው..ከእኔ ለመታረቅ እና ወደ ቤት

እንደምለስ ያላደረግችው ጥረት ያለመነችው ልመና አልነበረም…››

‹‹እና ተስፋ ቆርታ ተወችሽ ?››

‹‹እስከአሁን እንግዲህ እየተጠባበቅን እንኖራለን…እርግጠኛ ነኝ የሆነ ሆነ ቀን እንደማጠቃት

ትጠረጥራለች… ስለዚህ በተጠንቀቅ እና በመበርገግ ነው የምትኖረው..እኔም እንደዛው

ከፍራቻዋ የተነሳ ጥላዋንም የማታምን ሰው ስለሆነች የሆነ ነገረ ልታደርገኝ እንደምትችል

ስለማውቅ እንደሸከከኝ ነው.... የምኖረው ማን እንደሚቀድም እስከአሁን አለየም ››

‹‹በጣም ይገርማል…››

‹‹አዎ ይገርማል››

‹‹ስልኬ ጮኸ››

‹‹ከሻምቡ ነው..የእህቴ ልጅ ነች የደወለችው›

‹‹ሄሎ አጎቴ››

‹‹ሄሎ በሻዱ…ሰላም ነሽ ?››

‹‹ሰላም ነኝ….ነገ ትመጣለህ እንዴ ?››

‹‹አዎ መጣለው ..ምነው ?›

‹‹አይ ምንም አይደል.. ?እንዲሁ ነው የጠየቅኩህ እናንተ ቤት ነኝ››

‹‹መጣሽ እንዴ… ?››.

‹‹አዎ …አኩዬ ስትደውልልን እማዬ ሂጂላቸው አለቺኝ››

‹‹እና ሚጡ አስቸገረቺሽ ?››

‹‹አረ አላስቸገረቺኝም ..አሁን ተኝታለች››

‹‹አይ ጥሩ ነው..እማዬስ ?››

‹‹እሷም ተኝታለች››

‹‹በቃ ነገ አስከ ስድስት ሰዓት እደርሳለው…አሁን አንቺም ተኚ ደህና እደሪ››

‹‹አሺ ደህና እደር አጎቴ››ስልኩን ዘጋው፡፡

‹‹የእህቴ ልጅ እቤት መጥታ ነው..››

‹‹ገባኝ…አሁን ስትሄድ ምንድነው የምታደርገው ?››

‹‹ማለት.. ?›

‹‹ልጅህን ማነው የሚጠብቅልህ ?››

‹‹ሰራተኛ እፈልጋለዋ››

‹‹ታገኛለህ ?››

‹‹የግድ ማግኘት አለብኝ..ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተሯሩጠው ያገኙልኛል ብዬ አስባለው››

‹‹አይ ጥሩ ነው…››

እንግዲያው እኔም ወደ ሸገሬ ገብቼ ሶስት ቀን ሙሉ ወቋረጥኩተ ስራዬ ልመለስ….››

‹‹ስራዬ..የምን ስራ ?››ጥያቄው የእውነቴን ነበር…ስራዋ ምን ነበር…ምን ስትሰራ ነው

የተገናኘነው… ?ከአዕምሮ ተሰርዞል

‹‹የምን ስራ ትላለህ እንዴ.. ?ምን ስሰራ ነው ያገኘኸኝ ….ሽርሙጥና ነዋ››

‹‹ሽርሙጥና››

‹‹አዎ ሽርሙጥና››

‹‹በፍፅም ወደዛ ህይወት አትመለሺም..ሽርሙጥናውንም እንደስርቆቱ እርግፍ አድርገሽ

መተው አለብሽ….››

‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት››

‹‹እየቀለድኩ አይደለም..እኔ በህይወት እያለው አንቺ ዳግመኛ ወደ እዛ ሕይወት

አትመለሺም››

‹‹እና ታዲያ ምን ልሁን ?››

‹‹ምን ሁኚ ልበላት…ሌላ ምን ስሪ ልበላት….ድንግርግሬ ወጣ..በዚህ ጊዜ የእሷ ስልክ

ጠራ..አነሳችው

‹‹ሄሎ እሱባለው››

ማነው እሱ ባለው ? በአዕምሮዬ የመጣብኝ ጥያቄ ነው…‹‹ሄሎ እሱባለው››

‹‹አለሽ እንዴ ጂጂ….?››

‹‹አለውልህ››

‹‹ጥዋት ላገኝሽ ፈልጌ ነበር››

‹‹ትንሽ ራቅ ብያለው…ነገ ከሰዓት እንገናኝ….?››

‹‹ይቻላል››

‹‹ ግን ችግር የለም አይደል….?››

ንግግሯን ሳትጨርስ እና ለጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ ስልኩ ተቋረጠ‹‹…ምን አይነት ቁሺም

ነኝ… ቻርጅ ሳላደርግ ውዬ አሁን ስልኬ ተዘጋብኝ››

‹‹በእኔ ደውይአ››ብዬ አቀበልኳት

‹‹አይ ስልኩን በቃሌ አላቀውም..እንግባና ቻርጅ አድርጌ ደውልለታለው››አለቺኝ ..በውስጤ

ቅሬታ እየተሰማኝ እንዳለችኝ ሂሳብን ከፍዬ አስነሳዋትና አንድን እጄን ትከሻዋ ላይ ሌላውን

ደግሞ በወገቧ ዙሬያ ጠምጥሜ ይዤት ወጣው…

እንደደረስንና ቤርጎቸንን ከፍተን እንደገባን ሁለታችንም ወደ አልጋው ነው የሮጥነው…

አልጋው ላይ ከሰፈርኩ ቡኃላ ልብሴን ማውለቅ ስጀምር..እሷ በተቃራኒው ቀሚሱን

ሳታወልቅ ከውስጥ ጂንስ ሱሪዋን አደረገች

‹‹ሰው ሊተኛ ሲል ልብሱን ያወልቃል አንቺ በተቃራኒው ታደርጊያለሽ..….?››

‹‹መቼም ሁለታችንም አውልቀን አንተኛም››

‹‹ብንተኛ ምን አለበት….?››

‹‹ነገር አለበት››

‹‹የምን ነገር….?

‹‹ትልልቅ ሰዎች ሚያደርጉት ነገር..››

‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም..ልብስሽን አውልቀሽ ብተኚ ደስ ይለኝ ነበር››ቅሬት ባጋተ

የሚርገበገብ ድምጽ

‹‹ምንም አልገባህም እንዴ….?››አለቺኝ ሱሪዋን አጥልቃ ከጨረሰች ቡኃላ ቀሚሷን በአንገቷ

በኩል ሞሽልቃ እያወለቀች

‹‹ምኑ ነው ያልገባኝ….?››

‹‹በጣም እኮ ነው የወደድኩህ..እርግጥ እንዲህ ስል ውስጤን ንዴትና ብስጭት እየወረረኝ

ነው..ቢሆንም ግን ወድጄሀለው…ያ ደግሞ በእኔ ህይወት ትልቅ ነገር ነው ….አዲስ እና

ያልተለመደ ነገር…ስለዚህ ላበላሸው አልፈልግም..እስኪ ጥቂትም ቢሆን ከወንዶችም

መካከል ጥሩዋች አሉ ብዬ እንዳምንና እንዳወራ እርዳኝ››አለቺኝ ከላይ ቲሸርቷን ለብሳ አልጋ

ላይ እየወጣች….እኔም አወላልቄ ጨርሼ በፓንት እና በፓካውት ብቻ ነበርኩና እንደእሷ

አደረግኩ

‹‹አወሳሰብሺብኝ እኮ …. ››

‹‹ባክህ ለራሴም ተወሳስቦብኝ ነው ››

‹‹ቆይ ለአንቺ ወንዶች ሁሉ መጥፎዎች ሆነው ነው የሚታዩሽ….?››

‹‹አይ የሚታዩኝ ሳይሆን በርግጠኝነትም መጥፎዎችና የማረቡ እብሪተኞች ናቸው…እኔ ከጋሽ

ዜና በስተቀር ጥሩ የሚባል ወንድ አላጋጠመኝም..ያው እሷቸውም ምን አልባት አዛውንት

ስለሆኑ ሊሆን ይችላል…በጣም የተማሩ እና አንባቢም ስለሆኑ ሊሆኑ ይችላል …..አዎ

እሳቸው አስተሳሰባቸውም አኗኗራቸውም ሁለ ነገራቸውም ከብዙሀኑ ወንዶች ፍጽም የተለየ

ነው…

‹‹እኔስ…..….?››የምላስ ወለምታ ..አዳልጦኝ የጠየቅኩት ጥያቄ ነው፡፡

‹‹አንተ… እኔ እንጃ …ያንተ ሚዛን የተለየ ነው….ምን አንተ ላይ እንዳየው አላውቅም…….?

ምን አልባት ፍቅር ሲይዝህ በዛ ሰው በጣም ስትሳብና ግን ደግሞ መኑ እንዳማረከገህ

አይገባህም ይሁናል ….? ..ግን ደግሞ አብረኸው መሆን ትራባለህ…. በእቅፉ ውስጥ

መጥፋት ያጓጓሀል….በትንፋሹ መቅለጥ ያምርሀል …ወይም ጭው ያለ በረሀ ውስጥም

ቢሆን ከእሱ ጋር ብቻህን መኖርን ህልምህ ይሆናል….እሱን ስለማጣት ስታስብ ውስጥህ

በሽብር መናጥ ይጀምራል..አዎ ፍቅር የሚሉት የሰው ልጅ ጣጣ እንደዛ አይነቱ ነው

መሰለኝ››

‹‹የሚገርም አገላለጽ ነው….እና አሁን በገለጽሺው መጠን አፍቅረሺኛል ማለት ነው….?››

ደነገጠች‹‹ማ….? እኔ …….?ማንን….?››

‹‹እኔን ነዋ..››ቆፍጠን ብዬ

‹‹እንዴት ሊሆን ይችላል..….?ከተዋወቅን እኮ ገና ሶስተኛ ቀናችን ነው…..በሶስት ቀን

በፍቅር መያዝ አለ እንዴ…….?››

‹‹በፍቅር ለመያዝ ግን ስንት ቀን ያስፈልገል….? ….በሰከንድ ሽራፊም ሊሆን ይችላል እኮ…

እኔ ግን አፍቅሬሻለው…በጣም ነው የወደድኩሽ..ይሄንን ቃል ከሞች ሚስቴ ውጭ ለማንም

ሴት ተጠቅሜው አላውቅም…በጣም ነው ያፈቀርኩሽ…ስላፈቀርኩሽም ደስተኛ ነኝ››ወሬያችን

ሁለታችም ከጭንቅላታችን ቀና በማለት ትራሳችንን በመንተራስ ፊት ለፊት እየተያየን ነው

‹‹አይ እንዳልከው ከሆነ … ፍቅር ሳይሆን መጋኛ ነክቶሀል ..አየህ መጋኝ ድንገት ነው ለሊት

በራፍ ከፍተህ ስትወጣ..ወይንም ተዘግቶ የቆየ ቤት ድንገት ከፍተህ ስትገባ ..አዎ ያዝን

ጊዜ በጋኛ ድንገት አጠናገረው ይባለል…እና ፍቅርም እንደዛ ከሆነ ፍቅር ሳይን እርግማን ነው

በለው….እንዲህ ማረፊያውን እንኳን የማያውቅ….?››

‹‹ምን ማለት ነው..….?››

‹‹እሺ አፈቀርከኝ…ምን ልታደርገኝ ነው..ሰው እንዴት አንድ ሸርሙጣ ያፈቅራል….?››

‹‹እኔ ሸርሙጣ አላፈቀርኩም ..እኔ ያፈቀርኩት አንቺን ነው..አንቺ ደግሞ ሰው

ነሽ….ሰው….እጅጋየው የምትባለዋን ቆንጆ ብሩህ አዕምሮ ያላትን የሚደንቅ የህይወት ታሪክ

ባለቤት የሆነችውን ከአልማዝ የጠነከረች ልጅን እንዳፈቀርኩ ነው የማውቀው..በዛም

በጣም ዕድለኛ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ..››

በጭቃ ተለውሶ አደባባይ ላይ የተጣለን ወርቅ ወርቅነቱን አውቆ በማንሳት ጭቃውን አጽድቶ

ለመጠቀም እድልና ብልሀትን ይጠየቃል፡፡አኔ ብልህ ነኝ ብዬ ባላስብም እድለኛ ግን

እንደሆንኩ እርግጠኛ ነኝ፡፡››

‹‹ጥሩ ነው..ማፍቀር መፍትህ ነው..እኔ ግን ነገ የምለየውን ….መቼም ደግሜ የማላገኘውን

ሰው አፍቅሬዋለው ብዬ መጃጃል አልፈልግም..አዎ አልፈልግም……በፍፅም..አዎ አንተን

ማፍቀርማ የለብኝም››ለእኔ የምታወራ ሳይሆን ከራሷ ውስጠት ጋር ሙግት የገጠመች ነው

የሚመስለው፡፡

‹‹ለምን አንሄድም….?››

‹‹ወደ የት….?››

‹‹ወደ ሻንብ››

‹‹ምን ለማድረግ..….?››..

‹‹በቃ አብረን እንኖራለን..ሻንቡ ታያታለሽ..እርግጥ ካደግሺባት አዲስ አበባ ጋር ስትነጻፀር

ቀበሌ ልትሆንብሽ እና ሊደብርሽ ይችላል … ቢሆንም ልጄን ትተዋወቂያታለሽ..እሷን

በእርግጠኝነት በጣም ነው የምትወጂያት….እናቴም የምትወድሽ ይመስለኛል››

‹‹የእውነትህን ነው….?››

ለእሷ ሳይሆን ለእናንተ እወነቱን ልንገራችሁ የማወራው ነገር ሁሉ የእውነቴን ይሁን ወይስ

የሆነ ቅዣት ውስጥ ሆኜ የምዘባርቀው እርግጠኛ አይደለሁም….ይህቺ ልጅ አዕምሮዬን

እንዲሰለብ እና የማገናዘብ ኃይሌ እንዲሞጠጥ አደረገች እንዴ….?

‹‹እውነቴን ነው..በቃ አብረን እንሂድ ..ታይውና ከደበረሽ ትመለሺያለሽ››

‹‹ካልደበረኝስ…….?ሁሉ ነገር ቢመቸኝስ….….?››

‹‹እሱ አይደል የሚፈለገው..››

‹‹ምንህ አድርገህ ታኖረኛለህ….?››

‹‹ብታገቢኝ ደስ ይለኛል››

‹‹አረ …አንተ ሰው ጤነኛ አትመስለኝም..ነገ የምትፀፀትበትን ነገር ዛሬ አትዘባርቅ..ነው

ወይስ ሰከርክ….?››

‹‹እንዳልሰከርኩ አንቺም ታውቂያለሽ..እሺ ብለሺኝ ካገበሽ በእውነቱ በጣም እድለኛ ሰው

እንደሆንኩነው እራሴን የምቆጥረው…በእወነት አንቺን አጠገቤ እንድትኖሪ የማላደርገው ነገር

የለም..ምን አልባት እቤት መዋል ይደብረኛል የምትይ ከሆነ የሆነ ሱቅ ነገር ከፍትልሻለው…

በቃ ኮስሞቲክ ቤት..ወይንም ቡቲክ…የፈለግሽውን….››

‹‹አላምንህም››አለቺኝ ፍርጥም ብላ..እውነቶን ነው..ለወንዶች መራር ጥላቻና ከልክ ያለፈ

ንቀት ያላት ልጅ እንዲህ መሰሉን የእን ቅዣት እንደውም አመንኩህ ብትል ነበር

የሚገርመው…

‹‹አላምንህም.. ነገውኑ ማለት ጥዋት እዚሁ ደብተሬ ላይ ሀምሳ ሺ ብር አለ… ባንቺ ስም

አዞርልሻለው..አዛ ስንደርስና ስራ...ስትጀምሪ ደግሞ የተወሰነ ተጨማሪ

ጨምርልሻለው..አይዞሽ ልጅ ጠባቂ ያደርገህኛል ብለሽ ሰግተሸ ከሆነ እሷዋን የምትንከባከብ

ልጅ እንደማገኝ ማረጋገጫ ሰጥሻለው..››

‹‹አመረርክ እንዴ ሰውዬ ….?እኔ እንደውም አሁን ካልከኝ ሁሉ ያጓጓኝ ልጅህን መንከባከብ

እና እንደእናቷ ጉያዬ ውስጥ ሸጉጬያት ስታለቅስ ላባብላት እና እሹሩሩ እያልኩ ላስተኛት

ብችል ብዬ ነው…››

‹‹እና አድርጊዋ ..እናቷ ሁኚ…….. ››

‹‹በምንም አይነት መንገድ…….?ላገባህ እንደሆነ አልችልም..››

‹‹እሺ አታግቢኝ …ግን አብረን እንሂድ እና ሌላ ስራ ጀምሪ ….ቢያንስ እንደወንድምሽ

ቁጠሪኝና በቃ ባለውበት አካባቢ ኑሪ …ጥሩ ጓደኛሞች እንሆናለን..በፈጠረሽ ወደ እዛ ከተማ

አትመለሺ….ባይሆን በቅርብ ወደ ነቀምት ቅያሬ ጠይቃለው..ነቀምት ትልቅ ከተማ ስለሆነ

እዛ አይደብርሽም››

‹‹እኔ ሚስትህም እህትህም መሆን አልፈልግም››

‹‹አረ በፈጠረሽ››

‹‹ሰራተኛህ አድርገህ ቅጠረኝ››

‹‹ምን….?››

‹‹አዎ የልጅህ ሞግዚት አድርገህ ቅጠረኝ….ሚስትም መሆን ነጋዴም መሆን አልፈልግም››

‹‹እኔ አንቺን ሰራተኛ አድርጌ.….?.››

‹‹አዎ..ለሄደችው ሰራተኛህ ስንት ነበር የምትከፍላት….?››

‹‹በወር ሁለት መቶ ብር››

‹‹ለእኔ ሶስት መቶ ብር አድርግልኝ…››

‹‹እየቀለድኩ እኮ አይደለም….?››አልኮት ሹፈት አዘል በሚመስለው ንግግሯ ተበሳጭቼ…

‹‹እኔም ቀልዴን አይደለም..ነው ወይስ እድሜዬን በሙሉ በሽርሙጥና እና በስርቆት

ስላሳለፍኩ የሞያ ነገር ኔፓ ነች ብለህ አሰብክ….በሞያ አትጠራጠር…አድሜ ለዛች ጭራቅ

ሮማን ተብዬ ….እጄን በማማሲያ እየቀጠቀጠች ነው ሞያ ያስተማረችኝ››

ምመልስላትን አጣውና ዝም አልኩ….በዚህ መካከል እሷ ተነሳችና ተንጠራርታ ስልኳን

ከተሰካበት ነቀለችና ከፈተችው ….ደወለች

‹‹ሄሎ እሱባለው››

ጆሮዬን ቀስሬ ማዳመጥ ጀመርኩ……

‹‹ሄሎ ጂጂ..ስሞክርልሽ እኮ እንቢ አለኝ››

‹‹አዎ ስልኬ ቻርጅ ጨርሶ ነበር…››

‹‹እንደዛ እንደሆነ ገምቼ ነበር..››

‹‹አዎ….ምነው ግን ችግር የለም አይደል….?››

‹‹አረ ፒስ ነው… ዛሬ እሁድ አይደል..የዕቁብ ቀን እኮ ነው››

‹‹እና ጎደለብህ እንዴ….?..››

‹‹አረ አልጎደለብኝም..አስር ሺ ብር ጥዬ እንደውም አንድ ሺ ሶስት መቶ ብር ግልባጭ አለ››

‹‹አይ ጥሩ ነው….ግልባጩ አንተ ጋር ይቆይ..ስፈልገው ደውልልሀለው››

‹‹አይ ለዛ አይደለም የፈለግኩሽ..ዕቁቡ ወጥቶልሻል››

‹‹ወጣ ..››

‹‹አዎ ወጥቶልሻል…ግን አልተቀበልኩትም….አሁን የደውልኩት ጥዋት ተቀብዬ ላቀብልሽ

ወይ ለማለት ነበር…በቃ ከሌለሽ ስትመጪ ይደርሳል ….እንደደረሽ ደውይልኝ››

‹‹አይ አሁን የባንክ ቁጥር ልክልሀለው…. በዛ ታስገባልኛለህ››

‹‹እሺ እንዳልሽ…››

‹‹አሺ ደህና እደር..ደግሞም ግልባጩ የፍንጥር ይሁን››

‹‹አረ ይበዛል››

‹‹አብሽር…..››

‹‹እሺ ይመቺሽ ሲሱ››

ስልኩ ተዘጋ..የእኔ አዕምሮ ግን ክፍትፍት እንዳለ ነው…ወሬቸውን ከመጀመሪያ

እስከመጨረሻው ሰምቼያለው..ግን ግራ ግብትብት እንዲለኝ ነው ያደረጉት..መጀመሪያ እዛ

እራት ላይ እያለን ሲደውልላት..ከወንዶች ጋር የሚያገናኛት ደላላ ነበር የመሰለኝ..አሁን ግን

የሚያወሩት ስለቢዝነስ ነው ..ስለ ዕቁብ ነው››

‹‹የባንክ ቁጥርህን ንገረኝ››ስትለኝ ከሀሳቤ ተነጠልኩ እና ትኩረቴን ወደ እሷ መለስኩ

‹‹የምን የባንክ ቁጥር….?››

‹‹ያንተን ነዋ››

‹‹ምን ሊያደርግልሽ….?››

‹‹አልሰማህም እቁብ ወጣልኝ እኮ….ብሩ አንተጋር እንዲቀመጥልኝ ፈልጌ ነው…50 ሺ ብር

ሰጥተኸኝ የለ..እኔ መቶ ልጨምርበት እና አንድ ላይ 150 ሺ ብር ይሆንልኛል››

‹‹አረ ምን አይነት ናላ አዞሪ ልጅ ነሽ….?››

‹‹እሺ ስጠኝ..እንደውም ተወው ..››አለችና ከመኝታዋ ተነስታ የጃኬቴን ኪስ ጎርጉራ የባንክ

ደብተሩን በማግኘት በስልኳ ቁጥሩን ጻፈችና እንዳለችው ለልጁ ልካለት መሰለኝ ተመልሳ

ወደ መኝታዋ ገባች….አዎ አብራኝ ትሄዳለች ማለት ነው ስል አሰብኩ…ደስስስስ አለኝ

‹‹ለመሆኑ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽው….?››

‹‹እቁብ..››

‹‹እሱንማ አወቅኩ …ግን ምን ሰርተሸ….….?መቶ ሺ ስተይ የሰማው መሰለኝ››

‹‹አዎ ትክክል ነህ..ሚኒባስ አለኝ…ሮማን በተለየዋት በወሩ ወዳ ሳይሆን ፈርታ ትገድለኛለች

ብላ ይመስለኛል የሻከረ ልቤን ምታለሰልስ መስሏት ሚኒባሱን በስሜ አዙራ

መለሳልኛለች››

‹‹ሚኒባስ..እና ስራውን ለምን አልተውሽም…….?››

‹‹እኔ እንጃ …ከሌብነት እና ከሽርሙጥና በስተቀር ሌላ ስራ ያለ ስለማይመስለኝ

ይሆናል….አንድ ለማኝን ከጎዳና ወስደህ በቀን ለምነህ የምታገኘውን ብር በእጥፍ አድርጌ

ሰጥሀለው አንተ ልመናውን ተውና እቤትህ ተቀመጥ ብትለው በአንዴ እርግፍ አድርጎ

የሚተው ይመስልሀል..….?ተደብቋ ወይም ሌላ ሰፈር ቀይሮም ቢሆን ይለምናል..ሌባ

ላመሉ ዳቦ ይልሳል ይባል የለ….

‹‹ደግሞ ስድስት ወር ሆኖኛል በሽርሙጥና የማገኘውን ብር ለገዛ ራሴ መጠቀም ካቆምኩ››

‹‹እና ምን ታደርጊዋለሽ….?››

‹‹…ፒያሳ ውስጥ ከሸሌ ተወልደው ግን እናታቸው የሞቱባቸው በየበረንዳውም በየዘመዱም

ተጠግተው የሚኖሩ ፈላዎች ሞልተዋል…ልክ እንደእኔ አይነት ዕጣ ላይ ህይወት አሸቀንጥራ

የወረወረቻቸው…..እና ከነዚህ መካከል ስምንት ሚሆኑትን ጋሼ ዜና እቤታቸው ያኖሯቸዋል…

ያላቻቸው ቤት ባለአንድ ክፍል ብትሆንም በተደራረበ አልጋ ላይ እዛ ያሳድሮቸዋል…ከዛ በላይ

ሊያደርጉላቸው ግን አቅም የላቸውም እራሳቸውም የሚኖሩት በሽራፊ የጡረታ ብር ነው…እኔ

ደግሞ በቀን አንድ ጊዜ ምሳቸውን እችላቸዋለው..ከዛ የቀረውን እነሱ ተሮሩጠው በመሸቀል

እና እርስ በርስም በመረዳዳት ህይወታቸውን ይገፋሉ… አንድ ደግ የፒያሳ ሀብታም ደግሞ

የትምህርት ቤት ወጪያቸውን ትችላቸዋለች..ሁሉም ይማራሉ …..ከትምህርት ቤት ከቀሩ

ድራሻቸውን ነው የማጠፋቸው…. ጋሼ ዜናም በትምህርት ቀልድ አያውቁም…. ፡፡››

‹‹እኔ አንቺ የምታወሪውን ነገር ሁሉ ለማመን በጣም እየተቸገርኩ ነው..ለመሆኑ በቀን አንድ

ጊዜ እየበሉ እንዴት ነው ትምህርት የሚገባቸው….ለዛውም ህጸናት ሆነው፡፡

‹‹እና በቀን ሁለት እና ሶስቴ ከበሉማ ምኑን ችግረኛ ሆኑ…..ይችሉታል..ላያስችል አይሰጥም

ይባል የለ….ድግሞ ሁሌ በቀን አንዴ ብቻ ነው የሚበሉት ማለት አይደለም…ግን ቢያንስ

ከጠፋ ከጠፋ በቀን አንዴ እስኪጠግቡ ይመገባሉ…››

‹‹እና አሁን ቅር ይላቸዋላ….?፡፡››

‹‹ለምን….?››

‹‹ማለት ሳትነግሪያቸው ስለመጣሽ››

‹‹አይ …የምግቡን ኮንትራት በወር አንዴ ነው ምዘጋላቸው…እንዲሁ ለአይናቸው ሲያጡኝ

ይናፍቁኝ ይሆናል እንጂ ሌላ ችግር የለውም….ደግሞ ነገ ልመለስላቸው አይደል….?››

‹‹በየሰከንዱ ነው እንዴ ሀሳብሽን ምትቀያይሪው..አብረን እንሄዳለን አላልሽም››

‹‹መቼ ነው እንደዛ ያልኩህ….….?ወጣኝ….?››

‹‹ብር ባንተ ደብተር ይግባልኝ እያልሽ አልነበር….?››

‹‹እሱማ ይገባልኛል››

‹‹እና አብረሺኝ ካልመጣሽ ..ብርሽ ምን ያደርግልኛል….?››

‹‹ይቀመጥልኛ››

‹‹በፍፅም …እኔ ባንክ አይደለውም››ኮስተር ብዬ

‹‹እንግዲያው ጥፋቱ ያንተ ነው …ሰራተኛ አድርገህ ቅጠረኝ አልኩህ..እንቢ አልክ››

‹‹አሁንማ ምኑን ቀጠርኩሽ..ይልቅ አንቺው ብትቀጥሪኝ ይሻላል…ለሚኒባስሽ ሹፌር

ስትፈልጊ ንገሪኝ››

‹‹የእወነቴን ነው ቅጠረኝ… ሰራተኛህ ልሁን››

‹‹እሺ››አልኳት ምን አጨቃጨቀኝ ብዬ ….እኔ ራሴ ምን መሆኔ ነው..ከዛ ህይወት ወጥታ

ከእኔ ጋር ለመኖር ትወስናለች ብዬ መጓጓቴ

‹‹ሶስት መቶ ብር ትከፍለኛለህ….?››

‹‹እከፍልሻለው›በወር ሶስት ቀን ትፈቅድልኛለህ….?››

‹‹አረ ለበፊት ለሰራተኛዬ በስድስት ወር አንድ ቀን ብቻ ነው ፍቃድ እሰጣት የነበረው…››

‹‹ስለዚህ አሻሽለው…››

‹‹ለመሆኑ ሶስት ቀን ምን ያደርግልሻል….?››

‹‹አዲስ አበባ እየሄድኩ ልጆቼን የማይበት.. የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማሟላበት››

‹‹እንደዛ ከሆነ ተስማምቼያለው…››

‹‹እሺ ከነገ ጀምሮ የቤትህ ሰራተኛ የልጅህ ሞግዚት ነኝ…አሁን ለመጨረሻ ጊዜ እቀፈኝ››

ለመተኛት ትራሱንት አስተካክላ እየተዳለደለች … እኔ ተመሳሳዩን በማድረግና ለእንቀልፍ

እራሴን እያዘጋጀውና እሷንም እያቀፍኳት››

‹‹ለምንድነው ግን ማቀፌ የመጨረሻ የሚሆነው….?››

‹‹እንዴ የሄደችብህን ሰራተኛህ አቅፋህ ነበር እንዴ ምትተኛው….?››

‹‹በስመአብ ..ምን ለማለት ፈልገሽ ነው….? ››

‹‹ምንም.. ለማለት የፈለግኩት እኔም ከነገ ጀመሮ ሰራተኛህ ስለሆንኩ ላቅፍህም ሆነ

እንደዚህ ልስምህ አልችልም..ጭራሽ አብሬህም መተኛት አልችልም…›› ብላ ጉንጬን

ሳመችኝና.‹‹ደህ አድር›› ብላ አይኗቾን ጨፈነቻቸው..

እኔም ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋውና በስርአቱ አቅፉያት …ፀጉሯን እየዳበስኩ ወደ

እንቅልፍ ሳይሆን ወደ ማሰላሰል ውስጥ ገባው..እውነት ያለችው ነገር ከምሯ ሆኖ አብራኝ

ትሄድ ይሆን ….….?መቼስ ሰራተኛህ እሆናለው የምትለው የአመቱ ታላቁ ቀልድ መሆን

አለበት…ነግቶ የሚፈጠረውን ነገር ለማወቅ ቸኮልኩ..ይዤት ወደ ሀገሬ እበራለው ወይስ

እሷን በሚኒባስ ወደ አዲስ አበባ አሳፍሪያት እኔ በሀዘን እና በትካዜ ወደ ልጄ

እሄዳለው…..እስከዛሬ ለአመታ የኖርኩት ብቸኝነት አሁን አስፈራኝ…እንዴት ነበር ያን ሁሉ

አመት ያለ ፍቅር ያሳለፍኩት…….?ትታኝ ስትሄድ እንዴት ነው የምሆነው…….?አንዴት ነው

ዳግመኛ ማጣትን የምቋቋመው….….?ከእንቅልፌ ስባንን ሰዓቱ ንጊት አካባቢ ሆኖ ነበር…አስራ አንድ ሰዓት ተኩል…ቀስ ብዬ

ተጠንቅቄ መብራቱን አበራውት..ጄጄ ደረቴ ላይ ሽብልል ብላ የሰላም እንቅልፋን

እየለጠጠችው ነው፡፡አትኩሬ በጽሞና አስተዋልኳት…ፊቷ ላይ ፍጽም ሰላም እና መረጋጋት

ነው የሚነበበው…በዛ ሁሉ መከራ በዛ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ያለፈች አትመስልም…በፍፅም …

አረ እንደውም አሁን እንዲህ ሳያት ከቤተሰብ ጉያ ወጥታ የማታውቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤርጎ

ያደረች…ለማጀመሪያ ጊዜ ከእኔ ጋር የተኛች ነው የምትመስለው….

ጉዴ ፈላ… ይህቺን ልጅ በጣም ነው ያፈቀርኳት..አሁን እትኩሬ ሳያት እንኳን እንዴት የልቤ

ምት እንደጨመረ..እንዴት ደሜ በውስጤ ሞቆ መንተክተክ እንደጀመረ እኔ እና እግዜር ብቻ

ነን የምናውቀው…..አዎ ይህቺን ልጅ ከዚህ በላይ ላቅፋት ነው የምፈልገው ….ይቺን ልጅ

ከአዚህ በላይ ነው ልንከባከባት የምፈልገው….ይህቼን ልጅ ከዚህ በላይ ነው ልዋሀዳት

የምፈለገው….ይህቺን ልጅ ለዘላለሙ ነው አብሬያት መኖር የምፈልገው፡፡

ይገርመኛል ስለማንነቷ በአይኔ ያየዋቸው ከእሷም የሰማዋቸው ነገሮች እና በውስጤ ደግሞ

ስለእሷ የማስበው ፍጽም የተለያየ ነው….እንዴት ነወ ሰው በአይኖቹ ያየውን ነገር ላለማመን

የሚችለው…. ዛሬ አንድ አልጋ ላይ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ተቃቅፈን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ

ተጣብቀን ስንተኛ ለሶስትኛ ለሊት ነው…በዚህ ሶስት ቀን ሙሉ ግንኙነታችን በመንፈስ

መቆራኝታችን በብዙ እጥፍ ቢያድግም በአካል ቁርኝት በኩል ግን ከሶስት ቀን በፊት ያለበት

ቦታ ነው ያለው…ያገኘዋትም ቀን እንዲህ እሷ ከእነ ልብሶ እኔ ደግሞ እራቁቴን ተቃቅፈን

ነበር የተኛነው..ዛሬም በሶስተኛው ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ነው ተኝተን የምንገኘው…

…….እና እሷ ስለነገረቺኝ ነገር አይደለም ውስጤ እያሰበ ያለው…. ባሳለፈችው ህይወት

የተነሳ ወንዶች ላይ ባለት ጥላቻ የተነሳ እኔን ላለመጥላት ወደ ወሴባዊ ግንኙነት መግባት

እንዳማትፈልግ የነገረቺኝን አይደለም እያሰብክ ያለውት….ድንግል ሰለሆነች..ከዚህ በፊት

ወንድ ስለማታውቅ ፈርታ ወይም አፍራ እንቢ ያለቺኝ እና በድንብ ስትለምደኝ ሁሉ ነገሯን

ስትደብቅ እና ሳትሰስት ግልጽልፅ አድርጋ እንደምትሰጠኝ ነው የማስበው …፡፡ማልመውም

እንደዛ ነው…እንጂ እሷ ለእኔ አምስት አመት በውሲብ ንግድ ያሳለፈች ….በሺ ወንዶች

ወሲባዊ ላብ የወረዛች…ለሺ ቅንዝራም ወንዶች ጭኖቾን ያስጎበኝች…ከሺ ወንዶች ጋር

ተዳርታ መቶ ሺ ብሮችን የሰበሰበች....ከእድሜዋ እጥፍ የኖረች የችግሮች ማከማቻ..

የመከራ ጎተራ እንደሆነች ባውቅም ያንን እንዴት ማሰብ እችላላው..?በምንስ አቅሜ በዛ

አይነት ምስል እሷን ልሳላት እችላለው..?፡፡አዎ የሰማውትም ያየውትም ይሄንን ነው

..ውስጤ ግን እንዲህ አይደለም የሚያስበው… ልክ እንዷ ልጄን በምወዳት መጠን

ልወዳት..ልክ ልጄን በምጠብቅበት መጠን ልጠብቃት… ልክ የልጁን የነገ ህይወት

ለማሳመር በምጥርበት መጠን ለዚህችም ልለፋላት እፈልጋለው….ረዳት አልባ እና ደካማ …

ማረፊያ ጎጆ የሌላት ወፍ አድርጌ ነው የማስባት….አውቃለው እውነቱ ይሄ አይደለም..

እሷ… ይህቺ ክንዴን ተንተርሳ አንገቴ ውስጥ ተወሽቃ የተኛችው ልጅ ጥንካሬዋ ከአልማዝ

በላይ… በራስ መተማመኗ ከነገስታቶች የበለጠ...መከራ ማይበግራት…ችግር ጠምዝዞ

የማይሰብራት…ለወደደችው ህይወቷን እስከመስጠት የምትሰዋ.. የጠላችውን ህይወቱን

ለመቀማት ድፍረቱና ፅናቱ ያላት…የተራራ ግዝፈት እና ውቅያኖስን የሚያህል ጥልቀት

በሚጢጢ ልቧ ተሸክማ የምትዞር ልዩ ልጅ እንደሆነች አውቃለው….

እውነታው እሷን ለመጠበቅ..እሷን ለመንከባከብ ሳይሆን በእሷ ለመጠበቅ እና በእሷ

የእንክብካቤ ጥላ ውስጥ ለመሸሸግ የፈለኩት እኔ እራሴ ነኝ..በህይወቴ ውስጥ

የተተከለውን ስር የሰደደ ፍርሀት እንድታክምልኝ ነው የፈለኳት..በብቸኝነት እና በፍቅር እጦት

የሚዳክረውን ልፍስፍሱን እኔነቴን እንድትጠግንልኝ እና እንድታበረታልኝ ነው የፈለኳት ..ለገዛ

ሀጃዬ..ለገዛ ደንታዬ..አዎ እወነታው ያ ነው፡፡

1፡20 ላይ ባላችበት እጆቾን ዘረጋግታ ተንጠራራችና ቀስ በቀስ ዓይኖቾን ገለጠቻቸው

‹‹..አዎ ከነቃው ሁለት ሰዓት ሊሆነኝ ነው››

‹‹ሁለት ሰዓት ታዲያ ለምን አልቀሰቀስከኝም…..?ረፍዷል እኮ››

‹‹በተመስጦ እና በፍዘት እያየሁሽ …እንዴት እንደምታምሪ ከጨረቃ ውበት ጋር እንኳን

መዳደር እንደምትቺይ እያሰብኩ… በመደመም ላይ ሰለነበርኩ የሰዓቱ ርዝመት

አልታወቀኝም….››

‹‹ወሬ አለብህ…በል ተነስ››ብላኝ ቀድማኝ ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ገባች፡፡

ተነሳውና ልብሴን መለባበስ ጀመርኩ..እሷም መጣችና ከላይ የለበችውን ቲሸርት

አወለቀች…ያ እንደሰነፍ ገበሬ የእርሻ መሬት በተወለጋገ ጠባሳ እና ሰንበር የተሞላ ግማሽ

ሰውነቷን ዳግመኛ ፊት ለፊት ስትገትር ስቅጥጥ አለኝ….ደግነቱ ቶሎ ብላ ማታ የገዛውላትን

ቀሚስ አነሳችና ለበሰች…ተንፈስ አልኩ..ቀጠለችና ለብሳ ያደረችውን ሱሪ በማውለቅ

ፔስታል ውስጥ ጨመረችው…ሙሉ ዝግጅታችንን ጨርሰን ቤርጎውን አስረክበን ለመውጣት

15 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀብን፡፡

ወደ ሚኪናችን እያመራን ነው..የልቤን ምት አትጠይቁኝ.. ተፈጥርቃ በአፌ ልትወጣ

እየተንፈራገጠች ነው…የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ወደ መሰቀያው ወይም ወደ መቀያው

በፖሊስ ታጅቦ የሚሄድ ፍርደኛ በመጨረሻው ደቂቃ የሚሰማው አይነት ስሜት ነው

እየተሰማኝ ያለው…የእውነት አሁን አብራኝ ትሄዳለች…የእወነት ዛሬ ይህቺ ልጅ የእኔ ልትሆን

ነው….የእውነት ቀዝቃዛ አንሶላ ለብሼ በድን ትራስ ታቅፌ የምተኛበት ያለፈ የብቸኝነት

ህይወቴ መቋጫ ሊያገኝ ነው…

ገቢናውን ተንደርድሬ ከፈትኩላት..በዝምታ ገባችና ቁጭ አለች..ተመስገን ነው…ይህ

መልካምና የብሩህ ዕድል ብርሀናማ ምልክት ነው..አብራኝ ባትሄድ ኖሮ መኪናው ውስጥ

አትገባም ነበር፡፡ግን ለምንድነው የጨገጋት .. ..?ግን ለምንድነው ፊቷ ኮሶ እንደጠጣ ሰው

እንዲህ በጥዋቱ የተኮሰታተረው…....?ምን አይነት የሰነፍ ጥያቄ ነው እራሴን እየጠየቅኩ

ያለውት…...?ወደ ማታውቀው ሀገር እኳ ነው የምትሄደው… ተወልዳ ያደገችበት 19 አመት

የኖረችበትን ፒያሳን የመሰለች ያራዶች መንደር እኮ ነው ጥላ ልትሄድ የወሰነችው….

ብዙ ጓደኞቾን እና ብዙ ትዝታዎቾን እኮ ነው ለእኔ ስትል በመታው ወደ ማታውቀው ሀገር

ከማታውቃቸው ሰዎች ጋር ለመኖር የምትሄደው..እንደውም እሷ ስለሆነች እንጂ ሌላ

ልፍስፍስ እና ስሜተ ድፍርስ ሴት ብትሆን ኖሮ ይሄኔ ከመኮሳተር እና በዝምታ ከመሸበብም

አልፋ በእንባ ትታጠብ ነበር…በሽራፊ ሰኮንዶች ውስጥ ነው ይሄንን ሁሉ ያሰብኩት… ገቢና

ገብቼ የሹፌሩን ቦታ በመያዝ መኪናውን በማስነሳት ሞተሩ እስኪሞቅ እየጠበቅኩ

ባለውበት ሽራፊ ሰዓት…..

መኪናዋን አንቀሳቀስኩና ወደ በሩ እንቅስቃሴ ጀመርኩ.‹‹እርቦኛል›› አለቺኝ…ከሩቅ የተለቀቀ

በሚመስል የደከመና እና የተጎተተ ድምጽ

‹‹ምን ችግር አለው....?ቁርሳችንን በልተን ጉዞችንን መቀጠል እንችላለን››አልኳት ከግቢው

እየወጣን

‹‹ወደእዚህ ይሻለናል ወይስ ወደእዚህ....?››ደህና ቁርስ የምናገኘው በየትኛው አቅጣጫ

ብንሄድ እንደሆነ ከእሷ ምክር እየጠየቅኩ ነው…ምክንያታዊ ሳይሆን ግምታዊ ምክር

እንድትሰጠኝ…የነቀምትና አቅጣጫ ተወችና ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ በእጆ ምልክት

ሰጠቺኝ…የመኪናዋን አቅጣጫ ወደ እዛ አዞርኩት…የተከፈተ ቁርስ ቤት ከአስፓልቱ ግራና

ቀኝ እያየንበዝግታ እነዳው ጀመር..ግን ስራ የጀመረ ወይም የተከፈተ ቤት ለማግኘት

መነኸሪያው ድርስ መጓዝ ነበረብን…ከመነኸሪያው በተቃራኒ መንገዱን ተሸግሮ ካለ ህንጻ

ምድር ቤት ያለ ካፌ ተከፍቷል፡፡አንድ አምስት የሚሆኑ ደንበኛች በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው

ቁርስ ሲበሉ እና ትኩስ ነገር ሲጠቀሙ ይታያሉ… ወደ እዛው ነዳውና መሪዬን ጠምዝዤ

የመኪናዋን አፍንጫ ወደመሄጃችን ወደ ጉደር አቅጣጫ አዙሬ አቆምኩና

‹‹..በይ እዚህ እንብላና መንገዳችንን እንቆስቁስ››አልኳት

‹‹እሺ›› አለችና ፔስታሏን ይዛ ልትወርድ ተዘጋጀች….. ግራ ገባኝ ..በጣም

ደነገጥኩ..የድንጋጤ ግራ መጋባት፡፡

‹‹ምን ያደርግልሻል….....?ፔስታሉ ይቀመጥ እንጂ››

ትቃወመኛለች ብዬ ስጠብቅ…‹‹እሺ›› አለችና ፔስታሉን ከፍታ ጅንስ ሱሪያዋን አወጣችና

ከኪስ ውስጥ አነስተኛ የኪስ ቦርሳዋን በማውጣት ሱሪውን ወደ ፔስታሉ መልሳ ከታ

ወደነበረበት በመመለስ በአንድ እጇ የኪስ ቦርሳዋን በሌላ እጇ ሞባይሏን በመያዝ.‹‹.ቁርስ

ገባዦ እኔ ስለሆንኩ ገንዘብ ልያዝ ብዬ ነው››ብላኝ መኪናውን ለቃ ወረደች፡፡

የእፎይታ ትንፋሽ ተንፍሼ እኔም ከመኪናው ወረድኩና ቆልፌ ተከተልኳት

‹‹አንድ እንቁላል በስጋ እና አንድ ዱለት››አዘዝኩ

‹‹ አንድ ምግብ ይበቃ ነበር››

‹‹ምነው ከፋይ አንቺ ስለሆንሽ ቆጨሽ እንዴ..?››

‹‹አይደለም ..ጥዋት ስለሆነ አፒታይቱን ከየት እናመጣዋለን ብዬ ነው››አለቺኝ

‹‹ግድ የለሽም የቻልነውን ያህል እንሞክራለን..››አልኳት…..ወዲያው ሳናስበው ወደ

ዝምታችን ተመለስን…ሁለታችንም አንድ የፈራነው ነገር እንዳለ ያስታውቅብናል…ይህቺን

ከተማ መልቀቅ…ወደ ሻንቡ መብረር…ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገር…..

አንድ ልጅ እግር ሴት አንድ አመት የሚሆነው ሕጻን ልጅ የታቀፈች ከጎናችን

ተቀምጣለች….ልጇ በጣም እየረበሻት ነው…..በሀይለኛው ያለቅሳል..ዝም እንዲልላት

ልታባብለው እየሞከረች ነው…..ግን በዋዛ ሚደለል ልጅ አልነበረም….እፍ ውስጥ ጡጦ

ለማስገባት ትሞክራለች… ተንፈራግጦ ከአፉ ውስጥ በምሬት ያወጣል..

‹‹ምን ሆኖ ነው..?››አለቻት …እንደእኔ በልጁ ሁኔታ ቀልቧ የተሰረቀባት የእኔዋ ጂጂ

‹‹ጡት ስጪኝ እያለ ነው መከራዬን የሚያሳየኝ››

‹‹ጡት…!!!!››ግራ ገባኝ..አይኖቼን ወደ ደረቷ ላኳቸው… ዱባ ሚያካክሉ ግዙፍ ጡቶች

በደረቷ ግራና ቀኝ ይታዩኛል

.‹‹እና ለምን አታጠቢውም....?እናቱ አይደለሽም እንዴ....?ጡትሽ እንዳይወድቅ ፈራተሽ

እንዳይሆን....መቼስ ዘመኝኛ ሴቶች እራስ ወዳድነታችው ቅጥ እያጣ ነው››አልኳት

‹‹የልጅቷ ፊት በአንዴ ቅይርይር አለ…አይኖቾ በእንባ ተሞሉ..አረ ለቀቀችው….ልክ እንደነሀሴ

ጅረት መስመር እየሰራ በጉንጮቾ ላይ እየተንኳለለ..መርገፍ ጀመረ….ደነገጥኩ..በጣም

ደነገጥኩ

‹‹ምን አይነት ቀሺም ነህ....?የት ታውቃታለህ እንዲህ ምትዘባርቀው…..?››ጂጂ በእኔ ላይ

አውሬ ሆነችብኝ፡፡ደነገጥኩ፡፡

‹‹እኔ እኮ ስቀልድ ነው..እህቴ ይቅርታ… ማይኆን ነገር ዘባረቅኩ እንዴ..?››

‹‹ልጇን ማጥባት የማትፈልግ እናት እንዳለች እኔ አላውቅም..ለሌቱን ሙሉ እንቅልፋ በአይኔ

ሳይዞር ነው የደርኩት..እንዲመገብልኝ ያልሞከርኩት የህጻናት ምግብ አልነበረም …

ከማልቀስ በስተቀር አንድንም አልቀመሰልኝም..እና ይሄን ያህል በልጄ ምጨክን

ይመስልሀል..?፡፡››እየተነሰቀሰቀች በምሬት ተናገረች፡፡

‹‹አይዞሽ ተረጋጊ…ምን ሆነሽ ነው..?፡፡››ጅጅ ነች ልታረጋጋት እየሞከረች በሀዘኔታ

የጠየቀቻት

አሞኝ ከዋዩ ከተማ ነው ለህክምና የመጣውት …የጡነቀርሳ እንዳለብኝ ከሶስት ቅን በፊት

ነው የተነገረኝ…ለልጄ ጡት ማጥባቱት እንዳቆም አጥብቀው ነግረውኛል…እሺ ምን

ላድርግ….አሁን እዚህ የተቀመጥኩት ወድጄ መሰለህ..ጨንቆኝና የማደርገው ጠፍቶኝ

ነው..ዝም ቢልልኝ ብዬ ለመሞከር ነው….ልጇን አቀፈች… እቃዋን ሰበሰበችና መቀመጫዋን

ለቃ ወደ ታች መንገዷን ቀጠለች..ከአይኔ እስክትጠፋ በዓይኖቼ ሸኘዋት

…ምንም ልል አልቻልኩም..በጣም ነው በራሴ ያፈርኩት…እውነትም ጂጂ እንዳለችው ምን

አይነት ቀሺም ነኝ፡፡

‹‹በጣም አዝናለው..ልጅ ግን ወተት መጥባት ማለት ጡጦውን ለምንድነው እንዲህ

አልጠባም ብሎ ሚያሰቃያት፡፡

‹‹ወላጅ አይደለህ እንዴ ..?ስለእናት ጡት እና ስለ ላም ወተት ልዩነት አታውቅም....?የእናት

ጡት በሜኔራልና መአድን የበለፀገ እረሀብ ማስታገሻ ምግብ ብቻ አይደለም……የእናት ጡት

ከወተትነቱ ባሸገር ከእናቲቱ ልብ ከመነጨ ፍቅር ጋር የተቀየጠ የመንፈስ ምግብም ጭምር

ነው…ለዛ ነው የእናት ጡት ለህጻኑ ሙሉ ጤንነት የሚያጎናፃፈው …ለዛ ነው የእናቱን ጡት

በበቂ መጠን የጠባ ልጅ ዕድሜውን በሙሉ በአካልም በመንፈስም ፅኑና ጠንካራ

የሚሆነው..

አንድ ህጻን ልጅ የእናቱን ጡት ከላም ወተት ብዙ እጥፍ እስበልጧ የሚወደውና

የሚፈልገው የእናት ጡት የበለጠ ጣፋጭ ስለሆነ ይመስልሀል..አይደለም የእናት ፍቅርም

አብሮት እየተቀየጠ ስለሚፈስለት ነው….አንድን ህጻን በደህንት ከኖረበት የእናቱ መህጽን

ወጥቶ ከእናቱ የሚያገናኛው እትብቱም ሲበጠስበት በደመነፍስም ቢሆን ያዝናል

ያለቅሳል..ግን ያንን የሚያካክስለት ጡት ነው… ቀጥታ የእናቱን ጡት አፍ ውስጥ ሲገባ

በእትብቱ ምትክ ከእናቱ ሚገናኝበት የፍቅር ድልድይ ይሆንለታል…

‹‹ገባኝ..››አልኩ ከመግባትም በላይ ገለጻዋ እየገረመኝ..ቁርሱ ቀረበ… በቅጡ ግን

አልበላነውም …ሁለታችንም የምግብ ፍላጎታችን ቁልፍልፍ ብሎ ነበር..እንደነገሩ ቀማምሰን

ከጨረስን ቡኃላ ሂሳብ ከፈለች..ከዛ ድንገት..ፈጠን ብላ ቀድማኝ ተነሳች ወደ… እኔ

ቀረበች… ጉንጬን ጠበቅ አድርጋ ሳመችኝና ..ምንም ሳትናገር..ፊቷን አዙራ መንገዷን

ቀጠለች….አፌን ደም ደም አለኝ…..ምን እያደረገች ምን እየሆነች እንደሆነ መገመትም

እልቻልኩም….ከመቀመጫዬም አልተነሳውም..በተቀመጥኩበት ደንዝዤ በአይኔ ብቻ

እየተከተልኳት ነው..ዞር ብላም አላየችኝ..እንዳቀረቀረች በተጓተተ እርምጃ ቀጥታ እስፓልቱን

ተሸገረች… ሄደች …. ተጠመዘዘች..መነኸሪያ ጊቢ ውስጥ ገብታ ከእይታዬ ተሰወረች፡፡

እውነትም ይህቺ ወፍ ነች…የፒያሳ ሚስጥራዊ ወፍ……ምን ያህል ጊዜ እዛው ትታኝ የሄደቺኝ ቦታ ከነ ድንዛዜዬ እንደቆየው አላውቅም....ምን ሰዓት

ላይ መቀመጫዬን ለቅቄ መኪናዬ ውስጥ እንደገባውም ትዝ አይለኝም…ጉደርን አልፌ

ተራራማ እና ጠመዝማዛውን መንገድ ተያይዤው ጌዶ ከተማ ልገባ ሀያ ኪሎ ሜትር አካባቢ

ሲቀረኝ ነው በመጠኑ ወደ ቀልቤ የተመለስኩት..

ቆይ ግን ሳላውቅ ያስቀየምኳት ነገር ይኖር ይሆን እንዴ…..?ሁሉ ነገር በሳለም እየተጓዘ

አልነበረ እንዴ…..?ለሊት በእንቅልፍ ልቤ በማይሆን መልኩ የማይሆን ቦታ ነካክቼያት

ስሜቷን እስቆጣዋት ይሆን እንዴ..?ምንም ትዝ ሚለኝ ነገር የለም፡፡ነው ወይስ ያቺኝ እናት

ለቀልድ ብዬ የተናገርኩት ነገር ለእኔ ያላትን አመለካከት እንድትቀይር አድርጓት

ይሆን..?..አይ እንደዛማ አይሆንም…ለቀልድ ብዬ ባዳለጠኝ የምላስ ወለምታ ያን ሁሉ ፍቅር

..ያን ሁሉ ተስፋ እንዲህ በአንዴ ገደል አትከተውም..አዎ በፊቱንም ውሳኔዋ ወደ ፒያሳዋ

መመለስ ይሆናል

…አዎ እንደዛ ነው..እንደዛ መሆኑ ደግሞ ያንገበግባል…….አካባቢዬን ቃኘው …የት

እንደደረስኩ ሳውቅ ግርም አለኝ…እንዴት እንዴት ነው የነዳውት....?እንዴትስ ከሌላ መኪና

ጋር ሳልጋጭ....?ያስ ባይሆን እንዴት መንገድ ስቼ ወደ አንዱ ገደል ያልተሸቀነጠርኩ…...?ዝ

ግንን አለኝና አማተብኩ..አማትቤ ዞር ስል ከጎኔ ያለው መቀመጫ ስር ፔስታል አየው …

መኪናውን መንዳቴን ሳላቋርጥ ተንጠራራውና አነሳውት … አዎ የእሷ ቲሸርት እና ጄንስ ሱሪ

ነው…በመስኮቴ አሻግሬ ወደ ቁልቁለቱ ጫካ ውስጥ አርቄ ወረወርኩት….

እንኳን ቡትቶዋን ምኗንም አልፈልግም….አትረባም…እንዴት እንደዚህ ታደርገኛለች…..?

እንዴት እንደዚህ እንደህጻን ልጅ ታታልለኛለች…..?በእሷ ቤት እኔ የገጠር ልጅ ፋራ እሷ

የፒያሳ ልጅ አራዳ መሆኖ ነው….፡፡እሰከአሁን ለሶስት ቀን ስትደበርብኝ ነበር ማለት ነው…..?

ስለእሷ ማሰብ አልፈልግም፡፡›..ፎከርኩ …ግን ውስጤ አሁንም እየተቃጠለ ነው…የሆነ ሹል

ጦር መሳይ ነገር ልቤን እየሰቀሰቀኝ ነው…እና ደግሞ ድክምና ስልምልም እያደረገኝ ነው

…..እናንት በአንዴ መኖር እንዲህ ያስጠላል እንዴ…..? ግን ከዚህች ልጅ ጋር ያሳለፍኩት

ሶስት አመት ነው ወይስ ሶስት ቀን…....?ግራ ግብት አለኝ ፡፡ የእውነቴን እኮ ነው..በሶስት

ቀን ትውውቅማ እንደዚህ ብትንትኔ አይወጣም..እንደዚህ ፍርክስክስ አልልም….፡፡

ልጄ በጣም ናፈቀቺኝ ..መኪናዋ እንደፕሌን ክንፍ ኖሯት በአየር ላይ ብትበርልኝ እና ፈጥኜ

ሾንቡ ብደርስ ደስ ይለኝ ነበር..አሁን የሚያጽናናኝ የልጄ ፈገግታ ብቻ ነው..አሁን ሊያረጋጋኝ

የሚችለው የልጄ ትንፋሽ ብቻ ነው…ውስጥ እግሬን ሁሉ እያቃጠለኝ ነው…፡፡

….ጌዶ ደረስኩ… ዝምብዬ ከተማውን ሰንጥቄው ላልፍ አልኩና ቢያንስ እያቅለሸለሸኝ

ያለውን ነገር ያስታግስልኝ እንደሆን ጥቁር ቡና ልጠጣበት ፈለኩ… መኪናዬን አንድ የጀበና

ብና የሚሸጥበት ቤት አጠገብ አቆምኩና ወርጄ ብና አዘዝኩ…እየጠጣው እያለው ሞባይሌ

ድምጽ አሰማች… ተደውሎልኝ አይደለም…የመልዕክ መጥቶልሀል አብሳሪ ድምጽ

ነው..በግዴለሽነት ከፈትኩት…አፌውስጥ የነበረው ብና ወደ ስርኔ ሾለከ… ትን አለኝ

..እየጠጣው ያለውትን ሲኒ በድንጋጤ ለቀቅኩት …አካባቢው ያሉት ሰዎች ሁሉ

በረገጉ‹‹..አይዞህ…እኔን…ውሃ ጠጣበት››ሁሉም ሊያጽናኑኝ ሞከሩ …ማንንም አልሰማው…

ከኪሴ 5 ብር አወጣውና ጠረጵዛ ላይ አስቀመጬ ቦታውን ለቅቄ ሄድኩ …መኪናዬ ውስጥ

ገባው……

ሞተሩን አስነሳውና የመኪናዬን መሪ ጠምዝዤ አዞርኩ..ወደ መጣውበት ተመልሼ መንዳት

ጀመርኩ..በቃ ላብድ ነው….በትክክል እያበድኩ ነው……ይህቺ ልጅ እያሳበደቺኝ ነው….ሀያ

ኪሎ ሜትር ያህል ነዳው አቆምኩ…እና መንገዱን ተሸገርኩ…ከመኪናዬ ወረድኩና ቀስ ብዬ

በጥንቃቄ ገደሉን ወደ ታች እየተንሸራተትኩ ወረድኩ….ጫካ ውስጥ ገባው … እሾክ

ይወጋኛል አውሬ ያገኘኛል ብዬ ሳልጨነቅ ማሰስ ጀመርኩ… አዎ አገኘውት ..፡፡ተበታትኗል …

ጂንስ ሱሪው ለብቻው የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ተንጠልጥሏል… ቲሸርቱ ደግሞ ለብቻው መሬት

ላይ ተነጥፎ አገኘውት… በፈገግታ ሁለቱንም ከያሉበት አንስቼ ያዝኩ… ፔስታሉን ለማግኘት

ግን አልተሳካልኝም..ምን አልባት ንፋስ ወስዶት ይሆናል…አላስጨነቀኝም ..፡፡በዳዴ የመሄድ

ያህል እየቧጠጥኩ አቀበቱን ወጣው..ለካ መውጣት የመውረድን ያህል አይቀልም

…..ከወጡ መውረድ የሚከብደው ለካ ተመልሶ መውጣት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ

ከልምድ ስለሚታወቅ ነው፡፡

….እያለከለኩ ወደ መኪናዬ ሄድኩና ገቢና ገባው…ሱሪውን በስነስርአትና በጥንቃቄ

አጣጠፍኩ… ቲሸርቱንም በተመሳሳይ አጣጣፍኩት ..በፍቅር ወደ አፍንጫዬ አስጠግቼ ወደ

ውስጤ ማግኩት..በጣም በጥልቀት ሳብኩት..ጠረኗን ለማግኘት..አዎ ጠረኗ ወደውስጥ

ከማግኩት አየር ጋር ተቀላቅከሎ ወደ ውስጤ ገብቶ በሰውነቴ ውስጥ በመበተኑ እያንዳንዱ

የሰውነቴ ሴል ሲነቃቃ እና ሲፍታታ ታወቀኝ…ልብሱን ቦርሳዬ ውስጥ ከእኔ ልበሶች ጋር አንድ

ላይ አስቀመጥኩት… መኪናውን አንቀሳቀስኩ ቦታው ለማዞር ስለማይመች ሰፋ ያለ ቦታ

ለማግኘት የተወሰነ መንገድ ወደ ፊት መንዳት ነበረብኝ… ብዙ ተቸግሬ ነው ያዞርኩት….አሁን

ጭልም ባለ ሳይሆን በጭላንጭል ቢሆን አጨንቁሮ በሚታይ ተስፋ በመረጋጋት እየነዳው

ነው ..ተመልሼ ጌዶ ደርሼያለው….ዋናውን የአስፓልት መንገድን ለቅቄ ወደ ቀኝ ታጥፌ

የሻንቡን መንገድ ይዤያለው…አሁን እንደቅድሙ ቡና አላማረኝም ከተማዋን ሰንጥቄ

አለፍኩ….

ወይኔ የእኔ ነገር እንዲህ ያደረገኝ ምን እንደሆነ ሳልነግራችሁ… ..ማለት የጽሁፍ መልዕክት

ከባንክ ቤት ነው የተላከልኝ … የባንክ ደብተሬ ውስጥ 100 ሺብር እንደገባልኝ ሊነግሩኝ

ነው…ብሩ ወደ እኔ መላኩ አንድ ጭልም ያለ ተስፋዬን በመጠኑ አለምልሞልኛል..መቼም

ልታገኘኝ ባትፈልግ ኖሮ ብሩን አትልክም ነበር…የሚል ሀሳብ በውስጡ እንዲጸነስ ምክንያት

ሆኗል… ለዛ ነው ወደኃላ የተመለስኩት..አንድ ቀን ማለቴ በቅርብ..ነገ ወይም ተነገ ወዲያ

መጥታ ሱሪዬስ ስለትለኝ ጥዬዋለው ልላት ድፍረቱን ከየት አገኛለው… ለዛ ነው የጣልኩትን

ልብሷን ፍለጋ ወደ ኃላዬ ያን ሁሉ መንገድ የተጓዝኩት…..…

ግን ይህቺን ልጅ እኮ ላምናት አልችልም …..ብሩን ወደ እኔ ደብተር ማስገባት ያሰበችው

ቁጥሩንም ለልጁ የላከችለት ትናንት ማታ ነበር..ማታ ደግሞ ለእኔም ብዙ ነገር ብላኝ ነበር…

አብራኝ እንደምትመጣ…ለልጄ እናት መሆን እንደምትፈልግ ቃል ገብታልኝ ነበረ… ግን

አላደረገችውም..የማታ ንግግሯን ሙሉ በሙሉ ሰርዛዋለች..ታዲያ ይሄንንስ ለልጁ ማታ

የነገረችውን ነገር እንዳያደርገው መንገሩን ዘንግታው ቢሆንስ …..?ይሄንን ሳስብ ከእንደገና

በሰውነቴን ጥልቅ ድረስ ቅዝቃዜ ተሰራጨብኝ..ትንፋሼን ወደ ውስጥ መሳብ

አቃተኝ…..ወይኔ ሰውዬው … !!!!መኪናዋ ወዲህና ወዲያ ጆካ ማምታት ጀመረች…

እንደምንም በደመነፍስ ፍሬን ይዤ አቀዘቀዝኩና አቆምኩ…..መሪው ላይ ተደፍቼ ለመረጋጋት

መክርኩ…አስር የሚሆኑ ደቂቃዎችን በደነዘዘ ስሜት ካሳለፍኩ ቡኃላ ስልኬን አነሳው…

ደወልኩላት..በአራተኛው ጥሪ ተነሳ….

‹‹ሄሎ..››

ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ገባው‹‹ ልጁ ብሩን ተሳስቶ አስገብቶታል››

‹‹የቱን ብር..?››የደነገጠ እና የሚርገበገብ ድምጽ ተሰማኝ..ከሰማውት ድምጽ በእጥፍ

የእኔም...ድንጋጤ ጨመረ…

‹‹አይዞሽ…የባንክ ቁጥርሽን ላኪልኝና አሁን ዋዩ ወይም ፊንጫአ ስደርስ መልሼ

ልክልሻለው››

‹‹ምኑን ነው ምትልክልኝ..?››

‹‹መቶ ሺ ብሩን ነዋ…ደብተሬ ውስጥ እንደገባ አሁን በሚሴጅ አሳውቀውኛል››

‹‹…እ እሱን ነው እንዴ....?››ብላ ሌላ ቅዝቅዝ ያለ ስሜት ውስጥ ከተተቺኝ

‹‹አዎ..በሚሴጅ የባንክ ቁጥርሽን ላኪልኝ››

‹‹የባንክ ደብተር የለኝም…አንተ ጋር እንዲቀመጥልኝ ነው ያስላኩት››

‹‹ለምን..?››

‹‹እንዴት ለምን .. ..?ይቀመጥልኛ፡፡››

‹‹ይቀመጥልኝ ማለት .. ..?ትመጪያለሽ …..?ማለት ብርሽን ልትወስጂ››

‹‹በህይወቴ ወሳኝ የሆነ አንድ መፈጸም ያለብኝ የረጅም ጊዜ ዕቅድ አለኝ….ያንን ጉዳይ

በዕቅዴ መሰረት ለመፈፀም ከአስር እስከ ሀያ ቀን ይፈጅብኛል..ከተሳካልኝ ወዲያው

እመጣለው…ማለቴ ብሩ ጋር ሳይሆን አንተ ጋር..ይቅርታ አንተ ጋር ሳይሆን ልጅህ ጋር…

ልጅህን ልጄ ላደርጋት…..››

‹‹እቅድሽ እንዳሰብሽው ካልተሳካልሽስ..?››

‹‹ካልተሳካልኝማ አልተሰሳካልኝም ማለት ነው..ከዛ ቡኃላ እኔም የለውም ማለት ነው››

‹‹አልገባኝም..?››

‹‹በቃ.ጂጂ የምትባል ልጅ የለችም ማለት ነው..እስከ ዛሬ ወር ድረስ ያለህበት ድረስ

ካልመጣው የለውም ማለት ነው..መቼም አልመጣም መቼም አታገኘኝም ማለት ነው…››

‹‹የማትረቢ ነሽ …..የሰው ስሜት መሰባበር የሚያስደስትሽ መጥፎ ሰው ነሽ….በይ አሁን

ስለሌላው ነገር መቀባጠርሽን አቁሚና የባንክ ቁጥርሽን ላኪልኝ..አንቺን ነው እንጂ ብርሽን

አልፈልግም….››ብስጭትጭት ..ንጭንጭ..እልኩባት

‹‹እንግዲያው የባንክ ደብተር የለኝም አልኩህ እኮ››

‹‹የሌላ ሰው ቢሆንም ላኪልኛ …ትቀልጂ.. ››

‹‹ካንተ በላይ የማምነው ሌላ ሰው የለኝም››

‹‹አትቀልጂ.. እኔ መጫወቻ አሻንጉሊትሽ አይደለውም….››

‹‹አውቃለው አይደለህም ..አንተ እስከዛሬ ካወቅኮቸውና ከቀረብኮቸው ሰዎች መካከል

በጣም የተለየህ ተወዳጅ ሰው ነህ….አንተ የህልሜ ወንድ ነህ…በህይወት ካለው ካንተ ርቄ

መኖር አልፈልግም….ሆዴ አንድ ወር ጠብቀኝ ..አንድ ወር ብቻ…..እስከዛ ካልመጣውልህ

ተስፋ ትቆርጥብኛለህ..እስከዛ ካልመጣውልህ ትረግመኛለህ..እስከዛ ካልመጣውልህ

ትጠላኛለህ…እስከዛ ካልመጣውልህ ትረሳኛለህ…››

‹‹…ሄሎ አንቺ ምን እያልሽ ነው....?ሄሎ ..ሄሎ እኮ ነው የምለው..?››ስልኩ

ተዘግቷል..መልሼ ደወልኩ ጥሪ አይቀበልም ይላል….

ምን እያለች ነው....?ምንስ እያደረገች ነው....?ከእኔ እና እሷ ግንኙነት የሚበልጥ ምን

አይነት የህይወት አላማ ቢኖራት ነው…..?ከሞት ወዲህ ማዶ እና ከሞት ወዲያ ማዶ

መሸጋገሪያ ድልድይ ላይ የሚያቆም ጉዳይ ምን አይነት ጉዳይ ቢሆን ነው....?ከመስመሩ

በቀኝ በኩል ከወደቅኩ በህይወት ስለምኖር ወደ አንተ እመጣለው..ከመስመሩ ወደግራ

ከወደቅኩ ደግሞ ወደ ሞት አለም የሚያደርስ ገደል ውስጥ ስለምሰምጥ መምጣት

አልችልም እለቺኝ እኮ ..አዎ ቀጥታ እንደዛ ነው ያለቺኝ..…ልክ በእሳት ተንቀልቅሎ

እንደሚንበለበል የመስቀል ደማራ ወደ ምዕራብ ወደቀ ወደ ምስራቅ እያልን አወዳደቁን

በማየት ትርጉሙን ለመተንበይ እንደምንጨነቅ ….ህልውናን ለእድል አደራ መስጠት…

አንደምንም መኪናዬን አስነሳውና ጉዞዬን ቀጠልኩ… ዋዩን አለፍኩ…ገበቴን በድን ሆኜ

ሰነጠኳት… ፊንጫአ ደረስኩ ..የፊንጫአ ከተማ እንኳን ደህና በጣችሁ ብላ እንግዶቾን

የምትቀበለው በአስፓልቷ ነው… ከጌዶ የጀመረው ኮረኮንች መንገድ ልክ ከተማዋ መግቢያ

ጋር ያበቃና አስፓልቱ ይጀምራል ከተማዋ ስታልቅ አስፓልቱም አብሮ ያልቃል..›

እኔ ግን እስፓልቱ ከማለቁ በፊት መኪናዬን አቆምኩና የባንክ ደብተሬን ይዤ መንገዱን

ተሸገሬ ወደ ንግድ ባንክ ገባው….አዎ ገንዘብ ማውጫ ፎርም ላይ 100 ሺ ብር ጻፍኩና

ፈርማዬን በጥንቃቄ ፈርሜ አዘጋጀው…ሌላ ገንዘብ መላኪያ ፎርም አወጣው…የባንክ ደብተር

ቁጥር ባትልክልኝም በስሟ መላክ እችላለው….የሷን ብራም ፍቅሯንም እኔ ጋር አኑሬ

በስቃይ ማቃተት አልፈልግም …. ቢያንስ ብሯን ትውስድልኝ…ስለዚህ በስሟ

እልክላታለው…፡፡

ቀን ጻፍኩ..የላኪ ስም በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ሙሉ ስሜን ሞላው…የተቀባይ

ስም..ጂጂ..ተሳሳትኩ..ለካ እጅጋየው ነች….ግን እጅጋየው ማ…...?አላውቅም…የአባቷን

ስም አላውቅም..ምን አይነት ቀሺም ነኝ..ግን ይሄማ ቅሽምና አይደለም…ምን ጊዜ ኖሮኝ ገና

እሷን እንኳን በደንብ አውቄ መች ጨረስኩ …..?ለማንኛውም ስልኬን አወጣውና

ደወልኩላት..አሁንም ስልኳ ጥሪ አይቀበልም..ደገምኩት ተመሳሳይ ነው…የሞላውትን

ሁለቱንም ፎርም ጭምድድ አድርጌ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ወረወርኩና

ደብተሬን መልሼ ኪሴ ውስጥ በመክተት የባንክ ቤትቱ ግቢ ጥዬ ወጣው …ወደ መኪናዬ

ገባወና ነዳውት ….አሁን በቃኝ….. እንኳን ከእናንተ ጋር ከእራሴ ጋርም የማውራት አቅሙም

ሞራሉም የለኝም …

ይህቼ ልጅ መልሳ ወደ ህይወቴ ካልመጣች በስተቀር ከእናንተ ጋር መገናኘት

አልፈልግም…..ላወራችሁ ፍላጎቱም አቅሙም የለኝም..በቃኝ…ዝም ማለት ነው

የምፈልገው..ማሰብ ደክሞኛል..ማውራትም ደክሞኛል…

.

.

.

.

እንግዲህ ዋቅቶላ ጂጂ ዳግመኛ ወደ ህይወቴ እስካልተመለሰች ድረስ ምንም

አላወራችሁም ካለ ልናስገድደው አንችልም…ህገ መንግስቱም አይፈቅድልንም…ግን አንድ

ነገር አስቤያለው..ለምን ጂጂን እንከተላትም..እዛ አንቦ መነኸሪያ ጥለናት አይደል እሱን

ተከትለኝ ፊንጫአ ድረስ የመጣነው..እስኪ ደግሞ ወደ እሷ እንመለስና ታወራን እንደሆነ

እንሞክር….ከመቀመጫ ስነሳ.. ወደእሱ በፍጥነት ስራመድ… ጎንበስ ብዬ ጉንጩን ስስመው… ፊቴን

አዙሬ እና አንገቴን ደፍቼ ወደፊቴ ስርመድ..አስፓልቱን ተሸግሬ መነኸሪያ ግቢውስጥ

ስገባ..ይህን ሁሉ በብዥታ እና በደመነፍስ ነበር የከወንኩት….እዛ መቀመጫ ላይ ጥዬው

የመጣውት ሌላ ሰውን ሳይሆን የገዛ ግማሽ አካሌን እንደሆነ ነው የተሰማኝ..ነፍሴም

ስጋዬም ተገምሶ የቀረ…

ቋንቋ ድርጊትን በአግባቡ መግለፅ እና ማስረዳት ይችላል….ስሜትን ለመግለፅ ግን አቅም

ያንሰዋል…..፡፡ በፍፅም በቂ የሆነ አቅም አይኖረውም…በተለይ አንዳንድ ስሜቶችን ዛሬ እኔ

እንደተሰማኝ አይነት ስሜቶችን በትክክል አፍታቶና በታትኖ ለለማስረዳት ቃላቶች

ተሰባጥረው እና ተቀናብረው የሚፈጥሩት ዓረፍተ ነገር በቂ ሊሆን አይችልም….ዝም ብሎ

ሙከራ ነው..ላይ ላይን መዳከር…

...ወይኔ ጉዴ አንባዬ በጉንጬ ተንኳሎ እየወረደ ነው..ይሄ በጣም የሚገርም ነገር

ነው..ደግሞ የተለየ ለቅሶ ነው እያለቀስኩ ያለውት.. በአንድ አይኔ ብቻ ነው እንባዬ

የሚፈሰው…የአንድ አይኔ ምንጭ አሁንም እንደደረቀ ነው…..ቢሆንም ግን በአንድ አይኔም

ቢሆን እያለቀስኩ ነው…መነኸሪያ ውስጥ ገብቼ አጥር ጥግ ይዤ ድንጋይ ላይ ቁጭ

ብያለው….እንደዚህ ያደረግኩት አስቤበት አይደለም…ወደ አዲስአባ የሚሄደው ሚኒባስ

የትኛው እንደሆነ..? የት ጋር እንደምሳፈር…ወያላዎች ሲጣሩ ሰምቼም ሆነ ካፔላ አንብቤ

ወይንም ሌላ ሰው ጠይቄ ልሳፈር የምችልበት ሁኔታ ላይ አይደለውም…..ጆሮዎቼም

ተደፍነዋል አይኖቼም ታውረዋል….

እርግጥ ማታ የዘበራረቅኩት ነገር ትክክል እንዳልነበረ እየተሰማኝ ነው..አዎ

አጎጉቼዋለው…‹‹አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል›› ይባል የለ..በእንደእኔ አይነቱ ላይ

የተተረተ ነው…. እርግጥ በወቅቱ እኔም ተወዛግቤ ነበር…አንድ ልቤ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን

ተከትለሺው ሂጂ ሲለኝ… ሌላው ልቤ ደግሞ ወደ ፒያሳ ሲጎትተኝ ነበር፡፡

ይሄን ሰው በጣም ተሸንፌለተለው..ተሸንፌለታለው ስል አፍቅሬዋለው ለማለት አይደለም…

እርግጥ ለእሱ ለራሱ እንዳፈቀርኩት ነግሬዋለው…ልዋሸው ፈልጌ አይደለም..ግን ከፍቅር

የሚበልጥ ስሜት ነው ለእሱ እየተሰማኝ ያለው…ምን ማለቴ ነው…...? ከፍቅር የሚበልጥ

ስሜት ማለት ምን ማለት ነው…...?ምን አልባት ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር…...?አንድ ሰውን

ማፍቀር ማለት ለዛ ሰው የሚሰማን በጣም የተጋነነ እና ጫፍ ድረስ የተለጠጠ መውደድ

ማለት ነው…..አዎ ያንን አውቃለው..እኔ ግን ለዚህ አይነት ስሜት የታደልኩ ሰው

አይደለውም…ይሄንን ስሜቴን ሮማን ድሮ.. ገና ድሮ ከማንነቴ ውስጥ ሰርዛዋለች….የቀረውን

እንጥፍጣፊ ስሜት ደግሞ ግብዝ እና ትምክህተኛ ወንዷችን ቀን በቀን ተፈራርቀው

አንጠፍጥፈው ደምስሰውታል፡፡

ዋቆቶላን ሳገኘው…ከእሱ ጋር ያሳለፍኳቸው ቀናት …በቃ ሰው እንደሆንኩ እንዳስብ ነው

ያደረገኝ….አባቴ ይመስለኛል..ታላቅ ወንድሜ ይመስለኛል..አጎቴም ይመስለኛል….ከእሱ ጋር

ስሆን በብዙ የስጋ ዘመዶቼ ተከብቤ ምፈነድቅ ይመስለኛል…ይሄን ደግሞ ለዘመናት ከፍቅር

በላይ ስራበው የኖርኩት ስሜት ነው….ለአንድ ሰው ምንም አይነት ዘመድ ኖሮት ካለማወቅ

በላይ ስቃይ የሚሆንበት ነገር የለም….እና ዋቅቶላን ሶስት ቀን ሙሉ ስከተለው የዋልኩት

የማንነቴ ክፋይ ነው ብዬ አስቤ ነው…ይሄንን ክፍተት የደፈነልኝ ስለመሰለኝ ነው…የሆነ

ለዘመናት ጠፍቶ በተአምር ያገኘውት ዘመዴ.. የቅርብ ስጋዬ ..ታላቅ ወንድሜ መስሎኝ

ነው…፡፡

ተከትዬው ላለመሄድ የወሰንኩት አሁን ቁጭ ብለን ቁርስ እየበላን ሳለ ሳይሆን ለሊቱን

ነው…ለሊት እሱ ደረት ላይ ተለጥፌ በእቅፉ ውስጥ ሆኜ አይኖቼን ጨለማው ላይ አፍጥጬ

ለሳዕታት ሳስብ ነበር…..የእሱ አቅፍ ማለት ለእኔ የእናት ማህፀን ማለት ነው….ሲያቅፈኝ

ፍጽም ደህንነት ፍጽም ሰላም ነው የሚሰማኝ…እናቴን ካጣው ቡኃላ ፍጽም ተሰምቶኝ

የማላውቀው አይነት ሰላም…አዎ ሁሉ ነገር እንዳዛ እንዳቀፍኩት ለዘላለም ቢቀጥል ምኜቴ

ነው.. ይሄንን በእሱ እቅፍ ውስጥ የማገኘውን ደስታ ላለማጣት ስል ገነት እንኳን የእኔ

ብትሆን መተው እችላለው…አዎ ምንም ሳላቅማማ እተዋታለው…፡፡ግን በቀሌን ልተው

አልችልም..ፈጽሞ ሮማንን ለማጥፋት ለወራት የነደፍኩትን እቅድ መሰረዝ አልችልም….ለዛ

ነው ጥዬው ለመመለስ የወሰንኩት..አትፍረዱብኝ ፡፡ ይሄ በቀል ለእኔ ከገዛ ህይወቴ በላይ

ዋጋ አለው….፡፡ይሄንን ደግሞ ለእሱ ላስረዳው አልችልም..እንዴት አድርጌ..?፡፡ ስለዚህ

ዝም ብዬው መሄድ ነበር ያለብኝ ….ያደረግኩትም እንደዛው ነው….፡፡

ከአንድ ሰዓት ቡኃላ ይመስለኛል…አዲስአባ አዲስአባ የሚል የጥሪ ድምጽ በጆሮዬ ገባ…

የድንጋይ መቀመጫውን ትቼ ተነሳው..መንቀሳቀስ ግን አልቻልኩም..እግሬ አብጦ ዝሆኔ

የነፋፋው ይመስል ያበጠ መሰለኝ..ከእግሬም አልፎ ጭንቅላቴ ድረስ ነው ብዥ ያለብኝ….

ከድንዛዜዬ ለማገገም 5 የሚሆኑ ደቂቆችን ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ ማበከን የግድ ብሎኝ

ነበር..ከዛ ቀስ በቀስ እያለማመድኩ ወደ ሚኒባሱ ተራመድኩና ተሳፈርኩ…..ሚኒባሱ

እስኪሞላ ሃያ ደቂቃ ቆየን…

ይሄኔ ሄዶ ይሆን .. ..?ምን ተሰማቶት ይሆን…..?ልደውልለት ይሆን…..?ከአምስት ጊዜ

በላይ ስልኬን ለመደወል አመቻችቼ ነበር.. ላደርገው ግን አቅም አልነበረኝም…፡፡

አንቦን ለቀን ወጣን ቡራዩ ልደርስ 25 ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረኝ ነበር ስልኬ የጠራው…

….እሱ ነው የደወለው ..አዎ እሱ ነው ..ምን ማድረግ አለብኝ....?ዝም ልበለው....?

ላንሳው...?.ነፍስና ስጋዬ ነው የተላቀቀው…..ግን አነሳውት….

…..እሱባለው የእቁብን መቶ ሺ ብር በእሱ ደብተር እንዳስገባ ሊነግረኝ ነው

የደወለልኝ…..እና ያ በመሆኑ ደግሞ ከገመትኩትም በላይ አበሳጭቶታል…..የላኩለትን ብር

መልሼ እንድወስድለት ፈልጎል….መጨረሻ በስድብና በእርግማን ሲያንቧርቅብኝ

ድንጋጤውን መቋቋም አልቻልኩም… ጠረቀምኩት…. በፍጥነት መለሶ ሳይደውልልኝ በፊት

ሙሉ በሙሉ ስዊች ኦፍ አደረግኩት..

ምንድነው የሰራውት…...?ወራጅ ሁሉ ማለት አምሮኝ ነበር..እርግጠኛ ነኝ እራሴ የምነዳው

የግል መኪናዬ ቢሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት ምንም ሳላቅማማ ወደ ኃላ ተመልሼ ወደ እሱ እበር

ነበር …አዎ በርሬ እሄድና ጉያው ውስጥ ሽጉጥ ብዬ ለሳዕታት ፀጥ ብዬ የሰላም እንቀልፍ

እተኛ ነበር…ግን አሁን ምንም ማድረግ አልችልም… ወራጅ ብዬ ብወርድ ወደኃላም ሆነ ወደ

ፊት መጓዝ አልችልም..ወደ ሁለቱም አቅጣጫ ትራንስፖርት ማግኘት አልችልም…አውላላ

ሜዳ ነው….በእግርም የማይሞከር ነው..ስለዚህ ያለኝ አንድ ምርጫ ስሜቴን ዋጥ ማድረግ

ነው…ማፈን..፡፡የታፈነ ነገር ደግሞ ይቆያል እንጂ መፈንዳቱ አይቀር …እና

እንዳልፈነዳላችሁ፡፡

የተሳፈርኩበት ሚኒባስ አስኮ መነኸሪያ ወስዶ ጣለኝ …..ቀጥታ ወደ ፍል ውሀ ነው

የሄድኩት… ሰውነቴ ሲጠራ እና ሲነቃቃ ውስጤም ይፍታታልኛል ብዬ በማሰብ…አስከ12

ሰዓት እዛው ቆየው…አዎ ያሰብኩትን ያህል ባይሆንም በተወሰነ መልኩ ተረጋግቼያለው..

ግን ፈልውሀን ለቅቄ ወደፒያሳ መንገዴን ስቀጥል.. በሩቅ ያየውት ሰው ሁሉ ዋቅቶላን

እየመሰለኝ ጠርቼ ላስቆመው ሮጬ ልይዘው እፈልጋለው…እንዴት አንድ ሰው ሌላ ሰውን

እንደዚህ ይርባል…..?በፊት ‹

ሰው ራበኝ› ሲሉ ስሰማ ማጋነን ይመስለኝ ነበር…ለካ ሰውን

መራብ ከምግብ በላይ ነው ስጋንም መንፈስንም የሚያደክመው…ወደ ቤቴ አይደለም

የሄድኩት…

አሁን ጋሼን ማግኘት አለብኝ ..ከዚህ ቁዘማ ውስጥ ሊያወጣኝ የሚችለው የጋሼ ምክር ብቻ

ነው፡፡

ደረስኩና ገርበብ ያለደረስኩና ገርበብ ያለውን የቤቱን በራፍ ገፋ አደረግኩት… ሲጢጢ አለና ተከፈተልኝ..ሹልክ

ብዬ ገባው…ጋሼ አልጋው ላይ ጋደም ብለው መፃሀፍ ቅዱስ ያነባል…አይኛቸውን ወደ በራፍ

ሲመልሱ ተመለከቱኝ…ያ የተሸበበ ጨምዳዳ የሽማጊሌ ፊታቸው እየተላቀቀ… እየፈገገ

ሲደምቅ ታየኝ… ሲያነቡ የነበረውን መፃፋ አጥፎ ከመኝታቸው ቀና ብለው ተነሱ….››

‹‹አንቺ ወፍ የት አባሽ ጠፍተሸ ነበር...?ደግሞ አለባበስሽ ..ፐ..ፐ..ፐ እንዴት አባቱ ነው

ሚያምርብሽ…..?››

ምንም አልመለስኩለትም..አካባቢዬ ያገኘውትን ኩርሲ ያዝኩና ወደ እሳቸው ተራመድኩ…

ውሪዎቹ እቤት ባለመኖራቸው በጣም ነው ደስ ያለኝ….ኩርሲውን ወደ ራስጌው አስጠግቼ

አስቀመጥኩትና ተቀመጥኩበት ..አንገቴን አቀርቅሬ ዝም አልኩ….

‹‹ማን አባቱ ነው ..የእኔን ወፍ እንዲህ ያስከፋት..?››ጎተቱኝና ታፋቸው ላይ አስተኙኝ…

በእድሜ የጠነከረ ቆርፋዳ እጃቸውን ጭንቅላቴ ላይ አሳርፈው በፊቱም ተተረማምሶ

የነበረው ፀጉሬን ይበልጥ ያተረማምሱት ጀመር..እንዲህ ሲያደርጉ ደስ ይለኛል…በቃ ሁሌ

ሲከፋኝ ወደ እሳቸው የምሮጠው እንዲመክሩኝ ወይም እንዲያፅናኑኝ ብቻ አይደለም…

እንደውም ከዛ በላይ እንዲህ እንዲዳብሱኝ ነው የምፈልገው..ይሄ እናቴን ያስታውሰኛል…

በህይወት ሳለች እናቴ ከምታደርጋቸው ነገሮች መካከል ዋናው ይሄ ነው… ሲከፋኝ ወይም

ሲያመኝ ጭንቅላቴን በመዳበስ ማረጋጋት..ማባበል…ማስተኛት..

‹‹የእኔ ወፍ እንዲህ አምሮብሽ… እንዲህ ሴት መስለሽ ልትስቂና ልትደሰቺ ሲገባሽ

ምንድነው ሚያስከፋሽ…..?የእኔ ጀግና አንቺ እንዲህ ስትሸበሪ ማየት ጭራሽ ያስረጀኛል

ታውቂያለሽ አይደል…..?እኔ እንደውም ይሄን ሶስት ቀን ከአይኔ ስትጠፊብኝ ሰግቼ እኮ

ቢቸግረኝ ልጆቹን ተበትነው እንዲፈልጉሽ አዝዤቸው ነው …አንቺ እኮ ለእኔ ፒያሳዬ

ነሽ..ፒያሳን የሚያደምቅልኝ የሰው ትርምስ ወይም የሙዚቃው ጩኸት አይደለም…ያነቺ

በውስጦ መኖር ነው፡፡

እጆቻቸው በፀጉሬ ውስጥ እየተርመሰመሰ ጭንቅላቴን እየደባበሱ ያወራሉ..ሲያወሩኝ ዝም

ብለው ነው…መልስ እንድሰጣቸው ሳይሆን ዝም ብዬ እንዳዳምጣቸው ነው…

‹‹…..ልጄ ያቺ ከይሲ ተተናኮለቺሽ እንዴ…...?እንዴ አንቺ..!!!››ደንግጠው ቀና

አደረጉኝ….አትኩረው አዩኝ..ልክ እንደጥዋቱ አሁንም እንባዬ በአንድ ጉንጬ

ይፈሳል..ጎትተው አስነሱኝና አልጋቸው ላይ ከጎናቸው አስቀመጡኝ…አቅፈው ጉያቸው ውስጥ

ከተቱኝ…

ልጄ በራስሽ አትጨክኚበት…ግድ የለም እስቲ ለስሜትሽ ተሸነፊ….በእኛ ማህበረሰብ

ውስጥ ለስሜት መሸነፍ ደካማ ነት ነው…ለስሜት ስትሸነፊ ለሀጥያት እንደተሸነፍሽ ነው

የሚቆጠረው..ግን ግዴለሽም በእኔ ይሁንብሽ ለስሜት መሸነፍ ሰዋዊነት ነው….እንባሽን

አትገድቢው…ድምጽ አውጥተሸ አልቅሺ …ተንሰቅስቀሽ አልቅሺ..በአንድ አይንሽ ሳይሆን

በሁለቱም አይኖችሽ እንባሽ ይፍሰስ…ለዚህ እንዲረዳሽ ያበሳጨሽን ሰው ያደረገሽን ነገር

አስቢ..ያጣሻትን እናትሽንም አስቢ …ያም ካልበቃሽ ያቺን መሰሪ በህይወትሽን እንዴት

ስትጫወትብሽ እንደኖረች አስቢ…….››ጋሼ መሰሪ ብለው ሚጠሩት ሮማንን ነው..ከበፊትም

ጀመረው ስሟን መጥራት ይቀፋቸዋል..

የማላውቀው ኃይል ከልቤ ተቦጭቆ ተነሳ …ልቆጣጠረው የማልችለው እሳተ ጎመራ

ከውስጤ ፈነዳ… ድምጽ ከጉሮሮዬ እየተምዘገዘገ መውጣት ጀመረ…. እንባዬ በሁለቱም

አይኖቼ በሁለቱም ጉንጮቼ ይወርድ ጀመር..አዎ ያጋተው የስሜቴ ደመና ከውስጥ በፈነዳው

ኃይል ተበታተነ..የራሴን ድምጽ የራሴን መንሰቅሰቅ እራሴው አዳምጠው ጀመር …

ህእ..ህእ..ህእ……ህእ….

ጋሼ ዜና እያባበሉኝ አይደለም…እያወሩልኝም አይደለም..ብቻ እንዳቀፍኝ ነው…ብቻ

ጭንቅላቴን እየደበሱኝ ነው….

በተተረማመሰ ሁኔታ በራፉ ተከፈተ…

‹‹ጋሼ የለችም..››

‹‹ጋሼ አጣናት…››

‹‹እኔም አላገኘዋትም…››

ሁሉም በተሰማሩበት ተልዕኮ እንዳልተሳካላቸው እየተናገሩ ጋሼ ፊት ሲቆሙ …እኔን ጋሼ

ጉያ ውስጥ ኩርምት ብዬ ሌላ ሰው መስዬ(ቀሚስ ለብሼ አይተውኝ

ስለማያውቁ)ሲመለከቱኝ …በደስታ ተውጠው….

‹‹መጥታለች..››

‹‹እቺውና….››

ተራ በተራ እየትንደረደሩ እላዬ ላይ ተንጠለጠሉብኝ

‹‹..ቀስ ቀስ..አረ ገደላችዋት››ጋሼ ናቸው እየተከላከሉልኝ ያሉት..እኔም እንባዬን እንዳያዩ

በዘዴ እየጣራረግኩ ሁሉንም በየተራ ሳምኳቸው….

‹‹የት ጠፍተሸ ነው..?››

‹‹ፖሊስ ጣቢያ ሁሉ ጠየቅን እኮ››

‹‹እያለቀስን ነበር እኮ››

‹‹የት ተደብቀሽ ነው..?››

‹‹ለምን ቀሚስ አደረግሽ..?››

ሁሉም ያለመጣባበቅ እና ያለመደማመጥ የተሰማውን ያወራታል….፡፡አለው….ይሄው

መጣው አይደል…

‹‹ሁለተኛ ሳትነግሪን እንዳትጠፊ..››

‹‹አሺ አላደርገውም…አሁን እራት በላታችሆል....?››አልኳቸው… ከጭቅጭቃቸው

ለመገላገል

‹‹አይ አንቺን ስንፈልግ ነበር ..››

‹‹ስለዚህ እራት አምጡና አብረን እንባላ… ››በማለት ቦርሳዬን አወጣውና ሁለት መቶ ብር

አውጥቼ ሰጣዋቸው‹‹..ደስ ያላችሁን ምግብ ገዝታችሁ ኑ››

የሰጠዋቸውን ብር ተቀብለው ግር ብለው እንደገቡ ግር ብለው በደስታ እየተንጫጩ ወጡ…

‹‹ልጄ አየሽ አይደል እንዴት እንደሚወዱሽ…...?እራት በላችሁ ወይ ብለሽ ጠየቅሻቸው

አይደል…..?እራት ሳይሆን ምሳቸውን አልበሉም..ቀኑን ሙሉ አንቺን በመፈለግ ሲንከራተቱ

ነው የዋሉት…ሁላችንም በጣም ነው የምንወድሽ….አንቺም ትወጂናለሽ አውቃለው..፡፡ግን

እኛን ብቻ ሳይሆን ሌላ ሰውም ለመውደድ ሞክሪ…ቅድም እንደነገርኩሽ ለስሜትሽ መሸነፍን

ተማሪ….ስሜትሽ ውደጂ ካለሽ ውደጂ…..››

ደነገጥኩ… ጋሼ ምንድነው የሚያወሩት....?የምን መውደድ ነው....?ስለዋቅቶላ

ነግሬቸዋለው እንዴ....?ከእቅፉቸው ወጣውና አትኩሬ አየዋቸው… ጥያቄያዊ አስተያየት….

‹‹አዎ ገብቶኛል….እኔ እናትሽ እቅፍ ሆነሽ ጡት ከምትጠቢበት ጊዜ ጀምሮ

አውቅሻለው..አንቺ ማለት ለእኔ ልጄ ነሽ…. አባት ደግሞ የልጁን እያንዳንዱን የስሜት

ለውጥ ያስተውላል..ዛሬ ደሰ ብሎኛል… በአንቺ ላይ ባየውት የስሜት ለውጥ ደስተኛ ነኝ…››

‹‹እንዴ ጋሼ ስለከፋኝ ነው ደስ ያሚሎት....?ስላለቀስኩ ነው የተደሰቱት..?››

‹‹አዎ …በተለይ ስላለቀሽ ደስ ብሎኛል..ይሄ በአንቺ ህይወት አዲስ ባህሪ ነው …አዲስ

ባህሪ ደግሞ ሚወለደው በህይወት ውስጥ አዲስ ነገር ሲከሰት ነው..እርግጠኛ ነኝ አንድ

ሸጋ የልብሽ ደጃፍ ላይ ቆሞ እያንኳኳ ነው… አንቺ ደግሞ ያን በር መክፈት መሸነፍ አድርገሽ

ስለወሰድሽው እየገፋሽው ነው…ልብሽና አዕምሮሽ ጦርነት ገጥመዋል…..››

‹‹አረ ጋሼ እንደዛ አይደለም..››

‹‹ታዲያ እንዴት ነው..?››ሽማጊሌው በአባታዊ ትዝብት ጠየቁኝ

‹እርግጥ በጣም ጥሩ ሰው ነው…ግን በቃ ወንድሜ እንዲሆን ነው የምፈልገው… ታላቅ

ወንድሜ…ከእሱ ጋር መኖር ከእሱ ጋር ማደር እፈልጋለው..ግን እህቱ ሆኜ ….እንደዛ ነው

የምፈልገው..ያንን ማድረግ ስላልቻልኩ ነው የከፋኝ››

‹‹ፈገግ አሉ ጋሼ.. ይህቺን አይነት የጋሼን ፈገግታን አቃታለው…የነገር ፈገግታ ነች…

የምታወሪውን ነገር አላመንኩሽም የሚል መልዕክት አላት…የምታወሪውን ወንድ ከመውደድ

በላይ አፍቅረሽዋል እያለኝ ነው..ይሄንን ከሳቃቸው ተረድቼያለው››

‹‹ጋሼ እርሶ ደግሞ የውስጤን ከእኔ በላይ ያውቃሉ እንዴ…...?ጋሼ እኔ ልሙት እወነቴን ነው

አላፈቀርኩትም..ስታስበው እኔ...፡

በማግስቱ በጥዋት ነው ከጋሼ የተለየውት … ቀጥታ ወደ ስራዬ ነው የገባውት…ምንም

የሚባክን ጊዜ የለኝም…አዎ ጊዜ የለኝም…ቁርጤን ማወቅ አለብኝ፡፡አላማዬን ለማሳካት

ሶስት ሰዎችን መርጬያለው… ሶስት የልብ ጓደኛቼን ..በጣም የማምናቸውን እና

ህይወታቸውን ጭምር ብጠይቃቸው እንደማይከለክሉኝ የማምንባቸውን፡፡ይህንን ስል መቼስ

አይገባችሁም …የአንቺ ጓደኞች ማን የሚሏቸው ክርስቶስ ናቸው ለሰው ሲሉ ህይወታቸውን

የሚሰጡት…? ትሉኝ ይሆናል..፡፡ተሳስተሸል..ወይም ጓደኞችሽን በተመለከተ ያለሽ ግንዛቤ

የተጋነነ ነው ብላችሁም ምክር ልትለግሱኝ ትቃጡ ይሆናል፡፡ይሄንን ለእናንተ በማስረዳት

ላሳምናችሁ አልችልም…ማሳመንም አይጠቀበቅብኝም..እኔ ግን እንደዛ ነው የሚሰማኝ…ያ

ደግሞ በቂ ነው፡፡

..ለማኛውም እነዚህን ጓደኞቼን በመጠኑ ላስተዋውቃችሁ… ሶስቱም ሌቦች ናቸው፡፡

ስራቸውን ልብነት ነው ልላችሁ ፈልጌ ነው..ያው መተዳደሪያ ከሆነ መኪና ማጠብም ኪስ

ማጠብም ስራ ነው..ዋናው ገንዘብ ማስገኘቱ አይደል…ምነው ተሳሳትኩ እንዴ…? ሶስቱ

ሌቦች ሁለት ወንዶችና አንዷ ሴት ነች…እነዚህ ሶስት ሌቦች ዕድሜያቸው ያው ከ19-23

ይሆናል… ግምት ነው…፡፡ትውውቃቸውም ያው ከዕድሜያቸው ጋር ተቀራራቢ ነው…፡፡ይሄንን

ስላችሁ አንድ ቤት ነው እንዴ ያደጉት…? ወይም የአንድ ሰው ልጆች ይሆኑ እንዴ…?

ብላችሁ በውስጣችሁ ጥያቄ ማንሳታችሁ አይቀርም … ብዙም አልተሳሳታችሁም…አንድ

ቤት ባይሆንም አንድ በረንዳ ላይ አንድ ጆንያ እየተናጠቁ በመልብስ..አንድ ቂጣ ለሶስት

በጣጥቀው በመቃመስ …አጫሽ የጣለውን አንድ የሲጋራ ቁሩ ተቀባብለው በማጬስ…

ከጫት ቤት የተሰበሰበ ገራባ አንድ ላይ ተከፋሎ በመቃምና በመመርቀን…ከአንድ መኪና

በአንድ ትንፋሽ ቤንዚል በመሳብ ክፉውንም ደጉንም አብረው ያሳለፉ በአንድ ቤት ሳይሆን

በአንድ ልብ የሚኖሩ ልጆች በሏቸው..እርግጥ ሶስቱም በተለያዩ እናቶች ተፀንሰው

በተቀራራቢ ጊዜ ተቀራራቢ ቦታ ተወልደው በተለያየ ምክንያት እናቶቻውን ያጡ ፒያሳዊያን

ናቸው…..

….ሁለቱ ወንዶች አቃሟቸው ፍፅም ተቀራኒ ነው፡፡አንዱን ስንዝሮ እንለዋለን….ብጭጭ ያለ

ቀይ..አጭር…ቀጭን..ተንኮለኛ እና ለፍላፊ ነው፡፡ሌላኛው ዋርካ ብለን ነው የምንጠራው ...

ግዙፍ ነው..ረጂም ጥቁር…ዝግ ..ቢኮረኩሩትም የማይስቅ… የአፉ ስፋት ስንዝሮን

ጠቅልለው ቢያጎርሱት ሳያላምጥ ዋጥ ማድረግ የሚችል አይነት ተፈጥሮ ያለው ነው…

ትግስተኛና እርግታ የተላበሰ ነው..ግን የትግስቱ ጫፍ ላይ ከደረሰ በቃ አስር ሰው

አይመልሰውም….የቆሰለ ጎሽ በሉት….ፊት ለፊት ያገኘውን ሁሉ በመደረማመስ ከገደል

ሚደበላልቅ…

እንዲህ ተቃራኒ ባህሪ ያላቸው ሁለቱ ጓደኛሞች ግን የእወነት መንትያ ነው የሚመስሉት

..አንዱ ሳይናገር ሌላው ምን እንዳሰበ በቀላሉ ያውቃል…አንዱ ካንዱ ውጭ መኖር ፈጽሞ

አያስብም …እድሜ ልካቸውን የግል የሚባል ነገር የላቸወም..ህፃን ሆነው ውሻ ሲያሳድጉ

ራሱ ውሻው የጋራቸው ነበር….ፀባቸው የጋራ ነው ፍቅራቸውም የጋራ ነው፡፡በአንዱ

ሚወደደድ ሰው በሌላውም በተመሳሳይ መጠን ይወደዳል…በአንደኛው ቂም የተያዘበት

ሌለኛው ነው የሚበቀለው….ሌላው ይቅር ህመማቸው እንኳን የጋራ ነው…ልክ ከአንድ

እንቁላል ተከፍሎ እንደተሰራ እና ከአንድ ማህፀን በአንደ ጊዜ እንደወጣ የእውነት

ተፈጥሮአዊ መንታ አንዱ ከታመመ ከሳዕታት ቡኃላ ሌላውም ያታመማል….

ይሄ ሁሉ ስለእነሱ በቅርብ በሚያውቁ ሰዎች በገረሜታና በአድናቆት ሚያወሩላቸው

ታሪካቸው ነው…ግን ከዛም ከፍ ያለ ታሪክ አላቸው …ከኩኩሻ ጋር የሚያያዝ ታሪክ…ኩኩሻ

ሶስተኛዋ መንትያ ወይም ሴቷ ነች ..ሶስተኛዋ ተጣማሪያቸው ..ውሪ ህጻን ሳሉ ማንም

እንዳይተናኮላት ከህብረታቸው ቀላቀሏት..አብራቸው መኖር አብራቸው መተኛት

ጀመረች..ሰው እንዳይተናኮላት ወይም እንዳትፈራባቸው መሀከላቸው ነበር

የሚያስተኞት….እዛ ጎዳና ላይ ከኩታራነት እድሜያቸው ጀምሮ መሀከል አድርገዋት ግራና

ቀኞ ሲተኙ ከጥቃትም ከብርድም ነበር የሚከላከሉላት…እኩል እያጎረሷት እኩል እየጠበቋት

..እኩል እየተንከባከቧት አብራቸው አደገች…እኩል አደጉ..ለአቅመ መዳራትም እኩል

ደረሱ….የትኛው አጋጣሚ እና በምን ሁኔታ እንደሆነ አላውቅም ሁለቱም በእኩል ጊዜ

ከኩኩሻ ፍቅር ያዛቸው..…እኩል ጠየቋት..እሷም እኩል ተቀበለቻቸው..፡፡

ይለይልን ብለው አልተደባደቡም…የግሌ ነች ብለው አልተፈነካከቱም…ከሁለታችን አንዳችንን

ምረጪ ብለው ፈተና ውስጥ አላስገቧትም…በደስታ ፍቅራቸውን ቀጠሉ…

ይሄው አምስት አመት አስቆጥሯል ኩክሻ የስንዝሮ እና የዋርካው ሚስት

ከሆነች….የአንደኛው ደረት ላይ ተለጥፋ የአንደኛውን ከንፈር ስትስም ለሚመለከት ሰው

ፊልም እየሰሩ እንጂ የእውነት ህይወት አይመስልም…

የሚገርመው ኩክሻ እንደስንዝሮም ያላጠረች እንደዋርካውም ያረዘመች መሀከለኛ ቁመት

ያላት የጠይም ቆንጆ ሴት ነች… እና ሶስቱ አብረው ሲሄዱ ያስቃሉ..ብዙ ጊዜ እሷን

መሀከላቸው አድርገዋት ነው የሚሄዱት ልክ እንደልጅነታቸው እና ስታወራቸው ስንዝሮ

ወደላይ አንጋጦ ሲያዳምጣት ዋርካው ደግሞ ወደታች አዘግዝቆ ይሰማታል…ይሄም

ለተመልካች ፈገግ ያሰኛል፡፡

በነገራችን ላይ አሁን በረንዳ አይደለም የሚኖሩት ከበረንዳ ህይወት ከተላቀቁ ቢያንስ 7

አመት ይሆናቸዋል…አዋሬ አካባቢ ሁለት ክፍል ቤት ተከራይተው ይኖራሉ…ሁለት ክፍል ቤት

ስላችሁ መቼስ በአዕምሮችሁ ሁለቱም ክፍል ላይ አንድ አንድ አልጋ ተዘርግቶ አንዱ

የአንደኛው ሌላው ክፍል የሌላው ….፡፡እንደዛማ አይደረግም…አንደኛው መኝታ ቤት አንደኛው

ሳሎን ነው..አልጋቸው አንድ ብቻ ሆኖ ባለሜትር ከሰማንያ ሲሆን ሶስቱም የሚተኙት አንድ

አልጋ ላይ ነው…እስር ቤት ገብተው በመንግስት ቁጥጥር ስር የመሆን አጋጣሚ ካልተፈጠረ

በስተቀር አንደኛው ከአንደኛው ተለይቶ መተኛት የማይታሰብ ነው…ሲተኙ እሷን መሀል

አድርገው ነው….

በነገራችን ላይ ከሁለት አመት በፊት ወልዳላቸው ነበር…ምታምር እራሷን የምትመስል ሴት

ልጅ …አቤት እንዴት ይወዷት እንደነበር…አንዱ ሰውነቷን ሲያጥባት አንዱ ዳይፐር

ይቀይርላት ነበር..አንዱ ሲመግባት አንዱ ያጫውታታል….ክፋቱ ከስድስት ወር በላይ በምድር

እንድትቆይ አልተፈቀደላትም ነበር ..ድንገት ተቀጨችባቸው..ከእናትዬው በላይ ያዘኑት ሁለቱ

አባቶች ናቸው….አንድ የጋራ ልጃቸውን ነበር ያጡት…ከዛ ቡኃላ ግን እንዴት ደግማ

እንዳላረገዘችላቸው አላውቅም…እኔም ሀዘናቸውን መቀስቀስ ይሆናል ብዬ ስለሰብኩ

ጠይቄያቸው አላውቅም…ለማንኛውም የእኔ ጓደኞች እንዲህ አይነት ናቸው….ብዙ ብዙ ታሪክ

አብረን አሳልፈናል..ክፍውንም ደጉንም…ሌባ በነበርኩበት ጊዜም አብዛኛውን ስራዬን

ከእነሱጋር በቅንጅት ነበር የምሰራው…እወዳቸዋለው ይወዱኛል….

ዛሬ ለከባድ ተልዕኮ ጠረቼያቸዋለው..ለምን እንደፈልግኮቸው ስነግራቸው ያለምንም

ማንገራገር ሶስቱም በአንድ ድምጽ ተስማምተው ነው የመጡት….እነዚህ ጓደኞቼ ያው ጨዋ

ከሚባለው ማህበረስብ ሚለዩበት ነገር አላቸው….አሪፍ ፕሮፌሽናል ሌባን አምነህ አንድ

ሻንጣ ብር ብትሰጠው አትጠራጠር አድርስ ያልከው ቦታ አንድ ነጠላ ብር እንኳን ከላዩ ላይ ሳይቆነጥር ያደርሰልሀል…ህይወትህንም አደራ ከሰጠሀው ህይወቱን ሰጥቶ ይጠብቅልሀል…

ለዛ ነው እንዲህ በእነሱ ላይ የተማመንኩት….

አራት በአራት በሆነችው በእኔ ክፍል ውስጥ ነው ያለነው…እያንዳንዳችን አንድ አንድ ዙርባ

በለጬ ይዘናል….ከእኔ በስተቀር ሁሉም ኒያላቸውን እያቦነኑት ነው…እቤቷ ታፍናለች…እኔ

እራሴ ምርቅን ቅን ብያለው…ጫት ስቅም ከአምስት ቀን ቡኃላ ነው …ዕድሜ ለዛ ዋቅቶላ

ለተባለው ሰው… ከእሱ ጋር በሆንኩበት ጊዜ እኮ ሁሉን ነገር ትቼውና እረስቼው ነበር…

አይደለም ለመቃም ጫት ሚባል ነገር እንኳን መኖሩን ትዝ ብሎኝ አያውቅም ነበር…አይ የኔ

ነገር..ሰበብ ፈልጌ አስታወስኩት አይደል…?ምን ላድረግ ወድጄም አይደለ…በነገራችን ላይ

አሁን ጓደኞቼ ከመምጣታቸው ከአንድ ሰዓት በፊት ደውዬለት ነበር..እንዲህ ነበር የስልክ

ልውውጡ

‹‹ሄሎ ዋቅቶላ››

‹‹ሄሎ ..ደህና ነሽ…ላክሺልኝ››አለኝ ….ከዚህ ጥያቄ ይልቅ ሞቅ ያለ ሰላምታ ነበር

የጠበቅኩት…

‹‹ምኑን…?››

‹‹የባንክ ቁጥሩን..››

‹‹አንተ መቶ ሺብር ብርቅህ እው እንዴ .. …?እኔ እኮ ሰላም ልልህ ነው

የደወልኩት››ተንዘረዘርኩበት

‹‹ያንቺ ሰላምታ ከራስ ምታቴ ይፈውሰኛል……?ሰላምታሽ ናፍቆቴን ያስታግስልኛል….…?

ሰላምታ..ሰላምታ ››

‹‹አረ አረጋጋው››

‹‹አልረጋጋም ..ምንም ልረጋጋ አልችልም››

‹‹እና ምን ይሁን…?››ተበሳጨው..በጣም አበሳጨኝ

‹‹ምን ይሁን .. …?ነያ..መጣለው ብለሽ አልነበር …?ነይ..አብሬህ እኖራለው ብለሺኝ

አልነበር ነይና አብረን እንኑር››

‹‹አንድ ወር ጠብቀኝ ብዬአለው እኮ….…?››

‹‹አንድ ወር ማለት እኮ …. ቆይ ከተለየውሽ ስንት ቀን ሆነው…?.››

.‹‹አንድ ቀን››

‹‹እና ይሄ አንድ ቀን ምን ያህል ረጂምምምምምምመም እንደሆነ ታውቂያለሽ……?

አታውቂም….30 ቀን ማለት ደግሞ እስካአሁን ያሳለፍኩትን ጣር እና መከራ 30 ጊዜ እጥፍ

ማለት ነው…፡፡ታዲያ አስበሽዋል..…?ይሄንንማ አልችልም..ልጠብቅሽ አልችልም…፡፡ዛሬውኑ

ወይም ነገ ማትመጪ ከሆነ ልጠብቅሽ አልችልም..ካልሆነ አንቺን ከመጠበቅ መርሳት

መሞከሩ ይሻለኛል…››

‹‹ልመጣማ አልችልም..ጉዳዬን ሳልጨርስ ልመጣ አልችልም››

‹‹እሺ አንቺ ካልቻልስ እኔ ልምጣ…?››አለኝ በተሰባበረ እና በተቆራረጠ ድምጽ

‹‹ወደ የት…?››ሌላ ድንጋጤ

‹‹አንቺ ጋር ነዋ››

‹‹ልጅህስ…?››

‹‹ልጄ እናቴ ጋር እተዋታለው..ወይም እህቴ ጋር አስቀምጬያት መጣለው››

‹‹አይ እንድትመጣ አልፈልግም..ጊዜው ሲደርስ እራሴ እመጣለው››ኮስተር ብዬ

መለስኩለት ..እወነቴን ነው አሁን እዚህ እሱ መጣ ማለት እኮ ከእሱ ጋር ስንከረፈፍ

አላማዬን ሙሉ በሙሉ መዘንጋት ማለት ነው….አንዲመጣማ አልፈቅድለትም

‹‹አልፈልግም ..››አንቧረቀብኝ‹‹..ልጠብቅሽ አልችልም..ጂጂ የምትባል ሴት አላውቅም…

ፈጽሞ አይቼያትም አላውቅም..ጂጂ ቅዠት ነች..ዝም ብላ በህልሜ እየመጣች

የምትረብሸኝ መንፈስ ነች…እንዲህ ነው ማመን የምፈልገው..ስለዚህ እንዳትደውይልኝ…

ከዛሬ ጀምሮ አልፈልግም እንዳትደውይልኝ››ጠረቀመው…….ደነገጥኩ.. ፈራው ..በጣም

ፈራው…እና አልደውልለትም ማለት ነው……?ካልደወልኩለት ድምጽን ካልሰማው ምን

ሊውጠኝ ነው…?፡፡ለመሆኑ ለህይወቴ በጣም ሚያስፈልገኝ የትኛው ነው……?ሁለት ስሜቶች

ግራና ቀኝ ወጥረው ይዘውኛል..ለዋቅቶላ ያለኝ ስሜት እና ለሮማን ያለኝ ስሜት..አንዱ

የፍቅር ሌላው የበቀል(ጥላቻ)….ከበቀል እና ከፍቅር የትኛው ይጠቅማል ብዬ እራሴንም ሆነ

እናንተን አልጠይቅም..…?እንደዛ ብዬ ብጠይቅም የዋህነት ነው የሚሆነው..ትክክለኛው

ጥያቄ መሆን ያለበት ከፍቅርና ከበቀል የትኛው የበለጠ ኃያል ነው…? የሚል መሆን

አለበት…የትኛው ነው ይበልጥ አዕምሮን የሚበላው..…?የትኛው ነው ልብን የሚፍቀው..…?

የትኛው ይበልጥ የሚያቃትተው…?ያው ሁለቱም ስሜት በውስጤ ይገኛሉ.. የትኛው ነው

ባለድሉ….…?

ሁሉን ነገር አገናዝቤ ለመብርር ወሰንኩ.. ልሄድ …..ወቅቶላ ማረኝ ..ሁለተኛ አላበሳጭህም

ልለው..ሁለተኛ ጥዬህ ከስርህ አልሄድም ልለው…ወንድም ሁነኝ ልለው…ልብሴን ሁሉ

ሰበሰብኩ ሸንጣዬንም አዘጋጀው..በራሴ ሚኒባስ ልበር… አዎ ሹፌሩ ጋር ልደውል ቁጥሮቹን

መነካካት ጀመርኩ….ከመጥራቱ በፊት የቀጠርኮቸው ጓደኞቼ ጫታቸውን ተሸክመው

እየተንጋጉ ወደ ክፍሌ ሲገቡ ነው ስልኩን ያቆረጥኩት..ለካ ቀጥሬቸዋለው… እንደምንም

እራሴን አረጋግቼ ሁሉን ነገር ትቼ አብሬቸው ቁጭ ብዬ መቃም ጀመርኩ…

አሁን ቢያንስ ከተቀመጥን አንድ ሰዓት አልፎናል..መቃም ከጀመርን..እንሱ እንደተቀመጡት

የተቀመጥኩ እንሱ እንደሚቅሙት እየቃምኩ ቢሆንም ሀሳቤን ግን እንደነጋርኮችው

መሰብስብ ተስኖኛል…የልብ መሸፈት ለካ እንዲህ ከባድ ነው..

‹‹አሁን ስለ ዕቅዳችን መነጋገር ብንጀመር ምን ይመስልሻል…?››ስንዝሮ ነው ድንገት

ፀጥታውን ያደፈርሰው

‹‹ምን አልከኝ..…?ምን ……?ዕቅድ››ድንግርግሬ ወጣ

‹‹አዎ ..እንዴት እንድናደርግ ነው የምትፈልጊው .. …?እንድንገድላት ነው..እንግደላት

አይደል…?››አለኝ ምንም ማወላወል ሳይታይበት..በነገራችን ላይ እኚ ጎደኞቼ ስለ እኔ እና

ሮማን ታሪክ ጫፍ ድረስ ያውቃሉ..እኔ በምጠላትም መጠን ይጠሏታል…የእሷን አንገት

መቀንጠስ ለእነሱ የዶሮ አንገት የመቀንጠስ ያህል አያሳስባቸውም

የእሱ ንግግር ግን እኔን ወደ ቀልቤ መለሰኝ ተንሳፎ አየሩን ሰንጥቆ በመብረር ዋቅቶላ ጉያ

ሊወሸቅ ሲያኮበኩብ የነበረው ልቤን መንጭቆ በመመለስ ከቀልቤ እንድሆነ

አደረገኝ..በመጠኑም ቢሆን ማለቴ ነው…

ግን ቅድም ልሄድ የወሰንኩት ምን ነክቶኝ ነበር……?..የምን መልፈስፈስ ነው……?እሱ

ከተልፈሰፈሰ እኔም አብሬው መልፈስፈስ አለብኝ እንዴ..…?ለዛውስ እሱ እንዲህ የሚሆነው

ምን አልባት ፍቅር ይዞት ሊሆን ይችላል..…?አዎ ወንዶች መቼስ ወደ በፍቅር ባህር ውስጥ

ለማዋኘት ዘሎ በመግባትም እና ለሰከንዶች ተንቦራጭቀው ለመውጣት ሚቀድማቸው

የለም…እኔ ግን አላፈቀርኩት…እንዲሁ ደስ ሰለሚለኝ እንጂ ፍቅር አልያዘኝ…ትንሽም ቢሆን

ያው ሶስት ቀን አብሬው ስለዋልኩና ስለደርኩ ለምጄው ይሆናል ይቺ ታህል ልቤ

የምትዋልለው…አዎ …እርግጠኛ ነኝ ፡፡…ዋል አደር ስል ደግሞ ስለእሱ ማሰብና መጨነቅ

አቆማለው..አረ ጭራሽ እረሳዋለው…እወነቴን ነው ….፡፡

ስለዚህ አሁን ወደ አላማዬ ልመለስ… ትኩረቴን ልሰብስብ….እራሴን ለማሳመን

ያልቀባጠርኩት ነገር የለም…ለካ እራስን እንደማሳመን ከባድ ነገር የለም…ልብ ካልመሰለው

የአዕምሮ ሰበካ የቁራ ጩኃት ነው የሚሆንበት ..

‹‹እኔ ነኝ የምገድላት …በጣም እኮ ነው የምታስጠላኝ…››ኩለሻ ነች የፎከረችው

‹‹ኩኩሻዬ ፍቅር… አኔ እያለወልሽ አንቺ ምን በወጣሽ በዚህች ዳቢሎስ ደም ይሄንን

የመሰለ አለንጋ ጣትሽን ታቆሺሻለሽ....ለእሳ እኔ አለውላት››ስንዝሮ ተቃወማት..

‹‹ሁለታችሁም አትቸገሩ ..አኔ ነኝ አንገቷን ፈጥርቄ እስትንፋሶን የማቋርጠው››ዋርካው

ተናገረ…በግማሽ ልቤ እያደማጥኮቸው ነው…ይሄ የዘወትር ጭቅጭቃቸው ነው..እንዲህ

አይነት ለአደጋ መጋፈጥን የሚጠይቅ ስራ ሲኖረን እንዲሁ ናቸው..እኔ ቀድማለው..እኔ ነኝ

ምቀድመው..ለእኔ ተውሉኝ ለእኔ….አዎ ዝም ብላቸው ለአንድ ሰአት ይጨቃጨቃሉ…

ከጭቅጭቅም አልፈው ሊደባደቡ ሁሉ ይችላሉ..ይሄ ግን ለታሪክ ሽሚያ የሚያደርጉት

አይደለም..እንዲህ ገደልኩት..እንዲህ ጣልኩት ብሎ በማውራት ጀግና ለመሰኘት እና

ለመጎረር አይደለም…እርግጥ ከላይ ከላይ ለሚያዳምጣቸው ሰው እንደዛ ነው

ሚመስለው..ግን ሁሉም ሌለኛን ለመጠበቅ የሚያደርጉት ከቀናነት እና ከአሳቢነት የመነጨ ሚስጥራዊ ደባ ነው...አደጋ ካለ ከእናንተ በፊት ልቅደም እያሉ ነው...ሞት ሲመጣ ሶስቱም ምርጫቸው እድለኛ ሆኖ መትረፍ አይደለም..ከሶስት አንዱ መሞት የግድ ከሆነ ቀድሞ ለመሞት ነው የሚራኮቱት...እራስን  ለሞት አሳልፎ በመሥጠት ለተቀሩት ሁለቱ ህይወትን ለመስጠት ..እስርምሰ ሲመጣ እንደዛው ነው በራስ ላይ መስክሮ ሌላው ነፃ ማውጣት..ግን

ብዙውን ጊዜ ሶስቱም ቦሊስ እጅ ሲገቡ ሶስቱም እኔ ብቻዬን ነው ያተፋውት እነሱመምንም

አያውቁ ስለሚሉ ለፖሊስ ምርመራ ጣም ያስቸግራሉ…...እኔም ለዚህም ነው

የምወዳቸው..ለዚህም ነው በማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት የማልቀናውን በእነሱ

ምቀናባቸው… በምንም ላይ ባልተመረኮዘ እወነተኛ ንጽህ ፍቅራቸው…

…….ቆይ አንዴ ስልኬ ጮኸ …ማለቴ ሚሴጅ ገባልኝ.. እየጠበቅኩ ያለውት ነገር እንዳለ

ሁሉ አፈፍ አድርጌ አንስቼ ከፈትኩት..በምርቃናው ላይ ድንጋጤ አንቀጠቀጠኝ… ላብ

በአፍንጫ ቸፍ አለ..ምክንቱም የመጣው መልዕክት ከጠበቅኩት ቦታ ነው….ከዋቅቶላ..

‹‹ይቅርታ ቅድም አትደውይልኝ ያልኩሽ ስለናፈቅሺኝ ነው…እንዴ ካልደወልሺልኝማ

አብዳለው››ይላል…

አሁን ፈገግ አልኩ….እንደውም ስሬ ያሉትን ጓደኞቼ ይፎግሩኛል ብዬ ሼም ይዞኝ እንጂ

ተንከትክቼ መሳቅ ነበር ያሰኘኝ…ልቤ ላይ ተቋጥሮ የነበረና መተንፈስ ሁሉ ከልክሎኝ የቆየው

ቆጥኝ ነገር ደማሚት እንደተለኮሰበት አለት ፈንድቶ ሲበታተን ታወቀኝ…

.‹‹ አትደውይልኝ ብትልም መደወሌን አላቆምም ነበር..››ብዬ መለስኩለት..ግን ከዚህ በላይ

ብዙ ብዙ ነገር ነበር ልለው የደፈለግኩት..ግን ምን እለዋለው..…?ያው ጥሩ ጓደኛዬ

ስለሆንክ…አይ እንደዛ አይደለም የምለው..ወንድሜን ስለምትመስለኝ

ትናፍቀኛለህ….የትኛው ወንድሜን..…? (እናቴ በህይወት ቆይታ ቢሆን ኖሮ ምን አልባት

ትወልድልኝ የነበረውን) .. ያሰብኩት ሁሉ ስሜቴን በሙላት የሚገልፀልኝ ስላልሆነ ጽፌ

ላስተላልፍለት አልችልም…ስሜቴን በሙላት የሚገልጽልኝ ታዲያ ምን ብል ነው..…?ያንንማ

እኔ ራሴ የት አውቀውና ..ብቻ አንድ የሚረብሽ ነገር ዝም ብሎ ይተናነቀኛል…በአዕምሪዬ

ይጉላላል በስሜቴ ተዳፍኖ ያብሰለስለኛል…

..ወደ ጓደኖቼ ተመለስኩ‹‹ጭቅጭቃችሁን አቁሙ..››ፀጥ አሉ

‹‹እንድንገላት አይደለም የምፈልገው..ለመግደልመ እኔ ዛሬ ለሊቱኑ ፀት

አደርጋታለው….እናንተም አታስፈልጉኝም ነበር..፡፡የምፈልገው….እንድናሰቃያት ነው.እርግጥ

መጨረሻ ላይ እንድትገደል እፈልጋለው…፡፡ያንን ጊዜው ሲደርስ እራሴው የማደርገው ይሆናል

…አሁን ግን የእናንተን እገዛ ምፈልገው በቁም ነፍሷ በውስጧ እያለ የቁም ሞት

እንድንገድላት ነው..ፃረ ሞት እንድንሆንባት…እያንዳንዶን የሰራቻትን ሰይጣናዊ ድርጊት

እያሰበች በፀፀት እንድታጣጥር…ሞቷን እንድትለምን..ግደሉኝ ብላ እንድትማፀነን…

እያንዳንዱን በግፍ የሰበሰበቻትን ንብረቷን አጥታ ደቦ መግዛዣ እንድታጣ…መንገድ ላይ

ወጥታ እንድትለምን..

‹‹እንዴ የአሜሪካ አክሺን ፊልም አደረግሺብን….››አለኝ ያ ተንኮለኛው ሲንዝሮ

‹‹እንዴት…?››ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ስላልገባኝ ጠየቅኩት

‹‹ንብረቷን መቀማት..እሷን ለማኝ ማድረግ… ማስራብ… ማሳበድ..በስንት ጊዜ ውስጥ ነው

የምናደርገው››

‹‹መጀመሪያ ስድስት ወር ነበር የመደብኩላት..አሁን ግን ጊዜ የለኝም..በአንድ ወር ውስጥ

የአለምን ስቃይ ሁሉ ማየት አለባት..››

‹‹አንድ ወር..ምነው እንዲህ ቸኮልሽ…?››ኩኩሻ ነች የጠየቀቺኝ

‹‹ጌዜ የለኝም…ከዚህ አገር ልመርሽ አስቤያለው››

ሶስቱም ክው ብለው ደነገጡ…በተለይ ዋርካው ያን ፊቱን አጨማዶ ለንቦጩን ሲጥለው…

የሆነ የህጻናት ማሰፈራሪያ መሰለ

‹‹አይዞችሁ..እኔም እንዲህ አላዘንኩ››

አረ የመጬ አይነፋም..አንቺ እኮ የፒያሳ ልጅ ነሽ ፓሪስ ብትሄጂ እንኳን አትለምጂም››

‹‹አታስቢ …ገና እርግጠኛ ሆኜ አልወሰንኩም..ግን በቃ አንደ ወር ከተሰቃየችና ሞቷን

ካስመኘናት ይበቃል..ከዛ እኔ አጠናቅቃታለው…፡፡ማጠናቀቂያው ላይ እናንተን

አልፈልጋችሁም… ብቻዬን ነው የማደርገው…ፈረሰኛው ጊዬርጊስ ካላጋለጠኝ አሪፍ ነው…

ካልሆነም ዕቅዴ ይሳካ እንጂ ጋማ ብባልም ጣጣ የለውም ..ያው አንድ ሃያ አመት ጠጥቼ

ሼባ ሆኜ ስወጣ እንገናኛለን››

…ዋርካውን ደረት ላይ ተደግፋ ስንዝሮን ጡቶቾ መካከል አስደግፋ …‹‹አረ አይነፋም››አለች

ኩኩሻ አሁንም ደግማ።።ቀኑን ሙሉ ተኝቼ ነው የዋልኩት፡፡ይሄን ያደረግኩት ዛሬ ለሊት የመተኛት ዕድሉ ስለማይኖረኝ

ጥሩ እረፍት ለመውሰድ ነው፡፡ከእንቅልፌ ስነቃ 11 ሰዓት ነበር፡፡ዛሬ ለእኔ ልዬ ቀን ነች፡፡

ታላቅ ተግባር የማከናውንበት ቀን ….፡፡ከዛ በፊት ግን ዘና ማለት አለብኝ፡፡አዎ መንፈሴን

ንጽህ እና በጥራት የሚያስብ መሆን አለበት….ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ ጋሼ ዜናን ከቤት

ይዣቸው ወጥቼያለው..፡፡ለእኔ ምሳዬን ለጋሼ ደግሞ እራታቸውን አብረን ከበላን ቡኃላ

በአሁኑ ሰዓት ምግብ ቤቱን ለቀን አንድ አነስተኛ ካፊ በረንዳ ላይ ተቀምጠን የሆድ

የሆዳችንን እያወራን እግረ መንገዳችንን ወጪ ወራጁን እየተመለከትን እንገኛለን….

ብዙ ብዙ ወሬ ካወራን ቡኃላ ድንገት ያስደነገጠኝን ጥያቄ ጠየቁኝ‹‹‹ሰውዬሽ ደህና ነው…?››

‹‹የቱ ሰውዬ…?››

‹‹ያ ለሶስት ቀን ጠልፎሽ የነበረው…ነዋ››

‹‹እ!!! እሱን ነው……?እኔ እንጃ ሰላም መሰለኝ…ያው ጠልፎ ከመለሰኝ ወዲህ መች

አገኘውት..…?››

‹‹ጠልፎ ከመለሰኝ አልሽ .. …?››አሉኝ …በዛ የተለመደ ማሽሟጠጣቸው፡፡

‹‹አዎ ጠልፎ ከመለሰኝ..!!!››ምንም እንዳይሉኝ የፈራው በሚመስል የጠነከረ ንግግር

ግግም ብዬ

‹‹ምኑን መለሰሽ… አሁንም እኮ እሱ ጋር ነው ያለሺው››

‹‹ምን ማለት ነው ጋሼ ……?አልገባኝም…?››

‹‹አይ የእኔ ልጅ..አንቺ ስለ አካል መጠለፍ ነው የምታወሪው ..የአካል መጠለፍ ብዙም

አያሳስብ የልብ መጠለፍ ነው ከባዱ….አንድን ሰው የሆነ ቤት ውስጥ ከርችመሽበት

አሰርኩት ትይ ይሆናል.. ግን እውነታው እንደዛ አይደለም..እስር ቤት ከተሸ ቆለፍሽበት

ማለት ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ከለከልሺው ብቻ ማለት ነው…እውነተኛው እስር

በመንፈስም ስትታሰሪ ነው…በስነልቦና ስትሸነፊ ነው…፡፡

.ለምን ይመስልሻል አንዳንድ ሰዎች በተለይ የነፃነት ታጋዬች አስር ወይም ሃያ አመት አንድ

ጠባብ ክፍል ውስጥ ተከርችሞባቸው ከኖሩ ቡኃላ ሲለቀቁ…ስብርብር ብለው ፤ተስፋ

ቆርጠው እና አንገት ደፍተው እናያቸዋለን ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ በተቃራኒው አንገታቸውን

ቀና አድርገው ደረታቸውን ነፍተው ይበልጥ ገዝፈውና አስፈሪ ሆነው የሚወጡት…አካላቸውን

እንጂ መንፈሳቸው እንዲታሰር ለማንም ስለማይፈቅድ ነው…እጃቸውን እንጂ ልባቸውን

ለእስር አሳልፈው ስላማይሰጡ ነው፡፡

‹‹ጋሼ ጫወታህን ያው እንደልማድህ ፖለቲካዊ አደረግከው እኮ..››አልኩት ወደ አጀንዳው

ልመልሰው ስለፈለኩ

‹‹አይ ምሳሌ ልስጥሽ ብዬ ነው..አንቺ አካልሽን ከተጠለፍሺበት አስለቅቀሽ መጥተሸል

እናም በዛ እየተኩራራሽ ነው....ልብሽ ግን አሁንም እንደተጠለፈ ነው..ደግሞ ሳስበው

እንዲህ በቀላሉ የምታስመልስ አይመስለኝም፡፡

‹‹እንዴ ጋሼ አሁንም አልገባኝም…?››

‹‹ለመሆኑ ስሙ ማነው..…?››

‹‹ዋቅቶላ ይባላል…ወይኔ…ማለቴ የትኛ ሰውዬ…?›› ዘበራረቅኩ

‹‹የትኛው ሰውዬ አልሽኝ..…?ነገርሺኝ እኮ …ዋቅቶላ ብለሽ ነገርሺኝ…አዕምሮሽን የሞላው

ስም እሱ ነው…ደውለሺለት ታውቂያለሽ…?››

‹‹አዎ አንተን ከማግኘቴ በፊት ደውዬለት ነበር…ተወው ባክህ እሱ ነጭናጫ ነገር ነው…››

‹‹ነጭናጫ አልሽ..…?ፍቅር ሲይዝ እኮ እንደዛ ነው የሚያደርገወ ያነጫንጫል…››

ይሄንን አይነት ወሬ በዚህ ወቅት አልፈለግኩም..ይሄ ጫወታ ወደ ትካዜ የሚጨምረኝ እንጂ

ፈታ የሚያድገኝ አይደለም…የሚያልፈሰፍሰኝ እንጂ ጥንካሬ የሚያላብሰኝ አይነት ጫወታ

አይደለም..እና ጫወታውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለወጥኩት

ጋሼ እነዛን ፍቅረኛሞች አየሀቸው… እሷ እኮ እየለመነችው ነው ..እሱ ደግሞ

ይንጠባረርባታል…እንዲህ አይነት ወንዶች ያባሳጩኛል…

ፊት ለፊትችን እየተጨቃጨቁ ስለሚሄዱ ሁለት አፍላ ወጣቶች ነው የማወራው..ልጁ

ቀጫጫ ..ባለደበሌ ፀጉር..ግን ደግሞ ቆንጆ ነው…ዘመንኛ አለባበስ የለበሰ ሱሪው

በማጥለቅ እና በመውለቅ መካከል የሚዋልል የሚመስል..ላድርገው ወይስ ላውልቀው

እያለ ከራሱ ጋር ሲሞገት ቆይቶ መወሰን አቅቶት ሱሪው ባለበት መሀከል ቦታ ላይ ጥሎት

የወጣ የሚመስል…እሷ ፍቅረኛው…ለዕርቃን የተጠጋ አለባባስ ለበሰች…ከሰር ያጠለቀቻት

ብጣቂ ቀሚስ በብስጨት እንጣጥ እንጣት ስትል ንፋሱ ወደላይ ሲያነሳት ከስር

ያጠለቀችው ነጭ ፓንት በቀላሉ የሚታይ ..ከላይ የሁለቱ ቱቶቾ ሰማኒያ ፐርሰንት ግዛታቸው

ለእይታም ለንፋስም የተጋለጠ አለባበስ የለበሰች ነች፡፡

‹‹ምነው ተፈቅረህ አታውቅም እንዴ..…?አንተን በየሄድክበት እየተከተልኩ መለመን

አለብኝ…?››እየተንዘረዘረች ትጮህበታለች፡፡

እኔ ለምኚኝ አላልኩም ..ግን መጨናነቅ አልፈልግም …ትንፋሽ አሳጣሺኝ››ይላታል..በተ

ንገሸገሸ ስሜት….

እንደዛው እየተነጋገሩ አልፈውን ሄዱ…

የጋሼን የወሬ አቅጣጫ መለወጥ ተሳካልኝ…ግን በራሱ መንገድ ነው ያየው…

የእኔ ወፍ አየሽ ዘመን ብዙ ነገር ይቀይራል፡፡ወንድነትም ተቀይሯል… የእኛ ጊዜ ወንድ

የሚበላው ጮማ ስጋ … የሚጠጣው ደግሞ ንፅህ የማር ጠጅ ነበር…እንዲህ ስልሽ

በውስጥሽ ጥያቄ መፈጠሩ አይቀርም…ምክንያቱም ጮማውም አለ ጠጁም ቁም ነገሬ ብሎ

የሚጠጣው ሰው ባይኖርም አሁንም አለ ብለሽ ታስቢ ይሆናል… አዎ ትክክል ነሽ እኔም

መኖሩን አውቃለው …ግን ከእኛ ዘመን ጮማ ጋር ምኑም አይገናኝም ፡፡የአሁኑ ማለቴ

የእናንተ ዘመን የውሸት ነው፡፡በመድሀኒት የወፈረ አርቴፊሻል ጮማ እና ልብን የሚፍቅ

የስኳር ስሪት ጠጅ ነው ያለው፡፡

በተጨማሪም የአሁኑ ወንድ ሱስ አድክሞታል፡፡የሀሺሽ ሱስ …የጫት ሱስ …የገንዘብ

ሱስ..የፌስ ቡክ ሱስ..የመኪና ሱስ ….የቴክኖሎጂ ሱስ ….በቃ ሱስ በሱስ….. ስለዚህ

ለሴት የሚኖረው ፍላጎት ከእነዚህ ሁሉ ፍላጎቶች የተረፈ ሸርፍራፊ ስሜት ነው..ያቺ ሽርፍራፊ

ስሜትን ለመቀስቀስ ደግሞ እንዲህ እንደምታያት ብጣቂ ልብስ ለብሳ ማስታወስ እና

መፈታተን ከሴቲቱ ይጠበቃል..ለዛውም ከገባው…፡፡ቴዲ አፍሮ በቅርቡ የለቀቀውን

የሰብልዬን ክሊፒ አይተሸል…በዛብህ የሚማልለው የሰብለን ቁርጭምጭሚት እያየ ነው…

ሙሉ ያልተበታተነ ልብ ያለው አፍቃሪ ወንድ የሴት የፍቅረኛውን የእግር ኮቴ በጨረፋታ

ማየት እንኳን ወንድነቱን ይረብሸዋል…ውስጣዊ ስሜቱን ይነቀንቅበታል….…አየሽ ልዩነቱን..››

እንግዲህ ጋሼ እንዲህ ነው… አንድ ቁራሽ ነገር ካሳዩቱ ..ያንን አንዴት ተርጉሞት ከምን ጋር

አገናኛቶት እንደሚተነትነው ሁሌ ያሰገርመኛል…በነገራችን ላይ ከእሱ ጋር ዕድሜ ልኬን

ከመኖሬ የተነሳና እሱን ማዳመጥም ሰልችቶኝ ስለማያውቅ የእሱን ባህሪ ወርሼያለው…ነገር

ማሰፋፋት እና ማወሳሰብ እየተክንኩበት ነው…ሀይስኩል እንኳን ሳረግጥ ከዩኒቨርሲቲ

ምሩቆች ጋር ደረቴን ነፋ አድርጌ በማንኛውም ርእስ ላይ እኩል የማውራት እና የመከራከር

ችሎታ ከጋሼ ያገኘውት ውርስ ነው….እሱም ይሄንን ይመሰክራል…አዕምሮሽ እኮ በሁለት

በኩል የተሳለ ምሳር ነው ይለኛል…በልጅነትሽ ተነከባክባ በቅጡ ስላላሰደገችሽ እና በበቂ

መጠን ስላላስተማረችሽ ይህቺ ሀገር አጥታሻለች››እያለ ይቆጫል…

ሁለት ሰዓት ሲሆን ለልጆቹ የሚበላ ነገር ተሸክመን ወደቤት ሄድን …ጋሼን አስገብቼ

ምግብን ለልጆቹ ሰጥቼ ተሰናብቼያቸው ልወጣ ስል‹‹ከእኔ ጋር አታድሪም ዛሬ…?››ብሎኝ

ብሎ ተየቀኝ

‹‹አይ ዛሬ አቤቴ ነው የማድረው››

‹‹ስራውን ትተሸል አይደል…?››ብሎ ጠየቀ…ኝ ጥርጣሬ ባረበበበት ድምፀት

‹‹የቱን ስራ…?››የትኛውን ስራ እንደጠየቀኝ በደንብ ቢገባኝም…ደንግጬ ጠየቀኩት ..ልክ

ሰርቼው እንደማላውቅ….አረ ሰርቼው ሳይሆን ሲሰሩም አይቼ።።እንደማላውቅ ነገር

ተንገሽግሼ…

‹‹አይ ዝም ብዬ ነው…በቃ ደህና እደሪልኝ

የእኔ ወፍ..አምላክ ይከተልሽ››ብሎ መረቀኝና

አሰናበተኝ

እኔም ግንባሩን ስሜ ባለው ነገር እየተነጫነጭኩ ወጥቼ ሄድኩ..እንዴ ከዋቅቶላ ጋር

ከተመለስኩ ወዲሀ ሽርሙጥና ብዬ መንገድ ላይ ወጥቼ አላውቅም..ከዛሬ ቡሃላ ይቅርብኝ

ብዬ ወስኜ አይደለም..አረ ጭራሽ አላሰብኩበትም ነበር…ግን ልክ አንደሌብቱ

ሽርሙጥናውንም ተውኩ ማለት ነው……?ወይኔ ዋቅቶላ ይሄ ሰውዬ ምን አስነካኝ .. …?

አፍቅሬው ይሆን እንዴ..…?ስለፍቅር የምታውቁ እስቲ ስሜቱ እንዴት ነው..…?አሁን እኔ

ስተዩኝ ፍቅር ይዞኛል ማለት ይቻላል……?

ይሄንን ጉዳይ አሁን ለማሰብ ጊዜው አይደለውም…ቀጥታ ወደ ቤት ነው የሄድኩት …

ለመዘጋጀት፡፡ወዲያው ነበር ሶስቱን ጓደኞቼን የጠራዋቸው…ዝግጅታችንን ሙሉ በሙሉ

አጠናቀን ከቤት የወጣነው ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ነው፡፡

ከለሊቱ 8፡30 ሲሆን አራታችንም ሮማን መኖሪያ ቤት አቅራቢያ እንገኛለን..ሁላችንም ጥቁር

ላብስ ለብሰናል..እጆቻችን በጓንት ተሸፍኗል..ጥቁር ጭንብል ጭንቅላታችንን ሙሉ ፊታችንን

ሸፍነናል፡፡

…ይሄ መኖሪያ ቤት 1.7 ሚሊዬን ብር ነው የተገዛው…ከዚህ ውስጥ እርግጠኛ ሆኜ

የምነግራችሁ ሰማንያ ፐርሰንቱ የእኔ ንብረት ነው…የእኔ አልኩ እንዴ ……?ይቅርታ ተሳስቼ

ነው የእኔ ካልኩት ውስጥ ቢያንስ ዘጠና ፐርሰንቱ የእኔ አይደለም..የእሷም አይደለም….ያው

የሰፊው የአዲስ አበባ ህዝብ ነው…በእኔ አማካይነት ከሰፊው ህዝብ የተሰበሰበ የተዘረፈ

ማለትም ትችላላችሁ ብር ነው፡፡

…የተቀረው ደግሞ ስጋዬን ሸጬ የሰበሰብኩት ነው…ግን ስጋ መሸጥ ምን ማለት ነው ..

…? ግብረ ስጋስ የሚባለውስ ለምንድነው..…?አዎ አሁን ገብቶኛል ግብረ- ስጋ ማለት የስጋ

ብቻ ስራ ማለት ነው..፡፡አይደል……?አንድ ስጋ ከሌላ ስጋ ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ማለት

ነው…ፈቅር አልባ ወሲባዊ ግንኙነት፡፡

በፍቅር ውስጥ ያለ ወሲብ ግን ግብረ ስጋ ሲባል ትክክል አይደለም…ምክንያቱም በእወነተኛ

የፍቅር ተጣማሪዎች መካከል የሚደረግ ግንኙነት ስጋ ከስጋ ብቻ በማፋተግ የሚከወን

ሳይሆን የመንፈስም ቁርኝቱ የሚገዝፍበት በግንኙነታቸው ሰከንድ ሰማየ-ሰማያት

የሚንሳፈፉበት ..ከሰው በላይ የሚሆኑበት.. ከፕላኔቶች ጋር በስምም በጸሀይ ዙሪያ

የሚተሙበት ቅዱስ ክስተት ይሆናል..ይሄንን ታዲያ ግብረ ስጋ ማለት ትክክል

አይመስለኝም..እኔ በዛ መልክ አጣጥሜው ባለውቅም እንዲሁ ሳስበው ነገሩን ዝቅ

ማድረግ ይመስለኛል ..

….ወይ የእኔ ነገር አሁን እኮ ለከባድ ተልዕኮ ጓደኞቼን ይዤ አደገኛ ቦታ ነው ያለውት…

ታዲያ ስለዚህ አይነቱ ጉዳይ ምን አሳሰብኝ……?ለማንኛውም ጊቢ ውስጥ ገብተናል …

ጊቢወ ውስጥ ለመግባት ያን ያህል ከባድ አልነበረም …ዘበኛ የለውም..ወሻ

አልታሰረበትም…፡፡አጥሩም ያን ያህል አስቸጋሪ የሚባል አልነበረም…..በዛ ላይ እዚህ ጊቢ

ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ኖሬበታለው...መግቢያ እና መውጫውን በደንብ አውቃለው፡፡

ለዚህ ለዛሬው ተልዕኮ ከሳምንት በላይ ተዘጋጅተንበታል፡፡መጀመሪያ ስለዝግጅታችን

ከመናገሬ በፊት ስለቤቱ ልንገራችሁ…ባለአራት ክፍል መለስተኛ ቢላ ዋና ቤት እና ከጀርባ

ሶስት ክፍል ያላቸው ሰርቢስ ቤቶች አሉበት…፡፡ሶስቱን ክፍል ሰርቢስ ቤት አንድ ላይ

በማቀላቀል የሚትኖርበት ሮማን ነች..የእኔዋ ደመኛ ሮማን…አብረዋት አንድ ሚስኪን ሰራተኛ

እና አንድ ጥቁር ድመት ይኖራሉ….፡፡

ትልቁ ቤትን በወር ዘጠኝ ሺ ብር አከራይታው ነበር..ተከራዬቹ ከአራት ቀን በፊት ነው

የለቀቁት..የቤቱን ኪራይ በስድስት ወር አንዴ ነበር የሚከፍሉት…. ከአራት ቀን በፊት ሲለቁ

ተከፍሎ ያልተኖረበት የሶስት ወር ኪራይ ነበራቸው፡፡

…ድንገት ልንለቅ ነው ሲሏት… ‹‹ለምን…?›› እንኳን አላለቻቸውም

.‹‹ሂሳብ መልሺልኝ አትበሉኝ እንጂ መብታችሁ ነው››ነበር ያለቻቸው….ምርጫ

አልነበራቸውም ብሩን ጥለው ለቀቁ…..

እኚህን ተከራዬች ለማስለቀቅ እኛ የሰራነው ስራ ከፍተኛ ነበር…ስንዝሮ እና ዝግባው የቤቱ

አባ ወራን መግቢያ መውጫ ተከታተሉት ….ድክመቱን ለማግኘት….ሚስጥሩን ለማግኘት

..፡፡ብዙም ሳይለፉ እጃቸው ላይ ወደቀ….ከሁለት ልጆቹ እናት ደብቆ ሹልክ እያለ

የሚሄድባት ሌላ ውሽማ አለችው…እንደሚስት ተከራይቶ ያሰቀመጣት ውሽማ…ይሄንን

እንቅስቃሴ ለሁለት ቀን እየተከታተሉ በቪዲዬ የተደገፈ መረጃ ሰበሰቡበት…

ከዛማ አለፍ ብለው ሰውዬው ባሌለበት ውሽማዋን ቀርበው ያነጋገሯታል፡፡ከዛም ጠቃሚ

ነገር ያገኛሉ ፡፡ውሽሚት ውሽማ መሆኗን አታውቅም ነበር…፡፡እጮኛ እንደሆነች…እሷን

በቅርብ እንደሚያገባት..ከእናቱ እና ከእህቱ ጋር እንደሚኖር…እህቱ ሁለት ልጆች እንዳሎት

እና ከባሏ ተፋታ ወደ ቤት ተመልሳ አብራቸው እንደምትኖር ነበር የነገራት….. እንግዲህ

እህቴ ነች ያላት የገዛ ሚስቱን ነበር…..እንደዛ ነው ያሳመናት….ይሄንን መረጃ ሰብስበው

ከሰጡኝ ቡኃላ ..ደወልኩለት

‹‹አቤት ማን ልበል…?››

‹‹አታውቀኝም››

‹‹እሺ ምን ፈለግሽ…?››

‹‹መጀመሪያ የፈለኩትን ከመናገሬ በፊት ስለአንተ የማውቀውን ልንገርህ…ከእናትህ እና

ከሚስትህ ጋር በኪራይ ቤት ውስጥ ትኖራለህ…ሁለት ልጆች አሉህ…ግን የምትተዳደረው

በንግድ ነው..መርካቶ አካባቢ ነው የምትሰራው…አብነት አካባቢ ውሽማ አለህ …ስሟ

መሀሌት ስዩም ይባላል..እንደምታገባት እና የምትኖረውም ከእናት እና ከእህትህ ጋር

እንደሆነ በመናገር ዋሽተሀታል››

‹‹ይሄንን የማይረባ የውሸት ወሬ ከየት ነው የመጣሽው……?››

‹‹ለረጂም ጊዜ ስከታተልህ ነበር …ኢሜል አድርሻህን ሁሉ አውቃለው..አሁን የምነገርህን

መረጃዎች ሁሉ..የአብነቷን ውሽማህ ስለአንተ የነገረችኝን ሁሉ የተቀዳበትን እና

የተቀረፀውን አንድ ላይ አድርጌ ልኬልሀለው..እየው ››

‹‹ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው …?…አስር ሺ ብር..ሃያ ሺ ብር››

‹‹አይ ..ይቺን ይህል ብር እማ… ››

‹‹ሴትዬ እንደዛ ከሆነ ጊዜሽን የተሳሳተ ሰው ላይ ነው ያባከንሺው..የመርካቶ ነጋዴ ነው

ሲሉሽ ከመራካቶ ሀብታሞች ውስጥ አንዱ መስዬሽ ከሆነ ተሳስተሸል…ገና በሁለት እግሬ

መቆም ያልቻልኩ ለፍቶ አዳሪ ነኝ››

‹‹እና ሚስጥሩን ለውሽማህም ለሚስትህም ላከፋፍላቸው…?››

‹‹አይ እንደዛማ አታደርጊም ..ብቻ አቅሜን እየነገርኩሽ ነው››

‹‹እኔ የምፈልገው አሁን ከምትኖርበት ከሮማን ቤት በአራት ቀን ውስጥ ለቀህ እንድትወጣ

ነው…›

‹‹በቃ…?››

‹‹አዎ በቃ…››

‹‹ግን እኮ ገና ያልኖርኩበት ቅድሚያ የተከፈለ የ 3 ወር የቤት ኪራይ አለኝ…እሷ ደግሞ

በፍቃዴ ከወጣው አትመልስልኝም..እንደዛ አይነት አዘኔታ ያላት ሰው አይደለችም..››

‹‹እኔ ካንተ ምንም ጉዳይ የለኝም..ጉዳዬ ከሌላ ሰው ጋር ነው… እንድትጎዳ አልፈልግም..

ዛሬውኑ ቤትህ ፊት ለፊት የሚገኘው ደበበ ኪዬክስ በፖስታ 27 ሺ ብር

አስቀምጥልሀለው..ይሄ ለምታጣው የሶስት ወር ኪራይ ማካካሻ ነው››

‹‹በወር ዘጠኝ ሺ ብር እንደተከራየው በምን አወቅሽ..…?››

‹‹ስለአንተ ብዙ ብዙ ነገር አውቃለው አልኩህ እኮ..እንግዲህ ሶስት ቀን ሰጥቼሀለው..አሁኑ

የኪራይ ቤት መፈለግ ጀምር..ለቤተሰቦችህም ሆነ ለእሷ ምትነግረው አሳማኝ ምክንያት

ይኑርህ..ደግሞ ምንም ይሁን ምንም ስለዚህ ስምምነታችን አንድ ነገር ለማንም

ለሚስትህም ቢሆን ትንፍሽ ብትል በልጆችህ ህይወት መፍረድህን እመን››አልኩ ና ስልኩን

ዘጋውት… ፡፡ስቅጥጥ ነበር ያለኝ…አንድን ወላጅ በልጆቹ ህይወት ከማስፈራራት በላይ ጭካኔ

የለም..ግን አስተማማኝ የሚሆነው ደግሞ እንዲህ ሲሆን ነው… ምርጫ አልነበረኝም፡፡

በዚህ ሁኔታ።።።ድርድር ነው ሰውዬው በተሰጠው ቀን ቤቱን ለቆ የወጣው…ቤቱ በተለቀቀ ማግስት ነበር ደላሎች ሌላ ሰው ለማስጋባት መራወጥ የጀመሩት..ግን ለዝግባውና

ለስንዝሮ የተሰጣቸው ተልዕኮ ስለነበረ ሁሉም ድርድር አልተሳካም..ዋናው አላማችን ቤቱን

ለዛሬ ተልዕኮችን ባዶ ማድረግ ነው..ሰው እልባ ማድረግ፡፡

የባዶውን ቤት የተቆለፈ በር ለመክፈት ብዙም አልተቸገርን …የበራፍ ቁልፎችን ሰርስሮ

ለመክፈት ያለኝን ችሎታ ከዚህ በፊት የነገርኮችሁ መሰለኝ…ሁለታችን ወደ ውስጥ ገባን እኔ

እና ስንዝሮ…፡፡ኩክሻ እና ዝግባው ፈንጠር ፈንጠር ብለው ድምጽ አልባ መሳሪያቸውን

በተጠንቀቅ ወድረው ጨለማ ውስጥ በማድፈጥ ውጭ ቀርተዋል…

ዕቅዳችንን እቤት ውስጥ ሳንገባ ከውጭ ማድረግ እንችላላን…. ግን አስተማማኝ ለማድረግ

ወደ ውስጥ መግባት አለብን..ስንዝሮ በግራ እና ቀኝ እጆቹ ባለ አስር ሊትር ጄሪካኖችን ይዞ

ነው የገባው..እኔ ደግሞ በለበስኩት ጥቁር ካፖርት ሰፊ ኪስ ውስጥ ከአራት ተቀጣጣይ

የእጅ ቦንቦችን ይዤለው…ስንዝሮ እንደገባን አንደኛውን ጄሬካን አስቀመጠና አንደኛውን ከፍቶ

የጣውላ ንጣፍ የሆነውን የቤቱን ወለል ያዳርሰው ጀመር …ከአሮጌ ጠሬጳዛዎች በስተቀር

ብዙም ዕቃ የሌለውን ቤት በቤንዚል እጥለቀለቀው..ወደ ሌሎች ክፍሎች ሌለኛውን ጄሪካን

ይዞ ጋባ …በሰባት ደቂቃ ውስጥ ስራውን ጨረሰ…

አሁን የእኔ ተራ ነው..አራቱንም ቦንቦች ከኪሴ ውስጥ አወጣው…እነዚህን ቦንቦች የያዝኩት

ጠላት ልደመስስበት አይደለም…ጠላት ለመደምስ እማ ወደ እዚህ ባዶ ቤት ሳይሆን ወደ

ጎሮ ነበር መሄድ ያለብኝ ወደ ሰርቢሱ ቤት ..ሮማን ወደምትገኝበት ክፍል…ግን አሁን ጊዜው

አይደለም…

አሁን ቦንቦቹ ያስፈለጉኝ ይሄንን ቤት ድርምስምሱን እንዲያወጡልኝ ነው..ከብሎኬት የተሰራ

ሲሚንቶ ቤት ስለለሆነ እሳትን መቋቋም አቅሙ ጥሩ ሚባል ነው…የቤቱ ግድግዳ ጠቋቁሮ

ኮርኒሱ ብቻ ተቃጥሎ ሊተርፍላት ይችላል..እንደዛ እንዲሆን ደግሞ ፍጽም አልፈልግም…

ይሄ ቦንብ ግን ከእሳቱ ጋር ሲዋሀድ ሚፈጥረው ፍንዳታ ሁሉን ነገር ወደ ፍርስራሽነት

ይቀይረዋል….ከዛ ያቺ እባብ ይሄ ሲሆን ቆማ ታያለች…በውስጥ ልብሷ በድንጋጤ ተነስታ

እንደእብድ ጊቢውን እየዞረች ከሚቃጠለው ቤቷ የሚንበለበለው የእሳት ወላፈን ፊቷን

እየገረፋት ውስጧን እያነፈራት…የመጀመሪያ ቅጣቷን ትቀበላለች…ከዛ ሌላ አራት ተከታታይ

ቅጣት ይቀራታል…መጨረሻው ነፍሶን መንጠቅ ነው፡፡

አራቱን ተቀጣጣይ ቦንቦች ጥሩ ነው ያልኩበት ቦታዎች አስቀመጥኩና ጨረስኩ ..ከስንዝሮ

ጋር በምልክት ተነጋገርንና በየአንንዱ ክፈል አንድ የክብሪት እንጨት ለኩሶ ወደ ወለሉ

በመጣል ከቤት ወጠጣን.…የእሳት ነበልባል በቤቱ ዙሪያ መሽከርከር ጀመረ..እቤቱን

ዘጋውና መንገዴን ቀጠልኩ…

ስንዝሮ ከኃላ ተለከለትሎኛል..ግቢውን ለቀን ወጣን …ኩኩሸና ዝግባውም ተከተሉን…

አስተማማኝ እና ሰዋራ ቦታ እስክናገኝ እርምጃችንን አልገታንም…የሚንበለበል የእሳት

ላንቃ.. የሚትጎለጎል ጭስ መታየት ጀመረ…ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሆነ የሰው ድምፅ ግን

አይሰማም…የእሳቱ ኃይል እየጨመረ..ከዛ እኔን እራሴን የሥደነገጠኝ ፍንዳታ ተሰማ…በአንድ

ደቂቃ ልዩነት ሌላ ተመሳሳይ ፍንዳታ ..ከዛ ኹኹታ….የሰፈር ቤቶች ሁሉ መከፈትና

መተረማመስ…ከዛ በላይ እዛ መቆት እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ስለሆነ መንገዴን ቀጠልኩ….

ከሲኦል የተለቀቀ የሚመስለውን የሮማንን የጮኸት እና የድረሱልኝ ድምጽ ልክ እንደሙዚቃ

እያዳመጥኩ ጓደኞቼን ይዤ ወደ ቤት….የመጀመሪያ ተልዕኮ እንዲህ ተፈ ፀመ..ውጤቱን

ነገ ሲነጋ በብርሀኑ የምናየው ይሆናል..ስድሥት ሠአት ነው ከእንቅልፌ የተነሣሁት...ፈልጌ ወይንም እንቅልፌን ጨርሼ አይደለም...ጋሼ ዜና ናቸው የቀሰቀሱኝ...በንዴትና በቁጣ ነበር በራፉን በከዘራቸው እየቆረቆሩ ሲራገሙ ....

<<...ማነው...ምን ተፈጠረ....?>>ከአሥፈሪ ቅዠቴ ተላቅቄ በድንጋጤ ድምጽ አውጥቼ ጠየቅኩ..

<<አንቺ መናጢ...ክፈቺ>>

<<እርሶ ኖት እንዴ....?>>የተጨናበሰ አይኔን እያሻሸሁ እንደምንም አልጋዬን ለቀኩና በሩን ከፈትኩ..ገፍትረውኝ ወደ ውሥጥ ገቡና በቤት ውሥጥ በሚገኘው አንድ ብቸኛ ወንበር ላይ ተቀመጡ...ጥያቸው ወደ ሽንት ቤት አመራሁ...ሽንቴ ሥለመጣብኝ ብቻ ሳይሆን ስለደነገጥኩና ሥለፈራዋቸውም ጭምር ነበር...ተፀዳድቼ እና ተረጋግቼ ሥመለሥ ከቅድሙ በመጠኑ ነቃ ብዬ ነበር...

በራፉ ሲንኳኳ ፓሊሥ ነበር ..ያው ፈሥ ያለበት ዝላይ አይችልም ይባል የለ...ለነገሩ ጋሼም ከፓሊስ ብዙም አይሻሉም..የእሳቸው ስድብና ቁጣን መቋቋም እራሡ ለእኔ ከባድና አሥጨናቂ ነገር ነው።

<<ጨረሽ...?>>

<<አዎ ምነው ሠላም አይደሉም እንዴ...?>>

<<እረ ባክሽ ትቀላምጂብናለሽ አይደል...?>>

<<እንዴ ጋሼ!!!>>

<<ዝም በይኮ ነው የምልሽ>>ከዘራቸውን እያወዛወዙ እና ሊቀነድቡኝም እየቃጣቸው...

<<እሺ  ዝም አልኩ...ግን ምን አጠፋሁ..?>>

<<ለሊት የት አባሽ ነበርሽ...?>>

<<እቤቴ>>

<<እቤትሽ....ምን አይነት ደረቅ ነሽ ልጄ...ለመሆኑ ብቻሽን ነው እንደዛ ያደረግሽው..?>>

<<ምኑን ...?>> ጋሼ ምን ለማለት እንደፈለጉ ገብቶኛል...ሥለማታ ተልዕኳችን ሰምተው ነው እንዲህ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው የመጡት....

<<ሥንት አመት መክሬሽ...ሥንት አመት ለምኜሽ...እርሻት....ከአእምሮሽ አውጪያት...ኑሮሽን ኑሪ ብዬሽ...ሥንት ነገር ተነጋግረን ..የእሷን ቤት አወድማለሁ ሥትይ አንቺ እራሥሽ ወድመሽ ቢሆንሥ ኖሮ...?እረ ምኗ ጉድ ነሽ...ለመሆኑ እንዴት እንዴት አድርገሽ ነው ያን የሚያህል ህንጻ ወደ አመድና ፍርሥራሽነት የቀየርሽው.....?>>

በተዘዋዋሪ ብሥራት ነገሩኝ...ይሄንን ሥሠማ በጣም ደሥ አለኝ...አዎ ይሄንን የምሥራች ለመሥማት ሥንት አመት ጠብቂያለሁ...ሥንት ለሊት እንቅልፍ አጥቼ ሳሰላሥል አድሬያለሁ....

ከዚህ በላይ አይነ ደረቅ መሆን ጋሼን ይበልጥ ማበሳጨት ነው<<ለመሆኑ ያቺ ከይሲ ምን ሆነች...?>>ብዬ ጠየቅኩ....

<<ውይ ሰው እንደዛ አመድ ይነፋበታል...በአንዶኮ ከሠውነት ወደ ጣረ ሞትነት ነው የተለወጠችው...በድን በያት...በቃ በድን....አትናገር አትጋገር..ለፓሊሶች እንኳን ቃሏን መሥጠት አልቻለችም>>

<<እንዴ የምጠረጥረው ሠው አለ አላለችም...?>>

<<እረ እሷ...እንዴት ብላ...በምን አፏ...ብታያት እኮ ኩምሽሽ ብላ አእምሮዋን ያጣች የአማኑኤል ታካሚ ነው የምትመሥለው>>

<<እኔስ ያዙኝ ልቀቁኝ ብላ አገር ትደበላልቃለች ብዬ ነበር...ወደ እኔም ትጠቁማለች ብዬ ተዘጋጅቼ እየጠበኩ ነበር...>>

<<እሱ እንኳን ያው አንቺ እንዳደረግሺው አውቃለች...ለፓሊሥ ግን አልተናገረችም>>

<<እንዳወቀች እርሶ በምን አወቁ...?>>

<<እንደሠማሁ ሂጄ ነበር...አናግሬያታለሁ>>

<<እርሶ እርሷን አናገሯት...?>>

<<አዎ...ምን ለማድረግ እንዳሠበች ማወቅ ነበረብኝ..ጣቷን ወደ አንቺ ለመጠቆም ካሠበች ማሥቆም ነበረብኝ>>

<<ብዙውን ጊዜ ከእሷ ጋር ከማወራ ከሳጥናኤል ጋር ባወራ ይሻለኛል ይሉ ሥለነበር ነው>>

<<ታዲያ በጭንቅ ቀን እኮ ሳጥናኤልንም ቢሆን ማናገር ይናፍቅሻል..>>

<<እሺ ለመሆኑ ምን አለቾት...?>>

<<ሄድኩና የወደመውን ቤት ካየሁ በሁዋላ ወደ አለችበት ሰርቢሥ ገባሁ....ብዙ ሰዎች ነበሩ..ሊያጽኗኗትም ወሬ ለማጣራትም የመጡ...እኔም የማጽናናትና የምመክራት መሥዬ ግን ከሠው ገንጥዬ ወሠድኳትና.....

....ይሄ አሁን የሆነው ከሚገባሽ በጣም ኢምንቱ ነው..በቤት ውሥጥ እያለሽም ከውጭ ቀርቅረን ልናቃጥልሽ እንችል ነበር...ግን ያንቺን ያህል ጨካኝ ሰው ሥላይደለን እንደዛ አላደረግንም...እንድትማሪ እንጂ እንድትጠፊ አንፈልግም...እና አርፈሽ ተቀመጪ...ቢያንሥ በህይወት አለሽ....እፍጨረጨራለሁ ብትይ...ጣትሽን ወደ ሠው እጠቁማለሁ ብትይ....በቀጣይነት ቤትሽን ሳይሆን አንቺን እራሥሽን ነው የምናቃ ጥለው...የሚንቀለቀል እሣት ውሥጥ ነው እንደ ማገዶ የምንከትሽ...የልብ ንጽህና ኖሮሽ እንኳን እንደ ሠለሥቱ ደቂቅ ከእሣቱ የመትረፍ ተሥፋ የለሽም...የገዛ ሀጥያትሽ እራሡ ጋዝ ሆኖ በእሣት ላይ እሣት ሆኖ ነው የሚበላሽ....>>አልኳት....እየተንቀጠቀጠች አዳመጠችኝ...ያቺ ኩሩ ያቺ ጅንን ሴት እንደዛ አንገቷን ደፍታ ሳያት ትንፍሽ እንደማትል ገባኝ...ከእሷ ጋር እንደወጣሁ ነው ወደ አንቺ የመጣሁት...

በደሥታ ከተቀመጥኩበት አልጋ ተሥፈንጥሬ ተነሣሁና የጋሼን ግራና ቀኝ ጎንጮቻቸውን አገላብጬ ሞጨሞጭኳቸው>>

<<ምንድነው እሱ....?የምን ደሥታ ነው....?>>

<<ያሠብኩት ስለተሣካልኝ...እሷን ማሸማቀቅ ሥለቻልኩ...ግን ጋሼ ቆይ እንዲያ ሲያሥፈራሯት ቤቱን በማቃጠሉ እርሶ እንዳሉበት ሲነግሯት የእውነት አምና ትጠቁምዎት ይሆን እንዴ....?>>ሥጋት ቀሥፎ ያዘኝ

<<ታዲያ ምን ሆነና ፍልጎቴ....?አየሽ ካንቺ ሌላ የምትጠረጥረው ሠው ልሠጣት ሥለፈለኩ ነው...ደፍራ ወደ ህግ ከሄደች አንችን አሣልፈ ለመሥጠት እድል ማግኘት የለባትም>>

<<እና....?>>በገረሜታ 

<<እናማ...እኔን አሁን ቀሪ ህይወቴን ቂሊንጦ ገብቼ መንግሥት ቢጦረኝ ምን ይመሥልሻል...?>>

<<አይ ጋሼ......!!!በዚህ እድሜዎ ቅሊንጦ....?ያሾፋሉ>>

<<ምን ይቀርብኛል...?በይ ተነሽ አሁን እንሂድ>>

<<ወዴት...?>>

<<የደሥ ደሥ ምሳ ልጋብዝሻ...ለጀግንነትሽ>>

ፈገግ አልኩ<<...አሁንኮ በሀይለኛው እየተቆጡኝ ነበር>>

<<መቆጣትማ አሁንም እቆጣሻለሁ...ቢያንሥ እንደዚህ አይነት ከባድ ነገር ሥታደርጊ ልታማክሪኝ ይገባ ነበር...ሌላው ይቅር በጉልበት ባላግዝሽ በሃሣብ ማገዝ ያቅተኛል...? ተማክረው የፈሡት ፈሥ አይገማም ይባላል...ያን ባለማድረግሽ አብሽቀሽኛል...ግን ደግሞ የሆነውን ሣይ .....ያቺ መናጢ እንደዛ ኩምሽሽ ብላ ሳይ...በልጄ ጀግንነት አንጀቴ ቅቤ ጠጥቷል...አዎ እንደኮራሁብሽማ ልደብቅሽ አልፈልግን>><<እና የእውነት ይጋብዙኛል?>>

<<በትክክል...በይ ቶሎ ለባብሺና ውጪ>>ብለው ከወንበራቸው በመነሳት ቤቱን ለቀው ወጡ....

ቢጃማዬን አወለቅኩና የሚለበሥ ልብሥ ፍለጋ ሻንጣዬን ከፈትኩ....ሳልፈልግ አይኔ ዋቅቶላ የገዛልኝ ቀሚሥ ላይ አረፈ...

<<ዛሬማ በዚህ በተለየ ቀን የተለየ ነገር ነው የምለብሠው>>አልኩና አውጥቼ ለበሥኩት...ቀሚሱን ስለብስ እሱን እራሱን የለበሥኩት ነው የመሰለኝ...አጠገቤ እንዳለ ወይም እንዳቀፈኝና በሠውነቴ እንደተጠመጠመብኝ አይነት ሥሜት ተሠማኝ...ለብ ያለ የሙቀት ስሜት ...ጫማዬን አጥልቄ ቤቱን ቆለፍኩና ወጣሁ...ጋሼ በዝግታ እየተራመዱ ሲጠብቁኝ ደረሥኩባቸው...

<<አይ የእኔ ልጅ...ቆንጅዬኮ ነሽ>>

<<ቀሚሥ ሥለብሥ ግን በጣም አፍራለሁ>>አልኳቸው...የእውነት ራቁቴን ጎዳና ላይ የምሄድ ነው የሚመሥለኝ

<<አይ ጊዜ....>>አሉ እንደልማዳቸው<<አይ ጊዜ ድሮ በእኛ ጊዜ አንድ ሴት ሱሪ ስትለብስ ነበር...በእፍረት አቀርቅራ የምትሄደውና እርምጃ ሁሉ ጠፍቶባት እግሯ ሚምታታባት...ዛሬ ይሄው ባንቺ ጊዜ ቀሚስ ስትለብሺ ታፍሪና እርምጃ ሲጠፋብሽ ሳይ ከመገረም ውጭ ምን አደርጋለሁ...>>

ጋሼ ምግብ ከጋበዘኝ በሁዋላ ተለይቼያቸው ልሄድ ፈልጌ ነበር...ግን<<ዛሬማ ውልፍች የለም....አብረን ውለን አብረን ነው የምናድረው>>አሉኝ።

<<እንዴ ጋሼ ከጓደኞቼ ጋር ቀጠሮ አለብኝ>>

<<ምን ልትዶልቱ....?ተናግሬያለሁ ንቅንቅ የለም>>ቆፍጠን ብለው አሥጠነቀቁኝ....ጨነቀኝ የእውነቴን ነቅ ዛሬ ከሥንዝሮ ጋር ቀጠሮ ነበረብኝ..ሥለነገ የሁለተኛ ዙር ጥቃታችን ዝርዝር ዕቅዶችን የምናወጣው ዛሬ ነው...ግን ደግሞ አሻፈረኝ ብዬ ጋሼን ተራምጄ መሄድ አልችልም...ተያይዘን ወደ ቤት ሄድን..

ቤቱ ባዶ ነበር..ከፍተን ገባን...ጋሼ አልጋቸው ላይ አረፍ ሲሉ..እኔ ደግሞ ቡና ላፈላ ሽር ጉድ ማለት ጀመርኩ<<ልጄ ቡና ልታፈይልኝ እንዳይሆን>>ጠየቁኝ የህጻን ጉጉት በሚመሥል ሥሜት

<<መጠርጠሩሥ>>

<<አቤት ቡናሽንኮ እንደምናፍቅ...አንቺን እራሥሽን አልናፍቅሽም...>>

<<እሱ እንኳን ውሸት ነው..ከኔ ሚበልጥቦት የለም>> በኩራትና በጉራ መለሥኩላቸው....ነገሩ ጉራ ማለት እንኳን ይከብዳል....አዎ በጣም እንደሚወዱኝ...አንድ አባት ልጁን ከሚወደው እኩል እንዳንዴም ከዚያ በላይ እንደሚወዱኝ ነው ሁሌ ውሥጤ የሚነግረኝ...ውሥጤን ደግሞ አምነዋለሁ...

<<እሱንስ አልሳትሽም...ካንቺ ውጪ ማን አለኝ ብለሽ ነው>>አሉኝ ትክዝ በማለት..

ወደ ቡና ማፍላቴ ከመሄዴ በፊት ሥልክ ደውዬ ለጓደኞቼ ቀጠሯችን መሰረዙን መናገር አለብኝ...ስልኬን አነሳሁና ከፈትኩት....ለሊት ከተልእኮዬ በተመለስኩበት ወቅት እንደዘጋሁት ነበር...ላለመረበሽ...

ደወልኩና ለስንዝሮ ነገርኩት..ዘግቼ ላሥቀምጠው ስል...ጢጥ...ጢጥ የሚል ድምጽ ማሰማት ጀመረ...ሚሴጅ ላክ 35 የሚል ቁጥር አየሁ<<እንዴ ምን ጉድ ነው....?>> 35 ሚሴጅ ...ከፈትኩት..ሁሉንም ተርትሬ አየሁት ከሁለት ቴሌ ከላካቸቅ የዘወትር አሠልቺ ማሥታወቂያ መልእክቶች በስተቀር ሌሎቹ ከዋቅቶላ የተላኩ ናቸው...በዛሬው ግማሽ ቀን ውሥጥ ተላኩ

<<ሰላም አለሽልኝ የእኔ ፍቅር>>

<<ስልክሽ ምነው ተዘጋ?>>

<<ስራሽን አልተውሺውም ወይ?>>

<<ይህ መልእክት እንደደረሠሽ ደውይልኝ>>

<<ይሄን ሁሉ ሰአት እንዴት ሠው ሥልኩን ይዘጋል....?ሰው ያሥባል ብለሽ አታሥቢም እንዴ...?እንዴት አይነት ድንዙዝ መሆን ነው?>>

<<ምን አይነት ደንዳና ልብ ነው ያለሽ?>>

<<በጣም ታሥጠያለሽ...የማትረቢ ነሽ>>

<<በጣምኮ ነው የምወድሽ...ማበዴ ነው>>

.

.

.

.......ሁሉንም አንብቤ መጨረሥ አልቻልኩም..ገረመኝም...አሳዘነኝም...ደወልኩለት... ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው ይላል...ደግሜ ሞከርኩ አይሠራም...

<<ያንተ የራሥህም ስልክ አይሠራም...ደግሞ በአገር ሠላም ምን እንደዚህ ያነጫንጭሃል...?ባል ሆንክብኝኮ>>ብዬ መልእክት ላኩና ቀና ስል ጋሼ ለካ ነገረ ሥራዬን ይከታተል ኖሮ

<<ሰላም ነው ልጄ?>>ሲል ጠየቀኝ

<<አይ ሰላም ነው... ያ ነጭናጫ ሰውዬ ነው>>መለሥኩለት

<<ተይ አንቺ ልጅ...ይሄን ሠውዬ ሳላየው ቀልቤ ወዶታል...ጣል ጣል  አታድርጊው...ሁዋላ በተወደደ ባል እንድልታጪውና እንዳይቆጭሽ>>

ንግግራቸው ፈገግ አሥባለኝ<<ተወዷል እንዴ...?እኔኮ ባል አምሮኝ ልገዛ ወጥቼ ሥለማላውቅ ዋጋውን አላውቅም....ስንት ገባ...?>>በማለት ቀለድኩና ስልኬን ከጋሼ ጎን ጠረጴዛ ላይ ወርውሬ ቡና ልገዛ ወደ ኪዬክስ ወጣሁ....

.

.

.ሰንደሉንም... እጣኑንም..ቄጤማውንም...ቡናውንን ገዝቼ በአሥት ደቂቃ ውሥጥ ተመለሥኩ...።ከሠል አቀጣጠልኩ...ሲኒውን አቀራረብኩ...ቡናዬን አጠብኩና ቆላው...ጭስስ ብሎ ጭሱ ተትጎለጎለ ማንከስከሻ ወስጄ ወደ አፍንጫው አሥጠጋሁለት እና ቡናውን እንዲያሸት አደረኩት <<ሰማያዊ ሽታ በህይወትሽ ይሙላ>>ብለው መረቁኝ...

ቡናውን ወቀጥኩና አፈላዋ....ጋሼን አጠጣሁዋቸው...እኔም ጠጣሁ...ከተመ...ተመረቅኩ በጣም ተመረቅኩ...ከዛ እቃውን አጣጥቤ ካነሳሳሁ በሁዋላ...ከጋሼ ጎን ጋደም አልኩ...

እሳቸው እያወሩልኝ እኔ እያዳመጥኩ ብዙ ብዙ ከተጫወትን በሁዋላ በመሃል ስልኬ ጮኸ ተንጠራርቼ አየሁት...ዋው ዋቅቶላ ነው...ደሥ አለ ኝ ደውሎ ሊነጫነጭብኝ እንደሆነ ባውቅም መደወሉ ደሥ አሠኝቶኛል.....

ከዛም አልፎ ሊሠድበኝ ሁሉ እንደሚችል ብገምትም ማንሣቴን አላቆምኩም....በቃ የሆነ የበረሀ ጉዞ ላይ አንድ ጉንጭ የፊሪጅ ውሃ ገረገጭ ሲያደርጉ የሚሰማ አይነት የእርካታ ሥሜት ነው በመደወሉ ምክንያት የተሠማኝ...ተሥተካክዬ ቁጭ አልኩና አነሣሁት

<<ሄሎ>>ክው አልኩ...ድምጹ የዋቅቶላ አይደለም...እረ እንደውም የወንድ ድምጽ አይደለም..ማን ነች በእሱ ሥልክ የደወለችልኝ....?ውሽማ ትሆን እንዴ.....?ይሄን ሳስብ ልቤ ላይ ጦር የተሠነቀረብኝ መሰለኝ...<<ከዋቅቶላ ሥር ራቂ...ከእሱ ጋር እየተደዋወልሽ አትረብሽኝ>> ልትለኝና ልትሠድበኝ ነው አይደል የደወለችው...?ደም ሥሬ ሁሉ ግትርትር አለ...ልክ ሮማን ፊት ለፊት ለጠብ እንደቆምኩ አይነት....

<<ምን ነበር....?>>ደዋዬ የምታየኝ ይመሥል ኮሥተርተር ብዬ

<<ይቅርታ...ከሻንቡ ሆስፒታል ነው የምደውለው...>>

<<ምን?..ሆስፒታል...ሻንቡ>>አፌን የሞላው ምራቅ ወደ እሬትነት ተቀየረ

<<ተረጋጊ እህቴ...ከዚህ ሥልክ ላይ ያየሁት የመጀመሪያው ቁጥር ያንቺ ሥለሆነ ነው...ታውቂዋለሽ...?>>

<<አዎ በጣም አውቀዋለሁ...ምን ሆነ...?>>

<<ባለቤቱ ነሽ?>>

<<አይደለሁም ጓደ ኛው ነኝ....ምን ሆኗል እያልኩሽኮ ነው?>>አንባረቅኩባት

<<አይ ድንገተኛ ህመም ነው...እራሡን ሥቶ መንገድ ላይ ወድቆ ያገኙት ሠዎች አምጥተውት ነው...ያመጡት ሠዎችም ማንነቱን አያውቁቱም..>>

<<ምን ማለት ነው...?እንዴት ነው አሁን?>>የምለው የምናገረው ጠፋኝ<<እራሱን እንደሳተ ነው...ግን ለክፉ የሚሠጠው አይመሥለኝም..ምርመራ ላይ ነው...መምጣት ብትችይ>>

<<ከየት ነው የምመጣው?>>

ደዋዬ ተደነባበረች<<እንዴ ሻንቡ አይደለሽም እንዴ?>>

<<አዲስ አበባ ነኝ>>

<<ኦ ይቅርታ...በቅርብ ያለ ዘመድ ወይም የጓደኞቹን ሥልክ ትሠጪኛለሽ....?

<<አላውቅም...>>

<<እሺ ችግር የለውም በሥልኩ ላይ ሌላ ቁጥር ፈልጌ ቤተሠቦቹን ለማግኘት እሞክራለሁ>>

ስልኩ ተዘጋ....በድን ሆንኩ...እጄ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ ነው<<ምን ሆንሽ ልጄ....?..ምን ሰማሽ...?>>

<<ታ..ሟ..ል>>ቅርፍፍ ባለና በደከመ ድምጽ መለሥኩላቸው ለጋሼ

<<ምን ነካው ልጄ...?ዋቅቶላ ሥትይ ሰማሁ ልበል?>>

<<አዎ...>>

<<አይዞሽ መታመም ያለ ነው ...አትደንግጪ>>ግንባሬን እያሻሹልኝ

<<ሆስፒታል ገብቷልኮ ነው የምትለኝ?>>

<<አይዞሽ...ምንም አይለው..ሁኔታውን አይተን ካልተሻለው ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ሄደሽ ታይዋለሽ>>

<<ሄደሽ?>>በርግጌ አፈጠጥኩባቸው

<<አዎ...ምን አለበት ጓደኛሽ አይደል>>ተቃውሞ ያሠማሁ መሥሏቸው..

<<አይ ማለቴ አሁኑኑ ነው መሄድ የምፈልገው...ከአልጋው ላይ ተሥፈንጥሬ ተነሣሁ...ጋሼ አሁኑኑ መሄድ አለብኝ>>ቁርጥ ውሳኔዬን አሰማሁ....

<<እረ ተረጋጊ ካልሆነ ጥዋት ትሄጂያለሽ>>

<<እንዴት ሆኜ አድሬ?>>

በዚህ ንግግሬ ጋሼ ፈገግ አሉ...<<ምነው ልጄ ጀግና አይደለሽ እንዴ>>አሉኝ ፈገግ ብለው የእሳቸው ፈገግታ እኔን አበሳጨኝ..ግንባራቸውን ሥሜ ተሠናበትኳቸውና ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ...እያጉረመረምኩ..ጀግና አይደለሽም ወይ ይሉኛል እንዴ?

ጀግንነትን እዚህ ጋር ምን አመጣው...ከሮማን ጋር ለመፋለም ካልሆነ በሥተቀር ከዋቅቶላ ጋር ለመፋቀር ጀግንነት ምን ይፈይድልኛል...?ምን እያወራሁ ነው...?መፋቀርን ምን አመጣው...እኔና ዋቅቶላ ፍቅር...ምን ለማለት ፈልጌ ነው..?ስገርም?።

ብቻ ዋናው ጋሼ ግራ አጋብተውኛል...እንዳልሄድ አልተጫኑኝም..እረ በተሠማኝ ድንጋጤና ሀዘንም ብዙ ትኩረት የሰጡት አልመሰለኝ...ከፋኝ...ቀጥታ ወደ ቤቴ እየሄድኩ እሱባለው ጋር ደወልኩለት...የያዘውን ስራ አቋርጦ ሚኒባሷን እቤት ድረሥ ይዞ እንዲመጣ...ዛሬውኑ መብረር አለብኝ...ሰአቴን ተመለከትኩ...9 ሰዓት ሆኗል..በቃ መንገድም ቢሆን አድራለሁ እንጂ ዛሬውኑ መሄድ አለብኝ...ወሠንኩ.........ጂጂ.....


ከተማዋን ለቀን ወጥተን ቡራዩ ሥንደርሥ ከቀኑ 10 ሰዓት ሆኖ ነበር<<...በቃ እንደዚህ ነው የምትነዳው...>>

<<ማለት...?>>

<<በእግር እየሄድንኮ ነው የሚመሥለው>>

<<ከተማ ውሥጥኮ ነው ያለነው...30 የሆነው በምክንያት ነው ሲባል አልሠማሽም>>

ዝም አልኩት..ምን ብዬ ልከራከረው..እሡ ያለው ትክክል ነው...ህግ በሚፈቅድለት አግባብ የሞያ ሃላፊነቱን አክብሮ እየነዳ ነው ...እኔ ነኝ እንጂ የገዛ ሥሜቴን መሾፈር ያቃታኝ...።

እኔ አሁን በዚህ ሠአት በመኪና ተጭኖ በሚሽከረከር ጎማ ኪሎሜትር እየቆጠሩ መጓዝ አይደለም የምፈልገው...አቋራጩን ይዤ ሠማዩን ሰንጥቄ ክንፍ አውጥቼ መብረር ወይም ክንፍ ባለው ነገር ላይ ተንጠልጥዬ መክነፍ ነው የምፈልገው.. .

አሁኑኑ ሥሩ መገኘት...ግንባሩን ማሻሸት..እጆቹን መዳበሥ..ህመምን ማገዝና እሡን መንከባከብ ነው የምፈልገው...።ዳሩ ምን ያደርጋል ሠው የመሆናችን ዋናው ክፋቱኮ ውሥንነታችን ነው....ማድረግ በምንፈልገው የውሥጥ ፍላጎታችንና ማድረግ በምንችለው አቅማችን/ችሎታችን/መካከል ያለው የትየሌለ ልዩነት ነው...

<<መንፈሥ መሆን ነበር>>አልኩ ሳላሥበው ድምጽ አውጥቼ..

<<እረ በሥመአብ በይ>>አለኝ ሹፌሬ እሱባለው..ከእሱ ጋር መጨቃጨቅ አቆምኩና ሞባይሌን ከቦርሳዬ አወጣሁ...ደወልኩ...

"ሄሎ"

<<ሄሎ ማን ልበል...?>>

<<ቅድም የደወልሽልኝ ልጅ ነኝ..>>

<<እእእ..የአዲሣባዋ...?>>

<<አዎ...በእናትሽ እንዴት ነው...?>>

<<አይ...አሁን ደህና ነው...>>

<<ሊያናግረኝ ይችላል...?>>

<<እረ እንደዛማ አይደለም...ማናገር አይችልም...በዛ ላይ አሁንም ህክምና ላይ ነው...ምን አልባት ነገ ካልሆነም ከነገ ወዲያ ነው ልታናግሪው የምትችይው...>>

<<ዘመዶቹ አልመጡለትም.....?አላገኘሻቸውም...?>>

<<አይ አግኝቼያቸዋለሁ...እህቱ መጥታለች...ታናግሪያታለሽ ላገናኝሽ...?>>

<<አይ አታውቀኝም ይቅርብኝ...ባይሆን ቆይቼ አንቺኑ ደውዬ ሥለ ሁኔታው ብጠይቅሽ ይሻላል...እኔም እየመጣሁ ነው>>

<<በእውነት....?እየመጣሽ ነው...?>>የተደነቀና የተገረመ ድምጽ...ግራ ገባኝ....እመጣለሁ ማለቴ ልጅቷን ለምንድነው እንዲህ ያሥደነቃት....?የእኔ መምጣት ለእሷ ፋይዳው ምንድነው.....?ሥልኩን ከዘጋሁ በሁዋላ ሥለዚህ ጉዳይ ነበር የማሥበው...

ጉደር ሥንደርሥ 12 ሰአት ሆነ..እሡባለው እሱ ከሚፈልገው በጣም ፈጠነ አንዳንዴ እኔ ከምፈልገው ደግሞ በተንቀረፈፈ ሁኔታ እየነዳ ነው...ጭራሽ መንገዱን እያጋመሥን ሥንመጣ እና ሠአቱም ወደ ምሽቱ ሲቃረብ ጭንቀቴ በእጥፍ ጨመረ...መልሼ ሥልኬን መጎርጎር ጀመርኩ...ሥልኩ አይሠራም ...ደግሜ ደወልኩ<<የደወሉለት ደንበኛ ሥልክ ጥሪ አይቀበልም>>አለኝ

<<ምን አይነት ብሽቅ ነኝ...?>>

<<ምን ሆንሽ ደግሞ...?>>አለኝ እሱባለው በአንድ አይኑ የፊት ለፊቱን መንገዱን እያየ በአንድ አይኑ ደግሞ ሸርፎ እኔን እያየኝ እና በትዝብት እየሸረደደኝ....

<<ሥልኩ አይሠራም>>

<<የማን....?>>

<<የዋቅቶላ ነዋ...በእሡ ሥልክ ነበር ነርሷ ሥታናግረኝ የነበረው...አሁን ጥሪ አይቀበልም ይላል>>

<<ባትሪ ጨርሶ ይሆናላ>>

<<እ ሱማ እንደዛ ሆኖ ነው..ግን የነር ሷን ሥልክ መቀበል ነበረብኝ>>

<<ይዘጋል ብለሽ ስላላሰብሽ ነዋ>>ሊያጽናናኝ ሞከረ

<<እኮ ማሠብ ነበረብኝ...እሺ አሁን ምን ይውጠኛል...?>¢

<<ምን ይውጠ ኛል....?መታገሥ ነዋ....ወደዛው እየሄድንኮ ነው>>

<<እኮ....እዛ እሥክንደርሥሥ....>>

<<እረ  ሲሱ ተረጋጊ....ከመቼ ጀምሮ ነው ፎንቃ እንዲህ የጠለፈሽ...በእውነት በጣም ነው የገረመኝ>>

<<ምኑ ነው የሚገርምህ...ምን ወሬ ታበዛለህ..አሁን በህይወትና በሞት መካከል ሥላለ ሠው ማሠብና መጨነቅ በፎንቃ ከመያዝ ጋር ምን አገናኘው...>>

<<እረ ቀዝቀዝ...እንዲሁ ለጨዋታ ነው ያነሣሁት>>

<<ቢሆንሥ....?ዝም ብለህ ትዘባርቃለህ እንዴ....?>>

<<ይቅርታ አልኩ እኮ>>ግራ ገብቶትና ደንግጦ.....

<<በል እሺ አፍጥነው>>

<<ይቅርታ...እሡን አልችልም>>

<<ማለት...?>>አልኩት...ደም ሥሬ ሁሉ ግትርትር ብሎ በጥርሤ ልዘነጥለው በጥፍሬ ልቦጫጭረው እየዳዳኝ።...

<<ማለትማ ዳገትና ገደሉን እያየሽው አይደል እንዴ.....?በሠላም የፈለግሽው ቦታ ደርሠሽ ማየት የምትፈልጊውን ሠው ለማየት አትፈልጊም..?

<<እሡማ እፈልጋለሁ...>>አልኩ ቀዝቀዝ ብዬ...የመንገዱን ግራና ቀኝ እያየሁ...

...እውነቱን ነው አሁን ወደሚታየኝ ገደል መኪናዋ ተሽቀንጥራ ሥትገለባበጥና ሁለመናችን ብትንትን ሲል በአይነ ህሊናዬ ታየኝና ዘገነነኝ።ከዛም አልፎ ውሥጤ ሽብር ተሠራጨ...ሞትን በዚህ መጠን ሥፈራ የመጀመሪያ ልምዴ ነው....

በቀደመ ልምዴ ብሞት ምን አጣለሁ....?ከህይወትሥ ምን አገኛለሁ....? ብዬ ለመጠየቅ በምገደድበት አጋጣሚ ከውሥጤ አገኝ የነበረው መልሥ...በመሞት እና በመኖር መካከል ያለውን ልዩነት ምንም ነው የሚል ነበር።....አሁን ግን ለመኖር ያለኝ ጉጉት ሣላውቀው ወደ ላይ ተሥፈንጥሮ ሠማይ ላይ ተሠቅሎ አገኘሁት...ይሄን የታዘብኩት ደግሞ አሁን ነው..አሁን በዚህቺው ደቂቃ..

በሥንት ጣርና መከራ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ፊንጫ ከተማ ደረሥን።ግራ ገባኝ...እንቀጥል ወይሥ አልጋ ይዘን እዚሁ ፊንጫ አድረን ለሊት እንሂድ.......?

<<ምን ትላለህ......?>>አልኩት በራሴ መወሠን አቅቶኝ

<<ምኑን በተመለከተ...?>>

<<እንቀጥል ወይሥ እዚሁ ፊንጫ አድረን ለሊት እንሂድ....?>>

<<እንደኔ እንደኔ እዚሁ ብናድርና ለሊት ብንበር ይሻላል ባይ ነኝ...አሁን ብንሄድም እዛ ሥንድርሥ አራት ሠአት ያልፋል...በዛ ሠአት ደግሞ ሆሥፒታልም መግባትና ማየት አንችልም...አልጋም ልናጣ እንችላለን>>

<<አልጋው እንኳን ችግር የለውም ላንድ ቀን መኪና ውሥጥ ብንተኛሥ ለአንድ ቀን ምን አለበት....?>>አልኩት በትዝብት።

<<አይ እንደፈለግሽ....ንዳ ካልሽኝ ልንዳው>>አለ ኝ

<<ንዳው ልበለው ወይሥ ምን ይሻላል....?እያልኩ ከራሴ ጋር ሥወዛገብ ሥልኬ ጠራ....አየሁት።ጋሼ ናቸው።>>

አነሣሁት <<ጋሼ ምን ይሻለናል....?በጣም ነው የጨነቀኝ....? ሻንቡ መድረሥ አልቻልንም.....?እሡባለውን ዛሬ ቢያዩት በጣም ለግሟል...መኪና የሚነዳ ሣይሆን ጋሪ የሚገፋ ነው የሚመሥለው....አሁን ፊንጫ ከተማ ነን...ብንሄድም ሆሥፒታል መግባት አንችልም ብሎኛል...ሥልኩም አይሠራም..በጣም ጨንቆኛል>>ተንጣጣሁባቸው።

<<ልጄ አይዞሽ ተረጋጊ....በቃ ጥሩ ተቃርበሻል እኮ....ሥለዚህ አሁን እዛው ያላችሁበት እደሩ...ከዚያም ለሊት ተነሱና በጥዋቱ ትደርሣላችሁ....>>

<<እንደዛ ይሻላል ጋሼ...?>>

<<በእኔ ይሁንብሽ እንደዛ ነው የሚሻለው...በሉ አሁን መኝታ ፈልጉ...እራሥሽን አረጋጊና እራት በልታችሁ ተኙ>>

<<እሺ ጋሼ>>

<<በይ ደህና እደሪልኝ....ጥዋት እንደደረሽ እና የልጁን ሁኔታውን እንዳየሽ ደውይልኝ>>

<<እደውልሎታለሁ ጋሼ...አመሰግናለሁ>>ሥልኩ ተዘጋ....ወደ ያዲ ሆቴል መኪናችንን አሥገባን..ይሄ ሆቴል ከከተማዋ የተሻለውና ትልቁ ነው...ጎን ለጎን ሁለት አልጋ ያዝን..ወደየክፍላችን እየገባን ሣለ አሥቆመኝና<<…ቦርሣሽን አሥቀምጪና እራት እንውጣ...?>>አለኝ እሡባለው

<<አይ አንተ ወጣ በልና ብላ...እኔ ማረፍ ነው የምፈልገው>>

<<እረ ተይ...ለሊት ይርብሻል>>

<<ግድ የለህም..ይቅርብኝ>>

<<እሺ እዚሁ ይምጣልሽ....?>>

<<አይ አልፈልግም...ለሊት 11:30 እቀሠቅሥሃለሁ>>

<<ጥሩ ተሠናብቼው መኝታ ቤቱን ዘጋሁና...አልጋዬ ላይ ዘፍ አልኩ...ልተኛ  ሳይሆን ልተክዝ...

.

.

.

.

ዋቅቶላ...

እሷ መልሳ ካልመጣች በሥተቀር ምንም የምነግራችሁ ነገር የለም ብያችሁ ነበር..አይደል..?አሁን እንግዲህ አንሥቼዋለሁ...።እናንተም ናፍቃችሁኝግ ነበር....እውነቱን ለመናገር ግን ያው በእናንተ ለመወደድ ካልሆነ በሥተቀር እንኳን ልትናፍቁኝ ትዝ ብላችሁኝም አታውቁ...እውነቴን ነው...በዛ ሁሉ ሃሣብ...በዛ ሁሉ እራሥንም እሥከመርሣት በደረሠ መብሠልሠል ውሥጥ እንዴት ሥለእናንተ ላሥብ እችላለሁ.....?እራሴንም ረሥቼ ነው የከረምኩት...እንዴ !!!!!!!ለካ ፍቅር የሚባለው ውጥንቅጥ ሥሜት እንዲህ ነው እንዴ.......?እረ እንዲህሥ ከሆነ ለጠላትም አይስጥ...

አሁን ወደ ዛሬው ጉዳይ ልመለሥላችሁ...በደሥታ ጦሽ ልልላችሁ ነው..ጠረኗ እየሸተተኝ ነው...አዎ እኔ ወዳለሁበት እየቀረበች ነው..ይታወቀኛል...እድሜ ለአንድ ሠው...እድሜ ለጽድቁ ሽማግሌ...ለካ ወዳ አይደለም እሷም እንደዛ የምትወዳቸው እና ሁሌ ከአፏ የማይጠፉት...የሆነው እንዲህ ነው...ዛሬ ሰባት ሰዓት ላይ ነበር ሥልኬ የጠራው ...ጂጂ ነበረች...ደውዬ ካናገርኳት ከ10 ደቂቃ በሁዋላ ነበር መልሶ የተደወለልኝ..ሳነሳው ግን እሳቸው  ነበሩ...

<<ሄሎ>>

<<ሄሎ ዋቅቶላ>>የሚርገበገብ ደካማ ድምጽ

<<አቤት ማን ልበል...?>>አልኩ ግራ ገብቶኝ..

<<ዜና እባላለሁ...የጂጂ አባት ነኝ ማለት እችላለሁ>>

<<አወቅኮት...ማለት እሷ ሥለ እርሶ ነግራኛለች>>

<<ጎሽ..እንግዲያው አንድ ነገር ልንገርህ...ጂጂ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም>>

አቤት የደነገጥኩት አደነጋገጥ...የቅርብ ዘመዴን ሞት የተረዳሁ ነው ያሥመሠልኩት

<<አይ ማለቴ ለጊዜው ደህና ነች..ግን አሳዳጊዋን ሴትዬ ለማጥቃት እንቅሥቃሤ ላይ ነች..በዚሁ ከቀጠለች ደግሞ ወይ የሆነ ወንጀል ሥትሠራ ትያዝና እሥር ቤት ትወረወራለች አልያም አደጋ ደርሶባት ደመ ከልብ ትሆናለች ብዬ በጣም ፈርቼ ነው>>

<<ታዲያ ምን ላድርግ.....?ይንገሩኝ..ልምጣ እንዴ.....?መጥቼ ልጠብቃት...?>> ሁሉን ነገር ጥለህ ብረር ብረር የሚል ሥሜት ወረረኝ...

<<አይ ልጄ እንደዛ አይደለም...ወዳንተ ውሠዳታ...እንደዛ ነው የሚሻለው>>

<<አይ ፋዘር...እሡንማ ሞክርያለሁ..ብዙ ቀን ለምኛታለሁ..ላሣምናት ..አልቻልኩም እንጂ>>

<<ዘዴ ፍጠራ..የሆነ ዘዴ ከፈጠርክ ሥለምታፈቅርህ ትታለልሃለች>>

<<ሥለምታፈቅርህ ነው ያሉት....?እሷኮ ሠው ማፍቀር አትችልበትም>>

<<አይ ልጄ እሱን እንኳን ተወው..የአፏን ሰምተህ ነው አይደል....?የፍቅር ጉዳይ ልብ ላይ ነው የሚጻፈው እንጂ ምላሥ ላይ አይንጠለጠልም...ከአንደበቷ የሚወጣውን ቃል ሳይሆን የልብ ምቷን አድምጥና ሥለአንተ የምታሥበውን ለመረዳት ሞክር ያን ጊዜ እውነቱን ትረዳለህ...

እኔን ከጠየከኝ በቃ በጣም አፍቅርሃለች...ግን ማመን አልፈለገችም...እንዲህ አይነት ሽንፈት ተሸንፋ ሥለማታውቅ ማመን ከብዷት ነው....>>

<<የሚሉት እውነት ቢሆን ደሥ ይለኛል>>

<<ነው ልጄ እመነኝ...እሷን እድሜ ልኳን ነው የማውቃት..ለማንም ወንድ እንዲህ አይነት ሥሜት ሲሰማት እንዲህም ሥትብሰለሰል አይቻት አላውቅም....እና የምትወዳት ከሆነ ውሰዳት..ደግሞ እመነኝ ምን አልባት የተገናኛችሁት ጥሩ ያልሆነ ቦታ ሊሆን ይችላል..ግን ወርቅ የሆ ነች ልጅ ነች...ለወደደችው የምትሞት የራሴ ላለችው ሠው የምትኖር ልጅ ነች....

<<ፋዘር አውቃለሁ...ሶስት ቀን አብሬ ኑሬ ብዙ ነገር ሥለ እሷ አውቄያለሁ...በጣም ነው የምፈልጋት...እኔ ስላለፈው ደንታ የለኝም..የትናንቷን ጂጂን ሳይሆን የዛሬዋን...አሁን ያለችዋን ጂጁን ከነ ክፍተቷ ነው የምፈልጋት>>

<<ተባረክ ልጄ...ጥሩ ሰው ነህ....ወድጄሃለሁ...እና ተሥማምተናል ማለት ነው አይደል...?>>

<<ምኑ ላይ ነው የተሥማማነው ፋዘር...?>>

<<ትወሥዳታለህ..?>>

<<እንዴት አድርጌ ፋዘር...?>>

<>ይሄውልህ እኔ አንድ ዘዴ አለኝ..ከአንድ ሰአት በሁዋላ ደውልላት..>>

<<ደውዬሥ...?>>

<<ማለቴ አንተ ሣትሆን በሌላ ሠው ትልሥደውልልና አንተ አደጋ ደርሣሶብህ እራሥህን ሥተህ ሆሥፒታል እንደገባህ እንዲነግሯት አድርግ>>

<<እንዴ ጋሼ...ይሄ ምን ይጠቅማል....?>>

<<እሷን ወደ አንተ ለማምጣት ነዋ>>

<<እረ አትመጣም>>

<<ሞክርና እየዋ...በል ቻው አሁን እየመጣች ነው>>ብለው ሥልኩን ዘጉብኝ...10 ደቂቃ እዛው ባለሁበት በመደንዘዝ ውሥጥ ሆኜ ነው ያሳለፍኩት..ምን አይነት ዘዴ ነው የነገሩኝ...?እንድትመጣልኝ እፈልጋለሁ....በምንም ሆነ በየትኛውም ዘዴ ብትመጣልኝ ለእኔ  ሰርግ ነው...ግን ደግሞ ታምሚያለሁ ብዬ አሥደውዬላት ባትመጣሥ.......?በዛ የተነሣ ውሥጤ ቢቀየማትሥ......?ፍቅሬ ቢቀዘቅዝሥ.......?ፈራሁ.....የምሠሥትለትን ሥሜት እንዳላጣ ፈራሁ...።

እንዴት ሠው  ስቃዩ እንዳይድንለት ይፈራል....?ከእሷ ጋር ያለኝ ፍቅር ማለት ለኔ ስቃይና ጣር ነው የሆነብኝ ....እና ተሳክቶልኝ ቢተወኝ ..ከፍቅሯ ብፈወሥና ከ ሥቃዬ ብገላገል ምኑ ነው ክፋቱ.......?

እረ ከነ ሥቃዬ ለዘላለም ልኑር...ብዙ ደሥታዎች በሥቃዩች የታጠሩና የተለወሡ ናቸው...ሰው ቃሪያ ሲኮረሽም እየለበለበውና እያቃጠለው ቢሆንም የምግብ ጣእም ግን ይጨምርለታል..የጂጂ ፍቅርም ለእኔ እንደዛ ነው የሆነብኝ...ፍቅሯ ልክ እንደሚጠጣ የሚያቃጥል...ነገር ግን በኑሮዬ ላይ ስውር ጣእም ያለው ደሥታ የነሠነሠብኝ ነው።

ለማንኛውም ከብዙ ማሠብና ውዝግብ በሁዋላ ወሠንኩ...የመጣው ይምጣ ብዬ ወሠንኩ....አንድ የሥራ ባልደረባዬ የሆነች እንሥት ፓሊሥን ጠራዋትና ነገርኳት....እየሳቀችብኝ ሥልኩን ተቀበለችኝ.... ደወለችና ታምሜ ሆሥፒታል እንደገባሁ ነገረቻት....ኮሥተር ብላ ነገረቻት...።

ሌላውን ነገር ያው ከእሷ ጋር ሥለነበራችሁ ዝርዝር ታሪኩን ከእኔ በተሻለ ታውቁታላችሁ...

ወደ እኔ እየመጣችና ጉዞ እንደጀመረች ያበሰሩኝ ሽማግሌዎች ናቸው....ከዛ ምን ልንገራችሁ..ሰማይን የጨበጥኩ ጨረቃን የረገጥኩ ነው የመሠለኝ..የምሆነውን አጣሁ...

አሁን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ፊንጫ እገኛለሁ....አዎ መኪና ውሥጥ ሆኜ መድረሷን አይቻለሁ...አቤት ሳያት እንዴት ልቤ ስንጥቅ እንዳለ...ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁዋት ሁሉ...ከመኪናዬ ወርጄ ወደ እሷ ለመንደርደር ቃጥቶኝ ነበር...በግድ ነው እራሴን ያረጋጋሁት..እሷ በዚህን ሰአት ሆሥፒታል እንዳለሁ ነው የምታውቀው...

አዎ አሁን መኪናቸውን ዳር አሥይዘው በማቆም ሥልክ እያወራች ነው...ጨርሳ ዘጋችው።ደግሞ እንዴት ቆንጅዬ ሆናለች...ቀሚሥ ነው የለበሠችው..እኔ ገዝቼላት የነበረውን ቀሚሥ..እኔን እራሤን የለበሠችኝ ነው የመሠለኝ...ደሥ አለኝ...አዎ ወደ እኔ ሥትመጣ እኔ የገዛሁላትን ልብሥ ለብሣ መምጣቷ እኔን ለማሥደሠት ያላትን ፍላጎት ያሳያል..አዎ ሽማግሌው ትክክል ናቸው ታፈቅረኛለች....ከብዙ መወዛገብ በሁዋላ መኪናቸውን ወደ አንዱ ሆቴል አሥገቡት...የእኛም መኪና ከሁዋላ ተከተላቸው...አልጋ ሲይዙ ከመኪናችን ሳንወርድ እያየናቸው ነው...ክፍሏ ገብታ ሥትዘጋ ሁሉ እያየዋት ነበር...

ከዛ በላይ መጠበቅ አልተቻለኝም...ጓደኞቼን እዛው መኪና ውሥጥ ጎልቼ ወጣሁ..ወደ ክፍሏ ተንቀሳቀሥኩ..ደረሥኩና አንኳኳሁ...ᐸᐸማነው....?>>

ᐸᐸመታወቂያ>>አልኩ ድምጼን ጎርነን አድርጌ....

ከተወሠነ ሠከንድ መንገዳገድ በሁዋላ ተከፈተᐸᐸእፊቷ ተገተርኩ..ነገሬም አላለችኝ..ቀናም ብላ ሣታየኝ መታወቂያዋን አቀበለችኝ...

ᐸᐸአይታይም>>ብዬ ወደ ውሥጥ ገባሁ...ግራ በመጋባት ቀና ብላ አየችኝ...ወደ ሁዋላዋ ሸሸች

....አይኖቿን ጨፈነች...ገለጠች...መልሳ ጨፈነች...ነገረ ሥራዋ ሥላላማረኝ ለማንኛውም ብዬ በራፉን ዘጋሁት...ዋይይይይይይ....>>ጆሮዋን በሁለት እጇ ደፍና አንባረቀችው....መልሼ እኔው ደነገጥኩ..ቶሎ ብዬ አፏን በመዳፌ ደፈንኩት..ከውጭ የእግር ኮቴ...የመሯሯጥ ድምጽ ይሠማኛል...አዎ ትክክል ነኝ...በራፉ ተንኳኳᐸᐸምንድነው ጩኸቱ....?ችግር አለ እንዴ...?>>

ᐸᐸአይ ሠላም ነው..እቃ ወድቆብን ነው...ችግር የለም>>አፌ ላይ የመጣልኝን መልሥ ሰጠዋቸው..

እግዜር ይሥጣቸው በቀላሉ አምነውኝ ተመለሡ...እሷ ግን ትቀጠቅጠኝ ጀመር...በጥፊ...ደረቴ በጡጫ..ወደ ራሴ አፍኜ ጨምቄ አቀፍኳትᐸᐸደደብ ነህ...እንዴት እንደዚህ ታደርገኛለህ......?እንዴት እንዲህ ታሠቃየኛለህ.....?እንዴት እንደዚህ ታሥደነግጠኛለህ...?>>አለቀሠች...አለቀሠችኮ!!!አንገቴ ሥር ተወሽቃ የምታፈሠው እንባ ትካሻዬ ላይ እየነጠረ ወደ ገላዬ ሲሰርግ ቅዝቃዜው ይታወቀኛል...በእኔም አይኖች ውሥጥ እንባ ግጥም አለ...በዚህ መጠን ማፍቀር.....በዚህ መጠን መፈቀር....በዚህ አይነት መንሠፍሠፍ መተቃቀፍ...በዚህ አይነት ሥሜት እንባ ማፍሠሥ..ጌታ ሆይ ይሄን ደሥታ ህልም እንዳታደርገው...ህልም ከሆነ ደግሞ እንድነቃ አታድርግ...በቃ እሷ ከሌለችበት የእውነት ህይወት ከእሷ ጋር ባንድ ላይ የህልም አለም ውሥጥ ለዘላለሙ ብጠፋ ይሻለኛል>>ጨምቄ እንዳቀፍኳት ለአምላኬ ያሠማሁት ጸሎት ነበር....ከልብ የመነጨ የማጣት ፍርሃት የወለደው ፀሎት......አሁን ተኝቻለሁ እዚህ ቤት እዚህ አልጋ ላይ ማደር ከጀመርኩ 3 ቀን ሆነኝ።

መኝታ ቤቷ ሶስት በሶስት የሆነች የምታምር ክፍል ሥትሆን በውሥጧ መካከለኛ ሥፋት ያለው መዝቦልድ አልጋ ተዘርግቶበታል።

ሻንቦ ከተማን ወድጃታለሁ ብላችሁ ውሸት ይሆንብኛል ከተማዋ አንድ እድሜዋን በሙሉ ፒያሳ ለኖረች የአራዳ ልጅ ምንም የከተማነት ጣእም የሌላት እልም ያለች የገጠር መንደር ነች ብትል ጉረኛ ልትባል አይገባም ለነገሩ እኔ እንደዛ አልተሠማኝም ምክንያቱም ብዙም ለውጪው ማለቴ ለከተማዋ ሥፋትና ጥራት ትኩረት አልሠጠውም....ቤቱን ግን ወድጄዋለሁ ብቻ አይገልጸውም..ልጅቷን...አሮጊቷንሥ ቢሆን አሮጊቷ ያልኳችሁ የዋቅቶላን እናት ነው...በጣም ጥሩና ደግ አዛውንት ናቸው..ከአማርኛ ይልቅ ኦሮምኛ ቋንቋ ይቀናቸዋል...እኔም ቋንቋውን የማውቅ ይመሥላቸውና አንዳንዴ ድንግርግሬን ያወጡታል...

<<ልጄ ከቤተሠቦችሽ ጠፍተሽ ነ...?>>ይጠይቁኛል በመጨነቅ..

በእሳቸው እይታ እኔ ገና ክፉና ደጉን ለይቼ የማላውቅ አንድ ፍሬ ጨቅላ ልጃገረድ ነኝ።..ይህን ያልኩት ከምንም ተነሥቼ አይደለም...ከመጣሁ እለት ጀምሮ ከቤተሠብ ጋር አምሽቼ ለብቻዬ ለመተኛት እዚህች አሁን ወዳለሁባት ክፍል መግባቴ ከመፍራቴ...ጨዋ ከመሆኔ...ድንግልናዬን እንዲሁ በቀልድ ላለማሥወሠድ የማደርገው ጥረት አድርገው ነው የወሠዱት...እና ይሄ ደግሞ በእሣቸው ከፍተኛ ክብር አሰጥቶኛል።

<<ጎሽ ልጄ እንደዘመኑ ልጆች አይደለሽም>>አሉኝ...ፈገግ አልኩ..እውነትም ከዘመኑ ልጆች በተቃራኒ እየተሽኮረመምኩ በውሥጤ <<አልሠሜን ግባ በሉት...>>እያልኩ..በነገራችን ላይ እዚህ ሻንቡ ከተማ ከገባሁና እዚህ ቤት ከረገጥኩበት ቀን ጀምሮ አንገት ደፊ ተቅለሥላሽና በጣም ጭምት ልጅ ወጥቶኛል...ለራሤም እሥኪገርመኝ ድረሥ....መቼሥ ፒያሣ ላይ የሚያውቀኝ ሠው አሁን የሰሞኑን ሁኔታዬን ቢመለከት ምን አይነት አሥመሳይ ልጅ ነች ብሎ አሥተያየት መሥጠቱ አይቀርም...እኔ ግን ለማሥመሠል ብዬ ምንም የሞከርኩት ነገር የለም...ግን በቃ ውሥጤ ነው እንደዛ እንድሆን የሚገፋፋኝ..ልንቀልቀል ብልም እግሬ አይፈጥንልኝም...ልለፍልፍ ብልም አንደበቴ አይላቀቅልኝም...ልፍጠጥ ብልም ቅንድቤ አይበለጠጥልኝም...አሮጊቷ በሠሞኑ አብሮነታችን ልጃቸው ጥሎን ሲወጣ ያወሩኛል...<<አይዞሽ ልጄ...ክብሯን የምትጠብቅ ልጅ እወዳለሁ...ከጋብቻ በፊት እንዲች ብለሽ>>..በገዛ ልጃቸው ላይ ያሣድሙበታል...ወደድኳቸው...በውሥጤ እያፈርኩ ወደድኳቸው..ምነው እሳቸው የ ሳሏትን ልጅ ሆኜ ቢሆን ኖሮ ሥል እየተመኘሁ....

ልጃቸውን የማግባት ፍላጎት የለኝም...ግን እሳቸው እናቴ እንዲሆኑ እፈልጋለሁ..አይ አሁንም ይሄ ዙሪያ ጥምጥም መዞር አልተወኝም...እውነት ጂጂ ይቅርታ ሻንቡ ከመጣሁ ጀምሮ ከማገኛቸው አዳዲሥ ሠዎች ጋር ሥተዋወቅ እጅጋየሁ እባላለሁ....እጅጋየሁ ዜና ብዬ ሙሉ ሥሜን በወጉ መናገር ጀምሪያለሁ......ያው ዜና ትክክለኛ አባቴ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ...ዜና ጋሽ ዜና ናቸው...ከእኔ ሥም ቀጥሎ ለመጠራት ብቃቱም መብቱም ያለው ይሄ ዜና የሚሉት ሥም ነው....በእኔ ህይወት ውሥጥ ድርሻ ያለው...እና ወደ ነገሬ ልመለሥና <<እጅጋየሁ በእውነት ዋቅቶላን ማግባት አትፈልጊም....?የዚህ ቤት እማወራ ለመሆን ፍላጎት የለሽም...?ብዬ እራሤኑ ሥጠይቅ ....<<በፍጹም..>>ብዬ ለራሴ ልመልሥ አፌን እከፍትና መግጠም ያቅተኛል...ያንቀኛል....ቃላቱን ማሥፈንጠር ያቅተኛል።

ውይ የመኝታ ቤቱን በር የሚቧጭር ነገር አለ ...ምንድነው ሰአቴን አየሁ አራት ሠአት ተኩል ነው.....እረ የመንኳኳት አይነት ድምጽ እየተሠማኝ ነው...ደካማ የበር መንካት አይነት ድምጽ...ድምጹ ሌላ ክፍል እንዳይሠማ የመፍራት አይነት ስሜት ያለው.....<<ምን አይነት ድመት ነች ይሄን ከመሠለ ሃሣቤ መንጭቃ የምታወጣኝ.....?>>

እየተነጫነጭኩ ከወልጋዬ ወረድኩ...እርቃኔን ነኝ።በሠውነቴ ላይ ያለው ሠማያዊ ፓንቴ ብቻ ነው..በራፉን ቀሥ ብዬ ከፈትኩት...ድመቷን ላባርራት...<<በአራዳው ጊዩርጊሥ..!!!በራፉ ላይ ማን እንደተገተረ ታውቃላችሁ.....?እሥኪ ገምቱ>>አትቸኩሉ አላገ ኛችሁትም...ማለቴ ግምታችሁ ትክክል አይደለም...ዋቅቶላ መሥሏችሁ ነበር አይደል....?በራፍ ላይ የቆመችው የዋቅቶላ ትንሽ እርግብ ነች...በእንቅልፍ የደከሙ አይኖቿን በዛ የሚያምር ሚጢጢ እጇ እያሻሸች በሌላ እጇ በራፉን ሥትቧጥጥ የነበረችው......

<<ቦንቱ ምን ሆነሽ ነው...?>>

<<እማ እማ...>>እጆቿን እንደ ምርኮኛ ግራና ቀኝ አንከርፍፋ...እንዳቅፋት መሆኑ ነው>> በርከክ ብዬ አቀፍኳት እና ወደ ውሥጥ ገባሁ..በራፉን መለሥ አደረኩትና ወደ መኝታዬ ይዣት ወጣሁ...ክንዴን ተንተርሳ  ጡቶቼ መካከል ገብታ ውሽቅ አለች...

<<ምነው የኔ ጣፋጭ....?ጸጉሯን እያሻሸሁላት ..ምንም አልመለሠችልኝም..ጭራሽ አይኖቿን ከደነች...በውሥጤ የተሠማኝን ሥሜት ልነግራችሁ አልችልም...እንዴት እግዜር እንዲህ ደግ ሊሆን ቻለ......?

እሱ መቼሥ ሲሰጥ ስስት የለበትም።...እድሜዋን መሉ ሥትገፋና ሥትበደል የነበረች..ዘር ማንዘር ያልነበራት ወፍ ዘራሽ ልጅ በአንዴ ሙሉ ቤተሠብ ሲሰጣት ይሄ መቼሥ መመረቅ ነው....?እሥከ መቼ ይሆን ይሄ ደሥታ ከእኔ ጋር የሚቀጥለው....?

...የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና እኔ የሚያበቃልኝ ይሄንን አሁን የተሠ ጠኝን ፍቅር የተነጠቅኩ ቀን ነው።...

እሥከዛሬ ዋቅቶላ በምን ያህል መጠን እንዳፈቀረኝ ታውቃላችሁ...እናቱም እንዴት እንደተቀበሉኝ በመጠኑም ቢሆን ነግሬያችሆለሁ...የዚህችን ህጻን ያህል ግን የወደደኝ የለም...እንደመጣሁ ነው የተለጠፈችብኝ..ልክ ለብዙ ጊዜ እንደምታውቀኝና ሥትጠብቀኝ እንደኖረች አይነት..ቀኑን ሙሉ ወደ ሣሎን ሥሄድ ሥትከተለኝ.....ኩሽና ሥገባ አብራኝ ሥትገባ..ይገርማችሁዋል ሽንት ቤት ሥገባ እንኳን አታምነኝም<<...እማ...>>ሥትለኝ

የእውነት እናቷ የሆንኩ ነው የሚመሥለኝ...አሁን ከአንድ ሠአት በፉት እራት እየበላን ሣለ ክንዴ ላይ ነበረ እንቅልፍ የወሠዳት...ከዛ ቀሥ ብዬ ከአባቷ አልጋ ላይ አሥተካክዬ አሥተኝቼያት ነበር የመጣሁት...ከእሡ ጋር ሥለምትተኛ...ይሄው ስትነቃ እና ሥታጣኝ መጣች.....

እና ታዲያ መጨረሻዬ እንዴት ነው የሚሆነው......?እዚህ ቤት ውሥጥ ነገን ብቻ ነው የምውለው...የጀመርኩትን ነገር ለመጨረሥ ወደ አዲስ አበባ እመለሳለሁ...እቅዴን ለማሣካት ደግሞ ቢያንሥ አንድ ወር እዛው መቆየት ይጠበቅብኛል....በዛ ላይ አደጋ ሊያጋጥመኝ ይችላል...ልታሠርም እችላለሁ...

እና እንዴት ነው የምችለው......?እንዴት ነው ከዚህች መላእክ ተለይቼ የምኖረው......?እና ቢቀርብኝሥ.....?አዎ ቢቀርብኝሥ....ሮማንን ለመበቀል መባከኑ ቢቀርብኝ...እርግፍ አድርጌ ብተወው...ይቅር ብላት.....?

<<አይ ወይዘሪት ጂጂ ይሄማ ደካማነት ነው....ለአዕምሮሽ ፊት አትሥጪ...ያቺን አውሬ በቂ ቅጣት ሳትሰጪያት እና ከዚህች ምድር ሳታሰናብችያት ወደ ሁዋላ ብትይ የእናትሽ የሙት መንፈሥም ይቅር አይልሽም>>እራሴን ገሰጽኩ...አበረታሁ..አዎ በእቅዴ መሠረት ነገን ብቻ ውዬ መሄድ አለብኝ...አዎ ጠላቴን ለመበቀል..ከዚህ የበለጠ ፍቅር ቢሰጠኝ እንኳን እሰዋዋለሁ እንጂ አልታለልም..ሮማን በምትኖርበት ምድር ላይ እኔ መኖር አልፈልግም..የእኔ አዲሥ ህይወት መጀመር ያለበት በእሷ ሞት ላይ ነው....ውሳኔዬን አደሥኩ.....ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው..አሁንም ሳልቀረቅር የረሳሁት በራፍ በዝግታ ተከፈተ.....

ቀና ብዬ አየሁ...አሁን ደግሞ አባትዬው ነው..ዋቅቶላ።አንገቱን አስግጎ ወደ ውሥጥ እያየ ነው...

<<አንቺ ነሽ የወሠድሻት....?>>በማለት ጠየቀኝ.....ብንን ሲልና ልጁን ከጎኑ ሲያጣት ነው ፍለጋ የመጣው...አለመተኛቴን ሲያውቅ ወደ ውሥጥ ገባ

<<አይ...እራሷ ነች የመጣችው>>

<<ወይ ጉዴ...የእኔ ይሁን ልጄን ደግሞ ምን አሥነካሽብኝ....?>>እያለኝ መጣና አልጋው ጠርዝ ላይ አረፍ አለ..

<<ቀናህ እንዴ...?>>

<<አይ አልቀናሁም...ፈራሁ እንጂ>>ሲል መለሠልኝ።..አልመለሥኩለትም...ዝም አልኩት...ምክንያቱም እሱ ብቻ ሳይሆን እኔም ፈርቼያለሁ....ነገ በጣም ያሥፈራል።

.....ከተወሠነ በዝምታ የታገዘ መተከዝ በሁዋላ ተነሳ....ወደ ውጭ መራመድ ጀመረ....<<አይዞህ አታሥብ ከእኔ ጋር ይመቻታል>>አልኩት...ለልጁ እንዳይጨነቅ በራፉ ጋር ደረሠና ከፍቶ ይወጣል ብዬ ሥጠብቅ..ቀረቀረውና ተመልሶ መጣ...ደነገጥኩ..ልክ እሥከዛሬ አብሬው ተኝቼ እንደማላውቅ ሁሉ ደነገጥኩ...ልክ ልጃገረድ እንደሆንኩ አይነት...ልክ ተሳሥቶ እንዳያሣሥተኝ እንደፈራሁ አይነት...

<<ምን እየሰራህ ነው....?>>

<<እኔም ካንቺ ጋር ብተኛ ይመቸኛል....?>>

<<አይሆንም...>>

<<ለምን.....?>>

<<አይሆንማ እናትህ ምን ይሉናል....?>>

<<ምንም አትለንም....አብረው ተኙ ብቻ ነው የምትለን>>አልጋው ላይ ወጣና ከሁዋላዬ ተሻግሮ ብርድ ልብሱን ገልጦ ገባ......

<<ቀሺም ነህ.....እናትህ ሌላ ነገር እንዲያሥቡና እንዲደብራቸው አልፈልግም>>

<<አትነጫነጪ...ትንሽ ተኝቼ እሄድልሻለሁ>>ወደኔ ዞሮ አቀፈኝ...እኔ ፊቴን ወደ ቦንቱ ነው ያዞርኩት...እሱ እኔን እኔ ደግሞ የእሱን ልጅ እንዳቀፍን በፀጥታ ተዋጥን....ለረጅም ደቂቃ በፀጥታ....

<<ተኛሽ እንዴ...?>>አለኝ......ምንም አልመለሥኩለትም....እንደውም ቀና ብሎ ካየኝ ብዬ አይኖቼን ጨፈንኩ...ማውራት አልፈለኩም...ከጎኔ ሥለተኛ ደሥ ብሎኛል ግን ደግሞ ፈርቼያለሁ...እናቱ ቢያውቁሥ........?እንደዛ መክረውኝ.....እንደዛ አሥጠንቅቀውኝ.....ድንግልናዬን ላሥወሥድ....?የራሴው ቀልድ ለራሴው ፈገግ አሰኘኝ...

እንደገመትኩት ቀና ብሎ አንገቱን ወደፊት አሰገገና አየኝ....መተኛቴን ሲያረጋግጥ ወይም የተኛሁ ሲመሥለው ተንጠራራና መብራቱን አጠፋው......

እኔ ቀድሜ ከተኛሁበት ወጥቶ ይሄዳል ብዬ ነበረ ያሰብኩት እሱ ጭራሽ ለብሶ የመጣውን ቁምጣ እያወለቀ ነው.....ተመልሶ ተኛ....አቀፈኝ....መቀመጫዬ ላይ ተለጥፎ አቀፈኝ...መላ አካሉ አካሌ ላይ ተጣበቀ...እንዲህ ሲሆን የመጀመሪያ ቀናችን ነው....ሁለታችንም እርቃን ሆነን እንዲህ ተኝተን አናውቅም....የውሸት ማንኮራፋቴን ቀጠልኩ.....የውሸት ማንኮራፋቴን ቀጠልኩ...አዎ ማንኮራፋት አለብኝ...ምክንያቱም ጥልቅ እንቅልፍ ውሥጥ አይደለሁ ያለሁት...እሱ ይበልጥ ተጣበቀብኝ...እና ጨነቀኝ...በራሴ መተማመንም አቃተኝ...ለምንድነው ይሞቀኝ የጀመረው......?ደግሞ ምን አለ ጆሮ ግንዴ ላይ ባይተነፍሥብኝ...የትንፋሹ ሙቀት ቆዳዬ ላይ ብቻ ተበትኖ አይጠፋም ወደ ውሥጤ ሰርጎ ከደም ስሬ ጋር በመቀላቀል ወደ ጠቅላላ ሠውነቴ ሲሰራጭና የውሥጥ ሙቀቴን ሲያንረው ይታወቀኛል...

ቀኝ እጁ ከትካሻዬ ላይ ተንሸራቶ ጡቴ ላይ አረፈ...የጡቴን ጫፍ በስሱ ያሻሸው ጀመር....እንዴ ምን አባቱ እያደረገ ነው........?ተው እንዳልለው ደግሞ ተኝቻለሁ...እያንኮራፋሁ ነው...ምን ይሻለኛል....እረ ፓንቴም ሊቀደድ ነው...ምን አይነት ደረቅ ችካል ነው የሚሠረሥረኝ........?አሁንማ መንቃት አለብኝ.....አዎ ነቅቼ አይኖቼን ከፍቼ ይሄን ሠውዬ ከዚህ ቤት አሽቀንጥሬ ማሥወጣት አለብኝ....ግን አልቻልኩም.....እንዴት አድርጌ ልንቃ...?ይገርማል አይደል ሠው ከውሸት እንቅልፉ መንቃት ሲያቅተው ይሄ እንኳን ለሠሚውም ለእኔም ለእራሤ እንቆቅልሽ ነው....ግን የእውነቴን ነው..ለነገሩ በህይወት ውሥጥም የእውነት ከተኙት ይልቅ ለማሥመሠል ያሸለቡት ናቸው ዋናዎቹ እንቅፋቶች......

........አይኖቼን ለመግለጽ እየፈለኩ ነው እንቢ ያለኝ...እጆቼን ለማነቃነቅ እየፈለኩ ነው አልታዘዝ ያሉኝ.....አንደበቴን እራሡ አላቅቄ ተወኝ ማለት አልቻልኩም....እንዴ ጉድ ፈላ.....ጉድ ፈላ....ምን ተፈጠረ መሠላችሁ....የጠረጠርኩት ብቻ ሆኖ እንዳይሆን.....?የሆነ ሙቀት ነገር ጭኖቼ መካከል ተሠማኝ...እርጥበት ነገር...።

እረ ለወሬ አትቸኩሉ እሡ ረጭቶ አይደለም እኔው ነኝ በራሤው የረጣጠብኩት....።

....እንዲህ አይነት መሸነፍ እንዲህ አይነት መበላሸትማ አይደረግም...እንደምንም ከራሴ ታግዬ አይኖቼን ገለጥኩ...እጄን አንቀሳቀስኩና ብርድ ልብሱን ከላዬ ላይ አሽቀነጠርኩ...ቀሥ ብዬ ጥልቅ እንቅልፍ ላይ የምትገኘውን ቦንቱን ከእጄ ላይ አወረድኩና እንዳትነቃ በጥንቃቄ ትራሱ ላይ አሥተካክዬ አሥተኛዋት...ከዛ ቁጭ አልኩ...እሱ በፍራቻ አፈግፍጎ የግድግዳውን ጥግ ይዟል...

ቀኝ እጄን ወደ ጭኔ ላኩ...በፓንቴ ውሥጥ እጆቼን ሠድጄ ብልቴን ፈተሽኩ...አዎ በትክክል ዝናብ እንዳጥለቀለቀው መረሬ መሬት በፈሳሽ ላቁጧል...ይሄ ቀላል እንዳይመሥላችሁ...ይሄ በህይወቴ ገጥሞኝ የማያውቅ ክሥተት ነው..ይሄ ማለትኮ የእውነት በዚህ እሥሬ በተኛው ወንድ ለመሸነፍ ተዘጋጅቼያለሁ ማለት ነው...

....የእውነት ወሲብ በሚሉት አዚም ለመደሠት ቋምጪያለሁ ማለት ነው....።

መብራቱን ተንጠራርቼ አበራሁት..እርቃን ገላውን ኩርምትምት ብሎ ምን ይፈጠር ይሆን.....?በሚል ፍራቻ እየተቁለጨለጨች ያየኛል...ዝላይና ተጠምጠሚበት...እላዩ ላይ ወጥተሽ በደሥታ ጨፍሪበት...ከንፈሩን በከንፈርሽ ግመጪው...እነዚህንና የመሳሰሉትን ብዙ ብዙ ሥሜቶችን በአንዴ ሥትከፋፍይና ሥትሸራርፊ አድርጊ የሚል ሥሜት ቀሠፈኝ....ያደረኩት ግን ተቃራኒውን ነው...

<<ተነስ ውጣልኝ...አሁኑኑ ውጣልኝ>>አይኔን አጉረጥርጬ

......ምንም አልተከራከረኝም ሹክክ ብሎ ተነሳና ከወልጋው ላይ ወረደ አወላልቆ እዚህም እዚያም የወረወራቸውን ልብሶቹን ሰበሰበ...እንደ ህጻን ልጅ በጉያው ወሽቆ እርቃኑን ክፍሉን ለቆ ወጣ....

<<በቃ ተመለሥ>>ልለው ዳድቶኝ ነበር.....ቃላቱ ግን ከአንደበቴ ሊሾልክ አልቻለም...>>ተነሳሁና በሩን ቀረቀርኩት..እንባዬን አፈሠሥኩ...አዎ ልክ እንደበቀደም ለታው ዛሬም አለቀሥኩ

..ወደ መኝታዬ ተመለሥኩ..እንዲሄድ አልነበረም የፈለኩት<<…ምን አባሽ ሆንሽ...አልሄድም...እንዲጋፈጠኝና እንዲያሸንፈኝ....በቀላሉ ተሸንፎ ጥሎኝ ሲሄድ ውሥጤ ሥብርብር አለ.....እንዴት እንዲህ ያደርገኛል....?

መንጋት አይበለው ነጋ....የዋቅቶላ እናት ጣት የሚያሥቆረ ጥም ጨጨብሳ ሰርተው ከእርጎ ጋር ቁርሥ አቀረቡልን...በላን...በተለይ እኔ ደሥ ብሎኝና ጣፍጦኝ ነው የበላሁት...ዛሬ ቅዳሜ ሥለሆነ ዋቅቶላ ሥራ አልሄድም ብሎ በቢጃማ ነው ያለው...ሁለታችንም አይን ላይን መተያየት ፈርተናል..

የእሱን አላውቅም እኔ ግን ከማታው ነገር ይልቅ ዛሬ የሚሆነው ነው እያሥጨነቀኝ ያለው...ነገ እንደምሄድ አያውቅም...እንዴት አድርጌ እንደምነግረው ጨንቆኛል....እንዴት ብዬ ምንሥ ተናግሬ አሳምነዋለሁ......?ነው ወይሥ ዝም ብዬ ለሊት በተኙበት ሹልክ ብዬ ልሂድ...እንዲህ ባደርግ ደግሞ ጥሩ አይሆንም ..<<እረ ምናባቱ እነግረዋለሁ..አላገባሁት ምን አጨናነቀኝ..............................እራሴን አበረታሁ..ግን ምንም ነገር ለእሱ ከመንገሬ በፊት ቆይ በመጀመሪያ እነ ስንዝሮ ጋር ልደውል..ሁለተኛውን ተልእኮ እንዲፈጽሙ ትናንትና ፍቃድ ሰጥቺያቸው ነበር...

ሁለተኛው የበቀል ተልእኳችን ቀለል ያለ ሥለሆነ እኔም ባልኖር ችግር የለውም ብዬ ሥላመንኩ...ዛሬ በለሊት ሶስቱም የሮማንን ቤት ሰብረው ገብተው...ከአልጋዋ ጋር ጠፍረው አሥረዋት...ፊት ለፊቷ ያቺን የምትወዳትን ድመቷን (ሰው በእሷ አሠርታ ነው እንዲህ ከተራ ሽርሙጥና ተነሥታ ያለፈላት እያሉ ያሟታል)...እና ድመቷን አይኗ እያየ እንዲታረድባትና በድመቷ ደም ሰውነቷን እንዲያጥቧት...በቤቱ መቃጠል በውሥጧ የነገሠውን ፍርሃት ይበልጥ ነፍሷ ድረሥ እንዲሠማትና እንዲያንቀጠቅጣት...የምትደበቅበት ጥግ እንድታጣ....በቁሟ መባነን እንድትጀምር...የራሷ ጥላ እንዲሸክካት...አዎ ይሄን ማድረግ ደግሞ ለእነሱ በጣም ቀላል ነው።...

.....ከሶሥተኛው እሥከ አምሥተኛው ወይም መጨረሻው የሚደረገው ተልእኮ ግን በጣም ውሥብሥብና አደገኛ ሥለሆነ የግድ እኔን ይፈልጋል...ደግሞ እያንዳንዷን ስቃዮን በአይኔ ማየት አለብኝ..በእኔ ሥቃይ ውሥጥ ለአመታት ደሥታ ሥትሸምት እንደኖረች ሁሉ አሁንም እኔ በተራዬ ከእሷ ስቃይ በሚቀዳ ሳቅ ዘና ማለት እፈልጋለሁ።...

.....ሥልኬን ይዤ ከእነዋቅቶላ ተለይቼ በጓሮ በር ወደ ውጭ ወጣሁ...ደወልኩ ሥንዝሮ ጋር..ያው ነገሮችን የማብራራት እና አሳምሮ የማውራት ችሎታ የተፈጥሮ ሥጦታው ነው ብዬ ነው እሱ ጋር መደወል የሚቀናኝ....

<<ሄሎ ስንዝሮ>>

<<ሄሎ ወፏ...ላጮህልሽ ስል ነው የቀደምሽኝ>>

<<የለሊቱ ሚሽን እንዴት ሆነላችሁ....?>>ቀጥታ መሥማት ወደምፈልገው ርእሥ ወሠድኩት

<<ሚሽኑ ባክሽ ከሽፏል>>ክው ነው ያልኩት

<<ምን ተፈጠረ....?ምን ሆናችሁ....? ማን ታሠረ.....?>>

<<እረ እንደዛ አይነት ነገር አልተከሠተም>>

<<እና ታዲያ......?>>

<<ሴትዮሽ ተሠውራለች...>>

<<ተሰውራለች ስትል.....?>>

<<ሁለት ቀን ሆናት በአዲሥ አበባ ውሥጥ የትም ቦታ አልታየችም...በተለይ የፒያሳን አንድ ጓዳ ጎድጓዳ አልቀረንም...>>

<<እና......?>>

<<እናማ እየፈለግናት ነው>>

<<የትም መጥፋት የለባትም...እናቷ ሆድም ብትገባ ጎትቼ አወጣታለሁ...ብትሞት እንኳን ከሲኦልም ቢሆን እመልሳታለሁ...ከእኔ ማምለጥ አትችልም...>>

እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ከጣሪያ በላይ እየጮህኩ ነው የማወራው....ዋቅቶላ እና አሮጊቷ በጩኸቴ ተደናግጠው ተከታትለው ወደ አለሁበት ቦታ መጡ...ግራ በመጋባት እያዩኝ ነው...አሮጊቷ እንደዛ ጭምት የነበርኩት ልጅ እንዲህ ነብር ሆኜ ስላዩኝ ተደናግጠዋል...ፈርተዋልም

<<ዋቆ....ሙጬዬ ማል ታቴ......?ማልቱ አከነቲ መራቺሴ.....?>> ብለው ሲጠይቁት ሰማሁ....

እሱ እንደፈዘዘ ነው...ምንም አልመለሰላቸውን....እኔም ምን እንዳሉ ለመረዳት አልቻልኩም...

ስልኬን ዘጋሁና ወደ እሱ በማፍጠጥ መናገር ጀመርኩ<<መሄዴ ነው...ነገ መሄድ አለብኝ>>አልኩት....አሁን ንዴት ላይ ሥላለሁ ከይሉኝታ ውጪ ሆኛለሁ...

ለማንም ሥሜት መጨነቅ አልፈለኩም....

<<ልጄ ቤተሠቦችሽ ናቸው ያበሳጩሽ.....?አይዞሽ ያለፍቃዳቸው ወደዚህ ሥለመጣሽ ተናደውብሽ ይሆናል>>በማለት ሊያጽናኑኝ ሞከሩ አሮጊቷ...ውሥጣቸው ያለውን ሥጋት በማንሳት በገባቸው መጠን......

<<እማማ ግድ የለም አያሥቡ ምንም አልሆንም>>

<<አዎ ትክክል....እኔ እያለውልሽማ ምንም አትሆኚም...ይሄ የእኔ ጅልኮ ምኑንም አያውቅ....በእንዲህ አይነት ሁኔታ ከቤተሠቦችሽ ነጥሎ ይዞሽ መምጣት አልነበረበትም....ቀድሞ ቢያማክረኝ ኖሮ ሽማግሌ እልክ ነበ...አይዞሽ አሁንም ይሥተካከላል...በእኔ ይሁንብሽ ከቤተሠቦችሽ እንድትታረቂ አደርጋለሁ....>>

የእሳቸው ማጽናናት ከመጠን በላይ  ተለጥጦ ሊፈነዳ የነበረውን ሥሜቴን አሥተነፈሠው......ተንደርድሬ ወደ እሳቸው ሄድኩና ተጠመጠምኩባቸው<<....እማማ እኔ የሚቆጣ ቤተሠብ የለኝም...እናቴም አባቴም ሞተዋል...>>ተናዘዝኩላቸው...ግን የእናቴሥ እሺ ይሁን ሞታብኛለች ወይም ተገድላብኛለች አባቴ የሞተው መቼ ነው....?የሌለ ነገር እንዴት ሊሞት ይችላል...ለመሞት እንኳ መጀመሪያ ተፈጥሮ መኖርን ይጠይቃል....

<<ያ ዋቅዬ...አይዞሽ እኔ እናት እሆንሻለሁ...>>እያጽናኑኝ ይዘውኝ ወደ ቤት ገቡ....እሱ በፍራቻ እንደተሸበበ ሹክክ ብሎ ከሁዋላ ተከተለን...በዚህ ጊዜ ህጿኗ ቦንቱ አብራን አለመኗሯን ወደድኩት...አክስቷ ነበረች በጥዋት መጥታ ከእቅፌ ፈልቅቃ እያሥለቀሠች የወሰደቻት....እቤት ገብተን ገና ተረጋግተን እንኳን ሳንቀመጥ ሌላ ሥልክ ተደወለልኝ...አየሁት...ጋሽ ዜና ናቸው...

አነሳሁት<<አቤት ጋሼ>>

<<ሰላም ነሽ ልጄ......?>>

<<ሰላም ነኝ>>

<<እንዴት ይዞሻል.....?>>

<<ደህና ነኝ...ነገ እመጣለሁ>>

<<ምን ልትሠሪ......?>>ጠንከር ባለና በሚጋፋ ድምጽ 

<<እንዴት ምን ልትሠሪ....?ወደ ቤቴ ነዋ>>

<<ኤዲያ ምን ቤት አለሽ...ቤት ማለትኮ ድንጋይና ቆርቆሮ ውሥጥ የተከማቸ ቁሳቁስ ያለበት ሥፍራ አይደለም....ያ ቤት ሣይሆን መጋዘን ነው የሚባለው...ቤት ማለት ቤተሠብ ያለበት ቦታ ነው...ሥለዚህ አርፈሽ እዛው ቆዪ ደግሞ ሴትዬዋን ፍለጋ ከሆነ እንዳትለፊ>>ስለ ሴትዬዋ ሲያነሡ ሥሜቴ ተነቃቃ...

<<ምን ሆነች.......?ስለ እሷ የሚያውቁት ነገር አለ.......?>>

<<አምልጣሻለች>>ከንግግራቸው ስረዳ ስላመለጠችኝ የተደሠቱ ይመሥላሉ....ምን ይታወቃል...ሆን ብለው ይሆናል ከኔ ያሥመለጧት

ጥያቄዬን ቀጠልኩ<<ማለት የታባቷ ልትሄድ ትችላለች......?>>

<<ቤቱን ባንቺ ሥም አዙራ...ሶስት ገጽ የይቅርታ ደብዳቤ እኔ ጋር አሥቀምጣልሽ ጨርቄን ማቄን ሳትል ገዳም ብላ ተሠውራለች>>

<<ምን.......?ገዳም....?>>

<<አዎ ገዳም>>

<<እንዴ ሰይጣን ገዳም መግባት ይፈቀድለታል እንዴ....?>>

<<ልጄ መድሃኒትኮ ለበሽተኛ ነው የሚታዘዘው...ገዳም ከአምላክ የመታረቂያ እና ጽድቅን የመፈለጊያ ሥፍራ ከሆነ የሚገባው ለእንደሷ አይነት ሀጥያተኞች ነው ብዬ አሥባለሁ...ጻድቁማ አንዴ ጸድቋል...ሥልኩን ዘግቼ ዝም አልኩ...ምንድነው የማደርገው.....?ምን ይሻለኛል......? የትኛው ገዳም ይሆን የገባችው......?የትስ ብትገባ መቼሥ ገዳም ድረሥ ተከታትዬ አላጠፋት...ቀና ብዬ ዋቅቶላን አየሁት አይን አይኔን ሲያየኝ ስለነበር ተጋጨን... ከዋቅቶላ ጋር ስለሚኖረኝ የወደፊት የፍቅር ህይወትና ለቦንቱም ምን አይነት እናት እንደምሆንላት እያሰብኩ ፈገግ አልኩለት....... እሱም ከንፈሩን ገለጥ አድርጎ ከነጫጭ ጥርሶቹ ከፊሎቹን አስመለከተኝ.....

.

.

ከሳምንታት በሁዋላ እጅጋየሁ ዜና(ወፏ) የኔ የምትለው የራሷ ቤተሰብ ኖራት።የዋቅቶላ ህጋዊ ባለቤትና የቦንቱ እናት በመሆን አዲሱን ህይወቷን ምእራፍ አንድ ብላ ጀመረች። አዎ እግዜር ፍቅርን ከመዳፉ ፈልቅቆ በዋቅቶላ አሥመሥሎ ልቧ ውሥጥ አሰረገው..በመጨረሻም የመጨረሻውን ደስታ..ከአጽናፍ አጽናፍ የሚናኝ ደስታ በዋቅቶላ ጎጆ ውስጥ አገኘችው...ከወራቶች ምናልባትም ከአመታት በሁዋላ ለቦንቱ ታናሽ እህትም ይኖራት ይሆናል።

.

.

ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም..በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!

.

.

.

/////🎀 ተፈፀመ 🎀//////








.



No comments

Post a Comment

Popular Posts

© የፍቅር ቀጠሮ የፍቅር ታሪክ 2020
Maira Gall