Sunday, January 19, 2020

የፒያሳዋ ወፍ ክፍል ሶስት መጨረሻ

የፒያሳዋ ወፍ    ክፍል ሶስት መጨረሻ

Image result for የፒያሳዋ ወፍ

‹‹ልጄ እናቴ ጋር እተዋታለው..ወይም እህቴ ጋር አስቀምጬያት መጣለው››

‹‹አይ እንድትመጣ አልፈልግም..ጊዜው ሲደርስ እራሴ እመጣለው››ኮስተር ብዬ

መለስኩለት ..እወነቴን ነው አሁን እዚህ እሱ መጣ ማለት እኮ ከእሱ ጋር ስንከረፈፍ

አላማዬን ሙሉ በሙሉ መዘንጋት ማለት ነው….አንዲመጣማ አልፈቅድለትም

‹‹አልፈልግም ..››አንቧረቀብኝ‹‹..ልጠብቅሽ አልችልም..ጂጂ የምትባል ሴት አላውቅም…

ፈጽሞ አይቼያትም አላውቅም..ጂጂ ቅዠት ነች..ዝም ብላ በህልሜ እየመጣች

የምትረብሸኝ መንፈስ ነች…እንዲህ ነው ማመን የምፈልገው..ስለዚህ እንዳትደውይልኝ…

ከዛሬ ጀምሮ አልፈልግም እንዳትደውይልኝ››ጠረቀመው…….ደነገጥኩ.. ፈራው ..በጣም

ፈራው…እና አልደውልለትም ማለት ነው……?ካልደወልኩለት ድምጽን ካልሰማው ምን

ሊውጠኝ ነው…?፡፡ለመሆኑ ለህይወቴ በጣም ሚያስፈልገኝ የትኛው ነው……?ሁለት ስሜቶች

ግራና ቀኝ ወጥረው ይዘውኛል..ለዋቅቶላ ያለኝ ስሜት እና ለሮማን ያለኝ ስሜት..አንዱ

የፍቅር ሌላው የበቀል(ጥላቻ)….ከበቀል እና ከፍቅር የትኛው ይጠቅማል ብዬ እራሴንም ሆነ

እናንተን አልጠይቅም..…?እንደዛ ብዬ ብጠይቅም የዋህነት ነው የሚሆነው..ትክክለኛው

ጥያቄ መሆን ያለበት ከፍቅርና ከበቀል የትኛው የበለጠ ኃያል ነው…? የሚል መሆን

አለበት…የትኛው ነው ይበልጥ አዕምሮን የሚበላው..…?የትኛው ነው ልብን የሚፍቀው..…?

የትኛው ይበልጥ የሚያቃትተው…?ያው ሁለቱም ስሜት በውስጤ ይገኛሉ.. የትኛው ነው

ባለድሉ….…?

ሁሉን ነገር አገናዝቤ ለመብርር ወሰንኩ.. ልሄድ …..ወቅቶላ ማረኝ ..ሁለተኛ አላበሳጭህም

ልለው..ሁለተኛ ጥዬህ ከስርህ አልሄድም ልለው…ወንድም ሁነኝ ልለው…ልብሴን ሁሉ

ሰበሰብኩ ሸንጣዬንም አዘጋጀው..በራሴ ሚኒባስ ልበር… አዎ ሹፌሩ ጋር ልደውል ቁጥሮቹን

መነካካት ጀመርኩ….ከመጥራቱ በፊት የቀጠርኮቸው ጓደኞቼ ጫታቸውን ተሸክመው

እየተንጋጉ ወደ ክፍሌ ሲገቡ ነው ስልኩን ያቆረጥኩት..ለካ ቀጥሬቸዋለው… እንደምንም

እራሴን አረጋግቼ ሁሉን ነገር ትቼ አብሬቸው ቁጭ ብዬ መቃም ጀመርኩ…

አሁን ቢያንስ ከተቀመጥን አንድ ሰዓት አልፎናል..መቃም ከጀመርን..እንሱ እንደተቀመጡት

የተቀመጥኩ እንሱ እንደሚቅሙት እየቃምኩ ቢሆንም ሀሳቤን ግን እንደነጋርኮችው

መሰብስብ ተስኖኛል…የልብ መሸፈት ለካ እንዲህ ከባድ ነው..

‹‹አሁን ስለ ዕቅዳችን መነጋገር ብንጀመር ምን ይመስልሻል…?››ስንዝሮ ነው ድንገት

ፀጥታውን ያደፈርሰው

‹‹ምን አልከኝ..…?ምን ……?ዕቅድ››ድንግርግሬ ወጣ

‹‹አዎ ..እንዴት እንድናደርግ ነው የምትፈልጊው .. …?እንድንገድላት ነው..እንግደላት

አይደል…?››አለኝ ምንም ማወላወል ሳይታይበት..በነገራችን ላይ እኚ ጎደኞቼ ስለ እኔ እና

ሮማን ታሪክ ጫፍ ድረስ ያውቃሉ..እኔ በምጠላትም መጠን ይጠሏታል…የእሷን አንገት

መቀንጠስ ለእነሱ የዶሮ አንገት የመቀንጠስ ያህል አያሳስባቸውም

የእሱ ንግግር ግን እኔን ወደ ቀልቤ መለሰኝ ተንሳፎ አየሩን ሰንጥቆ በመብረር ዋቅቶላ ጉያ

ሊወሸቅ ሲያኮበኩብ የነበረው ልቤን መንጭቆ በመመለስ ከቀልቤ እንድሆነ

አደረገኝ..በመጠኑም ቢሆን ማለቴ ነው…

ግን ቅድም ልሄድ የወሰንኩት ምን ነክቶኝ ነበር……?..የምን መልፈስፈስ ነው……?እሱ

ከተልፈሰፈሰ እኔም አብሬው መልፈስፈስ አለብኝ እንዴ..…?ለዛውስ እሱ እንዲህ የሚሆነው

ምን አልባት ፍቅር ይዞት ሊሆን ይችላል..…?አዎ ወንዶች መቼስ ወደ በፍቅር ባህር ውስጥ

ለማዋኘት ዘሎ በመግባትም እና ለሰከንዶች ተንቦራጭቀው ለመውጣት ሚቀድማቸው

የለም…እኔ ግን አላፈቀርኩት…እንዲሁ ደስ ሰለሚለኝ እንጂ ፍቅር አልያዘኝ…ትንሽም ቢሆን

ያው ሶስት ቀን አብሬው ስለዋልኩና ስለደርኩ ለምጄው ይሆናል ይቺ ታህል ልቤ

የምትዋልለው…አዎ …እርግጠኛ ነኝ ፡፡…ዋል አደር ስል ደግሞ ስለእሱ ማሰብና መጨነቅ

አቆማለው..አረ ጭራሽ እረሳዋለው…እወነቴን ነው ….፡፡

ስለዚህ አሁን ወደ አላማዬ ልመለስ… ትኩረቴን ልሰብስብ….እራሴን ለማሳመን

ያልቀባጠርኩት ነገር የለም…ለካ እራስን እንደማሳመን ከባድ ነገር የለም…ልብ ካልመሰለው

የአዕምሮ ሰበካ የቁራ ጩኃት ነው የሚሆንበት ..

‹‹እኔ ነኝ የምገድላት …በጣም እኮ ነው የምታስጠላኝ…››ኩለሻ ነች የፎከረችው

‹‹ኩኩሻዬ ፍቅር… አኔ እያለወልሽ አንቺ ምን በወጣሽ በዚህች ዳቢሎስ ደም ይሄንን

የመሰለ አለንጋ ጣትሽን ታቆሺሻለሽ....ለእሳ እኔ አለውላት››ስንዝሮ ተቃወማት..

‹‹ሁለታችሁም አትቸገሩ ..አኔ ነኝ አንገቷን ፈጥርቄ እስትንፋሶን የማቋርጠው››ዋርካው

ተናገረ…በግማሽ ልቤ እያደማጥኮቸው ነው…ይሄ የዘወትር ጭቅጭቃቸው ነው..እንዲህ

አይነት ለአደጋ መጋፈጥን የሚጠይቅ ስራ ሲኖረን እንዲሁ ናቸው..እኔ ቀድማለው..እኔ ነኝ

ምቀድመው..ለእኔ ተውሉኝ ለእኔ….አዎ ዝም ብላቸው ለአንድ ሰአት ይጨቃጨቃሉ…

ከጭቅጭቅም አልፈው ሊደባደቡ ሁሉ ይችላሉ..ይሄ ግን ለታሪክ ሽሚያ የሚያደርጉት

አይደለም..እንዲህ ገደልኩት..እንዲህ ጣልኩት ብሎ በማውራት ጀግና ለመሰኘት እና

ለመጎረር አይደለም…እርግጥ ከላይ ከላይ ለሚያዳምጣቸው ሰው እንደዛ ነው

ሚመስለው..ግን ሁሉም ሌለኛን ለመጠበቅ የሚያደርጉት ከቀናነት እና ከአሳቢነት የመነጨ ሚስጥራዊ ደባ ነው...አደጋ ካለ ከእናንተ በፊት ልቅደም እያሉ ነው...ሞት ሲመጣ ሶስቱም ምርጫቸው እድለኛ ሆኖ መትረፍ አይደለም..ከሶስት አንዱ መሞት የግድ ከሆነ ቀድሞ ለመሞት ነው የሚራኮቱት...እራስን  ለሞት አሳልፎ በመሥጠት ለተቀሩት ሁለቱ ህይወትን ለመስጠት ..እስርምሰ ሲመጣ እንደዛው ነው በራስ ላይ መስክሮ ሌላው ነፃ ማውጣት..ግን

ብዙውን ጊዜ ሶስቱም ቦሊስ እጅ ሲገቡ ሶስቱም እኔ ብቻዬን ነው ያተፋውት እነሱመምንም

አያውቁ ስለሚሉ ለፖሊስ ምርመራ ጣም ያስቸግራሉ…...እኔም ለዚህም ነው

የምወዳቸው..ለዚህም ነው በማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት የማልቀናውን በእነሱ

ምቀናባቸው… በምንም ላይ ባልተመረኮዘ እወነተኛ ንጽህ ፍቅራቸው…

…….ቆይ አንዴ ስልኬ ጮኸ …ማለቴ ሚሴጅ ገባልኝ.. እየጠበቅኩ ያለውት ነገር እንዳለ

ሁሉ አፈፍ አድርጌ አንስቼ ከፈትኩት..በምርቃናው ላይ ድንጋጤ አንቀጠቀጠኝ… ላብ

በአፍንጫ ቸፍ አለ..ምክንቱም የመጣው መልዕክት ከጠበቅኩት ቦታ ነው….ከዋቅቶላ..

‹‹ይቅርታ ቅድም አትደውይልኝ ያልኩሽ ስለናፈቅሺኝ ነው…እንዴ ካልደወልሺልኝማ

አብዳለው››ይላል…

አሁን ፈገግ አልኩ….እንደውም ስሬ ያሉትን ጓደኞቼ ይፎግሩኛል ብዬ ሼም ይዞኝ እንጂ

ተንከትክቼ መሳቅ ነበር ያሰኘኝ…ልቤ ላይ ተቋጥሮ የነበረና መተንፈስ ሁሉ ከልክሎኝ የቆየው

ቆጥኝ ነገር ደማሚት እንደተለኮሰበት አለት ፈንድቶ ሲበታተን ታወቀኝ…

.‹‹ አትደውይልኝ ብትልም መደወሌን አላቆምም ነበር..››ብዬ መለስኩለት..ግን ከዚህ በላይ

ብዙ ብዙ ነገር ነበር ልለው የደፈለግኩት..ግን ምን እለዋለው..…?ያው ጥሩ ጓደኛዬ

ስለሆንክ…አይ እንደዛ አይደለም የምለው..ወንድሜን ስለምትመስለኝ

ትናፍቀኛለህ….የትኛው ወንድሜን..…? (እናቴ በህይወት ቆይታ ቢሆን ኖሮ ምን አልባት

ትወልድልኝ የነበረውን) .. ያሰብኩት ሁሉ ስሜቴን በሙላት የሚገልፀልኝ ስላልሆነ ጽፌ

ላስተላልፍለት አልችልም…ስሜቴን በሙላት የሚገልጽልኝ ታዲያ ምን ብል ነው..…?ያንንማ

እኔ ራሴ የት አውቀውና ..ብቻ አንድ የሚረብሽ ነገር ዝም ብሎ ይተናነቀኛል…በአዕምሪዬ

ይጉላላል በስሜቴ ተዳፍኖ ያብሰለስለኛል…

..ወደ ጓደኖቼ ተመለስኩ‹‹ጭቅጭቃችሁን አቁሙ..››ፀጥ አሉ

‹‹እንድንገላት አይደለም የምፈልገው..ለመግደልመ እኔ ዛሬ ለሊቱኑ ፀት

አደርጋታለው….እናንተም አታስፈልጉኝም ነበር..፡፡የምፈልገው….እንድናሰቃያት ነው.እርግጥ

መጨረሻ ላይ እንድትገደል እፈልጋለው…፡፡ያንን ጊዜው ሲደርስ እራሴው የማደርገው ይሆናል

…አሁን ግን የእናንተን እገዛ ምፈልገው በቁም ነፍሷ በውስጧ እያለ የቁም ሞት

እንድንገድላት ነው..ፃረ ሞት እንድንሆንባት…እያንዳንዶን የሰራቻትን ሰይጣናዊ ድርጊት

እያሰበች በፀፀት እንድታጣጥር…ሞቷን እንድትለምን..ግደሉኝ ብላ እንድትማፀነን…

እያንዳንዱን በግፍ የሰበሰበቻትን ንብረቷን አጥታ ደቦ መግዛዣ እንድታጣ…መንገድ ላይ

ወጥታ እንድትለምን..

‹‹እንዴ የአሜሪካ አክሺን ፊልም አደረግሺብን….››አለኝ ያ ተንኮለኛው ሲንዝሮ

‹‹እንዴት…?››ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ስላልገባኝ ጠየቅኩት

‹‹ንብረቷን መቀማት..እሷን ለማኝ ማድረግ… ማስራብ… ማሳበድ..በስንት ጊዜ ውስጥ ነው

የምናደርገው››

‹‹መጀመሪያ ስድስት ወር ነበር የመደብኩላት..አሁን ግን ጊዜ የለኝም..በአንድ ወር ውስጥ

የአለምን ስቃይ ሁሉ ማየት አለባት..››

‹‹አንድ ወር..ምነው እንዲህ ቸኮልሽ…?››ኩኩሻ ነች የጠየቀቺኝ

‹‹ጌዜ የለኝም…ከዚህ አገር ልመርሽ አስቤያለው››

ሶስቱም ክው ብለው ደነገጡ…በተለይ ዋርካው ያን ፊቱን አጨማዶ ለንቦጩን ሲጥለው…

የሆነ የህጻናት ማሰፈራሪያ መሰለ

‹‹አይዞችሁ..እኔም እንዲህ አላዘንኩ››

አረ የመጬ አይነፋም..አንቺ እኮ የፒያሳ ልጅ ነሽ ፓሪስ ብትሄጂ እንኳን አትለምጂም››

‹‹አታስቢ …ገና እርግጠኛ ሆኜ አልወሰንኩም..ግን በቃ አንደ ወር ከተሰቃየችና ሞቷን

ካስመኘናት ይበቃል..ከዛ እኔ አጠናቅቃታለው…፡፡ማጠናቀቂያው ላይ እናንተን

አልፈልጋችሁም… ብቻዬን ነው የማደርገው…ፈረሰኛው ጊዬርጊስ ካላጋለጠኝ አሪፍ ነው…

ካልሆነም ዕቅዴ ይሳካ እንጂ ጋማ ብባልም ጣጣ የለውም ..ያው አንድ ሃያ አመት ጠጥቼ

ሼባ ሆኜ ስወጣ እንገናኛለን››

…ዋርካውን ደረት ላይ ተደግፋ ስንዝሮን ጡቶቾ መካከል አስደግፋ …‹‹አረ አይነፋም››አለች

ኩኩሻ አሁንም ደግማ።።ቀኑን ሙሉ ተኝቼ ነው የዋልኩት፡፡ይሄን ያደረግኩት ዛሬ ለሊት የመተኛት ዕድሉ ስለማይኖረኝ

ጥሩ እረፍት ለመውሰድ ነው፡፡ከእንቅልፌ ስነቃ 11 ሰዓት ነበር፡፡ዛሬ ለእኔ ልዬ ቀን ነች፡፡

ታላቅ ተግባር የማከናውንበት ቀን ….፡፡ከዛ በፊት ግን ዘና ማለት አለብኝ፡፡አዎ መንፈሴን

ንጽህ እና በጥራት የሚያስብ መሆን አለበት….ለዚህም ይረዳኝ ዘንድ ጋሼ ዜናን ከቤት

ይዣቸው ወጥቼያለው..፡፡ለእኔ ምሳዬን ለጋሼ ደግሞ እራታቸውን አብረን ከበላን ቡኃላ

በአሁኑ ሰዓት ምግብ ቤቱን ለቀን አንድ አነስተኛ ካፊ በረንዳ ላይ ተቀምጠን የሆድ

የሆዳችንን እያወራን እግረ መንገዳችንን ወጪ ወራጁን እየተመለከትን እንገኛለን….

ብዙ ብዙ ወሬ ካወራን ቡኃላ ድንገት ያስደነገጠኝን ጥያቄ ጠየቁኝ‹‹‹ሰውዬሽ ደህና ነው…?››

‹‹የቱ ሰውዬ…?››

‹‹ያ ለሶስት ቀን ጠልፎሽ የነበረው…ነዋ››

‹‹እ!!! እሱን ነው……?እኔ እንጃ ሰላም መሰለኝ…ያው ጠልፎ ከመለሰኝ ወዲህ መች

አገኘውት..…?››

‹‹ጠልፎ ከመለሰኝ አልሽ .. …?››አሉኝ …በዛ የተለመደ ማሽሟጠጣቸው፡፡

‹‹አዎ ጠልፎ ከመለሰኝ..!!!››ምንም እንዳይሉኝ የፈራው በሚመስል የጠነከረ ንግግር

ግግም ብዬ

‹‹ምኑን መለሰሽ… አሁንም እኮ እሱ ጋር ነው ያለሺው››

‹‹ምን ማለት ነው ጋሼ ……?አልገባኝም…?››

‹‹አይ የእኔ ልጅ..አንቺ ስለ አካል መጠለፍ ነው የምታወሪው ..የአካል መጠለፍ ብዙም

አያሳስብ የልብ መጠለፍ ነው ከባዱ….አንድን ሰው የሆነ ቤት ውስጥ ከርችመሽበት

አሰርኩት ትይ ይሆናል.. ግን እውነታው እንደዛ አይደለም..እስር ቤት ከተሸ ቆለፍሽበት

ማለት ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ከለከልሺው ብቻ ማለት ነው…እውነተኛው እስር

በመንፈስም ስትታሰሪ ነው…በስነልቦና ስትሸነፊ ነው…፡፡

.ለምን ይመስልሻል አንዳንድ ሰዎች በተለይ የነፃነት ታጋዬች አስር ወይም ሃያ አመት አንድ

ጠባብ ክፍል ውስጥ ተከርችሞባቸው ከኖሩ ቡኃላ ሲለቀቁ…ስብርብር ብለው ፤ተስፋ

ቆርጠው እና አንገት ደፍተው እናያቸዋለን ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ በተቃራኒው አንገታቸውን

ቀና አድርገው ደረታቸውን ነፍተው ይበልጥ ገዝፈውና አስፈሪ ሆነው የሚወጡት…አካላቸውን

እንጂ መንፈሳቸው እንዲታሰር ለማንም ስለማይፈቅድ ነው…እጃቸውን እንጂ ልባቸውን

ለእስር አሳልፈው ስላማይሰጡ ነው፡፡

‹‹ጋሼ ጫወታህን ያው እንደልማድህ ፖለቲካዊ አደረግከው እኮ..››አልኩት ወደ አጀንዳው

ልመልሰው ስለፈለኩ

‹‹አይ ምሳሌ ልስጥሽ ብዬ ነው..አንቺ አካልሽን ከተጠለፍሺበት አስለቅቀሽ መጥተሸል

እናም በዛ እየተኩራራሽ ነው....ልብሽ ግን አሁንም እንደተጠለፈ ነው..ደግሞ ሳስበው

እንዲህ በቀላሉ የምታስመልስ አይመስለኝም፡፡

‹‹እንዴ ጋሼ አሁንም አልገባኝም…?››

‹‹ለመሆኑ ስሙ ማነው..…?››

‹‹ዋቅቶላ ይባላል…ወይኔ…ማለቴ የትኛ ሰውዬ…?›› ዘበራረቅኩ

‹‹የትኛው ሰውዬ አልሽኝ..…?ነገርሺኝ እኮ …ዋቅቶላ ብለሽ ነገርሺኝ…አዕምሮሽን የሞላው

ስም እሱ ነው…ደውለሺለት ታውቂያለሽ…?››

‹‹አዎ አንተን ከማግኘቴ በፊት ደውዬለት ነበር…ተወው ባክህ እሱ ነጭናጫ ነገር ነው…››

‹‹ነጭናጫ አልሽ..…?ፍቅር ሲይዝ እኮ እንደዛ ነው የሚያደርገወ ያነጫንጫል…››

ይሄንን አይነት ወሬ በዚህ ወቅት አልፈለግኩም..ይሄ ጫወታ ወደ ትካዜ የሚጨምረኝ እንጂ

ፈታ የሚያድገኝ አይደለም…የሚያልፈሰፍሰኝ እንጂ ጥንካሬ የሚያላብሰኝ አይነት ጫወታ

አይደለም..እና ጫወታውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለወጥኩት

ጋሼ እነዛን ፍቅረኛሞች አየሀቸው… እሷ እኮ እየለመነችው ነው ..እሱ ደግሞ

ይንጠባረርባታል…እንዲህ አይነት ወንዶች ያባሳጩኛል…

ፊት ለፊትችን እየተጨቃጨቁ ስለሚሄዱ ሁለት አፍላ ወጣቶች ነው የማወራው..ልጁ

ቀጫጫ ..ባለደበሌ ፀጉር..ግን ደግሞ ቆንጆ ነው…ዘመንኛ አለባበስ የለበሰ ሱሪው

በማጥለቅ እና በመውለቅ መካከል የሚዋልል የሚመስል..ላድርገው ወይስ ላውልቀው

እያለ ከራሱ ጋር ሲሞገት ቆይቶ መወሰን አቅቶት ሱሪው ባለበት መሀከል ቦታ ላይ ጥሎት

የወጣ የሚመስል…እሷ ፍቅረኛው…ለዕርቃን የተጠጋ አለባባስ ለበሰች…ከሰር ያጠለቀቻት

ብጣቂ ቀሚስ በብስጨት እንጣጥ እንጣት ስትል ንፋሱ ወደላይ ሲያነሳት ከስር

ያጠለቀችው ነጭ ፓንት በቀላሉ የሚታይ ..ከላይ የሁለቱ ቱቶቾ ሰማኒያ ፐርሰንት ግዛታቸው

ለእይታም ለንፋስም የተጋለጠ አለባበስ የለበሰች ነች፡፡

‹‹ምነው ተፈቅረህ አታውቅም እንዴ..…?አንተን በየሄድክበት እየተከተልኩ መለመን

አለብኝ…?››እየተንዘረዘረች ትጮህበታለች፡፡

እኔ ለምኚኝ አላልኩም ..ግን መጨናነቅ አልፈልግም …ትንፋሽ አሳጣሺኝ››ይላታል..በተ

ንገሸገሸ ስሜት….

እንደዛው እየተነጋገሩ አልፈውን ሄዱ…

የጋሼን የወሬ አቅጣጫ መለወጥ ተሳካልኝ…ግን በራሱ መንገድ ነው ያየው…

የእኔ ወፍ አየሽ ዘመን ብዙ ነገር ይቀይራል፡፡ወንድነትም ተቀይሯል… የእኛ ጊዜ ወንድ

የሚበላው ጮማ ስጋ … የሚጠጣው ደግሞ ንፅህ የማር ጠጅ ነበር…እንዲህ ስልሽ

በውስጥሽ ጥያቄ መፈጠሩ አይቀርም…ምክንያቱም ጮማውም አለ ጠጁም ቁም ነገሬ ብሎ

የሚጠጣው ሰው ባይኖርም አሁንም አለ ብለሽ ታስቢ ይሆናል… አዎ ትክክል ነሽ እኔም

መኖሩን አውቃለው …ግን ከእኛ ዘመን ጮማ ጋር ምኑም አይገናኝም ፡፡የአሁኑ ማለቴ

የእናንተ ዘመን የውሸት ነው፡፡በመድሀኒት የወፈረ አርቴፊሻል ጮማ እና ልብን የሚፍቅ

የስኳር ስሪት ጠጅ ነው ያለው፡፡

በተጨማሪም የአሁኑ ወንድ ሱስ አድክሞታል፡፡የሀሺሽ ሱስ …የጫት ሱስ …የገንዘብ

ሱስ..የፌስ ቡክ ሱስ..የመኪና ሱስ ….የቴክኖሎጂ ሱስ ….በቃ ሱስ በሱስ….. ስለዚህ

ለሴት የሚኖረው ፍላጎት ከእነዚህ ሁሉ ፍላጎቶች የተረፈ ሸርፍራፊ ስሜት ነው..ያቺ ሽርፍራፊ

ስሜትን ለመቀስቀስ ደግሞ እንዲህ እንደምታያት ብጣቂ ልብስ ለብሳ ማስታወስ እና

መፈታተን ከሴቲቱ ይጠበቃል..ለዛውም ከገባው…፡፡ቴዲ አፍሮ በቅርቡ የለቀቀውን

የሰብልዬን ክሊፒ አይተሸል…በዛብህ የሚማልለው የሰብለን ቁርጭምጭሚት እያየ ነው…

ሙሉ ያልተበታተነ ልብ ያለው አፍቃሪ ወንድ የሴት የፍቅረኛውን የእግር ኮቴ በጨረፋታ

ማየት እንኳን ወንድነቱን ይረብሸዋል…ውስጣዊ ስሜቱን ይነቀንቅበታል….…አየሽ ልዩነቱን..››

እንግዲህ ጋሼ እንዲህ ነው… አንድ ቁራሽ ነገር ካሳዩቱ ..ያንን አንዴት ተርጉሞት ከምን ጋር

አገናኛቶት እንደሚተነትነው ሁሌ ያሰገርመኛል…በነገራችን ላይ ከእሱ ጋር ዕድሜ ልኬን

ከመኖሬ የተነሳና እሱን ማዳመጥም ሰልችቶኝ ስለማያውቅ የእሱን ባህሪ ወርሼያለው…ነገር

ማሰፋፋት እና ማወሳሰብ እየተክንኩበት ነው…ሀይስኩል እንኳን ሳረግጥ ከዩኒቨርሲቲ

ምሩቆች ጋር ደረቴን ነፋ አድርጌ በማንኛውም ርእስ ላይ እኩል የማውራት እና የመከራከር

ችሎታ ከጋሼ ያገኘውት ውርስ ነው….እሱም ይሄንን ይመሰክራል…አዕምሮሽ እኮ በሁለት

በኩል የተሳለ ምሳር ነው ይለኛል…በልጅነትሽ ተነከባክባ በቅጡ ስላላሰደገችሽ እና በበቂ

መጠን ስላላስተማረችሽ ይህቺ ሀገር አጥታሻለች››እያለ ይቆጫል…

ሁለት ሰዓት ሲሆን ለልጆቹ የሚበላ ነገር ተሸክመን ወደቤት ሄድን …ጋሼን አስገብቼ

ምግብን ለልጆቹ ሰጥቼ ተሰናብቼያቸው ልወጣ ስል‹‹ከእኔ ጋር አታድሪም ዛሬ…?››ብሎኝ

ብሎ ተየቀኝ

‹‹አይ ዛሬ አቤቴ ነው የማድረው››

‹‹ስራውን ትተሸል አይደል…?››ብሎ ጠየቀ…ኝ ጥርጣሬ ባረበበበት ድምፀት

‹‹የቱን ስራ…?››የትኛውን ስራ እንደጠየቀኝ በደንብ ቢገባኝም…ደንግጬ ጠየቀኩት ..ልክ

ሰርቼው እንደማላውቅ….አረ ሰርቼው ሳይሆን ሲሰሩም አይቼ።።እንደማላውቅ ነገር

ተንገሽግሼ…

‹‹አይ ዝም ብዬ ነው…በቃ ደህና እደሪልኝ

የእኔ ወፍ..አምላክ ይከተልሽ››ብሎ መረቀኝና

አሰናበተኝ

እኔም ግንባሩን ስሜ ባለው ነገር እየተነጫነጭኩ ወጥቼ ሄድኩ..እንዴ ከዋቅቶላ ጋር

ከተመለስኩ ወዲሀ ሽርሙጥና ብዬ መንገድ ላይ ወጥቼ አላውቅም..ከዛሬ ቡሃላ ይቅርብኝ

ብዬ ወስኜ አይደለም..አረ ጭራሽ አላሰብኩበትም ነበር…ግን ልክ አንደሌብቱ

ሽርሙጥናውንም ተውኩ ማለት ነው……?ወይኔ ዋቅቶላ ይሄ ሰውዬ ምን አስነካኝ .. …?

አፍቅሬው ይሆን እንዴ..…?ስለፍቅር የምታውቁ እስቲ ስሜቱ እንዴት ነው..…?አሁን እኔ

ስተዩኝ ፍቅር ይዞኛል ማለት ይቻላል……?

ይሄንን ጉዳይ አሁን ለማሰብ ጊዜው አይደለውም…ቀጥታ ወደ ቤት ነው የሄድኩት …

ለመዘጋጀት፡፡ወዲያው ነበር ሶስቱን ጓደኞቼን የጠራዋቸው…ዝግጅታችንን ሙሉ በሙሉ

አጠናቀን ከቤት የወጣነው ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ነው፡፡

ከለሊቱ 8፡30 ሲሆን አራታችንም ሮማን መኖሪያ ቤት አቅራቢያ እንገኛለን..ሁላችንም ጥቁር

ላብስ ለብሰናል..እጆቻችን በጓንት ተሸፍኗል..ጥቁር ጭንብል ጭንቅላታችንን ሙሉ ፊታችንን

ሸፍነናል፡፡

…ይሄ መኖሪያ ቤት 1.7 ሚሊዬን ብር ነው የተገዛው…ከዚህ ውስጥ እርግጠኛ ሆኜ

የምነግራችሁ ሰማንያ ፐርሰንቱ የእኔ ንብረት ነው…የእኔ አልኩ እንዴ ……?ይቅርታ ተሳስቼ

ነው የእኔ ካልኩት ውስጥ ቢያንስ ዘጠና ፐርሰንቱ የእኔ አይደለም..የእሷም አይደለም….ያው

የሰፊው የአዲስ አበባ ህዝብ ነው…በእኔ አማካይነት ከሰፊው ህዝብ የተሰበሰበ የተዘረፈ

ማለትም ትችላላችሁ ብር ነው፡፡

…የተቀረው ደግሞ ስጋዬን ሸጬ የሰበሰብኩት ነው…ግን ስጋ መሸጥ ምን ማለት ነው ..

…? ግብረ ስጋስ የሚባለውስ ለምንድነው..…?አዎ አሁን ገብቶኛል ግብረ- ስጋ ማለት የስጋ

ብቻ ስራ ማለት ነው..፡፡አይደል……?አንድ ስጋ ከሌላ ስጋ ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ማለት

ነው…ፈቅር አልባ ወሲባዊ ግንኙነት፡፡

በፍቅር ውስጥ ያለ ወሲብ ግን ግብረ ስጋ ሲባል ትክክል አይደለም…ምክንያቱም በእወነተኛ

የፍቅር ተጣማሪዎች መካከል የሚደረግ ግንኙነት ስጋ ከስጋ ብቻ በማፋተግ የሚከወን

ሳይሆን የመንፈስም ቁርኝቱ የሚገዝፍበት በግንኙነታቸው ሰከንድ ሰማየ-ሰማያት

የሚንሳፈፉበት ..ከሰው በላይ የሚሆኑበት.. ከፕላኔቶች ጋር በስምም በጸሀይ ዙሪያ

የሚተሙበት ቅዱስ ክስተት ይሆናል..ይሄንን ታዲያ ግብረ ስጋ ማለት ትክክል

አይመስለኝም..እኔ በዛ መልክ አጣጥሜው ባለውቅም እንዲሁ ሳስበው ነገሩን ዝቅ

ማድረግ ይመስለኛል ..

….ወይ የእኔ ነገር አሁን እኮ ለከባድ ተልዕኮ ጓደኞቼን ይዤ አደገኛ ቦታ ነው ያለውት…

ታዲያ ስለዚህ አይነቱ ጉዳይ ምን አሳሰብኝ……?ለማንኛውም ጊቢ ውስጥ ገብተናል …

ጊቢወ ውስጥ ለመግባት ያን ያህል ከባድ አልነበረም …ዘበኛ የለውም..ወሻ

አልታሰረበትም…፡፡አጥሩም ያን ያህል አስቸጋሪ የሚባል አልነበረም…..በዛ ላይ እዚህ ጊቢ

ውስጥ ከአንድ አመት በላይ ኖሬበታለው...መግቢያ እና መውጫውን በደንብ አውቃለው፡፡

ለዚህ ለዛሬው ተልዕኮ ከሳምንት በላይ ተዘጋጅተንበታል፡፡መጀመሪያ ስለዝግጅታችን

ከመናገሬ በፊት ስለቤቱ ልንገራችሁ…ባለአራት ክፍል መለስተኛ ቢላ ዋና ቤት እና ከጀርባ

ሶስት ክፍል ያላቸው ሰርቢስ ቤቶች አሉበት…፡፡ሶስቱን ክፍል ሰርቢስ ቤት አንድ ላይ

በማቀላቀል የሚትኖርበት ሮማን ነች..የእኔዋ ደመኛ ሮማን…አብረዋት አንድ ሚስኪን ሰራተኛ

እና አንድ ጥቁር ድመት ይኖራሉ….፡፡

ትልቁ ቤትን በወር ዘጠኝ ሺ ብር አከራይታው ነበር..ተከራዬቹ ከአራት ቀን በፊት ነው

የለቀቁት..የቤቱን ኪራይ በስድስት ወር አንዴ ነበር የሚከፍሉት…. ከአራት ቀን በፊት ሲለቁ

ተከፍሎ ያልተኖረበት የሶስት ወር ኪራይ ነበራቸው፡፡

…ድንገት ልንለቅ ነው ሲሏት… ‹‹ለምን…?›› እንኳን አላለቻቸውም

.‹‹ሂሳብ መልሺልኝ አትበሉኝ እንጂ መብታችሁ ነው››ነበር ያለቻቸው….ምርጫ

አልነበራቸውም ብሩን ጥለው ለቀቁ…..

እኚህን ተከራዬች ለማስለቀቅ እኛ የሰራነው ስራ ከፍተኛ ነበር…ስንዝሮ እና ዝግባው የቤቱ

አባ ወራን መግቢያ መውጫ ተከታተሉት ….ድክመቱን ለማግኘት….ሚስጥሩን ለማግኘት

..፡፡ብዙም ሳይለፉ እጃቸው ላይ ወደቀ….ከሁለት ልጆቹ እናት ደብቆ ሹልክ እያለ

የሚሄድባት ሌላ ውሽማ አለችው…እንደሚስት ተከራይቶ ያሰቀመጣት ውሽማ…ይሄንን

እንቅስቃሴ ለሁለት ቀን እየተከታተሉ በቪዲዬ የተደገፈ መረጃ ሰበሰቡበት…

ከዛማ አለፍ ብለው ሰውዬው ባሌለበት ውሽማዋን ቀርበው ያነጋገሯታል፡፡ከዛም ጠቃሚ

ነገር ያገኛሉ ፡፡ውሽሚት ውሽማ መሆኗን አታውቅም ነበር…፡፡እጮኛ እንደሆነች…እሷን

በቅርብ እንደሚያገባት..ከእናቱ እና ከእህቱ ጋር እንደሚኖር…እህቱ ሁለት ልጆች እንዳሎት

እና ከባሏ ተፋታ ወደ ቤት ተመልሳ አብራቸው እንደምትኖር ነበር የነገራት….. እንግዲህ

እህቴ ነች ያላት የገዛ ሚስቱን ነበር…..እንደዛ ነው ያሳመናት….ይሄንን መረጃ ሰብስበው

ከሰጡኝ ቡኃላ ..ደወልኩለት

‹‹አቤት ማን ልበል…?››

‹‹አታውቀኝም››

‹‹እሺ ምን ፈለግሽ…?››

‹‹መጀመሪያ የፈለኩትን ከመናገሬ በፊት ስለአንተ የማውቀውን ልንገርህ…ከእናትህ እና

ከሚስትህ ጋር በኪራይ ቤት ውስጥ ትኖራለህ…ሁለት ልጆች አሉህ…ግን የምትተዳደረው

በንግድ ነው..መርካቶ አካባቢ ነው የምትሰራው…አብነት አካባቢ ውሽማ አለህ …ስሟ

መሀሌት ስዩም ይባላል..እንደምታገባት እና የምትኖረውም ከእናት እና ከእህትህ ጋር

እንደሆነ በመናገር ዋሽተሀታል››

‹‹ይሄንን የማይረባ የውሸት ወሬ ከየት ነው የመጣሽው……?››

‹‹ለረጂም ጊዜ ስከታተልህ ነበር …ኢሜል አድርሻህን ሁሉ አውቃለው..አሁን የምነገርህን

መረጃዎች ሁሉ..የአብነቷን ውሽማህ ስለአንተ የነገረችኝን ሁሉ የተቀዳበትን እና

የተቀረፀውን አንድ ላይ አድርጌ ልኬልሀለው..እየው ››

‹‹ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው …?…አስር ሺ ብር..ሃያ ሺ ብር››

‹‹አይ ..ይቺን ይህል ብር እማ… ››

‹‹ሴትዬ እንደዛ ከሆነ ጊዜሽን የተሳሳተ ሰው ላይ ነው ያባከንሺው..የመርካቶ ነጋዴ ነው

ሲሉሽ ከመራካቶ ሀብታሞች ውስጥ አንዱ መስዬሽ ከሆነ ተሳስተሸል…ገና በሁለት እግሬ

መቆም ያልቻልኩ ለፍቶ አዳሪ ነኝ››

‹‹እና ሚስጥሩን ለውሽማህም ለሚስትህም ላከፋፍላቸው…?››

‹‹አይ እንደዛማ አታደርጊም ..ብቻ አቅሜን እየነገርኩሽ ነው››

‹‹እኔ የምፈልገው አሁን ከምትኖርበት ከሮማን ቤት በአራት ቀን ውስጥ ለቀህ እንድትወጣ

ነው…›

‹‹በቃ…?››

‹‹አዎ በቃ…››

‹‹ግን እኮ ገና ያልኖርኩበት ቅድሚያ የተከፈለ የ 3 ወር የቤት ኪራይ አለኝ…እሷ ደግሞ

በፍቃዴ ከወጣው አትመልስልኝም..እንደዛ አይነት አዘኔታ ያላት ሰው አይደለችም..››

‹‹እኔ ካንተ ምንም ጉዳይ የለኝም..ጉዳዬ ከሌላ ሰው ጋር ነው… እንድትጎዳ አልፈልግም..

ዛሬውኑ ቤትህ ፊት ለፊት የሚገኘው ደበበ ኪዬክስ በፖስታ 27 ሺ ብር

አስቀምጥልሀለው..ይሄ ለምታጣው የሶስት ወር ኪራይ ማካካሻ ነው››

‹‹በወር ዘጠኝ ሺ ብር እንደተከራየው በምን አወቅሽ..…?››

‹‹ስለአንተ ብዙ ብዙ ነገር አውቃለው አልኩህ እኮ..እንግዲህ ሶስት ቀን ሰጥቼሀለው..አሁኑ

የኪራይ ቤት መፈለግ ጀምር..ለቤተሰቦችህም ሆነ ለእሷ ምትነግረው አሳማኝ ምክንያት

ይኑርህ..ደግሞ ምንም ይሁን ምንም ስለዚህ ስምምነታችን አንድ ነገር ለማንም

ለሚስትህም ቢሆን ትንፍሽ ብትል በልጆችህ ህይወት መፍረድህን እመን››አልኩ ና ስልኩን

ዘጋውት… ፡፡ስቅጥጥ ነበር ያለኝ…አንድን ወላጅ በልጆቹ ህይወት ከማስፈራራት በላይ ጭካኔ

የለም..ግን አስተማማኝ የሚሆነው ደግሞ እንዲህ ሲሆን ነው… ምርጫ አልነበረኝም፡፡

በዚህ ሁኔታ።።።ድርድር ነው ሰውዬው በተሰጠው ቀን ቤቱን ለቆ የወጣው…ቤቱ በተለቀቀ ማግስት ነበር ደላሎች ሌላ ሰው ለማስጋባት መራወጥ የጀመሩት..ግን ለዝግባውና

ለስንዝሮ የተሰጣቸው ተልዕኮ ስለነበረ ሁሉም ድርድር አልተሳካም..ዋናው አላማችን ቤቱን

ለዛሬ ተልዕኮችን ባዶ ማድረግ ነው..ሰው እልባ ማድረግ፡፡

የባዶውን ቤት የተቆለፈ በር ለመክፈት ብዙም አልተቸገርን …የበራፍ ቁልፎችን ሰርስሮ

ለመክፈት ያለኝን ችሎታ ከዚህ በፊት የነገርኮችሁ መሰለኝ…ሁለታችን ወደ ውስጥ ገባን እኔ

እና ስንዝሮ…፡፡ኩክሻ እና ዝግባው ፈንጠር ፈንጠር ብለው ድምጽ አልባ መሳሪያቸውን

በተጠንቀቅ ወድረው ጨለማ ውስጥ በማድፈጥ ውጭ ቀርተዋል…

ዕቅዳችንን እቤት ውስጥ ሳንገባ ከውጭ ማድረግ እንችላላን…. ግን አስተማማኝ ለማድረግ

ወደ ውስጥ መግባት አለብን..ስንዝሮ በግራ እና ቀኝ እጆቹ ባለ አስር ሊትር ጄሪካኖችን ይዞ

ነው የገባው..እኔ ደግሞ በለበስኩት ጥቁር ካፖርት ሰፊ ኪስ ውስጥ ከአራት ተቀጣጣይ

የእጅ ቦንቦችን ይዤለው…ስንዝሮ እንደገባን አንደኛውን ጄሬካን አስቀመጠና አንደኛውን ከፍቶ

የጣውላ ንጣፍ የሆነውን የቤቱን ወለል ያዳርሰው ጀመር …ከአሮጌ ጠሬጳዛዎች በስተቀር

ብዙም ዕቃ የሌለውን ቤት በቤንዚል እጥለቀለቀው..ወደ ሌሎች ክፍሎች ሌለኛውን ጄሪካን

ይዞ ጋባ …በሰባት ደቂቃ ውስጥ ስራውን ጨረሰ…

አሁን የእኔ ተራ ነው..አራቱንም ቦንቦች ከኪሴ ውስጥ አወጣው…እነዚህን ቦንቦች የያዝኩት

ጠላት ልደመስስበት አይደለም…ጠላት ለመደምስ እማ ወደ እዚህ ባዶ ቤት ሳይሆን ወደ

ጎሮ ነበር መሄድ ያለብኝ ወደ ሰርቢሱ ቤት ..ሮማን ወደምትገኝበት ክፍል…ግን አሁን ጊዜው

አይደለም…

አሁን ቦንቦቹ ያስፈለጉኝ ይሄንን ቤት ድርምስምሱን እንዲያወጡልኝ ነው..ከብሎኬት የተሰራ

ሲሚንቶ ቤት ስለለሆነ እሳትን መቋቋም አቅሙ ጥሩ ሚባል ነው…የቤቱ ግድግዳ ጠቋቁሮ

ኮርኒሱ ብቻ ተቃጥሎ ሊተርፍላት ይችላል..እንደዛ እንዲሆን ደግሞ ፍጽም አልፈልግም…

ይሄ ቦንብ ግን ከእሳቱ ጋር ሲዋሀድ ሚፈጥረው ፍንዳታ ሁሉን ነገር ወደ ፍርስራሽነት

ይቀይረዋል….ከዛ ያቺ እባብ ይሄ ሲሆን ቆማ ታያለች…በውስጥ ልብሷ በድንጋጤ ተነስታ

እንደእብድ ጊቢውን እየዞረች ከሚቃጠለው ቤቷ የሚንበለበለው የእሳት ወላፈን ፊቷን

እየገረፋት ውስጧን እያነፈራት…የመጀመሪያ ቅጣቷን ትቀበላለች…ከዛ ሌላ አራት ተከታታይ

ቅጣት ይቀራታል…መጨረሻው ነፍሶን መንጠቅ ነው፡፡

አራቱን ተቀጣጣይ ቦንቦች ጥሩ ነው ያልኩበት ቦታዎች አስቀመጥኩና ጨረስኩ ..ከስንዝሮ

ጋር በምልክት ተነጋገርንና በየአንንዱ ክፈል አንድ የክብሪት እንጨት ለኩሶ ወደ ወለሉ

በመጣል ከቤት ወጠጣን.…የእሳት ነበልባል በቤቱ ዙሪያ መሽከርከር ጀመረ..እቤቱን

ዘጋውና መንገዴን ቀጠልኩ…

ስንዝሮ ከኃላ ተለከለትሎኛል..ግቢውን ለቀን ወጣን …ኩኩሸና ዝግባውም ተከተሉን…

አስተማማኝ እና ሰዋራ ቦታ እስክናገኝ እርምጃችንን አልገታንም…የሚንበለበል የእሳት

ላንቃ.. የሚትጎለጎል ጭስ መታየት ጀመረ…ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሆነ የሰው ድምፅ ግን

አይሰማም…የእሳቱ ኃይል እየጨመረ..ከዛ እኔን እራሴን የሥደነገጠኝ ፍንዳታ ተሰማ…በአንድ

ደቂቃ ልዩነት ሌላ ተመሳሳይ ፍንዳታ ..ከዛ ኹኹታ….የሰፈር ቤቶች ሁሉ መከፈትና

መተረማመስ…ከዛ በላይ እዛ መቆት እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ስለሆነ መንገዴን ቀጠልኩ….

ከሲኦል የተለቀቀ የሚመስለውን የሮማንን የጮኸት እና የድረሱልኝ ድምጽ ልክ እንደሙዚቃ

እያዳመጥኩ ጓደኞቼን ይዤ ወደ ቤት….የመጀመሪያ ተልዕኮ እንዲህ ተፈ ፀመ..ውጤቱን

ነገ ሲነጋ በብርሀኑ የምናየው ይሆናል..ስድሥት ሠአት ነው ከእንቅልፌ የተነሣሁት...ፈልጌ ወይንም እንቅልፌን ጨርሼ አይደለም...ጋሼ ዜና ናቸው የቀሰቀሱኝ...በንዴትና በቁጣ ነበር በራፉን በከዘራቸው እየቆረቆሩ ሲራገሙ ....

<<...ማነው...ምን ተፈጠረ....?>>ከአሥፈሪ ቅዠቴ ተላቅቄ በድንጋጤ ድምጽ አውጥቼ ጠየቅኩ..

<<አንቺ መናጢ...ክፈቺ>>

<<እርሶ ኖት እንዴ....?>>የተጨናበሰ አይኔን እያሻሸሁ እንደምንም አልጋዬን ለቀኩና በሩን ከፈትኩ..ገፍትረውኝ ወደ ውሥጥ ገቡና በቤት ውሥጥ በሚገኘው አንድ ብቸኛ ወንበር ላይ ተቀመጡ...ጥያቸው ወደ ሽንት ቤት አመራሁ...ሽንቴ ሥለመጣብኝ ብቻ ሳይሆን ስለደነገጥኩና ሥለፈራዋቸውም ጭምር ነበር...ተፀዳድቼ እና ተረጋግቼ ሥመለሥ ከቅድሙ በመጠኑ ነቃ ብዬ ነበር...

በራፉ ሲንኳኳ ፓሊሥ ነበር ..ያው ፈሥ ያለበት ዝላይ አይችልም ይባል የለ...ለነገሩ ጋሼም ከፓሊስ ብዙም አይሻሉም..የእሳቸው ስድብና ቁጣን መቋቋም እራሡ ለእኔ ከባድና አሥጨናቂ ነገር ነው።

<<ጨረሽ...?>>

<<አዎ ምነው ሠላም አይደሉም እንዴ...?>>

<<እረ ባክሽ ትቀላምጂብናለሽ አይደል...?>>

<<እንዴ ጋሼ!!!>>

<<ዝም በይኮ ነው የምልሽ>>ከዘራቸውን እያወዛወዙ እና ሊቀነድቡኝም እየቃጣቸው...

<<እሺ  ዝም አልኩ...ግን ምን አጠፋሁ..?>>

<<ለሊት የት አባሽ ነበርሽ...?>>

<<እቤቴ>>

<<እቤትሽ....ምን አይነት ደረቅ ነሽ ልጄ...ለመሆኑ ብቻሽን ነው እንደዛ ያደረግሽው..?>>

<<ምኑን ...?>> ጋሼ ምን ለማለት እንደፈለጉ ገብቶኛል...ሥለማታ ተልዕኳችን ሰምተው ነው እንዲህ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው የመጡት....

<<ሥንት አመት መክሬሽ...ሥንት አመት ለምኜሽ...እርሻት....ከአእምሮሽ አውጪያት...ኑሮሽን ኑሪ ብዬሽ...ሥንት ነገር ተነጋግረን ..የእሷን ቤት አወድማለሁ ሥትይ አንቺ እራሥሽ ወድመሽ ቢሆንሥ ኖሮ...?እረ ምኗ ጉድ ነሽ...ለመሆኑ እንዴት እንዴት አድርገሽ ነው ያን የሚያህል ህንጻ ወደ አመድና ፍርሥራሽነት የቀየርሽው.....?>>

በተዘዋዋሪ ብሥራት ነገሩኝ...ይሄንን ሥሠማ በጣም ደሥ አለኝ...አዎ ይሄንን የምሥራች ለመሥማት ሥንት አመት ጠብቂያለሁ...ሥንት ለሊት እንቅልፍ አጥቼ ሳሰላሥል አድሬያለሁ....

ከዚህ በላይ አይነ ደረቅ መሆን ጋሼን ይበልጥ ማበሳጨት ነው<<ለመሆኑ ያቺ ከይሲ ምን ሆነች...?>>ብዬ ጠየቅኩ....

<<ውይ ሰው እንደዛ አመድ ይነፋበታል...በአንዶኮ ከሠውነት ወደ ጣረ ሞትነት ነው የተለወጠችው...በድን በያት...በቃ በድን....አትናገር አትጋገር..ለፓሊሶች እንኳን ቃሏን መሥጠት አልቻለችም>>

<<እንዴ የምጠረጥረው ሠው አለ አላለችም...?>>

<<እረ እሷ...እንዴት ብላ...በምን አፏ...ብታያት እኮ ኩምሽሽ ብላ አእምሮዋን ያጣች የአማኑኤል ታካሚ ነው የምትመሥለው>>

<<እኔስ ያዙኝ ልቀቁኝ ብላ አገር ትደበላልቃለች ብዬ ነበር...ወደ እኔም ትጠቁማለች ብዬ ተዘጋጅቼ እየጠበኩ ነበር...>>

<<እሱ እንኳን ያው አንቺ እንዳደረግሺው አውቃለች...ለፓሊሥ ግን አልተናገረችም>>

<<እንዳወቀች እርሶ በምን አወቁ...?>>

<<እንደሠማሁ ሂጄ ነበር...አናግሬያታለሁ>>

<<እርሶ እርሷን አናገሯት...?>>

<<አዎ...ምን ለማድረግ እንዳሠበች ማወቅ ነበረብኝ..ጣቷን ወደ አንቺ ለመጠቆም ካሠበች ማሥቆም ነበረብኝ>>

<<ብዙውን ጊዜ ከእሷ ጋር ከማወራ ከሳጥናኤል ጋር ባወራ ይሻለኛል ይሉ ሥለነበር ነው>>

<<ታዲያ በጭንቅ ቀን እኮ ሳጥናኤልንም ቢሆን ማናገር ይናፍቅሻል..>>

<<እሺ ለመሆኑ ምን አለቾት...?>>

<<ሄድኩና የወደመውን ቤት ካየሁ በሁዋላ ወደ አለችበት ሰርቢሥ ገባሁ....ብዙ ሰዎች ነበሩ..ሊያጽኗኗትም ወሬ ለማጣራትም የመጡ...እኔም የማጽናናትና የምመክራት መሥዬ ግን ከሠው ገንጥዬ ወሠድኳትና.....

....ይሄ አሁን የሆነው ከሚገባሽ በጣም ኢምንቱ ነው..በቤት ውሥጥ እያለሽም ከውጭ ቀርቅረን ልናቃጥልሽ እንችል ነበር...ግን ያንቺን ያህል ጨካኝ ሰው ሥላይደለን እንደዛ አላደረግንም...እንድትማሪ እንጂ እንድትጠፊ አንፈልግም...እና አርፈሽ ተቀመጪ...ቢያንሥ በህይወት አለሽ....እፍጨረጨራለሁ ብትይ...ጣትሽን ወደ ሠው እጠቁማለሁ ብትይ....በቀጣይነት ቤትሽን ሳይሆን አንቺን እራሥሽን ነው የምናቃ ጥለው...የሚንቀለቀል እሣት ውሥጥ ነው እንደ ማገዶ የምንከትሽ...የልብ ንጽህና ኖሮሽ እንኳን እንደ ሠለሥቱ ደቂቅ ከእሣቱ የመትረፍ ተሥፋ የለሽም...የገዛ ሀጥያትሽ እራሡ ጋዝ ሆኖ በእሣት ላይ እሣት ሆኖ ነው የሚበላሽ....>>አልኳት....እየተንቀጠቀጠች አዳመጠችኝ...ያቺ ኩሩ ያቺ ጅንን ሴት እንደዛ አንገቷን ደፍታ ሳያት ትንፍሽ እንደማትል ገባኝ...ከእሷ ጋር እንደወጣሁ ነው ወደ አንቺ የመጣሁት...

በደሥታ ከተቀመጥኩበት አልጋ ተሥፈንጥሬ ተነሣሁና የጋሼን ግራና ቀኝ ጎንጮቻቸውን አገላብጬ ሞጨሞጭኳቸው>>

<<ምንድነው እሱ....?የምን ደሥታ ነው....?>>

<<ያሠብኩት ስለተሣካልኝ...እሷን ማሸማቀቅ ሥለቻልኩ...ግን ጋሼ ቆይ እንዲያ ሲያሥፈራሯት ቤቱን በማቃጠሉ እርሶ እንዳሉበት ሲነግሯት የእውነት አምና ትጠቁምዎት ይሆን እንዴ....?>>ሥጋት ቀሥፎ ያዘኝ

<<ታዲያ ምን ሆነና ፍልጎቴ....?አየሽ ካንቺ ሌላ የምትጠረጥረው ሠው ልሠጣት ሥለፈለኩ ነው...ደፍራ ወደ ህግ ከሄደች አንችን አሣልፈ ለመሥጠት እድል ማግኘት የለባትም>>

<<እና....?>>በገረሜታ 

<<እናማ...እኔን አሁን ቀሪ ህይወቴን ቂሊንጦ ገብቼ መንግሥት ቢጦረኝ ምን ይመሥልሻል...?>>

<<አይ ጋሼ......!!!በዚህ እድሜዎ ቅሊንጦ....?ያሾፋሉ>>

<<ምን ይቀርብኛል...?በይ ተነሽ አሁን እንሂድ>>

<<ወዴት...?>>

<<የደሥ ደሥ ምሳ ልጋብዝሻ...ለጀግንነትሽ>>

ፈገግ አልኩ<<...አሁንኮ በሀይለኛው እየተቆጡኝ ነበር>>

<<መቆጣትማ አሁንም እቆጣሻለሁ...ቢያንሥ እንደዚህ አይነት ከባድ ነገር ሥታደርጊ ልታማክሪኝ ይገባ ነበር...ሌላው ይቅር በጉልበት ባላግዝሽ በሃሣብ ማገዝ ያቅተኛል...? ተማክረው የፈሡት ፈሥ አይገማም ይባላል...ያን ባለማድረግሽ አብሽቀሽኛል...ግን ደግሞ የሆነውን ሣይ .....ያቺ መናጢ እንደዛ ኩምሽሽ ብላ ሳይ...በልጄ ጀግንነት አንጀቴ ቅቤ ጠጥቷል...አዎ እንደኮራሁብሽማ ልደብቅሽ አልፈልግን>><<እና የእውነት ይጋብዙኛል?>>

<<በትክክል...በይ ቶሎ ለባብሺና ውጪ>>ብለው ከወንበራቸው በመነሳት ቤቱን ለቀው ወጡ....

ቢጃማዬን አወለቅኩና የሚለበሥ ልብሥ ፍለጋ ሻንጣዬን ከፈትኩ....ሳልፈልግ አይኔ ዋቅቶላ የገዛልኝ ቀሚሥ ላይ አረፈ...

<<ዛሬማ በዚህ በተለየ ቀን የተለየ ነገር ነው የምለብሠው>>አልኩና አውጥቼ ለበሥኩት...ቀሚሱን ስለብስ እሱን እራሱን የለበሥኩት ነው የመሰለኝ...አጠገቤ እንዳለ ወይም እንዳቀፈኝና በሠውነቴ እንደተጠመጠመብኝ አይነት ሥሜት ተሠማኝ...ለብ ያለ የሙቀት ስሜት ...ጫማዬን አጥልቄ ቤቱን ቆለፍኩና ወጣሁ...ጋሼ በዝግታ እየተራመዱ ሲጠብቁኝ ደረሥኩባቸው...

<<አይ የእኔ ልጅ...ቆንጅዬኮ ነሽ>>

<<ቀሚሥ ሥለብሥ ግን በጣም አፍራለሁ>>አልኳቸው...የእውነት ራቁቴን ጎዳና ላይ የምሄድ ነው የሚመሥለኝ

<<አይ ጊዜ....>>አሉ እንደልማዳቸው<<አይ ጊዜ ድሮ በእኛ ጊዜ አንድ ሴት ሱሪ ስትለብስ ነበር...በእፍረት አቀርቅራ የምትሄደውና እርምጃ ሁሉ ጠፍቶባት እግሯ ሚምታታባት...ዛሬ ይሄው ባንቺ ጊዜ ቀሚስ ስትለብሺ ታፍሪና እርምጃ ሲጠፋብሽ ሳይ ከመገረም ውጭ ምን አደርጋለሁ...>>

ጋሼ ምግብ ከጋበዘኝ በሁዋላ ተለይቼያቸው ልሄድ ፈልጌ ነበር...ግን<<ዛሬማ ውልፍች የለም....አብረን ውለን አብረን ነው የምናድረው>>አሉኝ።

<<እንዴ ጋሼ ከጓደኞቼ ጋር ቀጠሮ አለብኝ>>

<<ምን ልትዶልቱ....?ተናግሬያለሁ ንቅንቅ የለም>>ቆፍጠን ብለው አሥጠነቀቁኝ....ጨነቀኝ የእውነቴን ነቅ ዛሬ ከሥንዝሮ ጋር ቀጠሮ ነበረብኝ..ሥለነገ የሁለተኛ ዙር ጥቃታችን ዝርዝር ዕቅዶችን የምናወጣው ዛሬ ነው...ግን ደግሞ አሻፈረኝ ብዬ ጋሼን ተራምጄ መሄድ አልችልም...ተያይዘን ወደ ቤት ሄድን..

ቤቱ ባዶ ነበር..ከፍተን ገባን...ጋሼ አልጋቸው ላይ አረፍ ሲሉ..እኔ ደግሞ ቡና ላፈላ ሽር ጉድ ማለት ጀመርኩ<<ልጄ ቡና ልታፈይልኝ እንዳይሆን>>ጠየቁኝ የህጻን ጉጉት በሚመሥል ሥሜት

<<መጠርጠሩሥ>>

<<አቤት ቡናሽንኮ እንደምናፍቅ...አንቺን እራሥሽን አልናፍቅሽም...>>

<<እሱ እንኳን ውሸት ነው..ከኔ ሚበልጥቦት የለም>> በኩራትና በጉራ መለሥኩላቸው....ነገሩ ጉራ ማለት እንኳን ይከብዳል....አዎ በጣም እንደሚወዱኝ...አንድ አባት ልጁን ከሚወደው እኩል እንዳንዴም ከዚያ በላይ እንደሚወዱኝ ነው ሁሌ ውሥጤ የሚነግረኝ...ውሥጤን ደግሞ አምነዋለሁ...

<<እሱንስ አልሳትሽም...ካንቺ ውጪ ማን አለኝ ብለሽ ነው>>አሉኝ ትክዝ በማለት..

ወደ ቡና ማፍላቴ ከመሄዴ በፊት ሥልክ ደውዬ ለጓደኞቼ ቀጠሯችን መሰረዙን መናገር አለብኝ...ስልኬን አነሳሁና ከፈትኩት....ለሊት ከተልእኮዬ በተመለስኩበት ወቅት እንደዘጋሁት ነበር...ላለመረበሽ...

ደወልኩና ለስንዝሮ ነገርኩት..ዘግቼ ላሥቀምጠው ስል...ጢጥ...ጢጥ የሚል ድምጽ ማሰማት ጀመረ...ሚሴጅ ላክ 35 የሚል ቁጥር አየሁ<<እንዴ ምን ጉድ ነው....?>> 35 ሚሴጅ ...ከፈትኩት..ሁሉንም ተርትሬ አየሁት ከሁለት ቴሌ ከላካቸቅ የዘወትር አሠልቺ ማሥታወቂያ መልእክቶች በስተቀር ሌሎቹ ከዋቅቶላ የተላኩ ናቸው...በዛሬው ግማሽ ቀን ውሥጥ ተላኩ

<<ሰላም አለሽልኝ የእኔ ፍቅር>>

<<ስልክሽ ምነው ተዘጋ?>>

<<ስራሽን አልተውሺውም ወይ?>>

<<ይህ መልእክት እንደደረሠሽ ደውይልኝ>>

<<ይሄን ሁሉ ሰአት እንዴት ሠው ሥልኩን ይዘጋል....?ሰው ያሥባል ብለሽ አታሥቢም እንዴ...?እንዴት አይነት ድንዙዝ መሆን ነው?>>

<<ምን አይነት ደንዳና ልብ ነው ያለሽ?>>

<<በጣም ታሥጠያለሽ...የማትረቢ ነሽ>>

<<በጣምኮ ነው የምወድሽ...ማበዴ ነው>>

.

.

.

.......ሁሉንም አንብቤ መጨረሥ አልቻልኩም..ገረመኝም...አሳዘነኝም...ደወልኩለት... ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው ይላል...ደግሜ ሞከርኩ አይሠራም...

<<ያንተ የራሥህም ስልክ አይሠራም...ደግሞ በአገር ሠላም ምን እንደዚህ ያነጫንጭሃል...?ባል ሆንክብኝኮ>>ብዬ መልእክት ላኩና ቀና ስል ጋሼ ለካ ነገረ ሥራዬን ይከታተል ኖሮ

<<ሰላም ነው ልጄ?>>ሲል ጠየቀኝ

<<አይ ሰላም ነው... ያ ነጭናጫ ሰውዬ ነው>>መለሥኩለት

<<ተይ አንቺ ልጅ...ይሄን ሠውዬ ሳላየው ቀልቤ ወዶታል...ጣል ጣል  አታድርጊው...ሁዋላ በተወደደ ባል እንድልታጪውና እንዳይቆጭሽ>>

ንግግራቸው ፈገግ አሥባለኝ<<ተወዷል እንዴ...?እኔኮ ባል አምሮኝ ልገዛ ወጥቼ ሥለማላውቅ ዋጋውን አላውቅም....ስንት ገባ...?>>በማለት ቀለድኩና ስልኬን ከጋሼ ጎን ጠረጴዛ ላይ ወርውሬ ቡና ልገዛ ወደ ኪዬክስ ወጣሁ....

.

.

.ሰንደሉንም... እጣኑንም..ቄጤማውንም...ቡናውንን ገዝቼ በአሥት ደቂቃ ውሥጥ ተመለሥኩ...።ከሠል አቀጣጠልኩ...ሲኒውን አቀራረብኩ...ቡናዬን አጠብኩና ቆላው...ጭስስ ብሎ ጭሱ ተትጎለጎለ ማንከስከሻ ወስጄ ወደ አፍንጫው አሥጠጋሁለት እና ቡናውን እንዲያሸት አደረኩት <<ሰማያዊ ሽታ በህይወትሽ ይሙላ>>ብለው መረቁኝ...

ቡናውን ወቀጥኩና አፈላዋ....ጋሼን አጠጣሁዋቸው...እኔም ጠጣሁ...ከተመ...ተመረቅኩ በጣም ተመረቅኩ...ከዛ እቃውን አጣጥቤ ካነሳሳሁ በሁዋላ...ከጋሼ ጎን ጋደም አልኩ...

እሳቸው እያወሩልኝ እኔ እያዳመጥኩ ብዙ ብዙ ከተጫወትን በሁዋላ በመሃል ስልኬ ጮኸ ተንጠራርቼ አየሁት...ዋው ዋቅቶላ ነው...ደሥ አለ ኝ ደውሎ ሊነጫነጭብኝ እንደሆነ ባውቅም መደወሉ ደሥ አሠኝቶኛል.....

ከዛም አልፎ ሊሠድበኝ ሁሉ እንደሚችል ብገምትም ማንሣቴን አላቆምኩም....በቃ የሆነ የበረሀ ጉዞ ላይ አንድ ጉንጭ የፊሪጅ ውሃ ገረገጭ ሲያደርጉ የሚሰማ አይነት የእርካታ ሥሜት ነው በመደወሉ ምክንያት የተሠማኝ...ተሥተካክዬ ቁጭ አልኩና አነሣሁት

<<ሄሎ>>ክው አልኩ...ድምጹ የዋቅቶላ አይደለም...እረ እንደውም የወንድ ድምጽ አይደለም..ማን ነች በእሱ ሥልክ የደወለችልኝ....?ውሽማ ትሆን እንዴ.....?ይሄን ሳስብ ልቤ ላይ ጦር የተሠነቀረብኝ መሰለኝ...<<ከዋቅቶላ ሥር ራቂ...ከእሱ ጋር እየተደዋወልሽ አትረብሽኝ>> ልትለኝና ልትሠድበኝ ነው አይደል የደወለችው...?ደም ሥሬ ሁሉ ግትርትር አለ...ልክ ሮማን ፊት ለፊት ለጠብ እንደቆምኩ አይነት....

<<ምን ነበር....?>>ደዋዬ የምታየኝ ይመሥል ኮሥተርተር ብዬ

<<ይቅርታ...ከሻንቡ ሆስፒታል ነው የምደውለው...>>

<<ምን?..ሆስፒታል...ሻንቡ>>አፌን የሞላው ምራቅ ወደ እሬትነት ተቀየረ

<<ተረጋጊ እህቴ...ከዚህ ሥልክ ላይ ያየሁት የመጀመሪያው ቁጥር ያንቺ ሥለሆነ ነው...ታውቂዋለሽ...?>>

<<አዎ በጣም አውቀዋለሁ...ምን ሆነ...?>>

<<ባለቤቱ ነሽ?>>

<<አይደለሁም ጓደ ኛው ነኝ....ምን ሆኗል እያልኩሽኮ ነው?>>አንባረቅኩባት

<<አይ ድንገተኛ ህመም ነው...እራሡን ሥቶ መንገድ ላይ ወድቆ ያገኙት ሠዎች አምጥተውት ነው...ያመጡት ሠዎችም ማንነቱን አያውቁቱም..>>

<<ምን ማለት ነው...?እንዴት ነው አሁን?>>የምለው የምናገረው ጠፋኝ<<እራሱን እንደሳተ ነው...ግን ለክፉ የሚሠጠው አይመሥለኝም..ምርመራ ላይ ነው...መምጣት ብትችይ>>

<<ከየት ነው የምመጣው?>>

ደዋዬ ተደነባበረች<<እንዴ ሻንቡ አይደለሽም እንዴ?>>

<<አዲስ አበባ ነኝ>>

<<ኦ ይቅርታ...በቅርብ ያለ ዘመድ ወይም የጓደኞቹን ሥልክ ትሠጪኛለሽ....?

<<አላውቅም...>>

<<እሺ ችግር የለውም በሥልኩ ላይ ሌላ ቁጥር ፈልጌ ቤተሠቦቹን ለማግኘት እሞክራለሁ>>

ስልኩ ተዘጋ....በድን ሆንኩ...እጄ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ ነው<<ምን ሆንሽ ልጄ....?..ምን ሰማሽ...?>>

<<ታ..ሟ..ል>>ቅርፍፍ ባለና በደከመ ድምጽ መለሥኩላቸው ለጋሼ

<<ምን ነካው ልጄ...?ዋቅቶላ ሥትይ ሰማሁ ልበል?>>

<<አዎ...>>

<<አይዞሽ መታመም ያለ ነው ...አትደንግጪ>>ግንባሬን እያሻሹልኝ

<<ሆስፒታል ገብቷልኮ ነው የምትለኝ?>>

<<አይዞሽ...ምንም አይለው..ሁኔታውን አይተን ካልተሻለው ነገ ወይም ተነገ ወዲያ ሄደሽ ታይዋለሽ>>

<<ሄደሽ?>>በርግጌ አፈጠጥኩባቸው

<<አዎ...ምን አለበት ጓደኛሽ አይደል>>ተቃውሞ ያሠማሁ መሥሏቸው..

<<አይ ማለቴ አሁኑኑ ነው መሄድ የምፈልገው...ከአልጋው ላይ ተሥፈንጥሬ ተነሣሁ...ጋሼ አሁኑኑ መሄድ አለብኝ>>ቁርጥ ውሳኔዬን አሰማሁ....

<<እረ ተረጋጊ ካልሆነ ጥዋት ትሄጂያለሽ>>

<<እንዴት ሆኜ አድሬ?>>

በዚህ ንግግሬ ጋሼ ፈገግ አሉ...<<ምነው ልጄ ጀግና አይደለሽ እንዴ>>አሉኝ ፈገግ ብለው የእሳቸው ፈገግታ እኔን አበሳጨኝ..ግንባራቸውን ሥሜ ተሠናበትኳቸውና ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ...እያጉረመረምኩ..ጀግና አይደለሽም ወይ ይሉኛል እንዴ?

ጀግንነትን እዚህ ጋር ምን አመጣው...ከሮማን ጋር ለመፋለም ካልሆነ በሥተቀር ከዋቅቶላ ጋር ለመፋቀር ጀግንነት ምን ይፈይድልኛል...?ምን እያወራሁ ነው...?መፋቀርን ምን አመጣው...እኔና ዋቅቶላ ፍቅር...ምን ለማለት ፈልጌ ነው..?ስገርም?።

ብቻ ዋናው ጋሼ ግራ አጋብተውኛል...እንዳልሄድ አልተጫኑኝም..እረ በተሠማኝ ድንጋጤና ሀዘንም ብዙ ትኩረት የሰጡት አልመሰለኝ...ከፋኝ...ቀጥታ ወደ ቤቴ እየሄድኩ እሱባለው ጋር ደወልኩለት...የያዘውን ስራ አቋርጦ ሚኒባሷን እቤት ድረሥ ይዞ እንዲመጣ...ዛሬውኑ መብረር አለብኝ...ሰአቴን ተመለከትኩ...9 ሰዓት ሆኗል..በቃ መንገድም ቢሆን አድራለሁ እንጂ ዛሬውኑ መሄድ አለብኝ...ወሠንኩ.........ጂጂ.....


ከተማዋን ለቀን ወጥተን ቡራዩ ሥንደርሥ ከቀኑ 10 ሰዓት ሆኖ ነበር<<...በቃ እንደዚህ ነው የምትነዳው...>>

<<ማለት...?>>

<<በእግር እየሄድንኮ ነው የሚመሥለው>>

<<ከተማ ውሥጥኮ ነው ያለነው...30 የሆነው በምክንያት ነው ሲባል አልሠማሽም>>

ዝም አልኩት..ምን ብዬ ልከራከረው..እሡ ያለው ትክክል ነው...ህግ በሚፈቅድለት አግባብ የሞያ ሃላፊነቱን አክብሮ እየነዳ ነው ...እኔ ነኝ እንጂ የገዛ ሥሜቴን መሾፈር ያቃታኝ...።

እኔ አሁን በዚህ ሠአት በመኪና ተጭኖ በሚሽከረከር ጎማ ኪሎሜትር እየቆጠሩ መጓዝ አይደለም የምፈልገው...አቋራጩን ይዤ ሠማዩን ሰንጥቄ ክንፍ አውጥቼ መብረር ወይም ክንፍ ባለው ነገር ላይ ተንጠልጥዬ መክነፍ ነው የምፈልገው.. .

አሁኑኑ ሥሩ መገኘት...ግንባሩን ማሻሸት..እጆቹን መዳበሥ..ህመምን ማገዝና እሡን መንከባከብ ነው የምፈልገው...።ዳሩ ምን ያደርጋል ሠው የመሆናችን ዋናው ክፋቱኮ ውሥንነታችን ነው....ማድረግ በምንፈልገው የውሥጥ ፍላጎታችንና ማድረግ በምንችለው አቅማችን/ችሎታችን/መካከል ያለው የትየሌለ ልዩነት ነው...

<<መንፈሥ መሆን ነበር>>አልኩ ሳላሥበው ድምጽ አውጥቼ..

<<እረ በሥመአብ በይ>>አለኝ ሹፌሬ እሱባለው..ከእሱ ጋር መጨቃጨቅ አቆምኩና ሞባይሌን ከቦርሳዬ አወጣሁ...ደወልኩ...

"ሄሎ"

<<ሄሎ ማን ልበል...?>>

<<ቅድም የደወልሽልኝ ልጅ ነኝ..>>

<<እእእ..የአዲሣባዋ...?>>

<<አዎ...በእናትሽ እንዴት ነው...?>>

<<አይ...አሁን ደህና ነው...>>

<<ሊያናግረኝ ይችላል...?>>

<<እረ እንደዛማ አይደለም...ማናገር አይችልም...በዛ ላይ አሁንም ህክምና ላይ ነው...ምን አልባት ነገ ካልሆነም ከነገ ወዲያ ነው ልታናግሪው የምትችይው...>>

<<ዘመዶቹ አልመጡለትም.....?አላገኘሻቸውም...?>>

<<አይ አግኝቼያቸዋለሁ...እህቱ መጥታለች...ታናግሪያታለሽ ላገናኝሽ...?>>

<<አይ አታውቀኝም ይቅርብኝ...ባይሆን ቆይቼ አንቺኑ ደውዬ ሥለ ሁኔታው ብጠይቅሽ ይሻላል...እኔም እየመጣሁ ነው>>

<<በእውነት....?እየመጣሽ ነው...?>>የተደነቀና የተገረመ ድምጽ...ግራ ገባኝ....እመጣለሁ ማለቴ ልጅቷን ለምንድነው እንዲህ ያሥደነቃት....?የእኔ መምጣት ለእሷ ፋይዳው ምንድነው.....?ሥልኩን ከዘጋሁ በሁዋላ ሥለዚህ ጉዳይ ነበር የማሥበው...

ጉደር ሥንደርሥ 12 ሰአት ሆነ..እሡባለው እሱ ከሚፈልገው በጣም ፈጠነ አንዳንዴ እኔ ከምፈልገው ደግሞ በተንቀረፈፈ ሁኔታ እየነዳ ነው...ጭራሽ መንገዱን እያጋመሥን ሥንመጣ እና ሠአቱም ወደ ምሽቱ ሲቃረብ ጭንቀቴ በእጥፍ ጨመረ...መልሼ ሥልኬን መጎርጎር ጀመርኩ...ሥልኩ አይሠራም ...ደግሜ ደወልኩ<<የደወሉለት ደንበኛ ሥልክ ጥሪ አይቀበልም>>አለኝ

<<ምን አይነት ብሽቅ ነኝ...?>>

<<ምን ሆንሽ ደግሞ...?>>አለኝ እሱባለው በአንድ አይኑ የፊት ለፊቱን መንገዱን እያየ በአንድ አይኑ ደግሞ ሸርፎ እኔን እያየኝ እና በትዝብት እየሸረደደኝ....

<<ሥልኩ አይሠራም>>

<<የማን....?>>

<<የዋቅቶላ ነዋ...በእሡ ሥልክ ነበር ነርሷ ሥታናግረኝ የነበረው...አሁን ጥሪ አይቀበልም ይላል>>

<<ባትሪ ጨርሶ ይሆናላ>>

<<እ ሱማ እንደዛ ሆኖ ነው..ግን የነር ሷን ሥልክ መቀበል ነበረብኝ>>

<<ይዘጋል ብለሽ ስላላሰብሽ ነዋ>>ሊያጽናናኝ ሞከረ

<<እኮ ማሠብ ነበረብኝ...እሺ አሁን ምን ይውጠኛል...?>¢

<<ምን ይውጠ ኛል....?መታገሥ ነዋ....ወደዛው እየሄድንኮ ነው>>

<<እኮ....እዛ እሥክንደርሥሥ....>>

<<እረ  ሲሱ ተረጋጊ....ከመቼ ጀምሮ ነው ፎንቃ እንዲህ የጠለፈሽ...በእውነት በጣም ነው የገረመኝ>>

<<ምኑ ነው የሚገርምህ...ምን ወሬ ታበዛለህ..አሁን በህይወትና በሞት መካከል ሥላለ ሠው ማሠብና መጨነቅ በፎንቃ ከመያዝ ጋር ምን አገናኘው...>>

<<እረ ቀዝቀዝ...እንዲሁ ለጨዋታ ነው ያነሣሁት>>

<<ቢሆንሥ....?ዝም ብለህ ትዘባርቃለህ እንዴ....?>>

<<ይቅርታ አልኩ እኮ>>ግራ ገብቶትና ደንግጦ.....

<<በል እሺ አፍጥነው>>

<<ይቅርታ...እሡን አልችልም>>

<<ማለት...?>>አልኩት...ደም ሥሬ ሁሉ ግትርትር ብሎ በጥርሤ ልዘነጥለው በጥፍሬ ልቦጫጭረው እየዳዳኝ።...

<<ማለትማ ዳገትና ገደሉን እያየሽው አይደል እንዴ.....?በሠላም የፈለግሽው ቦታ ደርሠሽ ማየት የምትፈልጊውን ሠው ለማየት አትፈልጊም..?

<<እሡማ እፈልጋለሁ...>>አልኩ ቀዝቀዝ ብዬ...የመንገዱን ግራና ቀኝ እያየሁ...

...እውነቱን ነው አሁን ወደሚታየኝ ገደል መኪናዋ ተሽቀንጥራ ሥትገለባበጥና ሁለመናችን ብትንትን ሲል በአይነ ህሊናዬ ታየኝና ዘገነነኝ።ከዛም አልፎ ውሥጤ ሽብር ተሠራጨ...ሞትን በዚህ መጠን ሥፈራ የመጀመሪያ ልምዴ ነው....

በቀደመ ልምዴ ብሞት ምን አጣለሁ....?ከህይወትሥ ምን አገኛለሁ....? ብዬ ለመጠየቅ በምገደድበት አጋጣሚ ከውሥጤ አገኝ የነበረው መልሥ...በመሞት እና በመኖር መካከል ያለውን ልዩነት ምንም ነው የሚል ነበር።....አሁን ግን ለመኖር ያለኝ ጉጉት ሣላውቀው ወደ ላይ ተሥፈንጥሮ ሠማይ ላይ ተሠቅሎ አገኘሁት...ይሄን የታዘብኩት ደግሞ አሁን ነው..አሁን በዚህቺው ደቂቃ..

በሥንት ጣርና መከራ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ፊንጫ ከተማ ደረሥን።ግራ ገባኝ...እንቀጥል ወይሥ አልጋ ይዘን እዚሁ ፊንጫ አድረን ለሊት እንሂድ.......?

<<ምን ትላለህ......?>>አልኩት በራሴ መወሠን አቅቶኝ

<<ምኑን በተመለከተ...?>>

<<እንቀጥል ወይሥ እዚሁ ፊንጫ አድረን ለሊት እንሂድ....?>>

<<እንደኔ እንደኔ እዚሁ ብናድርና ለሊት ብንበር ይሻላል ባይ ነኝ...አሁን ብንሄድም እዛ ሥንድርሥ አራት ሠአት ያልፋል...በዛ ሠአት ደግሞ ሆሥፒታልም መግባትና ማየት አንችልም...አልጋም ልናጣ እንችላለን>>

<<አልጋው እንኳን ችግር የለውም ላንድ ቀን መኪና ውሥጥ ብንተኛሥ ለአንድ ቀን ምን አለበት....?>>አልኩት በትዝብት።

<<አይ እንደፈለግሽ....ንዳ ካልሽኝ ልንዳው>>አለ ኝ

<<ንዳው ልበለው ወይሥ ምን ይሻላል....?እያልኩ ከራሴ ጋር ሥወዛገብ ሥልኬ ጠራ....አየሁት።ጋሼ ናቸው።>>

አነሣሁት <<ጋሼ ምን ይሻለናል....?በጣም ነው የጨነቀኝ....? ሻንቡ መድረሥ አልቻልንም.....?እሡባለውን ዛሬ ቢያዩት በጣም ለግሟል...መኪና የሚነዳ ሣይሆን ጋሪ የሚገፋ ነው የሚመሥለው....አሁን ፊንጫ ከተማ ነን...ብንሄድም ሆሥፒታል መግባት አንችልም ብሎኛል...ሥልኩም አይሠራም..በጣም ጨንቆኛል>>ተንጣጣሁባቸው።

<<ልጄ አይዞሽ ተረጋጊ....በቃ ጥሩ ተቃርበሻል እኮ....ሥለዚህ አሁን እዛው ያላችሁበት እደሩ...ከዚያም ለሊት ተነሱና በጥዋቱ ትደርሣላችሁ....>>

<<እንደዛ ይሻላል ጋሼ...?>>

<<በእኔ ይሁንብሽ እንደዛ ነው የሚሻለው...በሉ አሁን መኝታ ፈልጉ...እራሥሽን አረጋጊና እራት በልታችሁ ተኙ>>

<<እሺ ጋሼ>>

<<በይ ደህና እደሪልኝ....ጥዋት እንደደረሽ እና የልጁን ሁኔታውን እንዳየሽ ደውይልኝ>>

<<እደውልሎታለሁ ጋሼ...አመሰግናለሁ>>ሥልኩ ተዘጋ....ወደ ያዲ ሆቴል መኪናችንን አሥገባን..ይሄ ሆቴል ከከተማዋ የተሻለውና ትልቁ ነው...ጎን ለጎን ሁለት አልጋ ያዝን..ወደየክፍላችን እየገባን ሣለ አሥቆመኝና<<…ቦርሣሽን አሥቀምጪና እራት እንውጣ...?>>አለኝ እሡባለው

<<አይ አንተ ወጣ በልና ብላ...እኔ ማረፍ ነው የምፈልገው>>

<<እረ ተይ...ለሊት ይርብሻል>>

<<ግድ የለህም..ይቅርብኝ>>

<<እሺ እዚሁ ይምጣልሽ....?>>

<<አይ አልፈልግም...ለሊት 11:30 እቀሠቅሥሃለሁ>>

<<ጥሩ ተሠናብቼው መኝታ ቤቱን ዘጋሁና...አልጋዬ ላይ ዘፍ አልኩ...ልተኛ  ሳይሆን ልተክዝ...

.

.

.

.

ዋቅቶላ...

እሷ መልሳ ካልመጣች በሥተቀር ምንም የምነግራችሁ ነገር የለም ብያችሁ ነበር..አይደል..?አሁን እንግዲህ አንሥቼዋለሁ...።እናንተም ናፍቃችሁኝግ ነበር....እውነቱን ለመናገር ግን ያው በእናንተ ለመወደድ ካልሆነ በሥተቀር እንኳን ልትናፍቁኝ ትዝ ብላችሁኝም አታውቁ...እውነቴን ነው...በዛ ሁሉ ሃሣብ...በዛ ሁሉ እራሥንም እሥከመርሣት በደረሠ መብሠልሠል ውሥጥ እንዴት ሥለእናንተ ላሥብ እችላለሁ.....?እራሴንም ረሥቼ ነው የከረምኩት...እንዴ !!!!!!!ለካ ፍቅር የሚባለው ውጥንቅጥ ሥሜት እንዲህ ነው እንዴ.......?እረ እንዲህሥ ከሆነ ለጠላትም አይስጥ...

አሁን ወደ ዛሬው ጉዳይ ልመለሥላችሁ...በደሥታ ጦሽ ልልላችሁ ነው..ጠረኗ እየሸተተኝ ነው...አዎ እኔ ወዳለሁበት እየቀረበች ነው..ይታወቀኛል...እድሜ ለአንድ ሠው...እድሜ ለጽድቁ ሽማግሌ...ለካ ወዳ አይደለም እሷም እንደዛ የምትወዳቸው እና ሁሌ ከአፏ የማይጠፉት...የሆነው እንዲህ ነው...ዛሬ ሰባት ሰዓት ላይ ነበር ሥልኬ የጠራው ...ጂጂ ነበረች...ደውዬ ካናገርኳት ከ10 ደቂቃ በሁዋላ ነበር መልሶ የተደወለልኝ..ሳነሳው ግን እሳቸው  ነበሩ...

<<ሄሎ>>

<<ሄሎ ዋቅቶላ>>የሚርገበገብ ደካማ ድምጽ

<<አቤት ማን ልበል...?>>አልኩ ግራ ገብቶኝ..

<<ዜና እባላለሁ...የጂጂ አባት ነኝ ማለት እችላለሁ>>

<<አወቅኮት...ማለት እሷ ሥለ እርሶ ነግራኛለች>>

<<ጎሽ..እንግዲያው አንድ ነገር ልንገርህ...ጂጂ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም>>

አቤት የደነገጥኩት አደነጋገጥ...የቅርብ ዘመዴን ሞት የተረዳሁ ነው ያሥመሠልኩት

<<አይ ማለቴ ለጊዜው ደህና ነች..ግን አሳዳጊዋን ሴትዬ ለማጥቃት እንቅሥቃሤ ላይ ነች..በዚሁ ከቀጠለች ደግሞ ወይ የሆነ ወንጀል ሥትሠራ ትያዝና እሥር ቤት ትወረወራለች አልያም አደጋ ደርሶባት ደመ ከልብ ትሆናለች ብዬ በጣም ፈርቼ ነው>>

<<ታዲያ ምን ላድርግ.....?ይንገሩኝ..ልምጣ እንዴ.....?መጥቼ ልጠብቃት...?>> ሁሉን ነገር ጥለህ ብረር ብረር የሚል ሥሜት ወረረኝ...

<<አይ ልጄ እንደዛ አይደለም...ወዳንተ ውሠዳታ...እንደዛ ነው የሚሻለው>>

<<አይ ፋዘር...እሡንማ ሞክርያለሁ..ብዙ ቀን ለምኛታለሁ..ላሣምናት ..አልቻልኩም እንጂ>>

<<ዘዴ ፍጠራ..የሆነ ዘዴ ከፈጠርክ ሥለምታፈቅርህ ትታለልሃለች>>

<<ሥለምታፈቅርህ ነው ያሉት....?እሷኮ ሠው ማፍቀር አትችልበትም>>

<<አይ ልጄ እሱን እንኳን ተወው..የአፏን ሰምተህ ነው አይደል....?የፍቅር ጉዳይ ልብ ላይ ነው የሚጻፈው እንጂ ምላሥ ላይ አይንጠለጠልም...ከአንደበቷ የሚወጣውን ቃል ሳይሆን የልብ ምቷን አድምጥና ሥለአንተ የምታሥበውን ለመረዳት ሞክር ያን ጊዜ እውነቱን ትረዳለህ...

እኔን ከጠየከኝ በቃ በጣም አፍቅርሃለች...ግን ማመን አልፈለገችም...እንዲህ አይነት ሽንፈት ተሸንፋ ሥለማታውቅ ማመን ከብዷት ነው....>>

<<የሚሉት እውነት ቢሆን ደሥ ይለኛል>>

<<ነው ልጄ እመነኝ...እሷን እድሜ ልኳን ነው የማውቃት..ለማንም ወንድ እንዲህ አይነት ሥሜት ሲሰማት እንዲህም ሥትብሰለሰል አይቻት አላውቅም....እና የምትወዳት ከሆነ ውሰዳት..ደግሞ እመነኝ ምን አልባት የተገናኛችሁት ጥሩ ያልሆነ ቦታ ሊሆን ይችላል..ግን ወርቅ የሆ ነች ልጅ ነች...ለወደደችው የምትሞት የራሴ ላለችው ሠው የምትኖር ልጅ ነች....

<<ፋዘር አውቃለሁ...ሶስት ቀን አብሬ ኑሬ ብዙ ነገር ሥለ እሷ አውቄያለሁ...በጣም ነው የምፈልጋት...እኔ ስላለፈው ደንታ የለኝም..የትናንቷን ጂጂን ሳይሆን የዛሬዋን...አሁን ያለችዋን ጂጁን ከነ ክፍተቷ ነው የምፈልጋት>>

<<ተባረክ ልጄ...ጥሩ ሰው ነህ....ወድጄሃለሁ...እና ተሥማምተናል ማለት ነው አይደል...?>>

<<ምኑ ላይ ነው የተሥማማነው ፋዘር...?>>

<<ትወሥዳታለህ..?>>

<<እንዴት አድርጌ ፋዘር...?>>

<>ይሄውልህ እኔ አንድ ዘዴ አለኝ..ከአንድ ሰአት በሁዋላ ደውልላት..>>

<<ደውዬሥ...?>>

<<ማለቴ አንተ ሣትሆን በሌላ ሠው ትልሥደውልልና አንተ አደጋ ደርሣሶብህ እራሥህን ሥተህ ሆሥፒታል እንደገባህ እንዲነግሯት አድርግ>>

<<እንዴ ጋሼ...ይሄ ምን ይጠቅማል....?>>

<<እሷን ወደ አንተ ለማምጣት ነዋ>>

<<እረ አትመጣም>>

<<ሞክርና እየዋ...በል ቻው አሁን እየመጣች ነው>>ብለው ሥልኩን ዘጉብኝ...10 ደቂቃ እዛው ባለሁበት በመደንዘዝ ውሥጥ ሆኜ ነው ያሳለፍኩት..ምን አይነት ዘዴ ነው የነገሩኝ...?እንድትመጣልኝ እፈልጋለሁ....በምንም ሆነ በየትኛውም ዘዴ ብትመጣልኝ ለእኔ  ሰርግ ነው...ግን ደግሞ ታምሚያለሁ ብዬ አሥደውዬላት ባትመጣሥ.......?በዛ የተነሣ ውሥጤ ቢቀየማትሥ......?ፍቅሬ ቢቀዘቅዝሥ.......?ፈራሁ.....የምሠሥትለትን ሥሜት እንዳላጣ ፈራሁ...።

እንዴት ሠው  ስቃዩ እንዳይድንለት ይፈራል....?ከእሷ ጋር ያለኝ ፍቅር ማለት ለኔ ስቃይና ጣር ነው የሆነብኝ ....እና ተሳክቶልኝ ቢተወኝ ..ከፍቅሯ ብፈወሥና ከ ሥቃዬ ብገላገል ምኑ ነው ክፋቱ.......?

እረ ከነ ሥቃዬ ለዘላለም ልኑር...ብዙ ደሥታዎች በሥቃዩች የታጠሩና የተለወሡ ናቸው...ሰው ቃሪያ ሲኮረሽም እየለበለበውና እያቃጠለው ቢሆንም የምግብ ጣእም ግን ይጨምርለታል..የጂጂ ፍቅርም ለእኔ እንደዛ ነው የሆነብኝ...ፍቅሯ ልክ እንደሚጠጣ የሚያቃጥል...ነገር ግን በኑሮዬ ላይ ስውር ጣእም ያለው ደሥታ የነሠነሠብኝ ነው።

ለማንኛውም ከብዙ ማሠብና ውዝግብ በሁዋላ ወሠንኩ...የመጣው ይምጣ ብዬ ወሠንኩ....አንድ የሥራ ባልደረባዬ የሆነች እንሥት ፓሊሥን ጠራዋትና ነገርኳት....እየሳቀችብኝ ሥልኩን ተቀበለችኝ.... ደወለችና ታምሜ ሆሥፒታል እንደገባሁ ነገረቻት....ኮሥተር ብላ ነገረቻት...።

ሌላውን ነገር ያው ከእሷ ጋር ሥለነበራችሁ ዝርዝር ታሪኩን ከእኔ በተሻለ ታውቁታላችሁ...

ወደ እኔ እየመጣችና ጉዞ እንደጀመረች ያበሰሩኝ ሽማግሌዎች ናቸው....ከዛ ምን ልንገራችሁ..ሰማይን የጨበጥኩ ጨረቃን የረገጥኩ ነው የመሠለኝ..የምሆነውን አጣሁ...

አሁን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ፊንጫ እገኛለሁ....አዎ መኪና ውሥጥ ሆኜ መድረሷን አይቻለሁ...አቤት ሳያት እንዴት ልቤ ስንጥቅ እንዳለ...ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁዋት ሁሉ...ከመኪናዬ ወርጄ ወደ እሷ ለመንደርደር ቃጥቶኝ ነበር...በግድ ነው እራሴን ያረጋጋሁት..እሷ በዚህን ሰአት ሆሥፒታል እንዳለሁ ነው የምታውቀው...

አዎ አሁን መኪናቸውን ዳር አሥይዘው በማቆም ሥልክ እያወራች ነው...ጨርሳ ዘጋችው።ደግሞ እንዴት ቆንጅዬ ሆናለች...ቀሚሥ ነው የለበሠችው..እኔ ገዝቼላት የነበረውን ቀሚሥ..እኔን እራሤን የለበሠችኝ ነው የመሠለኝ...ደሥ አለኝ...አዎ ወደ እኔ ሥትመጣ እኔ የገዛሁላትን ልብሥ ለብሣ መምጣቷ እኔን ለማሥደሠት ያላትን ፍላጎት ያሳያል..አዎ ሽማግሌው ትክክል ናቸው ታፈቅረኛለች....ከብዙ መወዛገብ በሁዋላ መኪናቸውን ወደ አንዱ ሆቴል አሥገቡት...የእኛም መኪና ከሁዋላ ተከተላቸው...አልጋ ሲይዙ ከመኪናችን ሳንወርድ እያየናቸው ነው...ክፍሏ ገብታ ሥትዘጋ ሁሉ እያየዋት ነበር...

ከዛ በላይ መጠበቅ አልተቻለኝም...ጓደኞቼን እዛው መኪና ውሥጥ ጎልቼ ወጣሁ..ወደ ክፍሏ ተንቀሳቀሥኩ..ደረሥኩና አንኳኳሁ...ᐸᐸማነው....?>>

ᐸᐸመታወቂያ>>አልኩ ድምጼን ጎርነን አድርጌ....

ከተወሠነ ሠከንድ መንገዳገድ በሁዋላ ተከፈተᐸᐸእፊቷ ተገተርኩ..ነገሬም አላለችኝ..ቀናም ብላ ሣታየኝ መታወቂያዋን አቀበለችኝ...

ᐸᐸአይታይም>>ብዬ ወደ ውሥጥ ገባሁ...ግራ በመጋባት ቀና ብላ አየችኝ...ወደ ሁዋላዋ ሸሸች

....አይኖቿን ጨፈነች...ገለጠች...መልሳ ጨፈነች...ነገረ ሥራዋ ሥላላማረኝ ለማንኛውም ብዬ በራፉን ዘጋሁት...ዋይይይይይይ....>>ጆሮዋን በሁለት እጇ ደፍና አንባረቀችው....መልሼ እኔው ደነገጥኩ..ቶሎ ብዬ አፏን በመዳፌ ደፈንኩት..ከውጭ የእግር ኮቴ...የመሯሯጥ ድምጽ ይሠማኛል...አዎ ትክክል ነኝ...በራፉ ተንኳኳᐸᐸምንድነው ጩኸቱ....?ችግር አለ እንዴ...?>>

ᐸᐸአይ ሠላም ነው..እቃ ወድቆብን ነው...ችግር የለም>>አፌ ላይ የመጣልኝን መልሥ ሰጠዋቸው..

እግዜር ይሥጣቸው በቀላሉ አምነውኝ ተመለሡ...እሷ ግን ትቀጠቅጠኝ ጀመር...በጥፊ...ደረቴ በጡጫ..ወደ ራሴ አፍኜ ጨምቄ አቀፍኳትᐸᐸደደብ ነህ...እንዴት እንደዚህ ታደርገኛለህ......?እንዴት እንዲህ ታሠቃየኛለህ.....?እንዴት እንደዚህ ታሥደነግጠኛለህ...?>>አለቀሠች...አለቀሠችኮ!!!አንገቴ ሥር ተወሽቃ የምታፈሠው እንባ ትካሻዬ ላይ እየነጠረ ወደ ገላዬ ሲሰርግ ቅዝቃዜው ይታወቀኛል...በእኔም አይኖች ውሥጥ እንባ ግጥም አለ...በዚህ መጠን ማፍቀር.....በዚህ መጠን መፈቀር....በዚህ አይነት መንሠፍሠፍ መተቃቀፍ...በዚህ አይነት ሥሜት እንባ ማፍሠሥ..ጌታ ሆይ ይሄን ደሥታ ህልም እንዳታደርገው...ህልም ከሆነ ደግሞ እንድነቃ አታድርግ...በቃ እሷ ከሌለችበት የእውነት ህይወት ከእሷ ጋር ባንድ ላይ የህልም አለም ውሥጥ ለዘላለሙ ብጠፋ ይሻለኛል>>ጨምቄ እንዳቀፍኳት ለአምላኬ ያሠማሁት ጸሎት ነበር....ከልብ የመነጨ የማጣት ፍርሃት የወለደው ፀሎት......አሁን ተኝቻለሁ እዚህ ቤት እዚህ አልጋ ላይ ማደር ከጀመርኩ 3 ቀን ሆነኝ።

መኝታ ቤቷ ሶስት በሶስት የሆነች የምታምር ክፍል ሥትሆን በውሥጧ መካከለኛ ሥፋት ያለው መዝቦልድ አልጋ ተዘርግቶበታል።

ሻንቦ ከተማን ወድጃታለሁ ብላችሁ ውሸት ይሆንብኛል ከተማዋ አንድ እድሜዋን በሙሉ ፒያሳ ለኖረች የአራዳ ልጅ ምንም የከተማነት ጣእም የሌላት እልም ያለች የገጠር መንደር ነች ብትል ጉረኛ ልትባል አይገባም ለነገሩ እኔ እንደዛ አልተሠማኝም ምክንያቱም ብዙም ለውጪው ማለቴ ለከተማዋ ሥፋትና ጥራት ትኩረት አልሠጠውም....ቤቱን ግን ወድጄዋለሁ ብቻ አይገልጸውም..ልጅቷን...አሮጊቷንሥ ቢሆን አሮጊቷ ያልኳችሁ የዋቅቶላን እናት ነው...በጣም ጥሩና ደግ አዛውንት ናቸው..ከአማርኛ ይልቅ ኦሮምኛ ቋንቋ ይቀናቸዋል...እኔም ቋንቋውን የማውቅ ይመሥላቸውና አንዳንዴ ድንግርግሬን ያወጡታል...

<<ልጄ ከቤተሠቦችሽ ጠፍተሽ ነ...?>>ይጠይቁኛል በመጨነቅ..

በእሳቸው እይታ እኔ ገና ክፉና ደጉን ለይቼ የማላውቅ አንድ ፍሬ ጨቅላ ልጃገረድ ነኝ።..ይህን ያልኩት ከምንም ተነሥቼ አይደለም...ከመጣሁ እለት ጀምሮ ከቤተሠብ ጋር አምሽቼ ለብቻዬ ለመተኛት እዚህች አሁን ወዳለሁባት ክፍል መግባቴ ከመፍራቴ...ጨዋ ከመሆኔ...ድንግልናዬን እንዲሁ በቀልድ ላለማሥወሠድ የማደርገው ጥረት አድርገው ነው የወሠዱት...እና ይሄ ደግሞ በእሣቸው ከፍተኛ ክብር አሰጥቶኛል።

<<ጎሽ ልጄ እንደዘመኑ ልጆች አይደለሽም>>አሉኝ...ፈገግ አልኩ..እውነትም ከዘመኑ ልጆች በተቃራኒ እየተሽኮረመምኩ በውሥጤ <<አልሠሜን ግባ በሉት...>>እያልኩ..በነገራችን ላይ እዚህ ሻንቡ ከተማ ከገባሁና እዚህ ቤት ከረገጥኩበት ቀን ጀምሮ አንገት ደፊ ተቅለሥላሽና በጣም ጭምት ልጅ ወጥቶኛል...ለራሤም እሥኪገርመኝ ድረሥ....መቼሥ ፒያሣ ላይ የሚያውቀኝ ሠው አሁን የሰሞኑን ሁኔታዬን ቢመለከት ምን አይነት አሥመሳይ ልጅ ነች ብሎ አሥተያየት መሥጠቱ አይቀርም...እኔ ግን ለማሥመሠል ብዬ ምንም የሞከርኩት ነገር የለም...ግን በቃ ውሥጤ ነው እንደዛ እንድሆን የሚገፋፋኝ..ልንቀልቀል ብልም እግሬ አይፈጥንልኝም...ልለፍልፍ ብልም አንደበቴ አይላቀቅልኝም...ልፍጠጥ ብልም ቅንድቤ አይበለጠጥልኝም...አሮጊቷ በሠሞኑ አብሮነታችን ልጃቸው ጥሎን ሲወጣ ያወሩኛል...<<አይዞሽ ልጄ...ክብሯን የምትጠብቅ ልጅ እወዳለሁ...ከጋብቻ በፊት እንዲች ብለሽ>>..በገዛ ልጃቸው ላይ ያሣድሙበታል...ወደድኳቸው...በውሥጤ እያፈርኩ ወደድኳቸው..ምነው እሳቸው የ ሳሏትን ልጅ ሆኜ ቢሆን ኖሮ ሥል እየተመኘሁ....

ልጃቸውን የማግባት ፍላጎት የለኝም...ግን እሳቸው እናቴ እንዲሆኑ እፈልጋለሁ..አይ አሁንም ይሄ ዙሪያ ጥምጥም መዞር አልተወኝም...እውነት ጂጂ ይቅርታ ሻንቡ ከመጣሁ ጀምሮ ከማገኛቸው አዳዲሥ ሠዎች ጋር ሥተዋወቅ እጅጋየሁ እባላለሁ....እጅጋየሁ ዜና ብዬ ሙሉ ሥሜን በወጉ መናገር ጀምሪያለሁ......ያው ዜና ትክክለኛ አባቴ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ...ዜና ጋሽ ዜና ናቸው...ከእኔ ሥም ቀጥሎ ለመጠራት ብቃቱም መብቱም ያለው ይሄ ዜና የሚሉት ሥም ነው....በእኔ ህይወት ውሥጥ ድርሻ ያለው...እና ወደ ነገሬ ልመለሥና <<እጅጋየሁ በእውነት ዋቅቶላን ማግባት አትፈልጊም....?የዚህ ቤት እማወራ ለመሆን ፍላጎት የለሽም...?ብዬ እራሤኑ ሥጠይቅ ....<<በፍጹም..>>ብዬ ለራሴ ልመልሥ አፌን እከፍትና መግጠም ያቅተኛል...ያንቀኛል....ቃላቱን ማሥፈንጠር ያቅተኛል።

ውይ የመኝታ ቤቱን በር የሚቧጭር ነገር አለ ...ምንድነው ሰአቴን አየሁ አራት ሠአት ተኩል ነው.....እረ የመንኳኳት አይነት ድምጽ እየተሠማኝ ነው...ደካማ የበር መንካት አይነት ድምጽ...ድምጹ ሌላ ክፍል እንዳይሠማ የመፍራት አይነት ስሜት ያለው.....<<ምን አይነት ድመት ነች ይሄን ከመሠለ ሃሣቤ መንጭቃ የምታወጣኝ.....?>>

እየተነጫነጭኩ ከወልጋዬ ወረድኩ...እርቃኔን ነኝ።በሠውነቴ ላይ ያለው ሠማያዊ ፓንቴ ብቻ ነው..በራፉን ቀሥ ብዬ ከፈትኩት...ድመቷን ላባርራት...<<በአራዳው ጊዩርጊሥ..!!!በራፉ ላይ ማን እንደተገተረ ታውቃላችሁ.....?እሥኪ ገምቱ>>አትቸኩሉ አላገ ኛችሁትም...ማለቴ ግምታችሁ ትክክል አይደለም...ዋቅቶላ መሥሏችሁ ነበር አይደል....?በራፍ ላይ የቆመችው የዋቅቶላ ትንሽ እርግብ ነች...በእንቅልፍ የደከሙ አይኖቿን በዛ የሚያምር ሚጢጢ እጇ እያሻሸች በሌላ እጇ በራፉን ሥትቧጥጥ የነበረችው......

<<ቦንቱ ምን ሆነሽ ነው...?>>

<<እማ እማ...>>እጆቿን እንደ ምርኮኛ ግራና ቀኝ አንከርፍፋ...እንዳቅፋት መሆኑ ነው>> በርከክ ብዬ አቀፍኳት እና ወደ ውሥጥ ገባሁ..በራፉን መለሥ አደረኩትና ወደ መኝታዬ ይዣት ወጣሁ...ክንዴን ተንተርሳ  ጡቶቼ መካከል ገብታ ውሽቅ አለች...

<<ምነው የኔ ጣፋጭ....?ጸጉሯን እያሻሸሁላት ..ምንም አልመለሠችልኝም..ጭራሽ አይኖቿን ከደነች...በውሥጤ የተሠማኝን ሥሜት ልነግራችሁ አልችልም...እንዴት እግዜር እንዲህ ደግ ሊሆን ቻለ......?

እሱ መቼሥ ሲሰጥ ስስት የለበትም።...እድሜዋን መሉ ሥትገፋና ሥትበደል የነበረች..ዘር ማንዘር ያልነበራት ወፍ ዘራሽ ልጅ በአንዴ ሙሉ ቤተሠብ ሲሰጣት ይሄ መቼሥ መመረቅ ነው....?እሥከ መቼ ይሆን ይሄ ደሥታ ከእኔ ጋር የሚቀጥለው....?

...የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና እኔ የሚያበቃልኝ ይሄንን አሁን የተሠ ጠኝን ፍቅር የተነጠቅኩ ቀን ነው።...

እሥከዛሬ ዋቅቶላ በምን ያህል መጠን እንዳፈቀረኝ ታውቃላችሁ...እናቱም እንዴት እንደተቀበሉኝ በመጠኑም ቢሆን ነግሬያችሆለሁ...የዚህችን ህጻን ያህል ግን የወደደኝ የለም...እንደመጣሁ ነው የተለጠፈችብኝ..ልክ ለብዙ ጊዜ እንደምታውቀኝና ሥትጠብቀኝ እንደኖረች አይነት..ቀኑን ሙሉ ወደ ሣሎን ሥሄድ ሥትከተለኝ.....ኩሽና ሥገባ አብራኝ ሥትገባ..ይገርማችሁዋል ሽንት ቤት ሥገባ እንኳን አታምነኝም<<...እማ...>>ሥትለኝ

የእውነት እናቷ የሆንኩ ነው የሚመሥለኝ...አሁን ከአንድ ሠአት በፉት እራት እየበላን ሣለ ክንዴ ላይ ነበረ እንቅልፍ የወሠዳት...ከዛ ቀሥ ብዬ ከአባቷ አልጋ ላይ አሥተካክዬ አሥተኝቼያት ነበር የመጣሁት...ከእሡ ጋር ሥለምትተኛ...ይሄው ስትነቃ እና ሥታጣኝ መጣች.....

እና ታዲያ መጨረሻዬ እንዴት ነው የሚሆነው......?እዚህ ቤት ውሥጥ ነገን ብቻ ነው የምውለው...የጀመርኩትን ነገር ለመጨረሥ ወደ አዲስ አበባ እመለሳለሁ...እቅዴን ለማሣካት ደግሞ ቢያንሥ አንድ ወር እዛው መቆየት ይጠበቅብኛል....በዛ ላይ አደጋ ሊያጋጥመኝ ይችላል...ልታሠርም እችላለሁ...

እና እንዴት ነው የምችለው......?እንዴት ነው ከዚህች መላእክ ተለይቼ የምኖረው......?እና ቢቀርብኝሥ.....?አዎ ቢቀርብኝሥ....ሮማንን ለመበቀል መባከኑ ቢቀርብኝ...እርግፍ አድርጌ ብተወው...ይቅር ብላት.....?

<<አይ ወይዘሪት ጂጂ ይሄማ ደካማነት ነው....ለአዕምሮሽ ፊት አትሥጪ...ያቺን አውሬ በቂ ቅጣት ሳትሰጪያት እና ከዚህች ምድር ሳታሰናብችያት ወደ ሁዋላ ብትይ የእናትሽ የሙት መንፈሥም ይቅር አይልሽም>>እራሴን ገሰጽኩ...አበረታሁ..አዎ በእቅዴ መሠረት ነገን ብቻ ውዬ መሄድ አለብኝ...አዎ ጠላቴን ለመበቀል..ከዚህ የበለጠ ፍቅር ቢሰጠኝ እንኳን እሰዋዋለሁ እንጂ አልታለልም..ሮማን በምትኖርበት ምድር ላይ እኔ መኖር አልፈልግም..የእኔ አዲሥ ህይወት መጀመር ያለበት በእሷ ሞት ላይ ነው....ውሳኔዬን አደሥኩ.....ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው..አሁንም ሳልቀረቅር የረሳሁት በራፍ በዝግታ ተከፈተ.....

ቀና ብዬ አየሁ...አሁን ደግሞ አባትዬው ነው..ዋቅቶላ።አንገቱን አስግጎ ወደ ውሥጥ እያየ ነው...

<<አንቺ ነሽ የወሠድሻት....?>>በማለት ጠየቀኝ.....ብንን ሲልና ልጁን ከጎኑ ሲያጣት ነው ፍለጋ የመጣው...አለመተኛቴን ሲያውቅ ወደ ውሥጥ ገባ

<<አይ...እራሷ ነች የመጣችው>>

<<ወይ ጉዴ...የእኔ ይሁን ልጄን ደግሞ ምን አሥነካሽብኝ....?>>እያለኝ መጣና አልጋው ጠርዝ ላይ አረፍ አለ..

<<ቀናህ እንዴ...?>>

<<አይ አልቀናሁም...ፈራሁ እንጂ>>ሲል መለሠልኝ።..አልመለሥኩለትም...ዝም አልኩት...ምክንያቱም እሱ ብቻ ሳይሆን እኔም ፈርቼያለሁ....ነገ በጣም ያሥፈራል።

.....ከተወሠነ በዝምታ የታገዘ መተከዝ በሁዋላ ተነሳ....ወደ ውጭ መራመድ ጀመረ....<<አይዞህ አታሥብ ከእኔ ጋር ይመቻታል>>አልኩት...ለልጁ እንዳይጨነቅ በራፉ ጋር ደረሠና ከፍቶ ይወጣል ብዬ ሥጠብቅ..ቀረቀረውና ተመልሶ መጣ...ደነገጥኩ..ልክ እሥከዛሬ አብሬው ተኝቼ እንደማላውቅ ሁሉ ደነገጥኩ...ልክ ልጃገረድ እንደሆንኩ አይነት...ልክ ተሳሥቶ እንዳያሣሥተኝ እንደፈራሁ አይነት...

<<ምን እየሰራህ ነው....?>>

<<እኔም ካንቺ ጋር ብተኛ ይመቸኛል....?>>

<<አይሆንም...>>

<<ለምን.....?>>

<<አይሆንማ እናትህ ምን ይሉናል....?>>

<<ምንም አትለንም....አብረው ተኙ ብቻ ነው የምትለን>>አልጋው ላይ ወጣና ከሁዋላዬ ተሻግሮ ብርድ ልብሱን ገልጦ ገባ......

<<ቀሺም ነህ.....እናትህ ሌላ ነገር እንዲያሥቡና እንዲደብራቸው አልፈልግም>>

<<አትነጫነጪ...ትንሽ ተኝቼ እሄድልሻለሁ>>ወደኔ ዞሮ አቀፈኝ...እኔ ፊቴን ወደ ቦንቱ ነው ያዞርኩት...እሱ እኔን እኔ ደግሞ የእሱን ልጅ እንዳቀፍን በፀጥታ ተዋጥን....ለረጅም ደቂቃ በፀጥታ....

<<ተኛሽ እንዴ...?>>አለኝ......ምንም አልመለሥኩለትም....እንደውም ቀና ብሎ ካየኝ ብዬ አይኖቼን ጨፈንኩ...ማውራት አልፈለኩም...ከጎኔ ሥለተኛ ደሥ ብሎኛል ግን ደግሞ ፈርቼያለሁ...እናቱ ቢያውቁሥ........?እንደዛ መክረውኝ.....እንደዛ አሥጠንቅቀውኝ.....ድንግልናዬን ላሥወሥድ....?የራሴው ቀልድ ለራሴው ፈገግ አሰኘኝ...

እንደገመትኩት ቀና ብሎ አንገቱን ወደፊት አሰገገና አየኝ....መተኛቴን ሲያረጋግጥ ወይም የተኛሁ ሲመሥለው ተንጠራራና መብራቱን አጠፋው......

እኔ ቀድሜ ከተኛሁበት ወጥቶ ይሄዳል ብዬ ነበረ ያሰብኩት እሱ ጭራሽ ለብሶ የመጣውን ቁምጣ እያወለቀ ነው.....ተመልሶ ተኛ....አቀፈኝ....መቀመጫዬ ላይ ተለጥፎ አቀፈኝ...መላ አካሉ አካሌ ላይ ተጣበቀ...እንዲህ ሲሆን የመጀመሪያ ቀናችን ነው....ሁለታችንም እርቃን ሆነን እንዲህ ተኝተን አናውቅም....የውሸት ማንኮራፋቴን ቀጠልኩ.....የውሸት ማንኮራፋቴን ቀጠልኩ...አዎ ማንኮራፋት አለብኝ...ምክንያቱም ጥልቅ እንቅልፍ ውሥጥ አይደለሁ ያለሁት...እሱ ይበልጥ ተጣበቀብኝ...እና ጨነቀኝ...በራሴ መተማመንም አቃተኝ...ለምንድነው ይሞቀኝ የጀመረው......?ደግሞ ምን አለ ጆሮ ግንዴ ላይ ባይተነፍሥብኝ...የትንፋሹ ሙቀት ቆዳዬ ላይ ብቻ ተበትኖ አይጠፋም ወደ ውሥጤ ሰርጎ ከደም ስሬ ጋር በመቀላቀል ወደ ጠቅላላ ሠውነቴ ሲሰራጭና የውሥጥ ሙቀቴን ሲያንረው ይታወቀኛል...

ቀኝ እጁ ከትካሻዬ ላይ ተንሸራቶ ጡቴ ላይ አረፈ...የጡቴን ጫፍ በስሱ ያሻሸው ጀመር....እንዴ ምን አባቱ እያደረገ ነው........?ተው እንዳልለው ደግሞ ተኝቻለሁ...እያንኮራፋሁ ነው...ምን ይሻለኛል....እረ ፓንቴም ሊቀደድ ነው...ምን አይነት ደረቅ ችካል ነው የሚሠረሥረኝ........?አሁንማ መንቃት አለብኝ.....አዎ ነቅቼ አይኖቼን ከፍቼ ይሄን ሠውዬ ከዚህ ቤት አሽቀንጥሬ ማሥወጣት አለብኝ....ግን አልቻልኩም.....እንዴት አድርጌ ልንቃ...?ይገርማል አይደል ሠው ከውሸት እንቅልፉ መንቃት ሲያቅተው ይሄ እንኳን ለሠሚውም ለእኔም ለእራሤ እንቆቅልሽ ነው....ግን የእውነቴን ነው..ለነገሩ በህይወት ውሥጥም የእውነት ከተኙት ይልቅ ለማሥመሠል ያሸለቡት ናቸው ዋናዎቹ እንቅፋቶች......

........አይኖቼን ለመግለጽ እየፈለኩ ነው እንቢ ያለኝ...እጆቼን ለማነቃነቅ እየፈለኩ ነው አልታዘዝ ያሉኝ.....አንደበቴን እራሡ አላቅቄ ተወኝ ማለት አልቻልኩም....እንዴ ጉድ ፈላ.....ጉድ ፈላ....ምን ተፈጠረ መሠላችሁ....የጠረጠርኩት ብቻ ሆኖ እንዳይሆን.....?የሆነ ሙቀት ነገር ጭኖቼ መካከል ተሠማኝ...እርጥበት ነገር...።

እረ ለወሬ አትቸኩሉ እሡ ረጭቶ አይደለም እኔው ነኝ በራሤው የረጣጠብኩት....።

....እንዲህ አይነት መሸነፍ እንዲህ አይነት መበላሸትማ አይደረግም...እንደምንም ከራሴ ታግዬ አይኖቼን ገለጥኩ...እጄን አንቀሳቀስኩና ብርድ ልብሱን ከላዬ ላይ አሽቀነጠርኩ...ቀሥ ብዬ ጥልቅ እንቅልፍ ላይ የምትገኘውን ቦንቱን ከእጄ ላይ አወረድኩና እንዳትነቃ በጥንቃቄ ትራሱ ላይ አሥተካክዬ አሥተኛዋት...ከዛ ቁጭ አልኩ...እሱ በፍራቻ አፈግፍጎ የግድግዳውን ጥግ ይዟል...

ቀኝ እጄን ወደ ጭኔ ላኩ...በፓንቴ ውሥጥ እጆቼን ሠድጄ ብልቴን ፈተሽኩ...አዎ በትክክል ዝናብ እንዳጥለቀለቀው መረሬ መሬት በፈሳሽ ላቁጧል...ይሄ ቀላል እንዳይመሥላችሁ...ይሄ በህይወቴ ገጥሞኝ የማያውቅ ክሥተት ነው..ይሄ ማለትኮ የእውነት በዚህ እሥሬ በተኛው ወንድ ለመሸነፍ ተዘጋጅቼያለሁ ማለት ነው...

....የእውነት ወሲብ በሚሉት አዚም ለመደሠት ቋምጪያለሁ ማለት ነው....።

መብራቱን ተንጠራርቼ አበራሁት..እርቃን ገላውን ኩርምትምት ብሎ ምን ይፈጠር ይሆን.....?በሚል ፍራቻ እየተቁለጨለጨች ያየኛል...ዝላይና ተጠምጠሚበት...እላዩ ላይ ወጥተሽ በደሥታ ጨፍሪበት...ከንፈሩን በከንፈርሽ ግመጪው...እነዚህንና የመሳሰሉትን ብዙ ብዙ ሥሜቶችን በአንዴ ሥትከፋፍይና ሥትሸራርፊ አድርጊ የሚል ሥሜት ቀሠፈኝ....ያደረኩት ግን ተቃራኒውን ነው...

<<ተነስ ውጣልኝ...አሁኑኑ ውጣልኝ>>አይኔን አጉረጥርጬ

......ምንም አልተከራከረኝም ሹክክ ብሎ ተነሳና ከወልጋው ላይ ወረደ አወላልቆ እዚህም እዚያም የወረወራቸውን ልብሶቹን ሰበሰበ...እንደ ህጻን ልጅ በጉያው ወሽቆ እርቃኑን ክፍሉን ለቆ ወጣ....

<<በቃ ተመለሥ>>ልለው ዳድቶኝ ነበር.....ቃላቱ ግን ከአንደበቴ ሊሾልክ አልቻለም...>>ተነሳሁና በሩን ቀረቀርኩት..እንባዬን አፈሠሥኩ...አዎ ልክ እንደበቀደም ለታው ዛሬም አለቀሥኩ

..ወደ መኝታዬ ተመለሥኩ..እንዲሄድ አልነበረም የፈለኩት<<…ምን አባሽ ሆንሽ...አልሄድም...እንዲጋፈጠኝና እንዲያሸንፈኝ....በቀላሉ ተሸንፎ ጥሎኝ ሲሄድ ውሥጤ ሥብርብር አለ.....እንዴት እንዲህ ያደርገኛል....?

መንጋት አይበለው ነጋ....የዋቅቶላ እናት ጣት የሚያሥቆረ ጥም ጨጨብሳ ሰርተው ከእርጎ ጋር ቁርሥ አቀረቡልን...በላን...በተለይ እኔ ደሥ ብሎኝና ጣፍጦኝ ነው የበላሁት...ዛሬ ቅዳሜ ሥለሆነ ዋቅቶላ ሥራ አልሄድም ብሎ በቢጃማ ነው ያለው...ሁለታችንም አይን ላይን መተያየት ፈርተናል..

የእሱን አላውቅም እኔ ግን ከማታው ነገር ይልቅ ዛሬ የሚሆነው ነው እያሥጨነቀኝ ያለው...ነገ እንደምሄድ አያውቅም...እንዴት አድርጌ እንደምነግረው ጨንቆኛል....እንዴት ብዬ ምንሥ ተናግሬ አሳምነዋለሁ......?ነው ወይሥ ዝም ብዬ ለሊት በተኙበት ሹልክ ብዬ ልሂድ...እንዲህ ባደርግ ደግሞ ጥሩ አይሆንም ..<<እረ ምናባቱ እነግረዋለሁ..አላገባሁት ምን አጨናነቀኝ..............................እራሴን አበረታሁ..ግን ምንም ነገር ለእሱ ከመንገሬ በፊት ቆይ በመጀመሪያ እነ ስንዝሮ ጋር ልደውል..ሁለተኛውን ተልእኮ እንዲፈጽሙ ትናንትና ፍቃድ ሰጥቺያቸው ነበር...

ሁለተኛው የበቀል ተልእኳችን ቀለል ያለ ሥለሆነ እኔም ባልኖር ችግር የለውም ብዬ ሥላመንኩ...ዛሬ በለሊት ሶስቱም የሮማንን ቤት ሰብረው ገብተው...ከአልጋዋ ጋር ጠፍረው አሥረዋት...ፊት ለፊቷ ያቺን የምትወዳትን ድመቷን (ሰው በእሷ አሠርታ ነው እንዲህ ከተራ ሽርሙጥና ተነሥታ ያለፈላት እያሉ ያሟታል)...እና ድመቷን አይኗ እያየ እንዲታረድባትና በድመቷ ደም ሰውነቷን እንዲያጥቧት...በቤቱ መቃጠል በውሥጧ የነገሠውን ፍርሃት ይበልጥ ነፍሷ ድረሥ እንዲሠማትና እንዲያንቀጠቅጣት...የምትደበቅበት ጥግ እንድታጣ....በቁሟ መባነን እንድትጀምር...የራሷ ጥላ እንዲሸክካት...አዎ ይሄን ማድረግ ደግሞ ለእነሱ በጣም ቀላል ነው።...

.....ከሶሥተኛው እሥከ አምሥተኛው ወይም መጨረሻው የሚደረገው ተልእኮ ግን በጣም ውሥብሥብና አደገኛ ሥለሆነ የግድ እኔን ይፈልጋል...ደግሞ እያንዳንዷን ስቃዮን በአይኔ ማየት አለብኝ..በእኔ ሥቃይ ውሥጥ ለአመታት ደሥታ ሥትሸምት እንደኖረች ሁሉ አሁንም እኔ በተራዬ ከእሷ ስቃይ በሚቀዳ ሳቅ ዘና ማለት እፈልጋለሁ።...

.....ሥልኬን ይዤ ከእነዋቅቶላ ተለይቼ በጓሮ በር ወደ ውጭ ወጣሁ...ደወልኩ ሥንዝሮ ጋር..ያው ነገሮችን የማብራራት እና አሳምሮ የማውራት ችሎታ የተፈጥሮ ሥጦታው ነው ብዬ ነው እሱ ጋር መደወል የሚቀናኝ....

<<ሄሎ ስንዝሮ>>

<<ሄሎ ወፏ...ላጮህልሽ ስል ነው የቀደምሽኝ>>

<<የለሊቱ ሚሽን እንዴት ሆነላችሁ....?>>ቀጥታ መሥማት ወደምፈልገው ርእሥ ወሠድኩት

<<ሚሽኑ ባክሽ ከሽፏል>>ክው ነው ያልኩት

<<ምን ተፈጠረ....?ምን ሆናችሁ....? ማን ታሠረ.....?>>

<<እረ እንደዛ አይነት ነገር አልተከሠተም>>

<<እና ታዲያ......?>>

<<ሴትዮሽ ተሠውራለች...>>

<<ተሰውራለች ስትል.....?>>

<<ሁለት ቀን ሆናት በአዲሥ አበባ ውሥጥ የትም ቦታ አልታየችም...በተለይ የፒያሳን አንድ ጓዳ ጎድጓዳ አልቀረንም...>>

<<እና......?>>

<<እናማ እየፈለግናት ነው>>

<<የትም መጥፋት የለባትም...እናቷ ሆድም ብትገባ ጎትቼ አወጣታለሁ...ብትሞት እንኳን ከሲኦልም ቢሆን እመልሳታለሁ...ከእኔ ማምለጥ አትችልም...>>

እራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ከጣሪያ በላይ እየጮህኩ ነው የማወራው....ዋቅቶላ እና አሮጊቷ በጩኸቴ ተደናግጠው ተከታትለው ወደ አለሁበት ቦታ መጡ...ግራ በመጋባት እያዩኝ ነው...አሮጊቷ እንደዛ ጭምት የነበርኩት ልጅ እንዲህ ነብር ሆኜ ስላዩኝ ተደናግጠዋል...ፈርተዋልም

<<ዋቆ....ሙጬዬ ማል ታቴ......?ማልቱ አከነቲ መራቺሴ.....?>> ብለው ሲጠይቁት ሰማሁ....

እሱ እንደፈዘዘ ነው...ምንም አልመለሰላቸውን....እኔም ምን እንዳሉ ለመረዳት አልቻልኩም...

ስልኬን ዘጋሁና ወደ እሱ በማፍጠጥ መናገር ጀመርኩ<<መሄዴ ነው...ነገ መሄድ አለብኝ>>አልኩት....አሁን ንዴት ላይ ሥላለሁ ከይሉኝታ ውጪ ሆኛለሁ...

ለማንም ሥሜት መጨነቅ አልፈለኩም....

<<ልጄ ቤተሠቦችሽ ናቸው ያበሳጩሽ.....?አይዞሽ ያለፍቃዳቸው ወደዚህ ሥለመጣሽ ተናደውብሽ ይሆናል>>በማለት ሊያጽናኑኝ ሞከሩ አሮጊቷ...ውሥጣቸው ያለውን ሥጋት በማንሳት በገባቸው መጠን......

<<እማማ ግድ የለም አያሥቡ ምንም አልሆንም>>

<<አዎ ትክክል....እኔ እያለውልሽማ ምንም አትሆኚም...ይሄ የእኔ ጅልኮ ምኑንም አያውቅ....በእንዲህ አይነት ሁኔታ ከቤተሠቦችሽ ነጥሎ ይዞሽ መምጣት አልነበረበትም....ቀድሞ ቢያማክረኝ ኖሮ ሽማግሌ እልክ ነበ...አይዞሽ አሁንም ይሥተካከላል...በእኔ ይሁንብሽ ከቤተሠቦችሽ እንድትታረቂ አደርጋለሁ....>>

የእሳቸው ማጽናናት ከመጠን በላይ  ተለጥጦ ሊፈነዳ የነበረውን ሥሜቴን አሥተነፈሠው......ተንደርድሬ ወደ እሳቸው ሄድኩና ተጠመጠምኩባቸው<<....እማማ እኔ የሚቆጣ ቤተሠብ የለኝም...እናቴም አባቴም ሞተዋል...>>ተናዘዝኩላቸው...ግን የእናቴሥ እሺ ይሁን ሞታብኛለች ወይም ተገድላብኛለች አባቴ የሞተው መቼ ነው....?የሌለ ነገር እንዴት ሊሞት ይችላል...ለመሞት እንኳ መጀመሪያ ተፈጥሮ መኖርን ይጠይቃል....

<<ያ ዋቅዬ...አይዞሽ እኔ እናት እሆንሻለሁ...>>እያጽናኑኝ ይዘውኝ ወደ ቤት ገቡ....እሱ በፍራቻ እንደተሸበበ ሹክክ ብሎ ከሁዋላ ተከተለን...በዚህ ጊዜ ህጿኗ ቦንቱ አብራን አለመኗሯን ወደድኩት...አክስቷ ነበረች በጥዋት መጥታ ከእቅፌ ፈልቅቃ እያሥለቀሠች የወሰደቻት....እቤት ገብተን ገና ተረጋግተን እንኳን ሳንቀመጥ ሌላ ሥልክ ተደወለልኝ...አየሁት...ጋሽ ዜና ናቸው...

አነሳሁት<<አቤት ጋሼ>>

<<ሰላም ነሽ ልጄ......?>>

<<ሰላም ነኝ>>

<<እንዴት ይዞሻል.....?>>

<<ደህና ነኝ...ነገ እመጣለሁ>>

<<ምን ልትሠሪ......?>>ጠንከር ባለና በሚጋፋ ድምጽ 

<<እንዴት ምን ልትሠሪ....?ወደ ቤቴ ነዋ>>

<<ኤዲያ ምን ቤት አለሽ...ቤት ማለትኮ ድንጋይና ቆርቆሮ ውሥጥ የተከማቸ ቁሳቁስ ያለበት ሥፍራ አይደለም....ያ ቤት ሣይሆን መጋዘን ነው የሚባለው...ቤት ማለት ቤተሠብ ያለበት ቦታ ነው...ሥለዚህ አርፈሽ እዛው ቆዪ ደግሞ ሴትዬዋን ፍለጋ ከሆነ እንዳትለፊ>>ስለ ሴትዬዋ ሲያነሡ ሥሜቴ ተነቃቃ...

<<ምን ሆነች.......?ስለ እሷ የሚያውቁት ነገር አለ.......?>>

<<አምልጣሻለች>>ከንግግራቸው ስረዳ ስላመለጠችኝ የተደሠቱ ይመሥላሉ....ምን ይታወቃል...ሆን ብለው ይሆናል ከኔ ያሥመለጧት

ጥያቄዬን ቀጠልኩ<<ማለት የታባቷ ልትሄድ ትችላለች......?>>

<<ቤቱን ባንቺ ሥም አዙራ...ሶስት ገጽ የይቅርታ ደብዳቤ እኔ ጋር አሥቀምጣልሽ ጨርቄን ማቄን ሳትል ገዳም ብላ ተሠውራለች>>

<<ምን.......?ገዳም....?>>

<<አዎ ገዳም>>

<<እንዴ ሰይጣን ገዳም መግባት ይፈቀድለታል እንዴ....?>>

<<ልጄ መድሃኒትኮ ለበሽተኛ ነው የሚታዘዘው...ገዳም ከአምላክ የመታረቂያ እና ጽድቅን የመፈለጊያ ሥፍራ ከሆነ የሚገባው ለእንደሷ አይነት ሀጥያተኞች ነው ብዬ አሥባለሁ...ጻድቁማ አንዴ ጸድቋል...ሥልኩን ዘግቼ ዝም አልኩ...ምንድነው የማደርገው.....?ምን ይሻለኛል......? የትኛው ገዳም ይሆን የገባችው......?የትስ ብትገባ መቼሥ ገዳም ድረሥ ተከታትዬ አላጠፋት...ቀና ብዬ ዋቅቶላን አየሁት አይን አይኔን ሲያየኝ ስለነበር ተጋጨን... ከዋቅቶላ ጋር ስለሚኖረኝ የወደፊት የፍቅር ህይወትና ለቦንቱም ምን አይነት እናት እንደምሆንላት እያሰብኩ ፈገግ አልኩለት....... እሱም ከንፈሩን ገለጥ አድርጎ ከነጫጭ ጥርሶቹ ከፊሎቹን አስመለከተኝ.....

.

.

ከሳምንታት በሁዋላ እጅጋየሁ ዜና(ወፏ) የኔ የምትለው የራሷ ቤተሰብ ኖራት።የዋቅቶላ ህጋዊ ባለቤትና የቦንቱ እናት በመሆን አዲሱን ህይወቷን ምእራፍ አንድ ብላ ጀመረች። አዎ እግዜር ፍቅርን ከመዳፉ ፈልቅቆ በዋቅቶላ አሥመሥሎ ልቧ ውሥጥ አሰረገው..በመጨረሻም የመጨረሻውን ደስታ..ከአጽናፍ አጽናፍ የሚናኝ ደስታ በዋቅቶላ ጎጆ ውስጥ አገኘችው...ከወራቶች ምናልባትም ከአመታት በሁዋላ ለቦንቱ ታናሽ እህትም ይኖራት ይሆናል።

.

.

ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም..በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!

.

.

.

/////🎀 ተፈፀመ 🎀//////


No comments

Post a Comment

Popular Posts

© የፍቅር ቀጠሮ የፍቅር ታሪክ 2020
Maira Gall